ETHIOPIA : ጤናዎትን በፅኑ ከሚያቃውሱት እነዚህን 5 የምግብ አይነቶች በጭራሽ ወደ አፍዎ ድርሽ አያርጉ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 2 окт 2024
  • በሙሉ ጤነት እርሶና ቤተሰቤ ለመኖር በተለይ ለልጆች ጤነት ግድ የሚሎት ከሆነ እነዚህን ፣5 የምግብ አይነቶች ጨርሶ መበላት ለማቆም ዛሬውኑ ይወስኑ። ዘመኖትን ሁሉ ከአስቸጋሪ የጤና ቀውስ ይተርፋሉ
    ኢትርሚተንት ፋስቲንግ ( intermittent Fasting play list)
    www.youtube.co....
    Water Fasting play list ( በውሃ ፅም ሁሉም ቪዲዮዎች )
    www.youtube.co....
    • በዚህ ትምህርት ውስጥ የሚገኙት መረጃዎች በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ጠቃሚ ሃሳቦችን ለማካፈል ብቻ ታቅደው የቀረቡ እንጂ በምንም ዓይነት መሠረታዊ የጤና እክሎችን ለመፍታት የሕክምና ምርመራንና የሐኪም ውሳኔዎችን ለመተካት የተሰጡ አይደሉም። የጤና ምርመራንና ሕክምና የሚሹ ጤና ነክ ችግሮችን በተመለከተ ሐኪምዎን እንዲያማክሩ በብርቱ እናሳስባለን
    • Disclaimer: This video is not intended to provide diagnosis, treatment or medical advice. Content provided on this RUclips channel is for informational purposes only. Please consult with a physician or other healthcare professional regarding any medical or health related diagnosis or treatment options. Information on this RUclips channel should not be considered as a substitute for advice from a healthcare professional. The statements made about specific products throughout this video are not to diagnose, treat, cure or prevent disease.

Комментарии • 1,7 тыс.

  • @yenetena
    @yenetena  4 года назад +338

    በተለይ ልጆች ላሏቸው ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን እንዲደርስ ላይክ ማድረግ እና ሼር በማድረግ ከኔ ጋር ህዝባችንን እናገልግል ጥያቄዎች እና አስተያየቶች በኮሜቱ ላይ ፃፋንኝ አመሰግናለሁ
    በግል ብዙ መረጃ ከፈለጉ ብዙዎች አየተጠቀሙ ያሉበትን የግል FB group join ያድርጉ ሊንኩ:facebook.com/groups/YeneTena/
    የምንወዳትን አገራችንን ሰላም ያድርግልን የሁሌም ፀሎቴ ነው

    • @fozifozi9841
      @fozifozi9841 4 года назад +4

      ወንድሜ ስኳር ምንም አንጠቀም? እንደው አንድ ማንኪያም ቢሆን? ያለ ሻይ መኖር የምችል አይመስለኝም እስኪ ንገረኝ

    • @zzzzh9723
      @zzzzh9723 4 года назад

      ዶክተር አላህ እድሜህን ያርዝመው ኮረና ይዞኝ ነበር እና ትንሽ እንዳገገምኩ መልሶ አገረሸብኝ ምን ይሻለኛል መፍትሄ ካለህ ዶክተር

    • @mesfintesma7974
      @mesfintesma7974 4 года назад +2

      Thank you doctor lactose milk ችግር አለው መጠቀም ?

    • @liaaye3126
      @liaaye3126 4 года назад +6

      @@zzzzh9723
      እግዚአብሔር ጨርሶ ይማርሽ እህቴ

    • @liaaye3126
      @liaaye3126 4 года назад +10

      ዶ/ር እናመሰግናለን ለምክርህ የትኛውን ዘይት ለምግብ ትመክረናለህ??

