ፊልሞና - ወንጌል ይለውጣል፣ ዕርቅ ያወርዳል፤ ማኅበራዊ ግንኙነቶችን ይቀይራል!

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 13 сен 2024
  • የፊልሞና መልእክት በሐዋርያው ጳውሎስ የተጻፈ ግላዊ ደብዳቤ ነው። ይህ መልእክት የተጻፈለት ፊልሞና በቈላስያስ ከነበሩ ባሪያ አሳዳሪዎች መካከል አንዱ ነበር። ፊልሞና አናሲሞስ የሚባል ባሪያ ነበረው። በእርሱና ባሪያው በነበረው በአናሲሞስ መካከል የነበረው ግንኙነት በአንዳች ምክንያት በመሻከሩ አናሲሞስ ተለይቶት ሄደ። አናሲሞስ የሄደበት ምክንያት በግልጽ ባይቀመጥም አንዳንዶች ሰርቆ በመሸሽ ላይ እያለ ከጳውሎስ ጋር እንደ ተገናኘ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ጥፋቱን በመረዳት እንዲያስታርቀው ወደ ጳውሎስ እንደ ሄደ ይሞግታሉ። አናሲሞስ ከጳውሎስ ጋር ሲገናኝ ከእርሱ በሰማው ወንጌል በማመን ክርስቲያን ሆነ። አናሲሞስ በወንጌል ተለውጦ የሚጠቅም ወንድም እና አብሮ ሠራተኛ ሆነ። ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ ለፊልሞና የጻፈበት ምክንያት ፊልሞና አናሲሞስን ይቅር ብሎ እንደ ወንድም እና አብሮ ሠራተኛ እንዲቀበለው ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ሊያዘው ቢችልም በፍቅር ይለምነዋል፤ ፈቃዱ ከሆነም ነጻ አድርጎ በወንጌል ሥራ ከእርሱ ጋር እንዲሳተፍ እንዲልከው ይጠይቀዋል። ይህ አጭር ደብዳቤ ወንጌል እንደሚለውጥ እና ለሌሎች ጠቃሚ ሰው እንደሚያደርግ ያሳያል። ወንጌል በማኅበረ ሰብ ውስጥ ያለን የተበላሸ ግንኙነት የሚያድስ ድንቅ መልእክት ነው። ይህን አጭር ቪድዮ በመመልከት የፊልሞናን ትኩረት እና ዳሰሳ መረዳት ይቻላል።

Комментарии • 11