69ኛb ገጠመኝ ፦ እንደቀልድ ፕሮቴስታንት የሆነችው ህይወት (በመምህር ተስፋዬ አበራ)
HTML-код
- Опубликовано: 24 янв 2025
- የ16 ዓመት ልጅ የሚጠይቀውን ሰምቼ ተደነቅሁ እህታችን ወደዚህ ሃይማኖት መሳይ ድርጅት የተቀላቀለችው በቀላሉ ( በተጭበረበረ ህልምና በመዝሙራቸው የዘፈን ዜማ ነው) ግን የቀደመችውን እምነታቸውን በመንፈሳዊ መነፅር ቢፈትሿት ከአገልጋዮቿ ውጪ ንፁህ መሆኗን ያውቁ ነበር ግን የቤተሰብ ዛር ይህን እንዲመረምሩ አይፈቅድላቸውም ....ለምን ይህን መንገድ ወደድኩት ብሎ መመርመር አንዱ የማንቂያ ደውል ሲሆን ....እውነተኛ መሆን ደግሞ ለነፍስ ድህነት መቆም ነው ....ማንኛውም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር የማያስማማ ስነምግባር የሌላቸው ለምንድነው ? ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
አዎ መምህር እኔ እየሱስ ክርስቶስን በህልሜ አይቼዋለው ሁለቴ አንዴ በውሀ ውስጥ ስዋኝ ከጥልቁ ውስጥ ጥቁር ዘንዶ ወጥቶ አባረረኝ ከዛ በረጅም ኮሪደር ላይ ስሮጥ ዞሬ ስመለከት ጥቁር ሰው ሆኖ ሲከተለኝ በጣም ፈርቼ ስሮጥ ኮሪደሩ 5 በሮች አሉት ሁሉንም እየበረገድኩ ስሮጥ በመጨረሻ ኢየሱስ ክርስቶስ ከላይ እስከታች ነጭ ልብስ ለብሶ እጆቹን ዘርግቶ ቆሞ እቅፉ ውስጥ ስገባ ሚያሳድደኝ ሲጠፋ ባነንኩ ሌሊቱን ሙሉ ሳለቅስ ነጋ ጼንጤ ከሆነች ጓደኛዬ ጋር ነበር አንድ ክፍል ውስጥ ምኖረው እሷም ሁኔታዬን አይታ ተጨነቀች ካዛ ደግሞ በዛው ስሞን በመስቀል እንደተሰቀለ ደሙ እየፈሰሰ በበራችን ሲገባ ደንግጪ ባነንኩ እናም በጣም አለቀስኩ በወቅቱ በሀጥያት ውስጥ ነበር ምኖረው ምን ይሆን እያልኩ ግን ህሊናዬ እረፍት አላገኘም የመጀመሪያውን ህልም ግን ከአምስት ወይም አራት አመት በኃላ ክርስቶስ በእጁ ያስገባኛል ብዬ ተረጎምኩት እውነትም ከአራት አመት በኃላ ሀገር ቀይሬ ታሪኬ ተቀይሮ ንስሀ ገብቼ ቅዱስ ቁርባን እየተቀበልኩ እድሜ ለመምህር ግርማ እግዚአብሔር ን እያመለኩ አለሁ ዛሬም እግዚአብሔር ይመስገን ።
Egziabehere yemesigen betam dese yelale ehitachin. beriche
እህታችን በጣም ደሰ ብሎኛአል በርቺ የድንግል ማሪያም ልጅ የተመሰገነ ይሁን
It is amazing wow
betelotsh asbign
ቤተሰቦቼ እና መምህሬ ስለማምላክ ብዬ እለምናችሃለሁ ፅጌ ማርያም ነኝ በፆሎታችሁ አስቡኝ እኔ ሃፃተኛ ነኝ ቤተሰቦቼ ባአድ አምልኮ ሲመልኩ ነዉ ደስስስ የሚላቸዉ እዲሁ በስቃይ እየኖርን እንገኛለን እኔም ስደት ነኝ ንሰሃ ገብቼ ስጋ ደሙን ተቀብዬ እመቤቴን አማልጅኝ እያልሁ እዳለምናት እኔስ ተሰቃየሁ ኡፍፍፍፍፍ
እኔ በልጅነቴ በማርያም ቤተክርስቲያን ሰንበት ተማሪ ሆኜ ስኖር ቆይቼ አገር ቀይረን ሌላ አገር በሄድኩበት አጋጣሚ በአንድ ወቅት መናፍቃን አዳራሽ ገብቼ በሀይቅ ውስጥ ተጠምቄም ነበር በዚያን ጊዜ አንድም ቀን እመቤቴን በድፍረት ተናግሬ አላውቅም ነበር የጌታዬ እናት ናት ብዬ ስለማምን እወዳት ነበር ። በኃላ ግን በመምህር ግርማ ሲዲ መናፍቃን ሲንፈራፈሩ ሲለፈልፉ አይቼ ደንግጬና ወደ እውነተኛዋ እምነት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተመልሼ እግዚአብሔር በበረከቱ ባርኮኛል እግዚአብሔር ይመስገን የድንግል ማርያም ልጅ የጌቶች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍ ከፍ ይበልልኝ።
እንኳን ደና መጣሽ ማርየ ፍፆሜሽን ያሳምርልሽ
እኔም እንዳንችው ወደ መናፍቅ ገብቼ ነበር ግን ከገባሁ ቡሀላ ሰላም አጣሁ በየ ቀኑ ዝም ብሎ ማልቀስ ምክንያቱ ምን እንደሆነ አላውቀውም ከዚያ እህቴ ወደ ቤተክርስቲያን ወሰደችኝ አንድ አባት ነበሩ ጸሎት አደረጉልኝ ቅባቅዱስ ቀቡኝ ከዛች ቀን ቡሀላ ሰላም አገኘሁ በየቀኑ የእለቱን ውዳሴ ማርያም ማንበብ ጀመርኩ ..አሁን ለስጋዎ ደሙ በቅቻለሁ እግዚአብሔር ይመስገን ።።
Amen dessssss ylal
መስገድ ከጀመርኩ ቦሀላ እናትና አባቴ የሚዘክሩት አቡነ #ገብረመንፈስ ቅዱስ በብርሀን ተከቦ እቤት ቁጭ ብሎ አይቻለሁ አምላክ ክብሩ ይስፋ
❤️❤️❤️❤️
Tadelatchu