  • @154messi
    @154messi 3 года назад +20

    በጣም ጠቃሚ ትምህርት ነው እናመሰግናለን ።
    በተለይ ምግብ ቤት ችፕስ የምትጠቀሙ ሰዋች መጠንቅቀ ያስፈልጋል ። ችፕስ የሚጠብሱበትን ዘይት ከሳምንት በላይ ነው የሚጠቀሙበት። ይህ ማለት ዘይት በተደጋጋሚ በሚሞቅበት ሥዓት ወደ መርዝነት ይቀየራል። ሌላው ቀላል መጠጦችን እንደ ኮካ ኮላ ፔፕሲ ሚሪንዳ የመሳሰሉትን. ኬሚካልና ስኳር የበዙበት ስለሆነ ለጤና በጣም ጉዳት ያደርሳል። ለምሳሌ በአንድ. 500 ml. ጠርሙስ ኮካ ውስጥ እስከ 6 ማንኪያ ስኳር ይገኛል። በተለይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ሰዋች ወፍረው ስናያቸው. የምቾት እንዳይመስላችሁ ።በኬሚካል ሆዳቸው ስለተነፋ ነው።

  • @selamleethiopia4985
    @selamleethiopia4985 3 года назад +5

    እግዚአብሔር ኑሮህን ቤተሰብህን ይባርክልህ አንተ ልዩ ሰው።
    ትምህርትህ አንጀት ውስጥ ነው ሰርስሮ የሚገባው።
    ወገኔ ይህንን ምክር ሰምተህ በተግባር አውለው

  • @ያረብልቤንበቁርአንአርጥብ

    ዶክተር ዳኒ በምን ቋንቋ እንደምናመሰግንህ አላውቅም ብርታቱን ይጨምርልህ ዶክተር በርታልን

  • @mimidawit4497
    @mimidawit4497 4 года назад +3

    ተባረክ ዶ/ር ዳኒ ሁሉን ስሳትሰስት ስለምታገለግለን በነገር ሁሉ ተባረክ

  • @asds8008
    @asds8008 4 года назад +4

    እንኳን ደናመጣህ ዶክተርዬ የምወድህ እና የማከበርህ

    • @yenetena
      @yenetena  4 года назад

      በተለይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ለሚያውቋቸው ሁሉ ይህም መልክት "ሼር" እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለው ። የብዙ ህፃናት ህይወት የብዙ ሰዎችም ጤና ሳያቁት እየተጎዳ ነው

  • @seblebirhanu6374
    @seblebirhanu6374 3 года назад +2

    ተባረክ ዶክተር ዳኒ፣ ለወገኖችህ የምታውቀዉን የምታሳውቅ በቅንነት!
    Amazing person.... God Bless you & your family!!

  • @munaali4698
    @munaali4698 4 года назад +4

    እናመሰግናለን ፈጣሪ ጤና እና እድሜ ይሰጥህ እሰከነቤተሰብህ

    • @yenetena
      @yenetena  4 года назад

      በተለይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ለሚያውቋቸው ሁሉ ይህም መልክት "ሼር" እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለው ። የብዙ ህፃናት ህይወት የብዙ ሰዎችም ጤና ሳያቁት እየተጎዳ ነው

  • @ekranmohammed7840
    @ekranmohammed7840 3 года назад +1

    ወላሂ።እንኳን ነገገርከኝ ተጥቃሚነበርኩ እነዚህን ሁሉ።ሽኩረንንን ።እረጅም እድሜ ይስጥህ

  • @ምህረትየተዋህዶልጅ
    @ምህረትየተዋህዶልጅ 4 года назад +5

    ውዱ ጊዜ ሰውተህ እኛን ስላስተማርከን ተባረክ ወንድማችን

    • @yenetena
      @yenetena  4 года назад

      በተለይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ለሚያውቋቸው ሁሉ ይህም መልክት "ሼር" እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለው ። የብዙ ህፃናት ህይወት የብዙ ሰዎችም ጤና ሳያቁት እየተጎዳ ነው

  • @kb1956
    @kb1956 4 года назад +2

    አመሰግን አለው Dr. እኔ በጣም ብዙ ነው የተማርኩበት አጠገቡም አልደርስም ካሁን ብሓላ ጌታ ይባርኽ!

