የደስታ ጊዜ ከጉራጌ እናቶች ጋር ለአረፋ 👏👏

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 7 сен 2024
  • የ 2ተኛ ዙር በተስፋ ነዳ አማካኝነት በማህበራዊ ሚዲያ ቤተሰቦች የመቶ ብር ቻሌንጅ ገንዘብ በማሰባሰብ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።
    በዚሁ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ላይ የዞንና ከተማ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ከሁለት መቶ በላይ ለሚሆኑ አረጋዊያንና አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም የወልቂጤ ማረሚያ ቤት ተቋም በህግ ጥላ ላሉ ጠያቂ ቤተሰብ ለሌላቸው የህግ ታራሚዎች የማዕድ ማጋራት መርሀ -ግብር ተደረገ ።
    በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው እንደገለፁት በጎነት ከፈጣሪው ከሰው ዘንድ የሚያስመሰግን ታላቅ ተግባር ነው ብለዋል።
    መደጋገፍና መተሳሰብ የሰው ልጆች ዋንኛ መገለጫዎች መሆናቸውን የገለፁት ከንቲባው ወጣት ተስፋ ንዳ እና በዚህ መልካም የበጎ ስራ ላይ የተሳተፉ ቤተሰቦች በከተማ አስተዳደሩ ህዝብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
    እንደ መንግስት ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን የተለያዩ ድጋፎች እንደሚደረጉ አንስተው ቀጣይ እቅድ ይዘን ተሻጋሪና በውጤት የተደገፈ ተሻጋሪ ስራ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
    የጉራጌ ዞን አስተዳደር ተወካይ እና የዞን ሰራተኛና ማህበራዊ መምሪያ ሀላፊ አቶ መኩሪያ ተመስገን እንደተናገሩት የኢትዮጵያን ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በዞናችን በርካታ የልማት ስራዎች እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን በተለይ በአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች በመርዳት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የሚያስመሰግን መልካም ተግባር ነው ብለዋል።
    አረጋዊያንና አቅመ ደካሞች መስራት በሚችሉበት ወቅት ሰርተው የኖሩ ግን በቆይታ በተለያዩ በተፈጥሮአዊ እና በዓደጋ ምክንያት የኛን ድጋፍ በሚሹበት ጊዜ ልንደግፋቸው ከጎናቸው ልንቆም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።
    ዛሬ በተደረገው ድጋፍ አቶ ተስፋ ንዳና ከጎሉ ሆነው ሲያግዙት ለነበሩ ቤተሰቦች አመስግነው እንደመንግስት ከዚህ በፊት እየሰራ ባለው የድጋፍ ስራ በማጠናከር የእቅድ አካል አድጎ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።
    የተስፋ ቲቪ ባለቤትና የእማት ጉራጌ ሚዲያ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋ ነዳ እንደተናገሩት እንደ ሀገር የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት " የፍቅር ምሳ " በሚል በኢትዮጵያ በሁሉም ከተሞች አረጋዊያንና አቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ በማጋራት የምንጠይቅበት ነው ብለዋል።
    ከምገባ በላይ ትኩረትና ድጋፍ የሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎችን አቅፈው የያዙ ድርጅቶች በማበረታታት በሌሎች ትኩረትና እገዛ እንዲያገኙ የማስቻል ስራ መስራት እንደሆነም ተናግረዋል ።
    በዛሬው "የፍቅር ምሳ" የአረፋን በዓል ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በእንድብር ሀገረ ስብከት የወልቂጤ የቅዱስ ሚካኤል አረጋዊያን ማዕከል የሚረዱ እና የወልቂጤ ማረሚያ ቤት ተቋም በህግ ጥላ ላሉ ጠያቂ ቤተሰብ ለሌላቸው ታራሚዎች ከ200 በላይ የሚሆኑ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን የምገባ ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን እንዲሁም አልባሳትም ተበርክቷል ብለዋል።
    አቶ ተስፋ አያይዘውም በሁለቱም ዙር "የፍቅር ምሳ" የመቶ ብር ቻሌንጅ ከ1400 ሰው በላይ ከ50 ብር ጀምሮ በማዋጣት እንዳቅሙ ድጋፍ የማድረግ ስራ መሰራቱን አብራርተዋል።
    በቀጣይ ሁሉም ሰው ትምህርት በመውሰድ ማገዝ በምንችለው አቅም ሁሉ እነዚህን አቅመ ደካሞችና አረጋዊያንን እንደግፍ በማለት በዚህ መልካም ተግባር ለተሳተፉ አካላት አቶ ተስፋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
    በመርሀ - ግብሩ ላይ የተሳተፉ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን በተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
    በመጨረሻም ፕሮግራሙ በተለያዩ በኪነጥበብ ስራዎች ታጅቦ ተሳታፊዎች በማዝናናት ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1445 በዓል የአረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በመድረኩ በማስተላለፍ መድረኩ ተጠናቋል ።
    በማለት የዘገበው Wolkite City Administration Government Communication Affairs Office ነው።

Комментарии • 12

  • @marrym8549
    @marrym8549 2 месяца назад

    እናቶቻችን እግዚአብሔር በእድሜ በጤና ይጠብቅልን ❤❤❤❤❤

  • @umhibetulahbntsherefa5672
    @umhibetulahbntsherefa5672 2 месяца назад

    የኔ ውድ ልዕልቶች ረጅም እድሜ ከሙሉጤናጋ ለእናቶቻችን ያረብ❤❤❤❤❤ማም እወድሻለሁ❤❤❤ሁሉንም እናቶች ወዳቹሃለሁ የኔ የዋሆች ኑርልን ጉራጌ በልፅገሽ ከፍታሽ አላህያሳየን የናቁንንሁሉ አላህ ከፍታችንንአሳይልን ለአንተሚሳንህየለምና

  • @samsunga2182
    @samsunga2182 2 месяца назад

    እናቶቼ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
    🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @amanichajm4981
    @amanichajm4981 2 месяца назад

    የተቢ❤

  • @marrym8549
    @marrym8549 2 месяца назад

    ❤❤❤❤❤❤❤

  • @sakeenaahmad5169
    @sakeenaahmad5169 2 месяца назад

    ❤❤❤❤🎉🎉🎉

  • @mahmodshamil8877
    @mahmodshamil8877 2 месяца назад

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @tebarekabas1919
    @tebarekabas1919 2 месяца назад +1

    Nk zeber ya dotenda

  • @fetijegnatube9887
    @fetijegnatube9887 2 месяца назад

    አኸ ኧርጅ አነምድኸ

  • @mercymercy7859
    @mercymercy7859 2 месяца назад

    ❤❤❤❤❤

  • @user-il9ui5vg8x
    @user-il9ui5vg8x 2 месяца назад

    ❤❤❤❤❤

  • @tsedufer5284
    @tsedufer5284 2 месяца назад

    ❤❤❤❤❤