እባካችሁ የለበሳችሁትን ልብስ ለቅርቦቻችሁም አትስጡ | እንደባለታሪካችን ወዛችሁ ይወሰዳል

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 29 авг 2024
  • እባካችሁ የለበሳችሁትን ልብስ ለቅርቦቻችሁም አትስጡ | እንደባለታሪካችን ወዛችሁ ይወሰዳል

Комментарии • 276

  • @user-ty4bg3pn8o
    @user-ty4bg3pn8o 4 месяца назад +77

    ወርቅአፈራሁ ይህ እኔም ገጥሞኛል እኔ ቀይሬ ስወጣ ከመኝታ ቤቴ ገብታ ለብሳ ትሄድ ነበር ግን መንገዳችን የተለያየ ነበር እኔ ጠንካራ ባልሆንም ስለእኔ የሚፀልዩልኝ ስለ ነበሩ ለተወሰነ አመት ተፈተንኩ ግን ገዳማት በመግባት በመጠመቅ በመስገድ በፈጣሪ ቸርነት ሂወቴ ተስተካከለ ከዛ በኃላ ጓደኛ እፈራለሁ ተጠንቁ በዚህ ፕሮግራም ትጠቀማላችሁ እናመሰግናለን ወርቅ🙏🏾

    • @meazaassefa
      @meazaassefa 4 месяца назад +8

      ፈጣሪ እንኳን ደረሰልሽ

    • @ethio125
      @ethio125 2 месяца назад

      እኔም ገጥሞኛል ጓደኛዬ አንድ ሃገር ነበር ያገባነው በፊትም አንድ ሰፈር ነበርን ሁለታችንም ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸው ናቸው ያገቡን እሷ የእርሻ መሬት አላቸው እኛ ግን ሰርተን ሱቅ ከፈትን እናቷ ጎራ ብላ ስትጠይቀኝ የሰው ልጅ እንዲህ ይኖራል ብላ ታለቃቅሳለች መጨረሻ ላይ አዲስ ነጠላ ስጪኝ ብላ ቤተሰቦቿ ጋር ሄደች ማሪያም ምስክሬ ናት ሰባት ቦታ እንዳይታወቅ አድርጋ ቆርጣ መለሰችንኝ አጥቤ ሳሰጣ ነው ያየሁት ጎረቤት ጠርቼ አሳየሁኝ ለእሷም አንቺ ነሽ የወሰድሽው ማን ከውስጥ ያነሳል ስላት አልተቀየመችኝም ዛሬ አመድ ላይ ነች ብሰደድም ከእሷ እበልጣታለሁ

  • @asnakechgurmu9148
    @asnakechgurmu9148 4 месяца назад +25

    ሳትጠራጠሩ ሁሉንም ለኢየሱስ ክርስቶስ አሳልፍችሁ ስጡ። ለኔ ሰርቷል።❤❤❤

  • @user-rt5vz1yn3z
    @user-rt5vz1yn3z 4 месяца назад +29

    እኔም ደርሶብኛል ነገር ግን አምላኬና ቅዱስ እስጢፋኖስና ቅዱስ ሚካኤል ፈቱኝ

    • @Tewodros-tm7bs
      @Tewodros-tm7bs 4 месяца назад +4

      Sint amilakoch fetuh?

    • @saronisrael752
      @saronisrael752 4 месяца назад +2

      አምላክ አላለም እስቲፋኖስ እና ቅዱስ ሚካኤል በምልጃቸው አምላክ በምህረቱ አንተ የተዋህዶ ጠላት

    • @derejeassefa9747
      @derejeassefa9747 4 месяца назад

      minayenet amlak new degaf yemifeleg behulet eredat yemikom

    • @11naniyechristiantube
      @11naniyechristiantube 2 месяца назад +1

      Amlakish Kidus Ye Hayalan Hayal Geta Egziabiher nw!!! Simun triw! Egziabeher Fetagn Bey!

    • @Tewodros-tm7bs
      @Tewodros-tm7bs 2 месяца назад

      @@saronisrael752 ye denqoro eminet nuw Ortofake.Egziabher,yayal,yisemal,yazinal,yidesetal...ke Eyesus kiristos Wich wede Wich.

  • @user-cw3qt3xy1p
    @user-cw3qt3xy1p 4 месяца назад +12

    በክርስቶስ እየሱስ አምኖ የተጠመቀ ይድናል የናዝሪቱ እየሱስ በቀራንዮ መስቀል የሞተውን አምላካችሁን እመኑ ሥሙ ሃይል አለው እመን እንጂ አትፍራ እየሱስ ያድናል አእሱ እያለ መተት በኔ ላይ አይሰራም የኔ አበባት አይጥለኝም አያጋልጠኝም እየሱሽስ ያድናል የታደግማል ፣👏👏👏

    • @FancyGT_
      @FancyGT_ 4 месяца назад

      That is right!!! Amen 🙏 Amen 🙏

    • @yosephmersha7885
      @yosephmersha7885 3 месяца назад +1

      ይህንን እጅህን ይዞ የፃፈልህ ማን ሆነና ነው? አጅሬ አይደለምን?

  • @AtinachAtinach
    @AtinachAtinach 4 месяца назад +21

    በዚህ ምክንያት በሀገረ አሜሪካ የምትኖር የአብሮ አደገ እህቴ ትዳሯ ሊፈርስ ነውና ፀዳለማርያም ብላችሁ በፀሎት አስቡልኝ መንፈሱ በእሷላይ እየተናገረ ባለቤቷግን አውቀሽ ነው መንፈስ እሚባል ነገር የለም አያለ በጣም ስቃይ ላይ ናት በወላዲተ አምላክ በፀሎት አስቧቸው!

    • @ethiopialove2772
      @ethiopialove2772 4 месяца назад +3

      ለምን ከቻለች ሀገር ቤት መሄድ ካልሆነ ደግሞ በምታምነው ታቦት ፀልያ ትጠመቅ አባቶችምጋ ትሂድና ይፀልዩላት ፀበልም ያጥምቋት እግዚአብሔር የትም ነው ያለውና

    • @Frey8089
      @Frey8089 4 месяца назад +5

      መድሃኔዓለም ከስዋ ጋ ይሁን

    • @AtinachAtinach
      @AtinachAtinach 4 месяца назад

      @@ethiopialove2772 አገር ቤት ለመሔድ አስባለች ግን ልጆቿን እንዴት ታድርግ ባለችበት ንሰሐ ገብታ ቁርባን መቀበል ትፈልጋለች ንሰሐ አባቷ መጀመሪያ እናንተ ተስማሙ በሚል ምክንያት ንሰሐዋን ሊፈቅዱላት አልቻሉም ቤቷ ግን ማድረግ እሚገባትን እየታገለች ነው የሁላችንም ፀሎት ያስፈልጋታል!

