ካልቪኒዝም || "ክርስቶስን መመስከር አያስፈልግም!!!!" ⚠️⚠️|| "አብያተ ክርስቲያናት ልክ አይደሉም"🚫🚫

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 27 янв 2024
  • Like, share and subscribe. ጌታ ይባርካችሁ!

Комментарии • 15

  • @solomongezachew
    @solomongezachew 5 месяцев назад +1

    ሁሉም ሊሰማው የሚገባ ድንቅ መልእክት። ተባረኩ

  • @ZewduRegassa
    @ZewduRegassa 2 месяца назад +1

    አባታችን ደህንነት ዘላለማዊ እንደሆነ በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ስራ እንደተደረገ መፅሐፍ ቅዱስ አስረግጦ ይናገራል።ተከፍሏል።
    ጌታ ኢየሱስን እንደግል አዳኝ አድርጎ የተቀበለ አማኝ የተቀበለው የእውነት መንፈስ ሀጢያተኝነትን ያስክደዋል።1ኛ ዮሀ 3:9
    _ቲቶ 2:11
    _ሮሜ 6:14
    _2ተኛ ቆሮ 5:12
    1ኛ ቆሮ 15 ኋለኛው አዳም በመጀመሪያው አዳም የገባውን ሀጢያት በመስቀሉ ጠርቆ አስወግዶታል።በትንሳኤው አስነስቶናል።
    ኤፌሶን 2 ከእርሱ ጋር ህይወትን ሰጠን ከእግዚአብሔር ጋር በቀኙ አስቀመጠን።
    እዚህ ጋር ልብ ይደረግ አስቀመጠን ነው already Done.ሊያስቀምጠን ይችላል አይልም።
    አማን ኢን ኬዝ ሀጢያት ቢሰራ ከአብ ዘንድ ጠበቃ ጌታ ኢየሱስ እንዳለው ይናገራል።
    የእግዚአብሔር ልጆች እንጂ ዲቃላዎች አይደላችሁም የተባሉ ናቸው።
    አረ ልጨምር 1ቆሮንጦስ 11:28 ጀምሮ ስለአማኞች የስጋ ቅጣት ነው የሚያወራው።ደክመዋል:ታመዋል:አንቀላፍተዋል ።አየህ ለአማኞች አንቀላፍተዋል ነው የሚባለው።ላላመኑት ደግሞ ሞተዋል ነው ልዩነቱ።ያንቀላፋት እዛው ክፍል ላይ በመጨረሻ እንደሚያስነሳቸው።ለጥቅማቸው እንደተቀጡ ይናገራል።
    ጌታ የልቦና አይኖቻችንን ያብራልን የእውነት ወንጌል ትውልድ እንዲሰማ።

  • @fetenemarkos4751
    @fetenemarkos4751 3 месяца назад

    Yes ተባረክ በጣም ጥሩ እይታ ነው

  • @enkumengist1668
    @enkumengist1668 5 месяцев назад

    ተባረኩ ደስ የሚል ውይይት ነው።

  • @shiferawalayu9046
    @shiferawalayu9046 4 месяца назад

    በእምነት ፀንተን እንድንኖር የሚያደርገው እራሱ እግዚአብሔር ነው

  • @enkumengist1668
    @enkumengist1668 5 месяцев назад

    ተበሰረኩ ደስ የሚል ውይይት ነው።

  • @yoa4954
    @yoa4954 3 месяца назад

    ውይኔ እንደዚህ ግልፅ አድርጎ ፣ ማስተማር ዛሬ ላይ ለአስተማሪዋች ህልም ሆነባቸው እኮ፣ ብዙዎች ጠፍተዋል ፣ ምክንያቱም እናንተ ስለተደበቃችሁ፣ አሁን ግን እግዝአብሆር ይመስገን ግዜው ደርሶል።
    በርቱ