እውነት ነው መምህር ቃልወት ያሰማልን እኔ እየሱስ ክርስቶስ አይቼዋለሁ እሱንም እኔ የፀወትር ፀሎት ሁሌም የማደርገው ኪዳነምህረት ስዕል ፊት ነበር እናም አንድ ቀን ምን እንደነካኝ አላውቅም በጣም መሮኝ ወደመድሀኒያለም ስህል ዞሬ አምላኬ ብዬ ለመንኩት በዛችው ለሊት ክርስቶስ በተከነቸረ እጆቹ ሲነካኝ ለምኚኝ እኔ የፈለግሽውን አደርግልሻለሁ ሲለኝ እናም እካብ ላይ ቁጭ ብሎ ዋሽንቶ ሲነፋልኝ እኔም ሰዎች ኑ ክርስቶስን እዩት ክርስቶስን እያልኩኝ ክርስቶስ ትቶኝ ሄደ እናም በቃ እግዚአብሔር ይመስገን እየለመንኩት ነው እሱም እያረገልኝ ነው መንገዴ ሁሉ ሰምሮልኛል እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬ ባለኝ ነገር ይመስገን ስል ስም አጠራሩ ክብር እና ምስጋና ይግባው
ቅዱስ ኤልሻዳይ
ቅዱስ አዱናይ
ቅዱስ የሀዌ
ቅዱስ እየሱስ ክርስቶስ
ስለስሙ በሙሉ ይክበር ይመስገን ስለሱ ስለፍቅሩ ስንቱን ልናገረው ሲሰጥ እንደሰው አይደለም ይመስገን
ይህን እንድናገር ስለፈቀድክልኝ መምህር አመሰግናለሁ
እግዚአብሔር ይመስገን
እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደስይላል
Betam dese yelale besloteshe Asbje ehita
አባክሽ እህቴ ገብረ ስላሴ ብለሽ በፀሎትሽ አስቢኝ።በከባድ ፈተና ውስጥ ስለሆንኩ መንፈሳዊ ወንድምሽ ነኝና አስቢኝ እባክሽ።@@giniholove6806
በፀሎትሽ አስቢኝ
በእውነት በጣም ደስ የሚል ገጠመኝ ነው #በተለይ የመዝሙር መሳሪያዎችን ትርጉም ስላወቅሁ በጣም ደስ ብሎኛል
ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን መምሕራችን ቃለ ሕይወት ቃለ በረከት ያሠማልን ጸጋውን ያብዛልዎት በጸሎት አስቡኝ ወለተ አረጋዊ እና ኃይለ ሩፋኤል ብለው ያስቡን መምህር
መምህር እኔም ክርስቶስ ለኔ ድጋሜ ተወጋልኝ ማርያምን መስቀሉን መቀበል በጣም ከበደኝ አንተ ማዳን ተስኖህ ነው የተሰቃየከው ብዬ አጠይቅ ነበር ግን እግዚአብሄር ይመስገን በህልሜ ያየሁት እልም በመንገድ እየሄድኩ ይመስለኛል እና ከመንገዱ ከታችና ከላይ ሰይፍ የያዙ ወንዶች ቆመዋል እና ማለፍ አልቻልኩም ሁሉም ሊወጉኝ ሰይፋቸውን ሲመዙ እፊልሙ ላይ የማየው እየሱስ ድንገት መጣ እና የአንደኛውን ሰይፍ ነጥቆ እራሱን ወጋ እና እኔን በእጁ ሂጂ የማለት ምልክት አሳየኝ ሰዎቹም ሰይፋቸውን ጣሉ አነሱም ምንም አላሉ እየሱስም ምንም አላለ በህልሜም እኔ ክርስቶስ ነኝ አላለኝም ሲመጣ ግን አውቀዋለሁ እና ባነንኩ አላምን ያለኝ ልቤ አብዝቶ አመነ ማንም የማይበግረው እምነት በውስጤ ታተመ ።አግዚአብሄርን አመስግኑልኝ
መምህር የኔ ቤተሰቦቸ ሙስሊሞች ናቸዉ እኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ
እና እቤት ዉስጥ ብዙ አምልኮት አለ ከጪሌ ጀምሮ ሁሉንም
ያልካቸዉን ሁሉ ያመልካሉ
በጰሎትህ አስበኝ
ስርጉተ ስላሴ ብለህ
ቃለሕይወትን ያሰማል እህታችን እግዛብሔር ያሰባት🙏
@@የማረያምልጅአዲሰአለም አሜን አሜን አሜን
@@sara-nd8mw weye eigzabher yerdash ache keberetash eigzabher yemesanaw nager yelem
Egzabiher yagezesh memher endemiastemrew seley sgejy egzabiher kanchi gara yehun
@@munamuna2128 አሜን አሜን አሜን እህቶቸ
አወ እሱ ምን ይሳነዋል
መምህራችን ባንተ ሁለተኛውን አለም እያየን ነውና እግዚአብሔር ከነ ቤተሰብህ ቀሪ ዘመናቹ የተባረከ ይሁን አሜን
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ለእህት ወንድሞቻችን የደረሰ እኛንም ይጎብኘን አሜን
ወላዲተ አምላክ የሁላችንም ቤት ታፅዳልን እሄ እርኩስ ስራው ብዙ ነው እግዚአብሔር ይገስፀው
እህታችን እመ ብርሀን ታስብሽ ከልጇም ጋ ታስታርቅሽ ቤተሰቦችሽንም ትማርልሽ
ለምስክርነት ታብቃሽ አሜን📖📚
አሜን አሜን አሜን ፈጣሪ ይመስገን እንዴት መታደል ነዉ
እግዚአብሄር ይመስገን ሁሉን ያደርገ እሱ ይመስገን ዎው በጣም የሚገርም ገጠመኝ
Amen Amen Amen kale hiwotin yasemalen wandemachin
መምህር ይሄ ሁሌም ላንተ መንገር እፈልግ ነበር ሚገርምህ ያንተን ትምህርቶች መከታተል ከጀመርኩ በዋላ ፀሎት ጀመሬአለሁ ታድያ ሌሊት ተነስቼ ከጨረስኩ ስለ ሀጥያቴ ብዙ አልቅሼና ስለነበር ሲደክመኝ ስተኛ መተኛት አልቻልኩም ከዛ በሠመመን ውስጥ እያለው ክርስቶስ የእሾህ አክሊል የለበሰ አይኔ እያየሁ እንቅልፍ ወሰደኝ
መምህር የክርስቶስን ያየሁትን ማለቴ የእሾህ አክሊል ከራሱ ላይ ደፍቶ እንዳየሁት አይነት ሥዕሉን እንድትስልልኝ እፈልጋለው እባክህን
እመ አምላክ አዛኝቷ አቁራሪተ መአት እቅፍ ድግፍ አድርጋ ለምስክርነት ነት ታብቃሽ
Genet Mokonen Amen amen amen 🙏
አሜን አሜን አሜን ጾሎትህ ይስማ