    • @AtinachAtinach
      @AtinachAtinach 4 месяца назад +1

      @@Frey8089 አሜን!!!

    • @MeronAmtat-je8ly
      @MeronAmtat-je8ly 4 месяца назад +2

      የክርስትና ስማችሁን በሚድያ እየተናገራችሁ ---እዲህ ሆን አትበሉ ከቻላችሁ በእምነት ቦታ ለአባቶች ነው መናገር ለበቁአባቶች በገዳም ነው በጸሎት አስቡኝ የሚባለው በሚዲያ ማነው ስለ ማን የሚፀልይ መልክቱን እንኳን ጨርሶ የሚያዳምጥ የለም-ፈጣሪም እርዱኝ እረዳችጟለሁ ነው ያለው

  • @tigistmulugata4336
    @tigistmulugata4336 4 месяца назад +19

    ወይ መድሐኒያለም ያልነቃ ትውልድ ሲሆን እንደዚህ በአደባባይ ይሸወዳል ትንሽ ስለቅዱስ እና ስለ እርኩስ የገባው ቢሆን ይሄ ባለ ታሪክ በሰአቱ በነቃ ነበር ። እግዚአብሔር ከአጋንት እይታ ከደብተራ እና ከጠንቋይ እይታ ይሰውረን ... የኛ እይታ በአጋዕዝተ አለም ስላሴ በመድሐኒያለም እና በክርስቶስ እናት በድንግል ማርያም እይታ ይሁንልን ።

  • @Seble7
    @Seble7 4 месяца назад +27

    ሽንቁሩ ሚካኤል ጸበል ቢሄድ በአንድ 3 ቀን ለውጥ ያያል እግዚአብሔር ጠላቶቻችንን በአጽረ መስቀሉ ይቀጥቅጥልን

    • @abaynewderbew526
      @abaynewderbew526 4 месяца назад

      Yelben nw yetnagershw tebareki kdus Mikael ye swn lej tarik yilewtal le ene abatem enaten kdus Mikael nw ruhruhu degu melak

    • @appus525
      @appus525 4 месяца назад

      የት ነው

  • @savannasav2609
    @savannasav2609 4 месяца назад +18

    መምህር ግርማ ቪዲዮ ላይ አንድ እስራኤል የሚኖር የመንግስት ባለስልጣን የሆነ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ ለድሆች ብሎ ሻንጣ ሞልቶ ልብስ እየወሰደ ይሰጥ ነበር ከዛም በሰጣቸው ልብስ መተት ተሰርቶበት የመምህር ግርማን ቪድዮ በማየት እየሰገደ ሰይጣንን አሸንፎ መንፈስ ሲሸኝለት ታይቷል እግዚአብሔር ይጠብቀን ሰው ሰይጣን ሰይጣን ሰው ሆኗል ።

  • @tsigenigatu3922
    @tsigenigatu3922 4 месяца назад +8

    እውነት ነው አምናለሁ። ነገር ግን ልብሱን ምን እናድርግ ራቅ ብሎ ለነደያን ወይም ለመቆዶንያ ቢሰጥስ፣ መቼም እቃ ከመለወጥ ይሻላል።ስንቱ የሚለብሰው ባጣበት በዚች ድሀ ሀገር ለማን እንስጥ። ?? ፈጣሪ ክፉዎችን እጅ እግራቸውን ይሰርልን አይናቸውን ጨለማ እግራቸውን ቄጤማ ያርግልን ይጠብቀን ይሸፍነን 🙏🙏

  • @mahedermariyam933
    @mahedermariyam933 4 месяца назад +9

    በርታ ወንድማችን እመብርሀን አንደበትህ ላይ ተቀምጣ የኛን ልቦና ከፍታ እንድናስተዉል እንድናዳምጥ ትርዳን

  • @martanigus5734
    @martanigus5734 4 месяца назад +7

    እኔም የእድል መተት የተደረገብኝ ትዳሬ ተበትኖ ስራዬ ከሰው በታች ነበርኩ አሁን በእመብርሃን በቃጥላዋ ንግስት ስራዬም ትዳሬንም መልሳልኛለች ።አሁን የመምህር ተስፋዬ ተማሪ ነኝ

    • @yenantw21
      @yenantw21 4 месяца назад +1

      ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

    • @MeMe-qw5yl
      @MeMe-qw5yl 4 месяца назад

      Ebaksh yet nacew memher tesfaya yamegagut

    • @martanigus5734
      @martanigus5734 4 месяца назад +1

      @@MeMe-qw5yl ለም ሆቴል ወይም ሾላ ከመብራት በታች

  • @SalamSalam-wv9to
    @SalamSalam-wv9to 4 месяца назад +8

    ፈጣሪ ይርዳው ህዝቤ ሰይጥኗል ፈጣሪ ልቦናቸውን ይመልሰው

  • @user-yj8bm3dv1f
    @user-yj8bm3dv1f 4 месяца назад +8

    በጣም ያሳዝናል ግን በመንፈስ የመጣ ሀብት መጨረሻው አይምርም እግዚአብሔር ያዘ አውድቅ ሀብቱን ቢያጣ ነብሱን ግን ያተርፍታል

  • @user-nu8jm1pd2f
    @user-nu8jm1pd2f 4 месяца назад +8

    ❤ እግዚያብሄር ያክብርልን ወርቅዬ ልክ ነህ ብዙ ሰዎች ከነበሩበት የሠላም ህይወትና በድካማቸው ካገኙት ንብረታቸው ተራቁተው እንዲሁም ለበሽታና ለእብደት ብሎም ለሞት የተማገዱ ብዙዎች ናቸው ያሳዝናል ሰው ያከማቸውን በልቶ ሳይጨርስ ሌሎች በልፈታቸው ያመጡትን ወስዶ ለራስ ማረግ ምን ይጠቅማል ያሳዝናል ወድማችን የደረሰበት ነገር ያሳዝናል እግዚያብሄር የፅድቅ አምላክ የፅድቅ ፈራጅ ነው ይፈርድልአል የተበተነው ሁሉ ነገርህ ይመለስልአል አይዞህ ፁም ፀልይ ሱባዬ ያዝ እግዚያብሄር እዲመልስልህ በተቻለህ መጠን ያተ የተወሰደብህ እድልህ ስለሆነ ይህ አተላይ ያለው መፈስ ግብር እየተሰጠው የሚታደስ ስለሆነ በተጫለክ መጠን ፀበል መጠመቅ ቢቻልክ መምህር ቀሲስ ሄኖክ አባ ሳሙኤል ጋር ኤደክ ይህ እድልህ እዲመለስ እና ሴጣኑም ስራው እንዲፈርስ የባቶች ቢፀልዩልህ መልካም ነው ፀጋ ሁሉ ልዩ ልዩ ነው ይላል ታላቁ ቅዱስ መፅአፍ አጋንትን የመለየት ስልጣን የተሰጣቸው አባቶች ስላሉ በተረፈ አይዞህ በርታ ነፃ ትወጣለህ ፁም ፀልይ