  • @almezelke7020
    @almezelke7020 5 месяцев назад

    ተባረኩ

  • @abebemamecha8684
    @abebemamecha8684 5 месяцев назад

    Nice Father

  • @saraelyas661
    @saraelyas661 5 месяцев назад

    👉 ጤናማው አስተምህሮ ይህ ነው ! እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

  • @ydidiabitsue4061
    @ydidiabitsue4061 5 месяцев назад

    መስማትና ማየት በድነት የሚኖራቸው ድርሻ
    በድነት ቀዳማይ ሥራ ላይ መስማትና ማየት ግዴታ እንደ ሆኑ ከሕያው ቃሉ ማረጋገጥ ይቻላል። እነዚህ ሁለት ቁልፍ ሁነቶች ከሰውና በሰው የሚመነጩ ቢሚስሉም ጠንሳሹ ልዑል አምላክ እንደ ሆነ ከሕያው ቃሉ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል።
    መጽሐፍ ቅዱስ እምነት ከመስማት እንደ ሆነና መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ፣ ለመስማትም ሰባኪ እንደሚያስፈልግ፣ ሰባኪው ከእግዚአብሔር መላክ እንዳለበት ይናገራል። ስለዚህ እግዚአብሔር ወንጌልን ሰምተው ለማመን የሚሰብከውን ካልላከ ለመዳን የሚሰማ ነገር አይኖርም። በዚህ ቀዳሚውና ወሳኙ የማዳን ሥራ ሰባኪውን የሚልከው እግዚአብሔር እንደ ሆነ መረዳት ይቻላል።
    ሌላው ( ኢሳ 6:9) ምን እንደሚል እንይ፦
    እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ “ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።"
    መስማትን እንደሚችሉ ነገር ግን እንደማያስተውሉ፣ ማየትም እንደሚያዩ ነገር ግን ልብ እንደማይሉ እግዚአብሔር በኢሳይያስ ሰምተው ስለማያስተውልትና አይተው ልብ ስለማይሉት በአጽንኦት ይናገራል።
    ምንም እንኳ እምነት በመስማት ቢሆንም፣ ሰምተው ካላስተዋሉ ስለ ሰሙ ብቻ አያምኑም። እዚህ ላይ የሰሙትን እንዲያስተውሉ የማድረጉ ሥራ የመለኮት እንጂ የሰው አይደለም። የሊዲያ ልብ ወይም ማስተዋል የከፈተ እግዚአብሔር እንደ ሆነ እናስተውል።
    ሰው እያየ ልብ ላይልም ይችላል። በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያለውን የሰው ልብ እግዚአብሔር "ብርሃን ይሁን!" ብሎ ካላዘዘ፣ ሰው ቢያይም ልብ ብሎ መመልከት አይችልም። ስለዚህ በቅድሚያ እግዚአብሔር በልዓላዊ ትዕዛዙ በልብ ውስጥ ተንሰራፍቶ የነበረውን ጨለማ ብርሃን ይሁን ብሎ ካላሸሸው ሰው በብርሃኑ ብርሃንን ማየት አይችልም።
    በእነዚህ በሦስቱ ማለትም፦
    1) ለመስማት ሰባኪውን መላክ 2) ሰምቶ ለማስተዋል ጀሮን መብሣትና 3) በብርሃኑ ብርሃንን እንዲያዩ በልብ ውስጥ ያለውን ድቅድቅ ጨለማ በብርሃን ማሸሽ የሰው አንዳች ድርሻ ሳይኖራቸው በመለኮት የሚከናወኑ ቁልፍና ቀዳሚ ድርጊቶች ናቸው። እነዚህ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገሮች ቸል ካልን በድነት ቅደም ተከተላዊ (order of salvation) አሠራር ላይ ተፋልሶ ሊያጋጥመን ይቻላል።
    ከመስማት ጋር የሚቆራኘው ጀሮን የመብሳት ስእላዊ አገላለጽ ማስተዋልን የሚያሳይ እንደ ሆነና ጀሮን የሚበሳው ደግሞ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ማወቅ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር የምሥራቹን ቃል ሰምተን አምነን እንድን ዘንድ ሰባኪውን ካልላከልን፣ ሰምተን እንድናስተውል ጀሮአችንን ካልበሣ፣ በልብ ውስጥ ተንሰራፍቶ ያለውን ድቅድቅ ጨለማ ብርሃን ይሁን ብሎ በማዘዝ ጨለማው በብርሃኑ ካላሸሸው፣ እምነትና ንስሓ ሊኖሩ አይችሉም።
    ማጠቃለያ፦ እምነት በመስማት ሲሆን፣ አዳኙ እምነት ጀሮው በእግዚአብሔር ተበስቶለት ሰምቶ እንዲያስተውል የተደረገ እንጂ እንዲሁ ከውጭ በሥጋዊ ጀሮ ያለ ማስተዋል (without understanding) የሚሰማው አይደለም። የልብ ዓይን የሚያበራውና የልብ ጀሮን ያስተውሉ ዘንድ የሚበሣው እግዚአብሔር በመለኮታዊ ልዕለ ተፈጥሯዊ ችሎታው እንጂ ሰው አይደለም።

  • @ydidiabitsue4061
    @ydidiabitsue4061 5 месяцев назад

    እባክዎትን አንዴ 1 ዮሐ 2:19 ረጋ ብለው ያንብቡ፦
    "ከእኛ መካከል ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ ይታወቅ ዘንድ ከእኛ ተለዩ።"
    መስለውና ተመሳስለው ይኖሩ ነበር፣ ነገር ግን ከመነሻው ወገን ስላልነበሩ ክደው ወጥቷል። ወገን ያለመሆናቸው በቅድሚያ ከእግዚአብሔር ያልተወለዱ ወንድሞች ስለ ሆኑ ነው። ስለዚህ በእምነታቸው ጸንተው እስከመጨረሻው የሚዘልቁት ከእግዚአብሔር በመወለዳቸውና ዘሩ በውስጣቸው የሚኖረውና፣ እምነታቸው በእግዚአብሔር ኀይል የሚጠበቅላቸው ናቸው (1 ጴጥ 1:5)
    እምነቱ በእግዚአብሔር ኀይል የሚጠበቅለት አማኝ እንዴት ከእምነቱ ሊያፈገፍግ ይችላል? ይችላል የሚባል ከሆነ የእርሱ የማፈግፈግ ኀይል እምነቱን ከሚጠብቀው ከእግዚአብሔር ኀይል ይበረታል ማለትስ አይደለን?

  • @ydidiabitsue4061
    @ydidiabitsue4061 5 месяцев назад

    በእውነት ዳግም የተወለደ ኀጢአት እንዳሻው እያደረገ ይድናል ሳይሆን የሚለው፣ ኀጢአትን አያደርግም ነው የሚለው። 1 ዮሐ 3:9 ይነበብ።
    "ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን አያደርግም፤ የእርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም።"
    ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአት የማያደርግበት ምክንያት የእግዚአብሔር ዘር በውስጡ ስላለ ነው። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአት የማያደርግ ከሆነ ታድያ ድነቱ እንዴት ሊነጠቅ ይችላል?

  • @Mrursi
    @Mrursi 21 день назад

    ነገሮችን ከመቃወም በፊት በትክክል መረዳታችንን ብናረጋገጥ እንዴት መልካም ነበር?

  • @enkumengist1668
    @enkumengist1668 5 месяцев назад

    ተባረኩ ደስ የሚል ውይይት ነው።