መምህር ተስፋየ በእውነት ረጅም እድሜ ያድልልን ቃል የለኝም በእውነት እግዚአብሔር ስራው ግሩም ነው በታናናሾች ስራውን ይስራል አይዞሽ እህታችን እመብርሃን ርህርት ልቦና ናት ልቦናሽን ትመልስው ምንኛ ቅን ልብ ነው ያለሽ ስላልተሳደብሽና ድንግል ማርያምን ስላልተሳደብሽ ነው የቀረበችሽ እኔም አስቀናሽኝ የእኔ እህት ተመለሺ ሃይማኖት አንዲት ናት እባክሽ ፀልይ
መምህር ተስፋየ የስንቱን ህይወት ታደገኽው የመምህር ግርማ ፍሬ እንዲህ ነው ከተማሩ አይቀር እንዲህ ነው
ሎሏፕ0
አዉ መምህር እኔም ባህሬን የሚባል አገር ስስራ ሳለ ሀጥያቴን እያሰብኩኝ መዝሙር ዳዊትን እያነበብኩኝ እመፀሀፉላይ ተደፈቸእያለቀስኩ እያለ እንቅልፍ ወስደኝ እናም ቸሩ መድሀንያለም ከቀይ ወጣት ልጅ ጋር መቶ ከተኛሁበት ቀስቅሶ ሲወስደኝ በህልሜ እያዬሁ ቀዮን ወጣቱን ልጅ ከፊት ከፊት እየመራ ዉደሱ ይወስደኝ ነበር እናም ለምን በሰፊዉ መንገድ አትወስደኝም ይህ እኮ ጠባብመንገድነዉ ሳትብሎኝ ብወድቅ ገደል እገባለሁ አልኩት እሱም አይ እኔ በምወስደሽ ብቻ ተከተይ በሰፊዉ መገድ ከሔድሽ ትሞቻለሽ ብሎኝ ስንሔድ መድሀንያለም ከዘራ ይዞ ብር ሲያንኳኳ የሚታየዉን ስእል ነዉ በትክክል ያገኘሁት ከዘራዋም ያችዉ ናት ምንገዱላይቁጭ ብሎ
ይጠይቀኛል ምንሆንሽ ምን ፈልገሽ ነዉ ሲለኝ አይ እኔ የምኖርዉ አርብ አገር ነዉ አልፆምም መፀለይ ብቻ እንጂ ሰለዉ ትሽ ቆይቶ አይዞሽ ሀጥያትሽ ተሰርየልሽ ይቅር ብየሻለሁ ከአሁን ቡሀላ አርብ አገር እንዳትደግሚ አለኝ እሺ ብዬ ደስስስስስብሎኝ የሚመራኝን ወጣት እያዬሁት ከእንቅልፊ ነቃሁ ስነቃም መፅሀፉ በምባ እርሶ ነበር ያገኘሁት
😮❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
እመብርሀን ከልጂሽ ጋራ ነይ ወደ እኛ ለህታችን የታርቅሻት ለሁላችንም ታርቂን አሜን
መምህር ቃለ ህይወት ያሰማልን በእድሜ በጸጋ እግዚአብሔር ያቆይልን ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር የድንግል ማርያም ልጅ የተመሰገነ ይሁን አሜን
መምህርዬ እኔም ክርስቶስን አይቼዋለሁ ግድግዳላይ ጆሞ ምግብቤት ውስጥ ፎቶ አንስቼዋለሁ ሦሥቴ ነው ያየሁት።ሁሌ ግን የማየው ተሰቅሎ ነው ሁሌ ሳዝን ስለማየው ነው መሰለኝ ግን ክብር ሁሉ ለመድሐንኤለም ክርስቶስ ይሁን ከፍ ይበል ሳገኝህ አሳያሀለሁ በእመብርሀን ፍቃድ በእግዚአብሔር።
አይ መምህር በየትኛው ስራዬ ጌታዬን ንጉሴን እንዴት አየዋለሁ እደው በምህረቱ ነው ያለሁት
መምህር ቃለህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏
ስለሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን መምህር ብዙ ብዙ ትምህርቶችን አግኝቼ በታለሁ እስከዛሬ ብምታስተላልፈቸው ገጠመኞች እንዲሁም አስተምህሮቶች ጸጋው ን ያብዛልህ በእድሜ በጤና ይጠብቅህ እህትታችን የዚህ ገጠመኝ ባለቤት አይዞሽ እመብርሀን እሩህሩህ እናት ነች ስለዚህ ያለመሰልቸትና ያለመታከት ለምኛት ነገረ ማርያምን ውዳሴዋን ... የሷይሆኑትን ነገሮች ሁሉ እያነበብሽ ለምኛት ከጠበቅሽው በላይ ነው መልስ የምትሰጥሽ እመብርሀን በደግነቷ በ አማላጅነቷ በ እናትነቷ ትጐብኝሽ ለሌሎችም በአዳራሽ ተሰብስበው ለሚጮሁትንም እውነቱን ሚስጥሩን ትግለይላቸው አንቺ ግን ሳቁብኝ አሾፉብኝ ብለሽ ልብሽ ለሁለት አይከፈል በእመቤታችን ጽኚ በስግደት ብጾም በጸሎትሽ ትጊ
አሜን እንቁዩ ምን ልበል የዘመናችን ታላቅ ሐዎርያ አንተን ያበረታህ አምላክ ይመስገን ግሩም ትምህርት ነው ልጁንም ፈጣሪ ይጠብቅልን እድለኛ ልጅነውፈጣሪ ቀርቦት መታደል ነው በነገራችን መምህር ልክ ፀሉት ላደርስ ልገባ ስል እመቤታችን ስእለ አድኖ ስር ተምበርክኬ ስለ ልጅቷቷ አቡነዘበሠማያት አልኩላት
Amen🙏 amen🙏🙏🙏
አወ መምህር እኔ እራሱ በስደት ነው ያለሁት እና ይህ የተረገመ አንበሶ እሚባል ሰይጣን ከቤታችን የናቴም ዛር መንፈስ አለባት እና ዝብለው ያዝ ለቀቅ ነው እሚያደርጉት ሲያማቸው ብቻነው ዶሮ ገዝተው ያሻሉ እና አባቴን ሲያመው አነደ ጸበል አንደ ሀኪም አንደ ዶሮ ሲሉ በመጨረሻ ሰይጣኑ ገደለብኝ እና አባቴን ስላላየሁትም ስለናፈቀኝ በጣም አዘንኩ ከዛ በህልሜ እየሱስ ክርስቶስ በደሙ እንደተነከረ አየሁት ከዛ ያባቴን ትንሽ ቁስል አሳየኝና ከሱ የኔ አይበልጥም አለኝ ከዛ በሗላ ሀዘኔን እየተውኩ መጣሁ ብዙ ጊዜ አየዋለሁ በደመና ሆኖከድንግል ማርያም ጋር ሆኖ አየዋለሁ እኔግን በጣም ሀጢያተኛ ነኝ በጸሎታችሁ አስቡኝ ወለተ ኪዳን እያላችሁ
አሜን አሜን አሜን
እመቤቴ ወደ እውነተኛዋ እምነት ትመልሳት
ወንድሟንም እግዚአብሔር በቤቱ ያፅናው
Amen memerachin kaleiwotin yesalign