  • @rebkagedion3023
    @rebkagedion3023 4 месяца назад +7

    የዲያብሎስን ስራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ

  • @user-dy6ls1to8l
    @user-dy6ls1to8l 4 месяца назад +8

    ይገርማል እኔ ልብሴን አላውቀውም ልብ የለኝም ልብሴን አላውቀውም እኔጋ ጓደኞቼ ሢመጡ ልብሴን ይለብሡታል አይመልሡም ይኸው እድሌ ባዶሁኝ ለመሥገድ ለመፀለይ እጥራለሁ ወር ተግቸ ብሠግድ ብቀጠቅጥ ሁለት ወር ያሥተኛኛል እራእይ ያሣየኛል ግን መትጋት አቃተኝ አሁን አሁንማ ትካሻየን የተሸከመኝ ያለ እሥኪመሥለኝ ለመፀለይ እደክማለሁ እባካችሁ ወለተመሥቀል ብላችሁ በፀሎት አሥቡኝለሠው ሥለመናፍት ሥመክር ሣሥተምር እውላለሁ በሌግን የአምልኮ ህይወት እንደ ተራራ እራቀኝ

    • @meazaassefa
      @meazaassefa 4 месяца назад +1

      በርቺ ፈጣሪ ይርዳሽ

    • @betyamb7138
      @betyamb7138 4 месяца назад +1

      ልክ እንደ እኔ

    • @user-kp2dk7vm5h
      @user-kp2dk7vm5h 4 месяца назад +2

      ayzoshi ema gedam gbi letewesene gzi

  • @user-zl3tn1nf1d
    @user-zl3tn1nf1d 4 месяца назад +9

    አኦ እውነት ነው እኔ በግሌ ህያው ምስክር ነኝ በቅንነት ሰጥቼ የተፈጠረው ይከብዳል ጆሮ ያለው ይስማ ድራማ አይደለም የደረሰብኝ።

  • @Yedingillij2127
    @Yedingillij2127 4 месяца назад +7

    የመምህር ተስፋዬ ተማሪ ነኝ ፀጉሬን የምትሰራ ሴት የለበስኩትን ሱሪ ወደድኩት ስትለኝ እኔ ደግሞ ወደመጣሁበት ልመለስ ሰለነበረ ስሔድ ይሰጡሻል ብያት ዘመዶቼ አጥበው ሰጧት ብዙም ሳይቆይ በህልሜ የፀጉር ቤቱ በር ጠቦ አላስገባኝ ብሎ አየሁ 2 ዓመት ተኩል ይሆነዋል ወርቅ በእግዚአብሔር በምትወደው ለመምህር ተስፋዬ አሰፈታው 🙏

  • @azfarabrha8735
    @azfarabrha8735 4 месяца назад +4

    አለን የመምህር ተስፍየ ልጆች እየሰማን ነው

  • @blackhabeshawit5954
    @blackhabeshawit5954 4 месяца назад +3

    ሌላ አልፈልግም እራሱን የለበሳቹትን ካሉ ትልቅ ችግር አለ ማለት ነው እግዚአብሔር ልባችንን ይግለጥልን 🙏አባቴ

  • @gdhhdh3718
    @gdhhdh3718 4 месяца назад +8

    እዉነት ልክ ነህ እኔ ሙስሊም የኚ ትምርትህን ተከታታይ ነኚ አክባሪህ ነኚ ወርቁዩ የኔ ወርቅ

  • @SaraSara-du4fm
    @SaraSara-du4fm 4 месяца назад +1

    እየሱስ ጌታ ነው

  • @zeetafesse732
    @zeetafesse732 4 месяца назад +3

    ወርቅእፈሪሁ በርታ. በጣም ጠቃሚ ነዉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  • @SesenBrhanu
    @SesenBrhanu 4 месяца назад +3

    እህ !ኣዎ የመምህር ተስፋየ ተማሪወች ይገባናል ሁላቹ እድሜና ጤና ይሰጣቹ

  • @seniethiopia796
    @seniethiopia796 3 месяца назад

    ይሄ የኔ ታሪክ ነው የመስለኝ ግን የድንግል ማርያምን ልጅ የያዘ ግን ይንገዳገድ ይሆናል እንጂ ውድቆ አይወድቅም እመን ፈጣሪህን

  • @Hanan-jx1zp
    @Hanan-jx1zp 4 месяца назад +4

    የገረመኝ ነገር የተማርሁበት እኔም አላምን ብዬ ነበር ሀብናም ናቸው ግን የኔ የለበስኩትን ወሰዱን ሀብታም ናቸው አላምንም ብዬ ነበር ግን ዛሬ ተረዳሁ ክበርልን ቀጥልበት

  • @user-qv1jw5gt5p
    @user-qv1jw5gt5p 4 месяца назад +1

    እኔም ተቸገርሁ ጌታሆይ ክፉውን አርቅልን ለሰሪዎች ልቦና ስጣቸው ከመቅጠር ወደ ቅጥረኝነት ገባሁ 😢

  • @user-cs4nq9qr8i
    @user-cs4nq9qr8i 4 месяца назад +6

    አዎ እንቢ ያለው ላቡ ያለበትን ልብስ ለማስመተት ስለፈልገው ነው
    ወንድማችንም እግዚአብሔር ይርዳህ በርታ ወርቅዬ በርታ

  • @romandeneke1651
    @romandeneke1651 4 месяца назад +1

    ሁለት ልብስ ያለው አንዱን ለሌላው ይስጥ የሚለውስ ይህንን ፈርቶ ሰው ለችግረኛ ላይሰጥ ነዋ የሚጠብቀን ጌታ የት ሄዶ ነው በእስራኤል ላይ አስማት ምዋርት አይሰራም እኛ እራሳችንን ጠብቀን አንችልም ደግሞ ሰው ወደ እግዚአብሄር መጠጋት ነው ያለበት በክርስቶስ ደም መሸፈን ነው በእርሱ ማመን ነው ድግምት በድግምት አይጠፋም በግላችን እምነታችንን ማጠንከር ነው አለም በክፋት ተይዛለች ይላል የእግዚአብሄር ቃል እኛ በእርሱ ካመንን ድግምቱ ጥንቆላው አይሰራም በአንቺ ላይ የተሰራ መሳሪያ አይሰራም ይላል የእግዚአብሄር ቃል መፍትሄው ወደ ጌታ ኢየሱስ ተጠግቶ ማምለጥ ነው

