አእምሮአችሁን ሪፕሮግራም ማድረግ (7 ቀናት ብቻ ነው የሚወስደው) ዶ/ር ጆ ዲፔንዛ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 15 сен 2024
  • ብዙ ሰዎች በጠዋት ተነስተው ስለ ችግሮቻቸው ማሰብ ይጀምራሉ.
    እነዚያ ችግሮች ከተወሰኑ ትውስታዎች ጋር የተገናኙ ናቸው እና እነዚያ ትውስታዎች ከተወሰኑ ሰዎች እና ነገሮች ጋር የተገናኙ ናቸው።
    አእምሯችን ልክ እንደ አሮጌ ቴፕ መቅረጫ ነው በየቀኑ ተመሳሳይ ካሴት ደጋግሞ እንደሚጫወትልን።
    አእምሮህ ያለፈው ታሪክ ከሆነ፣ ቀንህን በጀመርክበት ቅጽበት፣ ቀድሞውንም ያለፈውን እያሰብክ እና እየኖርክ ነው።
    እያንዳንዱ ትዝታችን ስሜት አለው እና ስሜቶቹ ያለፉ ልምዶች የመጨረሻ ውጤቶች ናቸው።
    ስለዚህ የችግሮችህን ትዝታዎች ባስታወስክ ቅጽበት በድንገት ደስተኛ አለመሆንህ ይሰማሃል፣ ታዝናለህ፣ ህመም ይሰማሃል።
    እንዴት እንደምታስቡ እና የሚሰማችሁ ስሜት የእናንተ የመሆን ሁኔታ ይፈጥራል, በሌላ አነጋገር, ባህሪያችሁን ይፈጥራል.
    ቀናችሁን ስጀምሩ አጠቃላይ የመሆናችሁ ሁኔታ ያለፈ ከሆነ፣ ያለፈው ጊዜዎ ይዋል ይደር እንጂ የወደፊት ዕጣችሁ ይሆናል ማለት ነው።
    ለምሳሌ ትላንት በሆነ ነገር ተናድደህ ዛሬ ነቅተህ አሰብክበት እና እንደገና ተናደድክ።
    ይህንን ለሁለት ቀናት ማድረጉን ቀጥል እና ሰዎች መጥፎ ቀን እያጋጠመህ እንደሆነ ያስባሉ።
    ለአንድ ሳምንት ያህል ማድረጉን ቀጥል እና ሰዎች አንተ በመጥፎ ስሜት ውስጥ እንደሆንክ ያስባሉ።
    በበቂ ሁኔታ ከቀጠልህ ብዙም ሳይቆይ ቁጣ የባህርይህ አካል ይሆናል።
    ሁሌም የሚናደድ ሰው በመባል ትታወቃለህ።
    ስለዚህ እንደምትመለከቱት, ሀሳባቻችሁ ከእጣ ፈንታችሁ ጋር ግንኙነት አላቸው.
    ይህ ማለት ያለፈውን ማሰብ ከቀጠላችሁ ተመሳሳይ ህይወት መፍጠራችሁን ትቀጥላላችሁ ማለት ነው።
    ሳታውቀው፣ የማትወደውን ህይወት መፍጠር ትቀጥላለህ።
    ብዙውን ጊዜ እንዴት እንደሚከሰት እነሆ።
    ነቅታችሁ ሞባይላችሁን ትይዛላችሁ።
    ኢንስታግራማችሁን ትመለከታላችሁ ፣ WhatsAppachun check ታረጋላችሁ፣ ጥቂት ኢሜይሎችን ወይም ጽሁፎችን ታነባላችሁ።
    ከዚያ ዜናውን ትመለከታላችሁ እና አሁን በመጨረሻ በህይወታችሁ ውስጥ ከሚታወቀው ነገር ጋር የተገናኛችሁ ይመስላችኋል።
    ከዚያ በኋላ, በተከታታይ የተለመዱ ባህሪያት ውስጥ ታልፋላችሁ.
    በተመሳሳይ ጎን ከአልጋህ ትነሳለህ፣ ወደ መጸዳጃ ቤት ትሄዳለህ፣ በምትወደው ኩባያ አንድ ኩባያ ቡና ትጣለህ፣ ፊትህን ትታጠባለህ፣ ትለብሰህ፣ ቁርስ ትበላለህ እና በተመሳሳይ አውቶቡስ ወይም ታክሲ ተሳፍራ ወደ ስራ ትሄዳለህ።