አሜን አሜን አሜን ቃልሕይወትን ያሠማልን መምህር እህታችን ን እናቴ ድንግል ማርያም ልቦናን ትመልስላት
ቃለ ሂወት ያሰማልን መምህር ፀጋውን ያብዛልን
Bewenti memeri bezu negeri tize algn beyewetaly yewenwe hulu
ወይኔ በእግዚአብሔር ስም መምህር በጣም ነው ደስ ያለኝ የድንግል ማርያም ልጅ ክብር ምስጋና ይድረሰው እንደምትመለስ ተስፋ አለኝ
🙏🙏🙏
አዎ መምህሬ እኔም ምስክርነት ይሁነኝ ጴንጤዎችን ሳያቸው በጣም ነው የሚማርኩኝ እናም ሁሌ አለቅስ ነበር በውስጤ የሚሳደብ ሰው ነበር እኛም እማምላክ ሆይ እኔ አይደለሁም ይህን መንፈስ አርቅልኝ እያልኩ ስፀልይ ሁሉ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅዱስ ገብርኤል ሁሉ አያቸው ነበር እኛም እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ደህናነኝ እድሜ ለአባቴ መምህር ግርማ ወንድሙ እግዚአብሔር እድሜ ጤና ይስጥልን ይህ ሁሉ የሆንኩት መበርከክ ስጀምር ነበር ክብር ለወላዲት አምላክ 🌷
እግዚአብሔር ስም የተመስገነ የሁን ወንድማችን እግዚአብሔር ያበርታህ አሜን
አዳል ሞቲ እግዚአብሔር ይገስፅሕ
እምብርሃን ሁሉን ነገር ታስተካክልልሽ እህታችን በጣም ደስ ብሎኛል
እናመሰግናለን በውነት ፀጋውን ያብዛለዎት መምህር የስት ሰው ነፍስ ከአምላክ ከመደሐኒያለም ታረቀች ክብርና ምስጋና ይግባው አምላካችን አሜን(፫)
አዎ መምህር እኔ ባንድ ወቅት በጣም አዝኜም እግዚአብሔርን አኩርፌውም ነበር አንተ ማነህ ላመልክህ እያልኩ በትክክል አጠገቤ ቁጭ ብሎ የማወራው እስክመስል ድረስ ብስጭት ብዬ አወራው ነበር ፀሎትም ለ 2 ዓመት ድረስ አልፀልይም ነበር ነገር ግን በጣም ከፍቶኝ ያወራሁት በዛው ሰሞን በህልሜ አንድ የማውቀው የቤተክርስትያን አገልጋይ ልጅ ከቤተክርስቲያን ግቢ ጀምሮ በመንገድ እያስተማረኝ እንሄዳለን ከዛን የሆነ ቦታ ላይ ስንደርስ ጨረስኩም ቻዎም ሳይል ካጠገቤ ይሄዳል ከዛን በጣም ይገርመኛል እንዴ ሰው ግን ምን ሆኗል ጨረስኩ ሳይል እልና ተገርሜ ከቆምኩበት ቦታ ከጀርባዬ የሆነ ሰፊ ግቢ ዉስጡ በጣም ውብ የሆነ በአረንጓዴ ሳር ያማረ ግቢ በሩ ሲከፈት ተሰማኝና ዞር ስል እረጅም ነጭ ቀሚስ ለብሶ ልክ አይምሮአችን እየሱስን በሚስለው መልኩ በሩ ላይ ቆሞ ፈገግ ብሎ እጁን ዘርግቶ አየሁት እኔም ወደሱ እንደዞርኩ ባነንኩ ከዛ በኃላ ፀሎትም ጀመርኩ ስብከቶችንም መዝሙሮች መከታተል ጀመርኩ ድንግልንም ከእርስዋ ጋር 3 ረጃጅም ሴቶች ሆነው ፃድቃኔ ፀበሉ ቦታ ከመሀል ያለች ሴት ስስቅ የሚያመኝ ቦታ ነበርና እዛ ቦታ ላይ እምነት ቀቢው ብላ ስትነግረኝ አየሁ ወድያውም ጠዋት እምነትዋ ነበረኝና ተቀባሁ ከዛ በኃላ ያ ስስቅ የሚያመኝ ነገር ተወኝክብር ምስጋና ላምላካችን ይሁን የድንግልም ምልጃና ፀሎት አይለየን::
amen
አሜን አሜን አሜን
አሜን አሜን እህቴ እግዚአብሔር አምላክ ወደተቀደሰው ሀይማኖት ይመልስሽ። ድንግል እመቤቴ ማርያም ትራዳሽ። እመቤቴ ድንግል ማርያም አንችን እንደታረቀችሽ የኔንም እህት ታረቅልኝ ዘንድ በፀሎት አንቡልኝ። ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር።
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህወት ያሠማልን
Amen egezehabeher wedebetu yametash ulu egezehabeher yefekedew new emehonew denegel mareyam benefesesh endetetarekesh besegam tetarekesh eganem yeserachenen yehateyatachenen satemeleket kelejewa tasetareken
ደስ እሚል ትምርት ነው በጣም አስተማሪ ነው እግዛብሔእ በምህረቱ ይጠብቅህ ወድማችን
በጣም ሚገርም ነው መምህር የተባረከ ልጅ እኔ ይህን ህልም ካየውት ቆይቻለሁ ባስ 1 አመት ይሆነዋል 3ም 1ም ይመስለኛል በመስቀል ተቸክሮ በጣም የማስፈሩ ትልልቅ ሰወች ከነመስቀሉ ይዘውት ወደኔ እየቀረቡ ይህንን ነው ምታመልኪው እውነቱን ተናገሪ ሲሉኝ አወ የማመልከው ለኔ ለሁሉም የተሰቀለውነው ስላቸው ይይዙኝና በጣም ችግር ያደርሱብኛል ጥቁር ፈሳሽ ነገር ያፈሱብኛል ግን በዛውስጥ ሁኝ እግዚያብሔርን እደማመልክ ነበር ምነግራቸው ግን መምህር ተናገሩ ስላልክ ነው እጅ እኔ እኳን የወደኩ ነኝ ሀጣተኛ ለምን እደታየኝ ባላቅም ግን በትክክል መስቀሉ ላይ ያየሁት ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ እደተሰቀለ እዳለው ነው ሶስትም አንድም ሆኖ ነው ሚታየኝ የገረምኝ እሔነው
መጨረሻህን ያሳምርልህ