  • @serkegesese5353
    @serkegesese5353 4 месяца назад +2

    ይድናል ከፈጣሪ በላይ አንዳች ነገር የለም ፈጣሪ ሁሉንም ወደ ነበረ ይመልስለታል

  • @solomon9058
    @solomon9058 4 месяца назад +2

    ❤❤❤❤ ወደ በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሄድ ንገረው በአጭር ቀን ለውጥ ያመጣል ❤❤❤❤

  • @user-qz3sz9vs1b
    @user-qz3sz9vs1b 2 месяца назад

    በእየሱስ ሰም ሰራቸው ይፍረሰ

  • @ZdKebede
    @ZdKebede 4 месяца назад +2

    አምላካችን እግዚአብሔር ይድረስለት 😢😢እግዚአብሔር ይድረስልን በደረሰብን ሁሉ አመስጋኝ እንጂ አማራሪ እንዳንሆን ይርዳን አሜን

  • @user-wg9ki3ms7k
    @user-wg9ki3ms7k 4 месяца назад +1

    እናመሰግናለን ወርቅ ቅዱስ አማኑኤል ይጠብቅህ ይጠብቀን አሜን

  • @Maria_Henock
    @Maria_Henock 4 месяца назад +2

    አቤቱ ማረን ፍቅርና እምነት ጨርሳ ከምድር ላይ ጠፍች።

  • @marrym8549
    @marrym8549 4 месяца назад +7

    ወንቅእሸት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ይሂድ ተፈዉሶ ይመጣል ሀብቱም ይመለሰለታል ታምራዊ ገዳም ነው እኔም እህቴ እንደዚህ ገጥሞዋት ነበር እዛሂዳ ዳነች በኔ ይሁንብህ ያሳዝናል😢😢😢

  • @love27210
    @love27210 4 месяца назад +4

    ልክ ነህ እኔም እድል እንደሚወሰድ የወኩት በአንተና በመምህር ተስፋዬ ጋር ባደረጋችሁት ቃለምልልስ ነው ጓደኛዬ አንዴ ቀሚስሽን ወደድኩት አንዴ መሶብሽን ወደድኩት ትለኝ ነበረ አዲስ ገዝቼ እሰጥሻለሁ ስላት ያደረግሽውን ነው የምፈልገው ትለኝ ነበር መጨረሻለይ ግን ሻርፔን ወሰደች እግዚዓብሔር ግን ልብን የሚያይ አምላክ ስለሆነ የቀጣትን ቅጣት ደውዬ ብነግርህ ደስ ይለኛል

  • @befikirdessalegn8135
    @befikirdessalegn8135 3 месяца назад

    እኔም በደዚህ አይነት ጣጣ ገና ከሙሽራ ቤት ተፈትነን ነበር ግን ሀያሉ አምላክ አዳነኝ ሰመአቱ ገርጊስ ቅዱስ ሚካኤል ሰመአቷ ቅድስት አርሴማ ተረባርበዉ በፀበል በድጋሚ ሰዉ ሆኛለዉ ተወልጃለዉ ❤❤🎉🎉🎉

  • @emu4176
    @emu4176 4 месяца назад +2

    እኔ ለስንቱ ነው አማረኝ ሲሉኝ እምሰጣቸው ማበጠርያዬ ሳይቀን ለዛ ነው እየለፋሁ ዜሮ የሆንኩት እረ አምላኬ በቃሽ በለኝ ድካም ብቻ አሁንማ ደከመኝ😢😢😢

  • @belayneshabebe7632
    @belayneshabebe7632 4 месяца назад +2

    የሚገርም ነዉ! እናመሰግናለን ወርቅ አፈራሁ! በጣም ጠቃሚ ኢንፎርሜሽን ነው የሰጠኸን!
    እኔ ነዋሪነቴ ዉጭ አገር ነዉ አገር ቤት ስሄድ ያለኝን ልብስ ሁሉ አራግፌ ነበር የምመጣዉ እናቴ ግን ሁሌ ጥቆጣኝ ነበር ተይ የለበስሽዉን ልብስ ወዝሽን ለሰዉ አትስጪ ጥሩ አይደለም ትለኝ ነበር አይ እማዬ ደግሞ ምን ችግር አለዉ እላት ነበር አሁን ነዉ የገባኝ! ከባድ ነው እግዚአብሔር ይጠብቀን 🙏🏽

  • @hiwet7-12y
    @hiwet7-12y 4 месяца назад +5

    እግዚአብሔር ይድረስለት

  • @tigistteka7896
    @tigistteka7896 4 месяца назад +3

    የኔ የሚገርመው የገዛ የአጎቴ ልጅ ከኔ የበለጠ ኑሮ ያላት ናት ቤቶ ሲሔድ የለበስኩትን ቲሸርት ያምራል ብላ ወሰደች ግንለብሳው አታውቅም ባጋጣሚ እሷ ወደውጪ ለመሔድ ስትል ቤቶን ጠብቂ ስትለኝ ከምቀመጥ ብዬ መይታ ቤቶን ሳፀዳ አልጋስር ከብዙ ስራስር ተጠቅልሎ አገኘሑት እሷም ወጪ ወጣች እኔግን ሑልጊዜ ሳስባት ይገርመያል እኔ ግን ስራም መስራትም ማግባትም ሑሉነገሬን ጠፋ እግዚሐብሔር ጤነያነኝ

  • @Emanmdawy
    @Emanmdawy 3 месяца назад

    ያረቢ ከሱ ትምህርት ኮሜንታተሮች እራሴን አሳመመኝ

  • @geteneshtamene9807
    @geteneshtamene9807 3 месяца назад

    ፈጣሪዬ እባክህ ልቦና ስጠን😢😢😢😢😢😢😢

  • @mekdesdesta6256
    @mekdesdesta6256 2 месяца назад

    መምህር እኔ በልጅነቴ ነው ግቢያችን ተከራይታ የምትኖር ጓደኛዋ ነች የለበሰኩትን ሹራብ ለቤተሰብ እንዳልናገር ነግራኝ ወሰደችብኝ ይሄው አለሁ እየተመሠቃቀ ህይወቴ😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @meseretwoaldegorgis9602
    @meseretwoaldegorgis9602 4 месяца назад +1

