የፊልሞና መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ / የፊልሞና መልእክት ለምን ተጻፈ?

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 28 авг 2024
  • በዚህ ቪድዮ አማካኝነት የፊልሞና መጽሐፍን በዐዲስ መንገድ ያጥኑ። ታሪካዊ ዳራውን በማወቅ ስለ ፊልሞና መጽሐፍ ጥልቅ መረዳት ያግኙ እንዲሁም መልእክቱን በሕይወትዎና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎ ተግባራዊ ያደርጉ። በሮም ግዛት ውስጥ የነበረውን ባርነት ጨምሮ የፊልሞና መጽሐፍን ታሪካዊ ሁኔታ ማወቅ ይህን መጽሐፍና መልእክቱን በተሻለ መንገድ ለመረዳት ያግዛል። የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ከኢየሱስ የተቀበልነውን ይቅርታና ዕርቅ ለሌሎች ማሳየት ማለት ነው።
    መጽሐፍ ቅዱስን፣ ታሪኩንና በሕይወታችን ውስጥ የሚያመጣውን ለውጥ በተሻለ መንገድ ለመረዳት እንዲሁም ሥነ ጽሑፋዊ ዐውዱንና ታሪካዊ ዐውዱን ለመረዳት በምናደርገው ጒዞ ዐብራችሁን እንድትጓዙ እንጋብዛችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ሂደት ውስጥ ይህ እጅግ ጠቃሚው ክፍል ሲሆን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብና ኑሮ እንዲኖረን ያግዘናል። የምናዘጋጃቸው ቪድዮዎች በሁሉም ዕድሜ ላይ ለሚገኙና የተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት ደረጃ ላላቸው ሁሉ የሚጠቅሙ ናቸው።
    #ፊልሞና #ዐዲስኪዳን #የመጽሐፍቅዱስጥናት
    www.thebibleeff...
    FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
    INSTAGRAM: / thebibleeffect
    ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
    ምዕራፎች
    0፡00 መግቢያ - ውጤታማ ደቀ መዝሙር አድራጊነት ምንድን ነው?
    0፡27 ለፊልሞና የተላከው ደብዳቤ ኹነት
    1፡14 ባርነት በሮም መንግሥት ውስጥ
    2፡11 ጳውሎስና አናሲሞስ
    4፡04 ተግባራዊነት- የውጤታማ ደቀ መዝሙር አድራጊነት ማሳያዎች

Комментарии • 5

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic  Год назад

    የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች
    1) ማኅበረ ሰቡ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ እንዳላቸው አድርጎ ለሚመለከታቸው ሰዎች ሊኖረን የሚገባው አመለካከት ምን መሆን አለበት።
    2) በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆን ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ምን ልንማር እንችላለን?
    3) ጳውሎስ እንደ አናሲሞስ ያለ ወጣት ክርስቲያንን እንዴት ነው ደቀ መዝሙር ያደረገው? ጳውሎስ እንደ ፊልሞና ያለ በዕድሜ የበሰለን ክርስቲያን እንዴት ነው ደቀ መዝሙር ማድረጉን የቀጠለው? ይህ ለምን የሆነ ይመስላችኋል?
    4) በፊልሞና መጽሐፍ ውስጥ በርግጥም ባርያ የኾነው ማነው? እንዴት?
    5) አንድን ሰው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ምን ያህል ዋጋ ትከፍላላችኹ?

  • @FesumeBafkadu
    @FesumeBafkadu 5 месяцев назад

    Tebarku

  • @endtimesinafaanoromoo
    @endtimesinafaanoromoo Месяц назад

  • @NerdiAsefa-si2jq
    @NerdiAsefa-si2jq 2 месяца назад

    ዋው እዴት ድቅ ነው

    • @thebibleeffectamharic
      @thebibleeffectamharic  2 месяца назад

      ቪዲዮው ለእርስዎ ጠቃሚ እንደነበር በመስማታችን ደስተኞች ነን! በረከት!