እውነት ከአምሮ በላይ ነው ግን ላመነ ሁሉ ይቻላል እውነት መምህር እነመስግነለን እግዚአብሔር በድሜ በጤና ይጠብቅህ ኑርልን
እህታችንንም እመአምላክ እመብዙሀን ሶልያና ወደ ቤቱ ታጣት እህታችን እግዚአብሔር ወደ ቤቱ ያጣልን
ቃለህይወት ያሰማልን በእውነት መምህራችን እናመሰግናለን እህታችን እመ ብርሐን ታስብሽ
አንዳዴ እንባ ይቀረኛል የአንተ ትምህርት የህይወት ምግባችን ነው✝️
አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገኑ የሆነ እውነት ደስ የመላ ነው ሰለ ሁለም ነገር እግዚአብሔር የተመሰገኑ የሆነ አም ሀይ እኛ ልጁ ችሁ ከከፋ ሀሎ ጠብቀን
እመቤቴማ እራሱዋ የኢትዬጵያ ኢንባሲ በአሜሪካ ውስጥ ይዛኝ ገብታ እንቢያሉኝን አሰጥታኛለች ጠላቶቻችንን በሞላ እየተዋጋች ነው በተለይ በዘር የሚያጣሉትን።እንደወታደር መምህርዬ ለልጆቿ ለኢትዮጵያኖች በአካል መጥታ ነው የምትዋጋው የሚደንቁ ብዙ ነገሮች እያደረገችልኝ ነው።በጣም በፍቅር ነው የምወዳት ቅንብር በላይ።
I heard the voice of God in my dream 23 years ago. When a dark thing approached me, I heard the voice of Egziabher from heaven. He said, this is a fight between me and the evil spirit. I said Egziabher you came to help me and asked him, Are you Egziabher?
He replied I am the eternal (Ene Hiyaw negne, Hulem yeneberku, lezelalem yemenor negne belo meleselegne.)
@Hanna Thank you! May God be with you all the times.
እግዚአብሔር ይመስገን በጣም ደስ ይላል እኛነም አይን ልቦነችንን ያብራልንንን. ፅጋውን ያብዛልህ ቃለ ህይወትን ያሰማልንን።
መምህር ቃለህይወት ያሰማልን በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን ያገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ መምህር እኔ ወንድማችን እየሱስ ክርሰቶሰን በህልሙ በማየቱ በጣም ደሰ ብሎኛአል እኔም አንድ ነገር ማለት የምፈልገው አንድ ነገር አለ ለሌሎች እህት ወንድሞቸ ትምህርት ከሆነ ማታ ማታ ጉባኤ እከታተል አለሁ እና ከጉባኤ በሗላ ጸሎት ሲደረግ እንደ ቸርነትህ ሲባል በአይነ ህሊናየ ተመሰጨ ነበር ወደሰማይ ቀጥ ብየ ሁል በተመሰጣ ሰመለከት በአይነ ህሊናየ እየሱስ ክርሰቶሰ ከመቃብር ሲነሳ ያለውን ሰእል በደንብ በአይነ ህሊናየ ተመሰጨ አየዋለሁ ሌላው ደግሞ ሰላሴ በሶስትነታቸው የለውን ሰእል አድኖ ወደሰማይ ሰመለከት ሰላሰች በሶሰትነት በብርሀን ተከቦ በአይነ ህሊናየ ተመሰጨ ለብዙ ጊዜ አያለሁ ወንድም እህቶቸ እኔ እጅግ በጣም ሀጸያተኛ ነኝ ነገር ግን ይህን ነገር ሁልጊዜ በማየቴ ለሰወች ለመናገርም ተቸግሬ አንድ ቀን ለጎደኛየ ነገርኳት በጣም ጥሩ ነው ሰትለኝ ተረጋጋሁ እህት ወንድሞቸ ሰትጸልዬ በተመሰጣ ከሆነ በጣም ደሰ ይላል እባካችሁ ሰትጸልዬ ከልባችሁ ከሆነ እየሱስ ክርሰቶሰን ከእናቱ ጋር ይገለጥላችሗል ሌላው ማለት የምፈልገው ለወንድማችን የምለው እግዚ ያብሔር በቤቱ ያጸናህ እህታችንንም የድንግል ማሪያም ልጅ ወደ ቤቱ ወደ ተዋህዶ ይመልሰልን ሰለሁሉም ደሰ ብሎኛአል እግዚያብሔር ይመሰገን
መምህራችን በእውነት ለስዋ የደረሰ እግዚአብሄር አምላክ ለኛንም ይድረስልን እንዴት ደስ ይላል መምህር እማምላክ ከክፉ ህሉ ነገር ከነ ቤተሰቦችህ ትጠብቅልን
መምህር ያገለግሎተህ ዘመን ይባረክልህ አሜን
ሰላምህ ይብዛልኝ ዉድ መምህሬ እንኳን ደህና መጣህ ስጠብቅህ ነበር
ቃለ ሂወት ያሰማልን ጰጋዉን ያብዛልህ
እግዝኣብሄር ይስጥልኝ የኣገልግሎት ዘመንህ ይባሪክ🙏🙏🙏
ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር እኔ ብፀልይም ጥላቴን ማሸነፍ አልቻልኩም በጸሎት አስበኝ ወለተ ማርያም ብለህ ቤተ ሰቦቼ በአድ አምልኮ ያመልካሉ ለዛነዉ በሰለኝ ብፆምም ብፀልይም ልቤን ከማፍን መፍትሄ አላገኝሁም ቢቻለህ ብታናግረኝ መምህር
ቃለሀይወት ያሠማልን በጣም አስተማሪ የሆነ ገጠመኝ ነው መምህራችን እህታችንም ቅን ልቦናዋ አይተው እግዚአብሔር ወደ ቤቱ ይመልሣት አሜን