    አግዚአብሔር ይመስገን ወንድማችን ወርቃፈራሁ
    የምትለው አዉነት ነዉ አኔ በየዋህነት ልብሴን ከወደድት አዉልቄ ነዉ የምሰጠዉ በጣም ይገርማል

  • @AmelworkyemerBesher
    @AmelworkyemerBesher 2 месяца назад

    ኑሪልኝ እግዚአብሔር ብርክ ያርግህ ብዙ ተማርኩ ብናፍቆት ነው የምጠብቀው

  • @samrawitnegatu6313
    @samrawitnegatu6313 4 месяца назад +1

    ይገርማል በጣም ብዙ ነገር አስታወስኩ አንድ ቀን ቦዲሽን ወደድኩት ብላ እዛው መንገድ ላይ አውልቀሽ ካልሰጠሽኝ ስትለኝ አይ ሌሎች አሉኝ የሰራዋቸው ስራ ቦታዬ ቅርብ ስለነበር ነይ ልስጥሽ ብላትም እምቢ አለችኝ እናም እኔ በቃእሺ እቤት ገብተን ባይሆን ልስጥሽ ብዬ አውልቄ ሰጠዋት ግን ከዛ ቦሀላ ጋርመንቴንም ዘግቼ ብዙ ችግር መከራ ልጆቼን መደብደብ ባሌን መጨቅጨቅ አረ ቡዙ ነው ብቻ መፀለይ ዋናው ነገር ነው

  • @user-zq4in3ru3w
    @user-zq4in3ru3w 4 месяца назад +7

    ሰላም ወርቃፈራሁ፡ ኢቺ፡የነገርከን፡ምን፡አላት፡የኔ፡ታሪክ፡ አንድ፡ሺ ፡ ገፅ፡ አይበቃውም ፡፡አንድቀን፡አገኝሐለው።አሁን ፡ግን፡ ሥላሴዎች፡ምረውኛል።

  • @sunshinebekelebekele9702
    @sunshinebekelebekele9702 4 месяца назад

    ወንድሜ ብዙ ግዜ እከታተልሀለሁ በጣም እወድሀለሁ ሰለ መልካም ምክርህ እና እኔ በስደት ነው ያለሁት ብዙ ችግር ሰላለብኝ ባማክርህ ሰልክህን ባገኝ ሰለ በእግዚአብሔር ሰም እማፀንሀለሁ

  • @mantegeboshbaddo9214
    @mantegeboshbaddo9214 4 месяца назад

    እግዚአብሔር ይስጥልን ወንድማችን ትልቅ ትምህርት ነው ያስተማርከን እድሜና ጤና ይስጥህ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @AbiyAhemdundected
    @AbiyAhemdundected 4 месяца назад +3

    ውንድማችን እግዚአብሔር ይባርክህ የባሌ እህቶች በጎርጢ ነው የሚያዩኝ እንድዝህ አይነት ለያድርጉብኝ ስለሚችሉ ብየ ኢትዮጵያ መሄድ አልፈልግም

  • @user-mv5jr7rl9r
    @user-mv5jr7rl9r 4 месяца назад +1

    ከመግደል ያልተናነሰ እኔ ግን ፈጣሪ እድሜ ና ጤና ይስጠኝ እንጂ እነሱም የኛን ስቃይ ሳያያት እንዳልሞት

  • @fyry8481
    @fyry8481 4 месяца назад +12

    ሠላም የክርስቶስ ቤተሰቦች እንደምን አመሻቹሁ ላይክ አድርጊ👍👈

  • @firehiwotworku2144
    @firehiwotworku2144 4 месяца назад +1

    Thank you my brother God bless to you 🙏

  • @woyintube617
    @woyintube617 3 месяца назад

    ያኔ ጉወደኘም እኔ ያላበስኩትን ሁሉ የምሪብሻል ስጭኝ እያለች ትወስድ ነበር አሁን ለይ ጥየቄ ይሆንብኝ ነበር እኔ እቤት ስሳራ አኮራፈችኝ ብቻ ብዙ ነገሮች አየዉ ፈጣሪ አይጣለኝ እንጅ ወዳ ስደትም ስመጣ እኔ ጋር ይሁንልሽ ብለ ሁሉንም ወሰደችዉ 🙏🙏🙏🙏🙏

  • @rahelhailu4085
    @rahelhailu4085 4 месяца назад

    አንተን ያነቃ አንቅቶም ለኛ ያተረፈህ ቸሩ መድሀኒዐለም የተመሰገነ ይሁን❤ፊትለፊት ያስቀመካት እመብርሀን ከ ጠላት ሴራ ትሸፍንልን❤

  • @abebaembiale3452
    @abebaembiale3452 4 месяца назад +1

    ስትጉድአለ ወድማችን እፍፍፍፍፍፍፍ እግዚያብሔርይፍታን።😢😢😢😢😢😢😢😢

  • @meremanasir4147
    @meremanasir4147 4 месяца назад +3

    ሰላም ወርቃፈራዉ እኔ የሆነግዜ ከዉጭ ወደ ሀገር ሄጄነበር የቅርብ የምለዉ ሰዉ ጋ ቤት በሱመንገድ የተሰራ ነበር ግን እኔብዙብሮችን አጥፍቶብኛል ለዛ ብዬ ወደሀገር ስሄድ አልነገርኩትም ነበር ከዛ መጥቻለዉ ስለዉ ደነገጠ ከዛ ቡሀላ ግን ቨሆነ አጋጣሚ ቶሎ ተመለስኩ ጉዳዩ ሳያልቅ ከዛ እንደነገ ልበር ማታደዉሎ የስልክሽን ቻርጅ አስቀምጪ ልኝ አለኝ እኔም ሌላ እገዛለዉ ብዬ በሰዉ እንዲደርሰዉ አስደረኩ ከተመለስኩ ቡሀላ ግን ሁሉ ነገሬ ተመሰቃቀለ ከትዳሬም ተፋታዉ ሰዎች ሁሉ ራቁኝ ከዛቡሀላግን ልጁ ሸሸኝ በስልክ ቁጥርህን ባገኝ ሙሉ ታሪኩን እነግርሀለዉ

  • @user-vv8vz2un8j
    @user-vv8vz2un8j 4 месяца назад +3

    ወይ ፈጣሪ ደግሞ ይሔም አለ። የተለበሱ ልብሶቻችንን በጎዳና ላሉና ለተቸገሩ ለመስጠት ብንፈልግ እንዴት ልንሆን ነው ታዲያ ልብሶቹ አይጣሉ??