    በመጨረሻም, ወደ ሥራ ትገባለህ እና ተመሳሳይ ስሜታዊ ቦታ የሚነኩ ተመሳሳይ ሰዎችን ታያለህ.
    ስራው ሲጠናቀቅ ነገም ተመሳሳይ ስራህን ለመስራት በፍጥነት ወደ ቤትህ ትመለሳለህ።
    ይህ የአንተ መደበኛ ውሎ ይሆናል እና መደበኛ ውሎ እንደ ኮምፒውተር ፕሮግራም ይሰራል፣
    እና አሁን ፕሮግራም ለማረግ ነፃ ፍቃድዎን አጥተሀል.
    ትዕይንቱን የምታካሂደው አንተ አይደለህም፣ ነገር ግን ድብቁ የአእምሮ ክፍል ላይ ያለው ፕሮግራም ነው።
    35 ዓመት ሲሞላን 95% የምንሆነው እኛ በቃል የተሞሉ የባህሪዎች ስብስብ፣ ስሜታዊ ግብረመልሶች፣ ሳናውቅ የምናረጋቸው ልማዶች፣ ጠንካራ አስተሳሰብ፣ እምነት እና እንደ ፕሮግራም የሚሰሩ ግንዛቤዎች ናቸው። ስለዚህ በ 5% ንቃተ ህሊችሁ ጤናማ መሆን እፈልጋለሁ ፣ ደስተኛ መሆን እፈልጋለሁ ፣ ነፃ መሆን እፈልጋለሁ ትላላችሁ ።
    ነገር ግን ሰውነታችሁ የሚመራው በተለየ ፕሮግራም ነው.
    5% ቱን የአእምሮን ክፍል ከ 95%ቱ የድብቁ የአእምሮ ክፍል ጋር እንዲወዳደር እያደረጋቸሁት ነው።
    ይህ normal ቀጫጫ ሰውን በኦሎምፒክ ደረጃ ክብደት አነሺ ጋር በክብደት ማንሳት ውድድር ላይ እንደማወዳደር ነው። ለውጦችን ማድረግ ባትችሉ እና ወደ አሮጌው ፕሮግራም ብትመለሱ እና ተመሳሳይ ህይወት መፍጠራችሁን መቀጠላችሁ ምንም አያስደንቅም.
    ታዲያ እንዴት ለውጦችን ማድረግ ትጀምራላችሁ? እሺ፣ ከትንታኔ አእምሮ በላይ መሄድ አለባችሁ፣ ምክንያቱም ንቁ አእምሯችሁን እና አና ድብቁ አእምሯችሁን የሚለየው የትንታኔ አእምሮ ነው። እና እዚያ ነው meditation የሚመጣው በmeditation ልምምድ አማካኝነት የአእምሮ wavochን እንዴት መቀየር እና ፍጥነት መቀነስ እንደሚችሉ መማር ትችላላችሁ.
    እና ያንን በትክክል ስታደርጉ, ወደ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ውስጥ መግባት ትችላላችሁ, እዚያም መሰረታዊ ለውጦችን ማድረግ ትችላላችሁ. ብዙ ሰዎች መለወጥ ለመጀመር ቀውስ ፣ ጉዳት ፣ በሽታ ወይም ከባድ ሀዘን ይጠብቃሉ። የጆ dispense መልእክት ይህ ነው።
    መጥፎ ነገሮች እስኪከሰቱ ድረስ ለምን እንጠብቃለን? በህመም እና በስቃይ ሁኔታ ውስጥ መማር እና መለወጥ ይሻላል, ወይም በደስታ እና በተመስጦ ሁኔታ ውስጥ መማር እና መለወጥ. ብዙ ሰዎች 70% የሚሆነውን ሕይወታቸውን የሚያሳልፉት ከእጅ ወደ አፍ በመኖር ነው። በውጥረት ውስጥ ይኖራሉ. ስለዚህ ካለፈው ልምድ በመነሳት ሁል ጊዜ በጣም መጥፎውን ሁኔታ እየጠበቁ ናቸው። በኳንተም መስክ ውስጥ ካለው ማለቂያ ከሌለው ምርጫ ውስጥ መጥፎውን ነገሮችን ፈልገው ይመርጣሉ።