አሜን መምህር እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል አምላክ ሁሉን የድርግ እርሱ የስተካክላቸው እና መምህ አኔም ሳይገባኝ እየሱሰ ከርሰቶሰን በህልሜ አይቸዋለሁ አንድ ቀን አንደተሰቀለ ከጎኑ ውሃ በጣም ሲፈስ አየሁ አንድ ቀን ደግሞ ቆሞ የትንሳኤ ለት ሲነሳ አንደለበሰው ነጭ ልብስ ለብሶ ከጎኑ አየሁት ፍቱ አይታይም እግዚአብሔር አምላክ እነደኛ ሐጢያት ሳይሆን እንደ እርሱ ቸርነት ነው ስሙ ለዘላለም ከፅንፈ እስከ ፅንፈ በፈጥረታት ሁሉ አንደበት የተመሰገነ ይሁን 💚💛❤
እህታችን እግዚአብሔር አምላክ መጨረሻውን ያሳምርልሽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤቷ ትመልስሽ
እኔ ብሆን አንድም ቀን ሳላድር ነበር ተጠምቄ ወደ ቀደመችው እምነቴ የምመለሰው ስራም ሐብትም ንብረትም በምድር ያለው ሁሉ አላፊ ነው የማታልፈዋን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ ወደነበርሽበት ተመለሽ ወስኚ እህቴ የምንሞትበትን ቀነ አናውቀውም
ተይዛ ነው እንጅ መንፈሰ በጣም አሰቸጋሬ ነው
በትክክል
በትክክል
እግዚአብሄር አምላክ ምሥጋናና ክብር ለአምላካችን ይሁን።ታርቃታለች ከዚህ በላይ ምን ማረጋገጫ ትፈልጋለች።መምህር ትግሥቱን አብዝቶ ሰቶታል።ሰው በጠራዎት ቁጥር እየተነሱ በተጠሩበት ሁሉ መሄድ በጣም ከባድ ነው።ልጆቾትን ይባርክሎት እድሜና ጤና ይሥጦት።እኔ ማለት ደግም የዚህ የወንድሜ አይነት ሰው ነኝ።ቤተሰቦቼ ወይም ወላጆቼ በአካባቢው ያለው ሰው ሁሉ የእግዚአብሔርንና የእርኩስ መንፈስን ለይቶ አያውቅም። አምላኬን የምለሞነው በፀሎቴ እባክህን አምላኬ ሆይ ባለማወቃቸው እርኩስ መንፈሰን የሚያመልኩትን አንተ እንደፈጠርካቸው ግለፅላቸው እያልኩ እፀልያለሁ።እግዚአብሔር የሚሳነው የለውም ተስፋ አደርጋለሁ።
amen amen amen💚💛❤
በእውነት መምህራችን ቃል ህይወት ያሰማልን
የአምላክን እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለሁላችን አማልጅነቱ አይለየን
እህታችን ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይመልስልን
መምህራችን ቃለህወትን ያሰማልን እህታችን እናታችን በእውነት ትመልስሽ መምህራችን በፀሎት ወለተ ማርያም አስቡኝ እህታችን በእውነት እደለኛ ናት
ዲስ ላይክ የምታረጉም ድንግል ትታረቃቹ በእውነት ብታውቁ እኛ እድለኛ ስለሆንን ነው የሄን የመሰለ እውነተኛ ታሪክ የምንሰማው ተው ተመስገን በሉ
መምህር በጣም ትልቅ ትምህርት ነው ለሁላችንም ጠቃሚ የሆነው ደስ የሚል ደጋግሜ አዳመጥኩት እናመሠግናለን እህታችን እናታችን ማርያም ወደቤቷ ትመልስልን❤🙏
Amen amen amen.memhr egziyabher andebetihn yubarkew yagelglot zebenihn yibarkew
መምህር በጣም ደስ ይላል በእዉነት እግዚአብሔር ይመስገን እህታችንን እግዚአብሔር በህልሙዋ እደጎበኛት በእዉንዋም ወደራሱ ይምራት እጅግ በጣም ተደስቼለሁ የድንግል ማሪያም ልጅ ስሙ በፈጠረዉ ፍጥረት ሁሉ የተመሰገነ ይሁን አሜንንንንን፫ መምራችን እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ ስለስተማርከኝና እድቀየር ምክኒት የሆንከኝ አንተነክ በእዉነት እዴት እደማመሰግንህ አላዉቅም እግዚአብሔር ከምታስበዉ በላይ ፀጋዉን ያብዛልህ በፀሎት አስበኝ አፀደ ማሪያም ብለህ አመሰግናለሁ
መምህር በእውነት እናመስግናለን ባአንድ ልጅ ቤተሰብ ያድናል በነገራችን ላይ እኔ አዲስ አበባ እያለሁ የምሰራባቸው ሰዎች ሶስት አይማኖት ነበራቸው እና በፍጽም አይስማሞ ነበር
እህታችን ደሞ እመቤቴ የጌታ እናት ጨርሳ ትማርሽ ወደ ቤቷ ታምጣሽ ዋነው ሀይማኖት ነው ስራ እራሱ እግዚአብሔር ይሰጥሻል
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን አሜን አሜንመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልህ አሜን አሜን አሜን
yes Memeher my sister saw Jesus in her dream, he was waking her up, telling her to get up and pray. same expression Memeher as you said, white cloth...Egziabeher yebarkeh. Am obsessed listening to you. I learned a lot from you. I was a protestant too, I had the same lack of peace when I was in there praying hall. I apologized for writing in English I don't have Amharic phonics on my computer. Emebete tetebek, betesebehen tebakeleh. Kalehiwoten yasemalen. Amen.
