የሮሜ መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ
HTML-код
- Опубликовано: 13 сен 2024
- የሮሜን መጽሐፍ እንዴት እናጥና? ጳውሎስ በሮም ለሚገኙ ክርስቲያኖች የጻፈው ደብዳቤ ከምንጊዜዎቹም ታላላቅ የወንጌል መልእክቶች ማብራሪያ አንዱ እንደሆነ ይታሰባል፡፡ ምንም እንኳ ጳውሎስ ገና ወደ ሮም ባይሄድም በጕዞዎቹ ሁሉ በየከተሞቹ ይሰብክ የነበረውን መልእክት ስልታዊ በሆነ መንገድ በማብራራት ራሱን አስተዋውቋቸዋል፡፡ ይህ ይሁን እንጂ በሮም ያለችው ቤተ ክርስቲያን ዋናዋ የሆነውን ክርስቶስን ማንጸባረቅ እንዳትችል የሚያደርግ አደጋ አጋጥሟት ነበር፡፡ በዚህ አስደናቂ ሥራ ውስጥ ሕይወት ለዋጭ የሆነውን የወንጌል መልእክትን ኀይል ይመልከቱ፣ ይለማመዱ፡፡
www.thebibleeff...
FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
INSTAGRAM: / thebibleeffect
ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
#ሮሜ #የእግዚአብሔርኃይል #TheBibleEffectAmharic
ለተጨማሪ ጥናት የሚያግዙ ጥያቄዎች
1) በሕይወቴ ውስጥ በሥራዬ፣ በማደርጋቸው ወይም በምሆናቸው ነገሮች ውስጥ እግዚአብሔርን ለማስደነቅ የምሞክርባቸው ነገሮች ይኖሩ ይሆን?
2) የሮሜ መጽሐፍ ስለ እምነት ከሚያስተምረው ትምህርት አንጻር በእግዚአብሔር የሚታመንን የእምነት ሕይወት እንዴት መኖር እችላለሁ?
3) “የሕይወት መንፈስ ሕግ በክርስቶስ ኢየሱስ ከኀጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶአችኋል” (ሮሜ 8፥2)፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው የሕይወት መንፈስ ሕግ መኖር የምችለው እንዴት ነው?
4) ጊዜ ወስዳችሁ ሮሜ 12ን በማንበብ የተማራችሁትን ነገር ግለጹ፡፡ እግዚአብሔር ምን አስተማራችሁ? የተማራችሁትንስ በተግባራ ማዋል የምትችሉት እንዴት ነው?
Thank you very much God bless you
❤God bless you too!
በጣም ጠቅሞኛል ጌታ ይባርካችሁ
ይህን በመስማቴ በጣም ደስ ብሎናል! መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናትህ እግዚአብሔር ይባርክህ!
Tnx yami
እልልል። በርቱልን።
Yamiye Bless u Brother
Even smaller ones can listen and understand it! Good work 👏👏👏
Thank you!! God bless you!
Tebarek Yami! I will never forget your story about the catacombs. It could be nice if you brought it to you tube ❤🙏
በጣም ጠቃሚ ነው ቢትቀትሉ እንደዚው ቢታብራሩ በታም እዎዳለው፣ እግ/ር ይባርካችው
አስተያየትዎን ስላጋሩ እናመሰግናለን! እግዚአብሀር ዪባርክህ!
Good job. God bless you
Thank you! Blessings to you as well!