    በጣም መጥፎውን ውጤት የሚያመጣውን ነገር እየመረጡ ነው። ይህ ማለቂያ በሌለው ምግብ እና መጠጦች ሜኑ መመልከት እና በጣም መጥፎውን አማራጭ እንደመምረጥ ነው። እንዲህ ነው የሚሆነው።
    መጥፎውን ክስተት በምታስታውሱበት ጊዜ ሁሉ ክስተቱ እንደገና እየተከሰተ እንዳለ በአእምሯችሁ እና በሰውነታችሁ ውስጥ ተመሳሳይ ኬሚስትሪ ይመረታሉ። ተመሳሳይ የስሜት ምልክቶች ወደ ሰውነታችሁ ይላካል.
    ሰውነትህ ንቁው አእምሮህ ነው፣ በተወሰነ መልኩ። ሰውነታችሁ ልዩነቱን አያውቅም።
    ሰውነታችሁ ክስተቱ በትክክል አሁን እየተከሰተ እንደሆነ ያስባል።
    ብዙ ሰዎች ስለመጥፎው ስሜታቸው በየቀኑ በማሰብ መጥፎ ሁኔታዎችን በየጊዜው እየፈጠሩ ነው። ስለዚህ ያንን መጥፎ ስሜት ለመተው ጊዜ ሲመጣ, በእውነት መለወጥ ትፈልጋላችሁ, ግን ችግሩ ሰውነታችሁ ከአእምሯችሁ የበለጠ ጠንካራ ነው. ሰውነት ለመጥፎ ስሜቶች ለዓመታት ተስተካክሏል.
    ሰውነታችሁ የሆነ ጊዜ አገልጋይ ነበር, አሁን ግን ጌታ ሆኗል. በድንገት ለመለወጥ እና ወደዚያ ያልታወቀ ለመግባት ስትወስን ሰውነቱ አይወደውም። ሰውነታችሁ የጥፋተኝነት ስሜት እና ስቃይን ይመርጣል, ምክንያቱም በደንብ ስለሚያውቀው እና ሊተነብየዉ ስለሚችል. በማይታወቅ ሁኔታ ውስጥ መገኘት ለሰውነት አስፈሪ ቦታ ነው, ወደማይታወቀው ውስጥ መግባት ወደ ጥልቅ ወንዝ እንደ መግባት ነው. ወደ ወንዙ ጫፍ ማለፍ ከተሳካልህ ሰውነት እንደሚሞት ያውቃል። እናንተን ለማቆም የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ለዚህ ነው meditate ማድረግ በጀመርሸ ቅጽበት በድንገት አፍንጫሽን መብላት ይጀምራል።
    ማድረግ ያለባችሁን አንድ አስፈላጊ ተግባር ታስታውሳላችሁ እና ካልታወቀ ቦታ, ከ 20 አመታት በፊት ትውስታ ታገኛላችሁ.
    ይህ ሰውነታችሁ ና ፣ በቃ ተስፋ ቁረጥ እና ወደ ቀደመው አሳዛኝ ህይወታችን እንመለስ የሚለበት መንገድ ነው።

Комментарии • 6

  • @DawedMohammed-ub2hu
    @DawedMohammed-ub2hu 2 дня назад +2

    አሪፍ 👍

  • @hdlidet
    @hdlidet 10 дней назад +2

    ለኔ ነው የመሠለኝ😢🎉❤

  • @yasirmisganaw6833
    @yasirmisganaw6833 15 дней назад +2

    የሚገርም ነገር ነው እስከዛሬ የት ነበርክ ለአመታት አንብቤያለሁ ስምቻለሁ ካንተ ቪዲዮ ያገኘኋቸው እውነታዎች አንድም አላገኘሁም አመሰግናለሁ

  • @yebcihatube6883
    @yebcihatube6883 14 дней назад +2

    በርታ እናመሰግናለን ወንድም 🙏🙏🙏🙏 ቆይ ግን ይሄን ያክል ሰው አይታችሁ ለምን like 👍 አታደርጉም እና አበረታቱት