ለክብርህ ካልሆነ መኖሬ
HTML-код
- Опубликовано: 16 дек 2024
- ለክብርህ ካልሆነ መኖሬለክብርህ ካልሆነ (2)
ምን ያደርግልኛል ኢየሱስ በሕይወቴ ካልታየ
ክርስቲያን ተብዬ መኖሬ ለእርሱ ካልተለየሁ/2*
በምድር ላይ እስካለሁ አንተን እንዳከብር
አምላኬ ሆይ እርዳኝ ለክብርህ እንድኖር
ኃላፊውን ነገር ከንቱን ሁሉ ንቄ
ፊት ለፊት እንዳይህ ጌታ አንተን አውቄ
በሥራዬም ሁሉ ከአለም ተለይቼ
መጓዝን ካልቻልኩኝ ኢየሱስን አይቼ
ምን ያደርግልኛል ክርስቲያን መባሉ
ከአህዛብ ተለይቼ ካልሆንኩ እንደቃሉ
የሱስ እንዲሠራኝ ካልተመኘሁኝ
ሕይወቴን በሙሉ ካልለወጠልኝ
መዳኔ ካልታየኝ ካላስደነቀኝ
ለሌላ ሰጥቼ ካላካፈልኩኝ
የነፍሴ እርካታ የኑሮ ትርጉሙ
ጣዕም የሚኖረው ደስታና ሰላሙ
ጌታ ኢየሱስ ሲከብር በመላ እኔነቴ
ያን ጊዜ ሙሉ ነው ክርስቲያንነቴ