  • @truneshtesema6944
    @truneshtesema6944 3 года назад +4

    ስለ ሁሉም ምክር እጅህ በጣም እናመሰግናለን ስለ ዘይት ግን አልገባኝም የትኛው ለጤና ጥሩ ነው ፣

  • @tibebesolomon7840
    @tibebesolomon7840 3 года назад +2

    የምታኮራ ዜጋ ነህ ተባረክ ብዙ አስተማርከን እናመሰግናለን

  • @sabianahmed7057
    @sabianahmed7057 3 года назад +17

    ohhhh ወደ ዋናው ጉዳይ ከመግባትህ በፊት የሚወሩት ነገሮች ባይበዙ, ብዙ ሰው ዋና መልዕክቱን ሳይሰማ ሰልችቶት ሊያቋርጠው ይችላል, so pleas try to cover the main ideas to be delivered than going around the bush

    • @sabrinaa4383
      @sabrinaa4383 3 года назад +2

      የሌላ አገር yoitubers በ5 min. የሚያጠናቅቁትን list እኮ ነው 24min ወስዶ ሚያወራው። ad. ማብዛት ስለሚፈልግ። ሁሉም የሱ video ረጃጅም ስለሆነ ማየቱን ትቻለሁ።

    • @sabianahmed7057
      @sabianahmed7057 3 года назад

      @@sabrinaa4383 ya u r right

  • @gelilakebede3118
    @gelilakebede3118 3 года назад +1

    እግዚያብሄር ይባርክህ ምንም የሚጣል ነገር የለዉም የምትናገረዉ ዘመንህ ይባረክ ሁሉም በተሰማራበት የዜግነት ግዴታዉን ቢወጣ ሀገራችን ህዝባችን የት በደረሰ በርታ ወንድሜ ያወከዉን ለወገንህ እንድታሳዉቅ የጌታ ፀጋ ይብዛልህ

  • @melkamaschalew8715
    @melkamaschalew8715 3 года назад +3

    ስለ ሰጠኸን ማብራሪያ እናመስግናለን ።

  • @kuwaitkuwait4611
    @kuwaitkuwait4611 2 года назад +1

    ዶከተር ፈጣሪ ይጠብቀን በሰደት ያለነዉን ናቹራል የሆነ ነገር በሀገሬ ኢትዮጵያ ነዉለምከር በጣም እናመሰግናለን ተባረክ

  • @yenetena
    @yenetena  4 года назад +13

    በተለይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ለሚያውቋቸው ሁሉ ይህም መልክት "ሼር" እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለው ። የብዙ ህፃናት ህይወት የብዙ ሰዎችም ጤና ሳያቁት እየተጎዳ ነው

    • @enathagertube4619
      @enathagertube4619 4 года назад +4

      ዶክተር ዳንኤል እባክህ ይህን አታርጉ ስትል በአንፃሩ ምን ብናደርግ የተሻለ እንደሆነ ብትጠቁመን እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @ሁሉንቻይ-ጠ2ከ
    @ሁሉንቻይ-ጠ2ከ 4 года назад +3

    ወይ ጉድ ይገርማል በጣም ፣ በእግዚአብሔር ቸርነት እኮ ነው ያለነው መቼም እውነት።

  • @emebetbekele7014
    @emebetbekele7014 Год назад +9

    ለእኛ እንደምትጠነቀቅልን አንተንና ቤተሰብህን እግዚአብሔር ይባርክልህ

  • @asresiegetu4549
    @asresiegetu4549 4 года назад +1

    ጆክተር ከመጠን በላይ አመሰግንሕ እልም Thank you very much
    I am weching you for Israel

  • @GetahunTefera-d7e
    @GetahunTefera-d7e 3 месяца назад +5

    ወንድማችን የኔ ጤና አዘጋጅ እያቀረብክ ያለዉ የጤና ትምህርት በርግጥ ምግብ ለመምረጥ እና አቅም ላላቸው ጥሩ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስንቱ ፐርሰንት ነው የምግቡንም ስም ይሚያዉቀዉ ዳቦ ላላገኘ አይከብድም?

