የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 12-ብፁዓን ናቸው (ክፍል 3)በማሙሻ ፈንታ-Matthew Teaching 12-Blessed are..(Part 3)| By Mamusha F

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 27 авг 2024
  • ይህ ትምህርት በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን፣ በአዲስ ክርስቲያን ላይፍ አሴምብሊይ አጥቢያ ዘወትር አርብ በማሙሻ ፈንታ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ነው።
    ትምህርቱን በቀጥታ ስርጭት መከታተል ለምትፈልጉ
    ዓርብ ምሽት 11:30 - 1:30
    Yoututube - Equip Media / @equipmedia2577
    Facebook - Equip Media Mamusha Fenta
    / 312726798871156
    አድራሻችን፡ ካዛንቺስ ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ባሻገር 200 ሜትር ገባ ብሎ
    ጉግል ማፕስ - google maps address
    maps.app.goo.g...

Комментарии • 63

  • @equipmedia2577
    @equipmedia2577  Год назад +7

    #እነሆ_ንጉሥሽ
    #የማቴዎስ_ወንጌል_ትምህርት_12
    #ብፁዓን_ናቸው (ክፍል 3)
    #በማሙሻ_ፈንታ
    📖 ማቴ 5:1-12
    - ብፅዕናዎች
    * የትዕዛዝ ሸክም አይደሉም፤ እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሰጠን። እነኚህ በመንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን እየመሠልን ስንመጣ በህይወታችን የምናፈራቸው ፍሬዎች ናቸው።
    * ሰው በክርስቶስ ይተከል እንጂ እነዚህን ማፍራቱ አይቀርም።
    * ለመጽደቅ የምናፈራቸው ሳይሆኑ ስለጸደቅን የምናፈራቸው ናቸው።
    * የመንግስተ ሰማይ መግቢያዎች አይደሉም፤ በክርስቶስ ነው የጸደቅነው።
    - ለአንዱ ክርስቶስ ታጭተናል፤ ለሱ እንኖራለን፣ እርሱን እናሳያለን።
    * የዛሬ ትኩረት ወደሩቅ ላሉ፣ ለሚያሳድዱ የሚገለጡ ብፅዕናዎች
    1) የሚምሩ (ቁ. 7)
    2) የሚሰደዱ (ቁ. 10)
    🙏 የሚምሩ
    - እግዚአብሔር የተቀበላቸው ምህረት የሚያደርጉ ናቸው፤ በረከታቸው ይማራሉ፤ በረከትን ያገኛሉ።
    - የእግዚአብሔር ምህረት በነጻ የሚገኝ ነው፤ ግን የተማሩ፤ ምህረትን ያገኙ ሰዎች ስለሆኑ፣ ምህረትን የሚያውቁ ሰዎች ስለሆኑ፣ እግዚአብሔር ስለማራቸው እነሱም ይምራሉ።
    - ይቅር የተባሉ ይቅርታን ስለሚያውቁ ይቅርታን ይሰጣሉ፤ በክፍያ ሳይሆን ምህረትን ስለተቀበሉ።
    - ሰርተን የምንቀበለው ምህረት፥ ምህረት ሊሆን አይችልም፤ ደመወዝ ነው። ለሰው ምህረት ሰጥተን ከእግዚአብሔር ምህረት አንቀበልም ግን ከእግዚአብሔር ምህረትን ስለተቀበልን፣ ምህረትን ስለምናውቅ ምህረትን እንሰጣለን።
    ➥ ምህረት
    * የእግዚአብሔር ባህሪ ነው
    * የእግዚአብሔር የማንነቱ መገለጫ ነው
    📖 ዘፀ 34:6
    📖 ሮሜ 12:2 (ርህራሔ)
    - ምህረት (ርህራሔ) ፦ ዋጋ ቢስ ለሆነ፣ ለማይጠቅም፣ ተስፋ ቢስ ለሆነ፣ ለውዳቂ ሰው፣ ለተሸነፈ ሰው የተገለጠ ፍቅር ነው።