መምህር በዚህ ታሪክ ውስጥ የአያቶቼ እና አክስቶቸ ስቃይ ታወሰኝ ልጅ ሆኜ ብዙ ነገር አይ ነበር እሱም ምን መሰለህ የአባቴ እናት እና አባቱ ዛር አለባቸው የወንዱ አያቴ እህቱ እና ወንድሙ በጨንገር እና በሙጬዘሪጋ ምክንያት ሰልመዋል አሁንም ሙስሊም ናቸው ከጊዜ በኋላ ግን አክስቴቼን እና አጎቴን መንፈሱ ተዋረሳቸው የኔ አባት ብቻ ነው ጤነኛ ምክንያቱም እንዲህ አይነት አምልኮ አይቀበልም ይሰድበው ነበር ላንተ ማን ይሰግዳል ገብርኤል እያለ ይለው ነበር ።
አንደኛዋ አክስቴ ስታጎራ የወንዱ አያቴን አባት ስም ጠርታ በቅድመ አያቴ ስም ነው የዋጋው ጌታ ብላ ነበር በአንድ እግሯ እሳት ላይ ቆማ የምታጎራው አሁንም አለች በህይወት ግን አይኗን በጣም ያማታል አንዷ ግን ምንም አይነት ሰንደልና ሽቶ እንዲሸታት አትፈልግም ቡዳ ዛር ነኝ በረኸኛ ነኝ በሰማይ በራሪ ነኝ ጥጥ ስትለቅም አገኜሁዋት ይል ነበር ከአመታት ስቃይ በኋላ ሞተች አጎቴን ግን በጨጓራ አስመስሎ ሳያስጎራ በድንገተኛ ቡዳ ገደለው አንዷን አክስቴም እንዲሁ ገደላት
እግዚአብሔር ይሄንን እርኩስ መንፈስ ይገስፅልን
እህቴ በጣም መፀለይ አለባችሁ የሚዋረስ መንፈስ እያደፈጠ ስራውን ይሰራልና ንሰሐ ገብታችሁ ፀልዩ
@@ENTube-vi5km ልክ ነሽ እናት ግን እግዚአብሔር ይመስገን የኔ እናት እና አባት ስለማያምኑበት ወደኛ አልመጣም ቢሆንም መፀለይ ግድ ነው እንዳልሽው በህይወቴ ብዙ ጥያቄ ሚያስነሱብኝ ነገሮች አሉ ከእግዚአብሔር ጋር መልስ አገኛለሁ ብዬ አምናለሁ
እግዚሐብሄር ለቃሉ ታማኝ ነው ቅረቢው እንቆቅልሽን ይፈታል ተባረኪልኝ እህቴ
ቃለ ህይወት ያሰማልን
በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን
አዎን ይገለጣል ኮመንት አላበዛም ብቻ ግን አዎን ቅርብ ነው የኛ ጌታ እኔ ሀጢያተኛ ነኝ ግን ብዙ ነገሮች አሳይተኛል እግዚአብሔር እና መመለሳችን ነው እሚፍልገው እህታችን አሁንም ህይወትሽን ሁሉ ታስተካክልልሽ እም ብርሃን አይዞሽ ሁሉም ይስተካከላል መምህራችን ፀጋውን ያብዛልህ
እመቤቴ ማርያም ትታረቅሽ
በፀሎትሽ አስቢኝ
ወለተ ሥላሴ ብለሽ
እህት አለም
መምህር በጣም አመሰግናለሁ የእግዚአብሔር በረከት ካንተ ለይ ይሁን እግዚአብሔር ባንተ ላይ አድረው እኛን አስተምሮ ምክንያት እንድትሆን ይፍፈጣሪ ስም የተባረከ ይሆን በጸሎተ ሀሰብን
እልል ልልል እ/ር ይመስገን የድንግል ማሪያም ልጅ ስሙ ይመስገን
መምህር ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዕድሜ ጤና ይስጥልን።
እግዚአብሔር ያበርታክ ወደቤተክርሰቴያን ገብተክ ለድቃን በግተክ የእግዜያብሄር አገልገዬ ያድርግ ወድማቸን በርልን መምህር ተሰፋዬ ያገልግሎት ዘመንክር ይባርክልክ የማቶሳላን እድሜ ይሰጥክ እኞም ከሰደት ተመልሰን እንድብርክታዬት ነጬን ለመልበሰ የሰብን ነው በፀሎት አሰበን እህተ ማሪያም ፣ወለተ ተክልአይማኖት ብለክ አንተንም ለማግኝት እናሰባለን እግዜዬብሄር ይራዳን እግዜያብሄር እሰከቤተሰብክ ይጠብቅህ በርታልን
እግዚአብሔር ይመስገን መምህራችን
Amen amen amen ehetane ahunem embata terdashi
እውነት ነው ይገለፃል ምንስ እንኳን ጠፍተን ስናሳደው ስንበድለው ስንወጋው ስናቆስለው ብንኖርም እድሜ ለአባታችን ለመላእከ መንክራት መምህር ግርማ ከልብ ስንመለስ መመለሳችን ነው የሚፈልገው በድለውኛል ብሎ የማይቀየም ጌታ ከቶውንም ብሉኝ ጠጡኝ የሚል አባት ሳይገባኝ ለእኔም ተገልፀውልኛል ከወልጀ ካደኩበት ቦታ ነው የሚመስለኝ ሁለቱም ኢትዮጵያ መሬት ላይ ዋክ እያደረጉ አለባበሳቸው የሀበሻ የባህል ልብስ ነው ንፃቱ መግለፅ ከምችለው በላይ ነው የሚገርመው ንፃቱ እኩል ነው ህልሙ ሰፋ ያለ ብዙ ሚስጢር ያለው ነው ባጭሩ ነው መግለፅ ፈልጌም አልነበር ግን መምህር በእግዚአብሔር ስላልክ ነው። መምህር ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ገጠመኙም ትምህርቱም ሁሌም ግሩም ድንቅ ነው የብዙወቻችን ሂወት የሚቀይር ነው እግዚአብሔር አምላክ እህታችን ወደ እውነተኛዋ ሀይማኖት ስለእናቱ ስለድንግል ማርያም ብሎ ይመልስልን።
መምህራችን እግዚአብሔር እድመሜና ጤና ከፀጋ ጋር አብዝቶ ይስጥልን እውነት በገጠመኙ ውስጥ አንዳንድ የራሳችንን ገፀ ባህሪ እናገኛለን በተለይ በውስጡ ስታስተምር የምትሰጠን ማብራሪያ ትልቅ ትምህርት አለው እመቤቴ ከነ ልጇ ሺ አመት ታኑርልን መምህራችን በጣም ጠቃሚ ትምህርት ናቸው የምትለቅልን የዳቢሎስን ሴራ ማወቅ እና እንዴት እንደምንዋጋው እየአየን ነው 🙏❤️
#ዲስ ላይክ የምታደርጉ ሰዎች ጤናችሁ ያሳስበኛል አትግቡ የተዋህዶ ትምህርት ላይ ምድረ መናፍቃን እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ ወደ እውነተኛ ህይወት ይመልሳችሁ በጣም ታሳዝናላችሁ የተሸወደ ትውልድ 😭
Amen Amen Amen kale eywoten yasemalen edema besgawen yadelelen Ehtachenm ken melawe batesboche denesh Lemsekernte yabekash ye dengele mareya lije
እግዚአብሔር መምህራችንን ባለታሪኮችንም ሁሉ ጸጋ በረከቱን ይብዛላችሁ:: አሜን::
በስመአብ (እናመልከው ስለነበር እግዚአብሔር እጁን ከኛ ላይ አንስቷል) የሚገርም ንግግር የክርስቶስን ነፃ መሆን መመስከራቸው ደስ ይላል የሙዙ ትንሺ አስቆኛል
Tel giram layi asagbny
መምህራችን እድሜና ጤና ይስጥልን በምታቀርባቸው ትምህርቶች በሂወቴ ላይ ለውጥ አምጥቶልኛል፡፡ አንድ ነገር ልንገርህ የመምህራችንን የመምህር ግርማ ትምህርቶች መከታተል ከጀመርኩ በኋላ በጠቂቱ አምልኮ ጀምሬ አሁንም ንፁህ አምልኮት ላይ ነኝ ብዬ ደፍሬ መናገር ባልችልም ይኸው ‘’ንቁ በሃይማኖት ቁሙ ጎልምሱ ጠንክሩ’’ የሚለው የጌታችን የማበረታቻ ቃል በሂወቴ እየተከናወነልኝ ነው፡፡ ነገር ግና ቤተሰቦቼ አምልኮት ውስጥ ስላልገቡ ከኔ የበረታችሁ የተዋህዶ ልጆች በፀሎታችሁ አስቡኝ!! እግዚአብሔር ለሁላችንም ንፁህ ልብ ይፍጠርልን!! መምህራችን ቅድስት ድንግል ማርያማ ፈተናዎቹን በፅናት የምታልፍበትን ብርታት በምልጃዋ ታግዝህ!!