  • @selamleethiopia4985
    @selamleethiopia4985 2 года назад +1

    ግሩም ድንቅ ትምህርት ነው በውነቱ። አረ እግዚአብሔር ዘርህን ይባርክልህ ዶክተርዬ

  • @yenetena
    @yenetena  4 года назад +7

    Join me live on the FB group in 15 minutes.facebook.com/groups/YeneTena/learning_content/

    • @se7141
      @se7141 4 года назад

      ዶር ዳንኤል ጌታ ይባርክህ !! ምግብ ስንሰራ olive oil መጠቀም እንችላለን ወይ?

    • @harmalaluchano1354
      @harmalaluchano1354 4 года назад +1

      ከልብ እናመስግናለን
      ፀጋውን ያብዛልህ
      እየፆምን ነው በርትተናል
      በርታልን

    • @yenetena
      @yenetena  4 года назад

      @@se7141 yes you can

    • @se7141
      @se7141 4 года назад

      Olive oil ምግብ ስናበስል ኮልስትሮሉ ከፍ ይላል የሚል ኢንፎርሜሽን ስለሰማሁ ነው .....በጣም አመሰግናለሁ ዶ/ር

  • @emebeterque8725
    @emebeterque8725 Год назад +1

    እናመስግናለን አላህ እውቀትህን ይባርክልህ thanks a lot u so helpful 💯🤞👍

  • @seifuhaile
    @seifuhaile 4 года назад +8

    ታዲያ ምን እንብላ ዶክተር ጭንቀት ለቀቀብኝ እስቲ የማንበላዉን ነገርከን የምንበላዉን ንገረን።

  • @ariamfeshaye6710
    @ariamfeshaye6710 Месяц назад +1

    Relay Egzabehare yemesgen God is giving to you Mastewal and Tibebe. Gegna. Bless you all family too Amen 🙏

  • @naomidaniel5411
    @naomidaniel5411 4 года назад +3

    For anyone wondering Try using olive oil as this is most natural. If you do a lot for Habesha cooking then use avocado oil because it can stand much more heat.

  • @newharg5548
    @newharg5548 4 года назад +2

    እግዚአብሔር ይባርክህ!!!!

  • @ShewayeFFB
    @ShewayeFFB 4 года назад +6

    ዶ/ር ዮሐንስ
    ‹‹ጤናዎትን በጽኑ ከሚያቋውሱት እነዚህን 5 የምግብ ዓይነቶች በጭራሽ ወደ አፍዎ ድርሽ አያርጉ›› የሚለውን ቪዲዮ ተመልክቼዋለሁ፡፡ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ግን መብላት የሚገባንን አያይዘህ ብትነግረን ጥሩ ነበር፡፡ ከእነዚህ 5 የምግብ ዓይነቶች ለመጠበቅ ጤነኞቹን ደግሞ ማወቅ አለብን፡፡ ምናልባት በሌላ ቪዲዮ ላይ በግልጽ ያብራራኸው ካለ ብትጠቁመን ደስ ይለናል፡፡ ታዲያ ምን እንብላ?

  • @astergezawe191
    @astergezawe191 2 года назад +1

    ቡሩክ ነህ Dr Donnie ጌታ ኢየሱስ ይባርክ

  • @temesgenmukuria
    @temesgenmukuria Год назад +6

    በጣም ጠቃሚ ትምህርት ነው።
    ጥያቄ አለኝ
    ስለ ቲማቲም ጥቅምና ጉዳት ልታስተላልፍልን ትችላልህ? አመሰግንሃለሁ
    ተመስገን።

  • @dimbarudimbaru7848
    @dimbarudimbaru7848 2 года назад +2

    በጣም እናመሰግናለን ህይወታችንን ቀየርከው

  • @blenTube
    @blenTube 3 года назад +3

    ብዙ ነገር ነው ያሳወከን ተባረክ

  • @hanatamerat2474
    @hanatamerat2474 3 года назад +2

    ተባረክ የኔ ወንድም

  • @ብሩክታይትከበደ
    @ብሩክታይትከበደ 3 года назад +8

    ግልፅ አይደለም 2% ካልተጠጣ ወይ ይሄኛው ይሻላል አላልከንም ሌሎቹም ቢሆኑ በንፅፅር መተኪያ ካላቸው ብታብራራቸው ጥሩ ነበር

  • @demesewmereid9147
    @demesewmereid9147 2 года назад +1

    Dany we all real ethiopians love love you!!! So thank you

  • @hareg6874
    @hareg6874 2 года назад +8

    እናመሰግናለን ስለጠቃሚ ምክርህ:: እሺ: ምን አይነት ዘይት እንጠቀም?