    - ፍቅር መልሶ ለሚከፍል ሳይሆን፣ ተስፋ ላለው ሳይሆን፣ ደስ የሚል ባህሪ ላለው ሳይሆን፤ ደስ ለማይለው፣ ተስፋ ለሌለው፣ ለወደቀ ሰው የተገለጠ ነው፤ ይህም ምህረት፤ ርህራሔ ይባላል።
    - ብቃት ላለው የተገለጠ ፍቅር እንካ በእንካ ነው፤ አንድ ቀን መልሶ ይከፍል ይሆናል።
    📖 ሉቃ 10:
    - ምህረት የተቀበሉ ሁሉ ይምራሉ፣ ምህረት ይሰጣሉ።
    - ምህረት የሀይማኖት ግርግር የሚያስረሳው ባህሪ ነው፤ በሀይማኖት ይሸፈናል።
    - መንገድ ላይ የወደቀን ሰው ተጸይፈን መጥተን ስላጠንለት የሚቀበለን ይመስለናል፤ እግዚአብሔር ግን አስቀድሞ ምህረት እንድናደርግ ይፈልጋል።
    📖 ሆሴ 6:6
    📖 ሚክ 6:6
    - እግዚአብሔር የሚፈልገው ምህረት እንድናደርግ ይፈልጋል፤ በሩቅ ላሉ፣ ለተቸገሩ፣ ለምስኪኖች፣ ለማናውቃቸው፣ ከእኛ ለተለዩ፤ በችግር ውስጥ ላሉ፣ ተስፋ ቢስ ለሆኑ።
    📖 ማቴዎስ 9:9
    - የብፁዓን ዋና አምልኮ ለተለዩ ሰዎች፣ ለተቸገሩ ፍቅርን ይሰጣሉ።
    - እምነት ችግረኞችን እንድንጸየፍ ካደረገን ከኢየሱስ አይደለም።
    🙏 የሚሰደዱ
    - የብፅዕና አንዱ መገለጫ ስደት ነው።
    - የእግዚአብሔር ሰዎች አንዱ መታወቂያቸው በአለም መሠደዳቸው ነው።
    - አለም መስቀል ጎሽ አይልም፤ ሌላ ነገር ቀባብተን ካልሆነ።
    📖 ዮሐ 15:18
    📖 ፊል 1:29
    📖 2ጢሞ 3:12
    - ስደት አይቀሬ ነው፤ መከራ አይቀሬ ነው። ምክንያቱም ሲነቅፏችሁ ሲያሳድዷችሁ፣ በእኔ ምከንያት ክፉውን ሲያወሩባችሁ ነው የሚለው እንጂ ካወሩባችሁ አይልም።
    - ክርስትና ዋጋ ማስከፈል አለው።
    📖 1ጴጥ 3 እና 4
    - ስደት ስለስሙ፣ ስለኢየሱስ፣ ስለጽድቅ መነቀፍ ነው እንጂ በማንኛውም መከራ መሰደድ አይደለም።
    - ስደት የወንጌል ባህሪ ነው። አመቻምቾ ስዴትን ማስወገድ ይቻላል፤ እውነተኛው ወንጌል ግን ስደት አለው።
    - ላለመሰድ ወንጌልን አናቅጥን፤ አንቀላቅል ዋጋን እያሰብን እንደሰት እንጂ።
    - ስደት የእውነተኝነት ሰርተፍኬት ነው፤ የተሰደደ ሁሉ ግን እውነተኛ ነው ማለት አይደለም። እውነት ሳይሆኑ የሚሰደዱ ብዙ አስተሳሰቦች አሉ። ስለ ክርስቶስ መነቀፍ የነቢያቱ ህይወት ነው።

  • @SaraSara-nm9mk
    @SaraSara-nm9mk Год назад +2

    D/r mamusha gata abzeto yebarkeh
    Bante bizu tebarkalhu❤❤❤❤

  • @user-ek2tw9fh3p
    @user-ek2tw9fh3p Год назад +2

    አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን አሜን ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ሃሌሉያ ጌታ ኢየሱስ ስሙ ይባረክ

  • @mahederezeleke6946
    @mahederezeleke6946 Год назад +2

    3 geze semahut tebateku

  • @RahbotNhzbey
    @RahbotNhzbey Год назад +2

    Egziabiher Amlak Abzto ybarkh pastor Mamusha. Tkkle yalenbet geta yetenageren new. Egziabiher Amlak yrdan.

