እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል እና ለግሪጎሪያን አዲስ ዓመት (2025 ዓ.ም) በሰላም አደረስዎ!
HTML-код
- Опубликовано: 13 янв 2025
- ሰው ሁሉ ከአንድ ተፈጥሯል። ስለዚህ ሰው’ነት አንድ ነው። የቀለም፣ የጾታ፣ የቋንቋ፣ የባህል፣ የመልክዓ ምድር ልዩነቶች ውጪያዊ ስለሆኑ ሰውን ከሰው በመሠረታዊነት ሊለዩት አይችሉም። ስለዚህ ሌላው ሰው እኔን ነው፤ እኔም ሌላውን ሰው ነኝ። ሌላው ሲጎዳ ሰው’ነት ተጎድቷልና እኔም የጉዳቱ ተጋሪ ነኝ። ሌላው ሲጠቀም በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ እኔም እጠቀማለሁ። ይህ አመለካከት ብርሃን ነው። ከዚህ የወጣ ሁሉ ጨለማ ነው። ጨለማ የብርሃን አልቦነት ነው። ብርሃንም በጨለማ ይበራል ጨለማም አያሸንፈውም።
ሰው’ነት ክቡር ነው። እንደ ድህነት ይልቁንም እንደ አስከፊ ድህነት ክቡሩን ሰው የሚያዋርድ ነገር የለም። በዓለም ላይ በርካታ ድሆች አሉ። ችግሩ ግዙፍ ስለሆነ አንዳች ማድረግ አልችል ይሆናል። ነገር ግን ዓይኔ ሊያየው፣ ጆሮዬ ሊሰማው በሚችል ቅርበት ያለ የእኔን ዕርዳታ የሚሻ/የምትሻ ሰው አይቼ ማለፍ አልፈልግም። ቀርቤ ላናግረው/ላናግራት፣ በምችለው አቅሜ ልረዳው/ልረዳት እጥራለሁ። ይህንን የማደርገው ለማንም ሳይሆን ለራሴ ነው። እኔ ሰው ነኝና! በአስከፊ ድህነት ውስጥ ያለን ሰው ለመርዳት ባለጠጋ መሆን የግድ አያስፈልገኝም። በፍቅር ባለጠጋ ከሆንኩ ለውጥ ማምጣት እችላለሁ። ስለዚህ እኔ እያለሁ በአቅራቢያዬ የሚበላውና የሚጠጣው የሚያጣ፣ የሚለብሰው የሚቸገር፣ ታክሞ ሊድን እየቻለ የሚሞት፣ ልጆቹን ትምህርት ቤት መላክ እየፈለገ የማይችል ሰው እንዲኖር አልፈልግም። “ላቭ ዩር ኔበር” የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ታላቅ ትዕዛዝ ለመተግበር የቆመ ድርጅት ነው። እርስዎም ሰው ነዎትና ይህንን በአቅራቢያችን ያሉ ሰዎችን ከአስከፊ ድህነት ውስጥ የማውጣትና በዘላቂነት ሕይወታቸውን የመለወጥ ራዕይና ተልዕኮ እንዲቀላቀሉ ተጋብዘዋል።
www.loveyourneighbor.et
lynethiopia@gmail.com