    • @tsigetadele1507
      @tsigetadele1507 2 месяца назад +1

      ayedelem eteb aregen lemayaweken letecheger mesetet new lemiyawekut sayehon lemayakut mestet

  • @user-zg8ol4ze5y
    @user-zg8ol4ze5y 4 месяца назад +4

    ከመተት ለማምለጥ በቸኛው መንገድ አባቶች ሳይሆን ጌታ እየሱስን እንድግል አዳኝ አድርጎ ይቀበል ይድናል ለአንተም ያስፈልግሀል ።

    • @MayoshaTa
      @MayoshaTa 3 месяца назад +1

      ትክክል❤ ኢየሱስ ብቻውን ያድናል።

  • @tigisit2534
    @tigisit2534 4 месяца назад +1

    ወርቅዬ እኔ አረፈድኩኝ እኔም እህቴም ፓንት ሳይቀር ነው የሰጠን ይሄው ጸበል ስገባ የስብና መንፈስ ይላል ደሞ ሳይሸኝ ተከልክለን አረብ ሀገር ምጥት 🥹🥹አስር ዓመት የባከነ ህይወት ብር. አስቀምጥ ይጨንቀኛል 😭😭😭😭😭

  • @blackhabeshawit5954
    @blackhabeshawit5954 4 месяца назад

    ይሄ በሁላችንም ሕይወት ውስጥ ያለ ከባድ ችግር ነው ከእህቴ ችግር በኋላ የሴት ጓደኛን እንድታርቅልኝ ኪዳነምህረት እናቴን ሁሌም ስለምናት የማይበጁን አራቀችል በራሷ መንገድ ተመስገን እኔም አለው
    እነሱም መኖር የማይባል ሕይወት ይኖራሉ

  • @user-qm2gv7zl7n
    @user-qm2gv7zl7n 4 месяца назад

    ቃለሂወት ያሰማልን ወንድማችን

  • @harrieelias5756
    @harrieelias5756 4 месяца назад

    I am a victim of such METET, by co-worker lady, again by my house maid.
    This is extremely common demonic power that has been going on in Ethiopia
    However, it got worse when the agamewotch came to power.
    I am grateful and thankful for your daring honesty talking about a subject most people go through but it is kept secret or hash hash.
    This video is an eye opener for everyone in Ethiopia.
    Thanks again. God bless you!

  • @abigailgirum8928
    @abigailgirum8928 4 месяца назад

    Beautiful message

  • @user-ge3lh6gl4v
    @user-ge3lh6gl4v 4 месяца назад +4

    ልብሱን አጥበን ብንሰጥስ?

  • @KedirAli-lz8ox
    @KedirAli-lz8ox 3 месяца назад

    ፈጣሪ ይጠብቅ

  • @uaeuar50
    @uaeuar50 4 месяца назад

    ልክእደኔትዳር፡እፍፍፍፍፍፍፍ፡የኔህይዎትአሁላይልክእደዝህነው፡ለየምለብሰውምልብስ፡ታሥቀመጥኩበትተቀዶ፡አዱንልብስ።ግማሹንቀደውአኑረውትአገኘሁት፡አሁላይበጣምእነገርላይነውያለሁት

  • @alemtsehayejigu8alemtsehay825
    @alemtsehayejigu8alemtsehay825 4 месяца назад +1

    በትክክል እኔ የገጠመኝ ነዉ በተደጋጋሚ ለዛዉ ከቅርብ ቤተሰቤ

  • @shasheayele3783
    @shasheayele3783 3 месяца назад

    ጠንቃይ ለጠንቃይንእየሄዱ የ35 አመት የስደት ባሌን አፍርስው ሌላ አጋቡት አንድ ወር ተኩል ሆነው በሀዘንላይ ነኝንአመስግናለሁንወንድሜ ለምክርህ

  • @bfhdhhjjejdjh
    @bfhdhhjjejdjh 4 месяца назад +4

    የኔም ትዳር የፈረሰው በቤተሰቦቸ ምክኗት ነው 😢😢😢ልጂ ከወለድን ቡሀላ ተለያየን😢😢😢😢

    • @savannasav2609
      @savannasav2609 4 месяца назад +1

      በዚህ ፆም ሱባኤ ግቢ እግዚአብሔር መልስ አለው።

  • @helensahle6071
    @helensahle6071 4 месяца назад +1

    Betam yikirta Ethiopia eko sint teamir tselot betekirstian ehen Hulu gubae ahun eko Ethiopiawi sibal yasferal . Mechem yedha amlak yfred😢😢😢😢😢

  • @user-bz9ss5ue4r
    @user-bz9ss5ue4r 3 месяца назад

    ❤❤❤❤ አባቴ እግዚአብሔር ይጠብቅክ ላወራክ ምፈልገው ነገር አለ እንዴት ላግኝክ

  • @user-kf5ek1wf7q
    @user-kf5ek1wf7q 2 месяца назад

    ይህ ልጅ ለእህቱ ቤት ገዝቷል አንድ ባለፈው የተሰራው ያየሁት እህቱን ደበድቦ እናት አባት ከአወረሳቸዉ ቤት ያወጣ ነበር

  • @mekdesjaleta522
    @mekdesjaleta522 4 месяца назад

    ወረቅአፈራሁ እናቴ የነጠላዋን ቁጨት ዘርፉን ከጫፍና ከጫፍ ቆረጡት ከዛ በኋላ እናታችን ምንም አይነት አዲሰ ልብሰ እንዲሁም የፀዳ ልብሰ አያሰለብሳትም እንዲሁም ልጆችዋን ሁሉ ጠላችን መግባባት አቃታት

