አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ፡ የክብር ዶ/ር አበበች ጎበና የህይወት ታሪክ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 29 окт 2022
  • #SUBSCRIBE # for more videos!
    Abebech Gobena Biography
    የዛሬው የታላቅ ነፍስ ዕንግዳችን የብዙሃን እናት ናቸው፣ ለበጎነት የማይሰለች እጅ፣ ለሰብዓዊነት የማይታክት መንፈስ ያለቸው እና ገድላቸው ከትውልድ ወደ ትውለድ የሚሸጋገር ኢትዮጵያዊ አንፀባራቂ ፈርጥ ናቸው፡፡ ታላቋ ነፍስ በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደምት የሆነውን ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ መስራች ናቸው። ለዚህም መነሻ የሆነው በወሎ በሚገኘው የግሸን ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ለመሳለም ሃይማኖታዊ ጉዞ ባደረጉበት ወቅት ነው። ቦታው በረሃብ ተጠቅቶ የነበረ ሲሆን ከጉዟቸው ሲመለሱም አንድ ህፃን ልጅ ከሞተችው እናቱ አጠገብ ተኝቶ አዩ። ልጁንም አንስተው ወደ ቤታቸው ወሰዱት። በዚህም አላበቃም ከሞተ አባቱ አጠገብ ተኝቶ ያገኙትንም ሁለተኛ ህፃን ልጅ እንዲሁ ወደ ቤታቸው ወሰዱ። በአንድ አመት ውስጥም 21 ወላጅ አልባ ህፃናትን ለማሳደግ ወደቤታቸው ያመጡት የብዙሃን እናት፣ ፍቅርና ደግነታቸውም ለአራት አስርት አመታት አብሯቸው ቀጠለ። እኛም ታድያ በዛሬው የታላቅ ነፍስ ዝግጅታችን ስለአንጋፋዋ የበጎ ተግባር አገልግሎት ሰጪ፤ ሕጻናትን ከመንገድ አንስተው እና በተለያዩ መንገዶች ተቀብለው በማሳደግና በመንከባከብ ስለሚታወቁት፣ በዓለማችን ካሉ ድንቅ ሴቶች አንዷ ስለሆኑት -- የአፍሪካዋ ማዘር ቴሬሳ ዶክተር አበበች ጎበና -- አጭር የህይወት ታሪክ እንካችሁ አለን!
    ቀናችን ልዩ የቅዳሜ ከሰዓት የመዝናኛ ሾው ዘውትር ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 - 11፡00 በዋልታ ኤፍ ኤም 105.3 ጣብያ፡፡ የአፍሪካ ፈርጥ፣ ልሳነ-ዜማ፣ ታላቅ ነፍስ፣ የጥበብ ስንቅ እና ሌሎች አዝናኝ እና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በቀናችን ሳምንታዊ የመዝናኛ ሾው ያገኛሉ፡፡

Комментарии •