  • @wendesenhaile2321
    @wendesenhaile2321 Год назад +4

    ዶክተር ማሙሻ ስላንተ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። አንተ ለክርስቶስ አካል ትልቅ ሥጦታ ነህ። የምትናገረዉ ዕዉነትና ጤናማ ቃል ነው።
    ደግሞም መልዕክቱ እንዲሰማና ወደ ሰዉ ሕይወት እንዲገባ የእግዚአብሔር ፀጋ በሙላት አለበት።
    ስለሆነም እንደኔ አተያየ አገልግሎታችሁ በዕዉቀትም በቅባትም ነዉ። እንድንኖረው የጌታ ፀጋ ይብዛልን።
    ቆርኔሌዎስ "እንግዲህ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዝኸውን ሁሉ እንድንሰማ እኛ ሁላችን አሁን በእግዚአብሔር ፊት በዚህ አለን" እንዳለ ይህንን አገልግሎት የምንጠብቅ ብዙዎች ነንና በርቱ።
    (My short reflection)
    "በክርስቶስ እንደግ እንጂ እነዚህ (ክርስቶስን የመምሰል ባህሪያት) መንዠርገጋቸዉ አይቀርም"
    "እንተከል እንጂ ማፍራታችን አይቀርም"
    "እነዚህ (ምሕረት አስታራቂነት የጽድቅ ኑሮ) ለመፅደቅ የምንሠራቸዉ ሳይሆን ስለፀደቅን የምናፈራቸዉ ናቸዉ"
    "ምህረት ርሕራሄ ለወደቀና ተስፋ ለሌለዉ ሰው የሚገለጥ ፍቅር ማለት ነው"

  • @haregmulat1gmail
    @haregmulat1gmail Год назад +6

    የመንፈስ ፍሬ ይብዛልኝ ጌታሆይ አንተ በሰራኸው ወደከበረው ህይወት አፈለስከን ስሙ ይባረክ በማስተማር የምትተጉ ትጋትን። የሰጣችሁ ጌታ ስሙ ይባረክ እናንተም ለሀሳቡ ፈቅዳችሁ ግዜያችሁን ህይወታችሁን ለእኛም ለጌታም ስለሰጣችሁ ተባረኩ ዘራችሁ ይባረክ እናንተን የሚተካ ዘር አግኙ አሜን

  • @mame251
    @mame251 Год назад +5

    ተባረክ ወንድም ማሙሻ
    ትምህርቱ ስለምህረት ያለኝን መረዳት አስተካክሎታል
    በእሁድ መድረኮቻችን እንደነዚህ አይነት ትምህርቶችን ያብዛልን
    ፀጋው ይብዛልህ🙏

  • @bogaleagga9026
    @bogaleagga9026 Год назад +2

    አሜን🙏🏾

  • @emu6850
    @emu6850 Год назад +2

    አሜን አሜን 🙏🙏🥰

  • @lemlemlabite1284
    @lemlemlabite1284 Год назад +1

    ተባረክ ዶ/ር ማሙሻ

  • @taaadu9514
    @taaadu9514 Год назад

    አሜን አሜንን የሚያዋጥን እርሡ ብቻ ነው

  • @thevoiceofvoicelesslm4308
    @thevoiceofvoicelesslm4308 Год назад

    Ameeen.❤️❤️❤️❤️❤️

  • @meseretgetachew3744
    @meseretgetachew3744 Год назад +2

    አሜን ሃሌሉያ

  • @kabeshibshii8944
    @kabeshibshii8944 Год назад +1

    Amen Amen Geta eysus yibarki tabarki kibir lgeta yuni

  • @EleniYacob
    @EleniYacob 8 месяцев назад +1

    Thank you for equipping us. What a message. Be blessed more and more .