  • @getahunhabtemariam1771
    @getahunhabtemariam1771 3 года назад +1

    ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ህዝባችንን እያነቃኸው ስለሖነ ወገኖቼ እንጠቀምበት።

  • @bezaTal
    @bezaTal 3 года назад +8

    Oliv oil ✅
    Avocado oil✅
    Coconut oil ✅
    Butter (kbe)✅

  • @fifiikonjo6712
    @fifiikonjo6712 3 года назад +1

    አመሰግናለው ዶክትር ፣ ብዙ ተማርኩበት

  • @swagdawg3243
    @swagdawg3243 2 года назад +5

    ዶር ፡ ህዝባችንን ፡ ከሞት ፡ ለሚያተርፈው ፡ ትሞህርተህ ፡ እግዚአብሄር ፡ አብዝቶ ፡ በሁሉም ፡ ይባርክህ።

  • @AT-fu3sp
    @AT-fu3sp 2 года назад +2

    ዶ/ር ለምታደርገው እርዳታ የዓለምመድኃኒት እድሜን ጤና ከነቤተሰቦችህ ይስጥልኝ እባክህ የኑግ ዘይት እቤት ውስጥ ለማውጣት የሚያስፈልጉ እቃዎችንና አሰራሩን ብትልክልኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ አሜን!!! እናትህ

  • @yesasye3947
    @yesasye3947 4 года назад +6

    እስካሁን 2% የሚለውን ነበር የምጠቀመው አሁን ከትምህርቱ በኋላ የትኛው አይነት ወተት መጠቀም እንችላለን?

  • @conniebistat9930
    @conniebistat9930 4 года назад

    በጣም እናመስግናለን ወንድሜ ትልቅ ትምህርት ነው የምታስተምረን:- እግዚአብሔር ይባርክህ::

  • @fozifozi9841
    @fozifozi9841 4 года назад +7

    ቀጣም ምን ምን ብንበላ ለጤናችን ይጠቅማል የሚለው አቅርብልን

  • @adishanan9611
    @adishanan9611 3 года назад

    ዶክተር ዬ አንተን አለማመስገን ሀጢያት ነው እግዚአብሔር አምላክ ዘመንህን ይባርክ!

  • @samtariku2819
    @samtariku2819 Год назад +6

    ብዙ ግዜ ቪዲዮዎችህ በጣም ረጅም ናቸው አጠር ቢሉ አሪፍ ነው

    • @addisengeda4194
      @addisengeda4194 Год назад +1

      ስንት ደቂቃ ትፈልጋለችሁ 5 mints 10, or 20

  • @raheldemssie197
    @raheldemssie197 2 года назад

    እግዚአብሔር ይስጥልን ዶክተር በጣም ጥሩ እውቀት ነው የሰጠህን በተለይ ለልጆቻችን እናመሰግናለን በርታልን

  • @yeshimebet5398
    @yeshimebet5398 4 года назад +7

    ሰላም ዘይቱን መጥፎውን አሳየህን ግን መፍቴውንም አንድላይ አስቀምጥልን

  • @bezawitdinku5017
    @bezawitdinku5017 2 года назад +1

    አመሠግናለሁ ዶ/ር ተባረክ

  • @wondafrashbutta4760
    @wondafrashbutta4760 3 года назад +6

    አመሰግናለሁ ።ወገኔ በመሆንህ እኮራብሃለሁ።

  • @fatomahmohd9211
    @fatomahmohd9211 3 года назад

    ምክርህ በጣም በጣም የማናውቀውን ነገር አውቀናል እናመሰግናለን

  • @tsegayefanta
    @tsegayefanta 4 года назад +6

    ምክሩ ጠቃሚ ነው፣ እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን 24 ሴኮንድ ክሊፕ ማድመጥ ብዙ ፍራንክ ይወስድብናል አጠር ተደርጎ በአምስት ደቂቃዎች ብታቀርብልን ደስ ይለናል፣ አመሰግናለሁ ።