እንኳን በሠላም መጣህ መምህር ቃለ ሂወት ያሠማልን ፀጋውን ያብዛልህ ግሩም ድንቅ ነው
እግዚአብሔር ይመስገን አሜን ለሰተማረን ለመከሩን መምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን ፀጋውን ያብዛላችው የአገልግሎት ዘመናቸው ያርዝምልን በእውነት በቤቱ ያጽናልን ስልክ ጥሩ አስቀምጡልን ከስረ
መምህር እባክህን የእግዚአብሔር ስሞች መጹሁፍ ልቀቅልን አንተ ስታወራ ልኒይዘው አልቻልም
እውነት ነው ከተወሰነ አመት በፊት በጣም ተከፍቼ በየቀኑ ማታ ማታ አልጋዬ ላይ ሆኜ መዝሙረ ዳዊትን እያለቀስኩ አነበው ነበር በህልሜ በተራራ ላይ ሆኖ ተምበርክኮ ሲፀልይ ያለው ስዕለአድዕኖ ከቤቴ ጣራ ላይ ሆኖ አይዞሽ እኔ አለሁሽ በደንብ ፀልይ አለኝ።
ሌላው የካቲት 10 አካባቢ የመስኮቴን መጋረጃ ስገልጥ ከጐረቤት ባዶ የሆነ ቤት (በወቅቱ ተከራይ የለውም ነበር) ውስጥ እሱም በመስኮት በኩል ሲያልፍ ፈገግ ብሎ አለሁሽ አለኝ ከሳምንት በኋላ በጣም ታመን ነበርን ዳንን።
Amen amen amen kalhwet yasmalen 🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ቃል ህይወት ያሰማልን
ልዑል እግዚአብሔር በቤቱ አፅንቶ ለድቁና ያብቃህ መልካም ተጋድሎ ነው በዚህ እድሜህ በጣም የሚደነቅ ነው
በህልሜ ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሀን ተከቦ መጥቶ ሁሉንም ነገር የማደርግ በምክንያት ነው ብሎኛል በሌላ ጊዜ ደግሞ ቅዱስ ዳዊትን ሳኦልን እና ቅዱስ ጊ ዮርጊስን በህልሜ አይቻለሁ በሌላ ጊዜ ደግሞ ቅዱስ ዮሴፍን እና እመቤታችን ንፅሂት ቅድስት ድንግል ማርያምን አይቻለሁ
እመ አምላክ ትርዳሽ እሱ ናት ወደ ክርስቶስ መውጫ መሰላላችን።
ቃለ ህይወት ያሰማልን እህታችን ወደ እውነተኛዋ ቤተ መቅደስ ወደ እውነተኛይቱ እምነት ኦርቶዶክሳዊት ሀይማኖት ይመልስሽ ።
ቃለህይወት ያሠማልን ፀጋውን ያብዛልህ
የኔም አያቶቼ ጨሌ ጭዳ ምናም የተባሉትን ያመልኩ ነበር አሁን ግን ትተናል ብለውኛል እግዚአብሔር ይመስገን እንደዛም ሆኖ አያቴ በጣም በህመም እየተሰቃዬ ነው ሁሌም ያመዋል
በፀሎትህ አስብልኝ መምህር ወልደ ኪዳን እያልህ
እበራችንም ላይ አድባር አለ የሰፈሩ ሰው እየተሰበሰበ ለልደታ በወር በወሩ እያፈሉ ሰንደል እያጨሱ በሰኔ እና በመስከረም ፍየል ይታረዳል ተው ሲባሉ አይሰሙም ሌላው ቀርቶ የሆነ ነገር ሲሆን ይሳላሉ ከዛ ዳቦ ምናምን የማያረጉት የለም ቡና ያፈላሉ ያካባቢው ሰው ተሰብስቦ ይጠጣሉ ህፃኖች ሳይቀሩ በቃ ጭራሽ ምንም ነገር ሲሆን የአድባሩን ስም እየጠሩ ነው የሚሳሉት እንደዛም ሆኖ ለጊዜው ይሆንላቸዋል ከዛ በዛው ሁሌም ይች አድባር ደራሽ ነች ክፉ አታስነካንም እያሉ ደሞ እንደሴት አንቺ ነው የሚሏት😓
እግዚአብሔር ይርደሽ እውነት እህታችን
መምህራችን በእውነት ፀጋውን አቡዙቶ አቡዙቶ ይስጥልን። ቃለህወት ያሰማልን። በእውነት የተጠማች ነፊስ ምግባዋን እያገኘች ነዉ። በሪታልን መምህራችን ተስፈ ስላሴ ።
በጣም ደስ ይላልእህታችን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ትታረቅሽ እግዚአብሔር በቤቱ ይመልስሽ እኛ አይማኖታችን በጣም ነው ሚያኮራን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይውን ለዘላለም 🙏መምህራችን ቃለ እይወት ያሰማልን
እግዛብሄር ይባርክህ መመምህር
እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ህልማችንን ታሳካልን እውነት እህታችንም እመቤቴ ትሰብሽ ወንድማችን እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም መጨረሻህን ታሳምርልህ በፆለታችሁ አስቡኝ ደካማ እህታችሁን ወለተ ሰንበት
እግዚአብሔር ወደትክክለኛዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ይመልስሽ:: ልዑል እግዚአብሔር የቅድስት ድንግል ማርያምን የቅዱሳኑን ሁሉ ፍቅርና ፀጋውን ይግለፅልሽ ያድልሽ:: አሜን::