  • @abigailgirum8928
    @abigailgirum8928 4 месяца назад

    Thanks very much brother information

  • @mesfinmersha7769
    @mesfinmersha7769 4 месяца назад +2

    ወርቅዬ አንዳንዴ እግዚአብሄር ለምን ድክመታችንን እያወቀ ለምን ለድክመታችን አሳልፎ እንደሚሰጠን ግራ ነው ሚገባኝ ቆይ አንኳኳ እከፍትልሀለው ጠይቀኝ እሠጥሀለው ለምነኝ ታገኛለህ እያለኝ ስጠይቅ እማይሰጠኝ ሳንኳኳ ለምን እንደማይከፍትልኝ ከዛ ደሞ እድሌ በማንም ጠንቋይ ሲሰረቅ ዝም በቃ ዝም ለምን ስትል በቃ ዝም ለምን ስለማንም ስለምንም አይመለከተኝም ብቻ ግን እግዚአብሄር ለኔ እሚያደርግልኝን መልካሙን ነገር ለባልንጀሮቼ ማለትም ለወንድሞቼ በስራ ቦታዬ ላስቀየሙኝና ላስቀየምኳቸው አለቀ ከዛ በዘለለ በእግዚአብሄር አርአያ ለተፈጠረ ለማንኛውም ፍጡር ቅንጣት ታክል መጥፎ ነገርን አልመኝም በቃ በሂወቴ እግዚአብሄርን እና እናትና አባቴን ወንድሞቼን even ጠላቶቼን እሚያሳዝን ምንም ነገር ማየት መስማት መናገር ማድረግ አልፈልግም ታዲያ ምንድነው በግድ ተጎትቼ የመንፈሳዊውም ይሁን የአለማዊው ዝባዝንኬ በህይወቴ የሚከሰተው ለምንድነው ደደብ የሆኑ ሰዎች የህይወቴ አካል የሆኑት ለምንድነው እድሌ አእምሮዬ የመሳሰሉት እስኪወሰድ ልክ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ዲያብሎስ የፈለገውን መርጦ ለራሱ መስዋት እስኪያደርገን ድረስ ወርቅዬ እኔ ግራ ነው የገባኝ

    • @ituneethiopia8427
      @ituneethiopia8427 4 месяца назад +2

      አይዞህ! ለምን እንደተፈተንክ የሚገባህ አንድ ቀን ከስራትህ ፈጣሪ ሲፈታህ ነው።።። ለምን ፈጣሪን ሰቀሉት ምንም በደል ሳይኖረው? ይሄን አስብ በቃ ፅበል ተጠመቅ, በንስሀ ተመላለስ, አንድ ቀን ይፈታሀል።። ደሞ እኮ እዚህ አለም የምንኖረው ስንቅ ይዘን ወደ ሰማይ ለመሄድ ነው እነሱ ግን በሰማይ ቤት የላቸዉም በዚህ አንተ ተሰቃየህ በላይ እነሱ ዘላለም ይሰቃያሉ። ይሄ የነሱ ሀገር ነው ያንተ ሀገር በሰማይ ነው ስለዚህ በምድር ለሰማይ ቤትህ ስንቅ አዘጋጂ

    • @zeetafesse732
      @zeetafesse732 4 месяца назад +2

      ወንድም. ያለ ክርስቶስ በቀር እንድ እንኳን በፍፁም የለም ብርሀን እለ ጨለማ እለ መልካም እለ ክፉ እለ መተት የሚያደርግ የሀይማኖት ስም እልፍ እይኖርበትም ዉደፈተናእታግባን ብለን የምንፀልየው. ፈተና ስላለ ነው ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ጠላታችሁ ዲያቢሎስ ዙሪያችሁን እያገሳ ይዞ ሪል. ሲል ጠላት ሆኖ የሚመጣው ስው ነዉ መንፈስ ነው የሚወርስው በዚች እልም ስትኖሩ ፈተና እለባችሁ. ትጉ ፅልዩ. ተመስገን የማይተው እም ልክ የበርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ ፀበል ሄዶ የማይድን የለም

    • @zeetafesse732
      @zeetafesse732 4 месяца назад +1

      እመን እትጠራጠር

    • @emebetzewde7492
      @emebetzewde7492 4 месяца назад +2

      እግዚአብሄርማ ሁሉን ስጠን ሁሉንም አደረገልን መጥፎው የዲያብሎስ ነው መልካሙ ሁሉ ጥሩው ነገር ሁሉ የእግዚአብሄር ነው መምረጥ የኛ ፋንታ ነው እግዚአብሄር ግን የማይወቀስ የማይከስስ ፍፁም እውነት ፍቅር የሆነ አምላክ ነው የማይሳሳት ይችን ምድር ተጠቅመንባት ስርተን እንድንበላባት ስጠን እኛ ግን ይኽው የክፋታችን ጥግ ሁሉ የስጠንን በመስቀል እስከ መስቀል አደረስን እርሱን ስንከተል ደግሞ ፈተናችንም ይበዛል የፃድቃን የስማእታት ህይወት ምሳሌ ይሁነን

    • @savannasav2609
      @savannasav2609 4 месяца назад

      የፃፍከው ፁሁፍ እራሱ ከእግዚአብሔር የሚያርቅ ሰይጣንን የሚጠራ ነው። ፃድቁ እዬብ ምን አጠፋ?

  • @AnchialemHailu
    @AnchialemHailu 4 месяца назад +1

    መምህር አንተን መከታተል ከጀመርኩ በኋላ አንድ ነገር አስታወስኩ ምንመሰለክ ቤት ውስጥ አንዲት ድመት መጥታ የባለቤቴን ቁምጣ ከልብስ መሀከል መርጣ ቀጥብላ ወደ መጣችበት ቤት ወሰደችው እኔም ይህ ሀሳብአልመጣልኝም ግን ልብሱን ለማስጣል ሞከርኩ ወስዳ አደረሰች ቤቱከአጠገባችን ስለነበር የተወሰነ ቆም ብልም ተቀብለው ዝም አሉ።

    • @Emanmdawy
      @Emanmdawy 3 месяца назад

      ያረቢቢ ፊልምም ነው እየሆነብኝ ያለው አላሁመ በእዝነትህ ጠብቀን

  • @samirasam7016
    @samirasam7016 4 месяца назад

    እኔ አድናቂህ ነበርኩ የአጥማቂያን ተከተይ ሁነክ ሰላየሁህ በጣም አዘንኩ😢

  • @hm4004
    @hm4004 4 месяца назад +1

    What about those wearing salvage closes?