  • @hannagetachew9024
    @hannagetachew9024 4 года назад

    TEBAREK DR.DANIYE🙏🙏🙏🙏 YOU ARE VERY SPECIAL FOR ALL ETHIOPIANS AND ERTRIANS.

  • @angawatakiltiwoubetu2692
    @angawatakiltiwoubetu2692 2 года назад +5

    አንድ ነገር ተው ሲባል እኮ በተውነው ምትክ ይህንን ተጠቀሙ ይባላል፣ አየር ላይ ተንሳፈን ቀረን ፣ አሳርፈን። part2 ይቀጥል

  • @aronbrhane8725
    @aronbrhane8725 3 года назад

    ዶክተር እናመሰግናለን በሌላ ነገር ደግሞ ተመለሰን

  • @osmanmekbul8064
    @osmanmekbul8064 Год назад +4

    ደ/ር በጣም ጥሩ ምክር ነው እና እኔ አንድ ጥያቄዎች አሉኝ እነሱም
    1) ሙሉ ቅባት ያለው እርጉ እና ወተት በየሱፕርማርኬት የሚገኝ መጠቀሙ እንዴት ነው ችግር የለውም ማለት ነው? በኲልስትሮል ፣በጉበት እና ሌላ ችግርስ አያመጣም ወይ ??
    2)በአገራችን ዋና ያለው ምግብ ነጭ ዱቄት ነው አብዛኝው ስው ከለው የኑሮ ሁኔታ ዱቄት ከመመገብ ሌላ አመራጭ ስለ ሌለው ምን ብደረግ ይሻላል?
    3) አሁን በገበያ ከለው የምግብ ዘይት ተመራጩ ምን አይነት ነው ከማህበረሰቡ አቅም ጋር የሚሄድ ?

  • @tesfuamah566
    @tesfuamah566 6 месяцев назад +2

    ስለ አርቴፊሻል ስኳር ለስኳር ህመምተኞች ጥቅሙንና ጉዳቱን ብትሠራበት

  • @ermiyesketema299
    @ermiyesketema299 Год назад +6

    ቆጮ በቃሪያ ከአሁን በኋላ የምበላው ጥሬ ጎመን

  • @asterkebede8588
    @asterkebede8588 4 года назад

    ዶ/ር ከምግብ ጠቀሜታ አንጻር ብዙ ግንዛቤ ሰለ ሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ።

  • @Tina-wz4nl
    @Tina-wz4nl 3 года назад +5

    ዶክ እናመሠግናለን ሆኖም እያንዳንዱን ምግም መጥፎ የሆኑትን ስትነግረን ባንፃሩ በምን እንደምንለውጠዉ ለምሳሌ ነጭ ፉርኖ ዳቦ በ holemeal እያልክ ቢሆን ይመረጣል እስካሁን የነገርከን መጥፎ የሆኑትን ብቻ ነው።

  • @hanihabeshawit4648
    @hanihabeshawit4648 2 года назад +2

    Doctor dani ewunet ante tleyaleh betam bzu neger new yetemarkut fetari selamhn yabzalh

  • @shewayehaile8130
    @shewayehaile8130 3 года назад +5

    መልካም ዜጋ ነህ ዶክተር ቀና ኢትዮጵያዊ እግዚአብሔር ይስጥልን

  • @di3910
    @di3910 8 месяцев назад +1

    Omg thank you soo much for the lesson

  • @abzabity177
    @abzabity177 2 года назад +5

    ከልብ አመሰግናለሁ ቆይ ምን አይነት ዘይት እንጠቀም ወየስ አማራጭ

  • @johnabraham681
    @johnabraham681 2 года назад +1

    Thank you doctor Daniel

  • @Talasp-ik5kk
    @Talasp-ik5kk 5 месяцев назад +5

    ምን እንመገብ

  • @selammelaku4352
    @selammelaku4352 Год назад +2

    Thanks dr

  • @belayedrese2037
    @belayedrese2037 Год назад +3

    Dr can you make one video English language for our kids?
    God bless you abundantly for your

