የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ | የማርቆስ ወንጌል - ክፍል 2 | ፓስተር አስፋው በቀለ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 13 сен 2024
  • የማርቆስ ወንጌል ከወንጌላት ሁሉ ቀዳሚ ነው ብለው ምሁራን ይሞግታሉ። ሌሎች የወንጌል ጸሃፍትም በማርቆስ ወንጌል ተመስርተው ወንጌላትን እንደጻፉም ይባላል። የማርቆስ ወንጌል በአምስት ዐቢይ ክፍሎች ይከፈላል፡፡ በመጀመሪያ፣ ማርቆስ ወንጌሉን የሚከፍተው ስለ ኢየሱስ መሲህነት በ1፥1-13 በሚሰጠው አጭር አዋጅ ነው፡፡ ሁለተኛ፣ የመሲሁን ኃይል የሚገልጠው ሰፋ ያለው ከ 1፥14 - 8፥26 ያለው ትረካ ነው፡፡ ሦስተኛ፣ በ8፥27-30 የሚገኘው፣ አጭርና ሐዋርያት ስለ መሲሁ የሰጡትን ማረጋገጫ የሚያቀርበው መዘውር ነው፡፡ አራተኛ፣ ሌላኛውና የመሲሁን መከራ የሚናገረው ከ 8፥31 - 15፥47 የሚዘልቀው ረጅሙ ትረካ ነው፡፡ አምስተኛ ደግሞ፣ አጭሩና የመሲሁን ድል የሚዘግበው በ16፥1-8 ያለው ነው፡፡ እነዚህን የማርቆስ ክፍፍሎች በበለጠ ጥልቀት እንመለከታቸዋለን፣ በመሲሁ አዋጅ እንጀምራለን፡፡
    ለሌላ ተጨማሪ ትምህርቶች፦
    - https: //www.operationezra.com
    • www.operationezra.com ...
    • www.operationezra.com ...
    © Operation Ezra Bible College

Комментарии • 47