  • @alemwoin3630
    @alemwoin3630 4 месяца назад

    Werkaferauye yehe Tarik betam mulu bemulu yene Tarik new zare new yenkahut yebanenkut. Betam thank you yehew leaedet bemalawekew huneta enoralu

  • @user-ng7ki8xk7p
    @user-ng7ki8xk7p 4 месяца назад

    ምን ማድረግ አለብን ነው የተደረገው የኔም እድል የባለቤቴ ጤና ምስቅልቅል እንድሆን ተድርጎል ብዙ ነገር ይጠፋኛል ብቻ ሰላም እንዳይኖረን እሱ ለእኔ እንዲጠላ እንዳያም ነኝ አንች ነሽ ያደረግሽ ብኝ ይለኛል እኔ ግን እግዛብሄርን ይዠ አለሁ እንጅ እነሱ ብዙ ነገር አድርገዋል ብች የደብተራ ነገር ይገርማል ሁሉ ነገር በጅምር እንድቀር አድርገዋል ፈጣሪ ይሁነን

  • @ertaerta726
    @ertaerta726 3 месяца назад

    የስው ክፋት ከሴጣን በልጣል በተለይ ደብተራ የተባሉት እግዚአብሔር የረገማችው

  • @user-xs8el3xb9l
    @user-xs8el3xb9l 4 месяца назад

    Wendmachin betam enamesegnalen. Bene yederese new hulum lbsenm wesdew yihew hiwoten azeberarekut ahun hulum gebagni

  • @hussishadamtew4720
    @hussishadamtew4720 4 месяца назад +1

    እግዚአብሄርም በስሙ ያለንን እንድናካፍል፣ የታረዙትን እንድናለብስ የተራቡትን እንድናበላ ያዝዘን የለምን? ኣወቀች መጽሀፍ አጠበች አይነት ሆነብኝ። ወርቃፈራሁ እኔ አፈርኩብህ በዚህኛው ፕሮግራምህ። በቅርቡ ወደጥንቆላው በመዝሙር ታጅበህ እየመጣህ ነውሳ! ወዴት ወዴት?

  • @gudayetessema5939
    @gudayetessema5939 4 месяца назад

    Ewinet new! Egziabher Amlak yimarew!!!

  • @yosephmersha7885
    @yosephmersha7885 4 месяца назад +1

    ዲያቢሎስ ለተቸገሩት በመስጠት እንደሚፀደቅ ስለሚያውቅ የሚጠቀምበት ክፉ ዘዴ ነው!!!

    • @MayoshaTa
      @MayoshaTa 3 месяца назад

      መፅደቅ የሚቻለው ኢየሱስን የነፍስ ጌታ አድርጎ በመቀበል ነው

  • @ephrembarkessa72
    @ephrembarkessa72 4 месяца назад

    ነገሩን ውስብስብ የምያደርገው ይህን አጋንንታዊ ሥራ የምሰሩት የሃይማኖት አባት መሆናቸው ነወ ።

  • @user-uc9nl8vm2v
    @user-uc9nl8vm2v 4 месяца назад +2

    እኔም ተቸግሪያለሁ ጕደኛዩ ከኔ በጣም ትበልጣለች ሆቴል ሁላ አላት እኔ ደም ምንም የለኝም በሀብት ግን የለበስኩት ልብስ ያረኩት ጫማ ቦርሳ በቃ የኔ ሁላ ነገር ትፈልጋለች አሁን ነዉ የገባኝ 😢

    • @efratayirdaw992
      @efratayirdaw992 4 месяца назад

      ንቂ እህቴ የመምህር ተስፋየን ትምህርት አዳምጭ በዩትዩብ

  • @NigstWelde
    @NigstWelde 3 месяца назад

    ኧረረረ ይሄ የኔም ቤት ጉድ ነው ትዳሬ ልጆቼ ብትንትን ብለን እኔም ስደት ነኝ😭😭😭

  • @user-gt1mx3bd5m
    @user-gt1mx3bd5m 4 месяца назад +1

    ወርቅዬ ሠላምህ ይብዛልን ወርቅዬ ከቻልክ የመምህር ተስፋዬን ቁጥር አሥቀምጥልኝ አመሠግናለሁ

  • @user-zt5bz5fy2p
    @user-zt5bz5fy2p 4 месяца назад

    I am it's happens to me I lived 21 years I worked hard very smart but ........ I know who did to me

  • @ayfikercw2460
    @ayfikercw2460 4 месяца назад

    Washer before giving to avoid the problem

  • @user-mv5jr7rl9r
    @user-mv5jr7rl9r 4 месяца назад +1

    መፍቴሄ የምትሉትንስ ለምን አትነገሩንም እኛቤት ደሞ በአባት ወገን አሰያሉ ሰዎች አስረው ነው ያስቀመጡን መፍቴሄውን አስተምሩ😢

    • @savannasav2609
      @savannasav2609 4 месяца назад +3

      ንስሃ መግባት መስገድ መፀለይ ፀበል መጠመቅ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ምፅዋ መስጠት አስራት ማውጣት መጨረሻ መንፈሱን በመቁጠሪያ መቀጥቀጥ ማሰር አትርሳ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ።

  • @user-qk2tk9pl1e
    @user-qk2tk9pl1e 3 месяца назад

    እንዴት ሁሉም ሰዉ አንድ ተደርጎ ይታያል ምን አይነት አስተምሮ ነዉ የሚጣረስ አትስጡ?
    እንዴ የማንጠቀመዉን ለሚለብስ ወይም ለሌለዉ መስጠት ነዉ
    ምነዉ ሰልባጅ ስንገዛ አይደል እንዴ የምንዉለዉ የሌሎችን ወዝ
    ኧረ ተጠራጣሪ አታድርጉን ወደዛ

  • @user-ge3lh6gl4v
    @user-ge3lh6gl4v 4 месяца назад

    በትክክል ነው

  • @hussishadamtew4720
    @hussishadamtew4720 4 месяца назад

    ታዲያ ከተለያዩ አገሮች ተለብሶ በሳልባጅ የመጣውን ልብስ ምን ልትለው ነው? የአሜሪካኖችን ሳልባጅ በመልበስ ወዛቸውን ብንወስድ በቀላሉ እንበለጽግ ነበራ!!

    • @MayoshaTa
      @MayoshaTa 3 месяца назад

      😂😂😂 ነበር❤❤❤❤

  • @user-ki2sb8ti7s
    @user-ki2sb8ti7s 4 месяца назад

    እኔም ደርሶብኛል የባለቤቴ እህት ሙሽራ ሆኜ ለሠርጌ ያደረኩትን ጫማ ወደድኩት ፎቶ ተነስቼ በት አመጣልሻለሁ ብላ ሰጠኃት ከዚያ ጠፋብኝ ገዝቼ እተካልሻለሁ ብላ አለችኝ ከዚያ አፍሬ ዝም አልኩ በቃ ትዳሬም ሁሉ ነገሬ ተመሰቃቀለብኝ ብዙ ነገር ሆንኩኝ አሁን ነዉ የገባኝ

  • @blackhabeshawit5954
    @blackhabeshawit5954 4 месяца назад

    የወሰዱት ሁሉ የራሳቸው አይሆንም እኮ ልፉ ቢላቸው እንጂ 🥲እህህህህ