  • @denbelomelore4118
    @denbelomelore4118 4 года назад +1

    Thank you God bless you

  • @alemnigusse6279
    @alemnigusse6279 2 года назад +3

    እግዚአብሔር ይስጥህ ዶ/ር

  • @hhhhh8689
    @hhhhh8689 3 года назад

    በጣምእናመሠግናል ዶክተር መገኛ አለህ እባክህ ተባበረኝ

  • @ethiopiamusic5285
    @ethiopiamusic5285 3 года назад +7

    ዋንው ባርካችሁ ብሉ

  • @yosithegreat7877
    @yosithegreat7877 Год назад +1

    Thanks for sharing this information Dr.

  • @lailaal5904
    @lailaal5904 4 года назад +4

    ዲስ ለይክ የምትሉ ሰዎች ቀድማቹ ተማሩ

    • @ሃያትሃያት
      @ሃያትሃያት 4 года назад

      በትክክል

    • @yenetena
      @yenetena  4 года назад +1

      በተለይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ለሚያውቋቸው ሁሉ ይህም መልክት "ሼር" እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለው ። የብዙ ህፃናት ህይወት የብዙ ሰዎችም ጤና ሳያቁት እየተጎዳ ነው

  • @JustYdidia
    @JustYdidia 4 года назад +1

    Thanks docterye this the issue what I need most of the people who live Europe please give attention for diet specially enjera made of wheat !!!

    • @naomidaniel5411
      @naomidaniel5411 4 года назад +2

      Hi Rute! Yes it is so important to pay attention to what we are putting in our bodies.

  • @jwfixurthought7
    @jwfixurthought7 3 года назад +3

    ይህንን ቪዲዮ ወደ ኋላ ተመልሼ ነው review ያደረኩት ጥያቄ ለማንሳት ብዬ ። ይህም በተለይ ለልጆች የሚሆኑ ከእነዚህ (low fats) ከተባሉትና cereal የመሳሰሉትን ተክቶ ለልጆች የሚሆኑ የምግብ ዓይነቶችን ብትነግረን? ለጥረትህ ሁሉ እናመሰግናለን።

  • @rahelmesele6709
    @rahelmesele6709 3 года назад

    እናመስግናለን በጣም ጠቃሚ ምክር ነው

  • @senaitshumeegato1803
    @senaitshumeegato1803 3 месяца назад +4

    ስለቅንነተህ ተባረክ ዶክተር

  • @akbaratkidan9189
    @akbaratkidan9189 4 года назад +2

    Thanks dani

  • @SM-Mg
    @SM-Mg 3 года назад +6

    እሺ በምን አይነት ዘይት ሰርተን እንብላ???? ደሞስ ይህንን አትብሉ ስትለን በምትኩ ደሞ ይህንን ብትጠቀሙ ብለህ ማስተማር አለብህ

    • @yenetena
      @yenetena  3 года назад +2

      i did go and watch the next video

    • @yenetena
      @yenetena  3 года назад +1

      ruclips.net/video/_Ju2ETK9edE/видео.html

    • @eshetubeyene9557
      @eshetubeyene9557 3 года назад

      ተናግሯል አንቺ አልሰማሽም እንጂ

  • @kalkidangezahgne6642
    @kalkidangezahgne6642 4 года назад +1

    I do agree!

  • @birukendryas65
    @birukendryas65 3 года назад +4

    ዶክተር የምትሰጠው ትምህርት በጣም አራፍ ነው ግን አንድ ነገር ግልጽ አልሆነልኝም ምን አይነት ዘይት ብንጠይቅም ትመክረናልክ እባክህን መልስልኝ

  • @yordanosteclehaimanot7694
    @yordanosteclehaimanot7694 4 года назад +2

    ጌታ ይባርክህ

  • @zdseed4880
    @zdseed4880 4 года назад +5

    ዘይቱነው የጨነቀኝ ትክክለኛው ዘይት የቱነው

  • @SelamHAGOS-s3p
    @SelamHAGOS-s3p 3 года назад +1

    ተባረክልን ወንድም ጤና😍😍😍👍🇪🇷

  • @et1206
    @et1206 4 года назад +4

    የሚገርም ነው ላካ ለዚህ ነው ከሆነ አመት በኋላ የ ኢትዮጵያ የጤና ዘይቤ ተየዛባው እኛ ዘመናዊነት እየመሰለን የራሳችንንም የልጆቻችንንም ጤና እየበከልን ነው

  • @marakizanou5511
    @marakizanou5511 4 года назад +1

    Thank you so much! Bless you

  • @tsegayedelebo7319
    @tsegayedelebo7319 3 года назад +3

    ሰላም ዶክተር አንድ ነገር ለስቸግርህ ሰውነት ብዙ ውፍራት የለኝም ግን ቦርጭ አለኝ ምን አይነት ስፖርት ልስረ

  • @የመንዝወርቅ
    @የመንዝወርቅ 4 года назад +1

    እናመሰግናለን🙏

  • @oneethiopiae
    @oneethiopiae 2 года назад +4

    ዶ/ር ሁሉንም ደስ እያለኝ ነው ያዳመጥኩት ግን ዘይት በኛ ሀገር ደረጃ ልንመርጥ
    ቀርቶ ከምን , የት እንደተሠራ ሳናውቅ እየተጠቀምን ነው ። ዘይቱም ጠፋ

  • @abigaildesta5906
    @abigaildesta5906 4 года назад +1

    Ur point is right but better to suggest the replacement like uf we don't use vegetable oils, yoghurt....then what type??? Thanks

  • @menberekebede4373
    @menberekebede4373 2 года назад +4

    ሰላም ዶክተር ስለሰጠህን ምክረ እመሰግናለሁ ግን ኢትዬጵያ ሁሉም ዘይት ለጤና ጎጂ የሆኑ ናቸው ኦሊብ ዘይት በጣም ውድ ነው የኑግ ዘይት ድሮ ነበር አሁን ካአገር ያለ አይመስለኝም ብቻ ኢትዬጵያን እግዛብሔር ይጠብቃት

  • @hiamanotwentworth2834
    @hiamanotwentworth2834 Год назад +1

    Dr. Daniel, thank you so much. You are much appreciated. So much to learn.
    If I may , I would like to ask is it ok to use organic canned lentils / vegetables soup and tuna tuna ?

  • @bezaTal
    @bezaTal 3 года назад +5

    Veggies oil 🚫
    Sunflower oil 🚫
    Canola oil 🚫
    Soy been oil 🚫
    Corn oil🚫

  • @እናቴሁሌምከውስጤነሽእወድ

    Thanks 🙏 doctors

    • @yenetena
      @yenetena  4 года назад

      በተለይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ለሚያውቋቸው ሁሉ ይህም መልክት "ሼር" እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለው ። የብዙ ህፃናት ህይወት የብዙ ሰዎችም ጤና ሳያቁት እየተጎዳ ነው

  • @genetdagnachew2123
    @genetdagnachew2123 4 года назад +80

    መቃብራችን የምንቆፍረው በገዛ ጥርሳችን ነው::

  • @kassamikru
    @kassamikru 2 года назад +2

    Tebarek

  • @ነኝመንገደኛ
    @ነኝመንገደኛ 4 года назад +5

    ለካ ይኸ ነው የጎዳኝ እረ በጣም አመሰግናለሁ

    • @yenetena
      @yenetena  4 года назад +3

      በተለይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ለሚያውቋቸው ሁሉ ይህም መልክት "ሼር" እንዲያደርጉ በአክብሮት እጠይቃለው ። የብዙ ህፃናት ህይወት የብዙ ሰዎችም ጤና ሳያቁት እየተጎዳ ነው