  • @rabihcall4540
    @rabihcall4540 Год назад +1

    ክብር ለእግዚአብሔር ይሁንንን አሜንንንንንንን ዶ/ር ማሙሻ ለምልም ተባረኩ❤❤❤

  • @martydawit5489
    @martydawit5489 Год назад +1

    አሜን🙏🙏🙏

  • @fireselam6578
    @fireselam6578 Год назад +2

    አሜንንን የእግዚአብሔር ጸጋ ይብዛልን!!
    አገልግሎትህን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክ!!

  • @salameskyes7240
    @salameskyes7240 Год назад +4

    ❤አሜንንንንንን የቃሉ ባለቤት እግዚአብሔር ይመስገን ❤ዶክተር ማሙሻ ዘመን ይለምልም❤ተባረኩ❤❤❤

  • @biliseedaanii3611
    @biliseedaanii3611 Год назад

    Ameeen Dr Tebareku

  • @mulukenmihretu
    @mulukenmihretu Год назад +2

    ክብር ሁሉ ለጌታ ለኢየሱስ ይሁን ተባረኩ በጌታ በኢየሱስ ስም 🙏❤️❤️

  • @yonasnegasa4493
    @yonasnegasa4493 Год назад

    Waaqayyoo si haa eebbisuu! sin jaalladha!

  • @kalkidanakalu9180
    @kalkidanakalu9180 6 месяцев назад

    ማሙሻዬ ጌታ ዘመንህን ይባርክ።

  • @taaadu9514
    @taaadu9514 Год назад +2

    ክብር ሁሉ ለጌታ ይሁን ክብሩን ሁሉ ይውሰድ። በዚህ ዘመን አንትን ከወንድሞቻችን መካከል አንተን ስለሠጠን ማደሪያው ይባረክ 👏👏👏👏👏

  • @Jesusislove-gf3ox6wo8m
    @Jesusislove-gf3ox6wo8m Год назад +3

    ዋው ስለ ዚህ ትምህርት ቃል የለኝም ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን ጌታ ስለ አንተ ይህን ፀጋ ስለሰጠህ አምላኬን አመሰግናለሁ ❤❤ d.r ፀጋ ይብዛልህ ባለቤትህን ልጆችህን ያንተ የሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ!!❤❤

  • @tseghewoldu4016
    @tseghewoldu4016 Год назад +1

    May God bless you and uses more and more for his glory 🙏 Amazing

  • @kassahunmekuria4629
    @kassahunmekuria4629 Год назад +1

    አሜን

  • @liyaelias2773
    @liyaelias2773 Год назад +1

    እራሴን እንዳይ ነው ያደረገኝ ተባረክ ማሙሻዬ

  • @shalomdr7shalomdr757
    @shalomdr7shalomdr757 Год назад +1

    Gbu
    Brother Mamusha!

  • @user-nx2lo8fy8v
    @user-nx2lo8fy8v Месяц назад

    ዶ/ር ማሙሻ ተባረክ ትምርቱን በደንብ ተምሬ ለመረዳት እየሞከርኩኝ ነው።

  • @zinashmamo9676
    @zinashmamo9676 Год назад +1

    ❤❤❤❤አሜንንንንንንንንን አሜንንንንንንን ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን አሜን ተባርኩ❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @nigusalemayehu0199
    @nigusalemayehu0199 Год назад +1

    Dr tabarak

  • @beshook9281
    @beshook9281 Год назад

    God bless you Mamusha.

  • @user-xf5dy8oi6n
    @user-xf5dy8oi6n Год назад +1

    አሜንንንንንን አሜንንን አሜንንንንተባረክልን

  • @sosenanaser8565
    @sosenanaser8565 Год назад +1

    በእውነት ፀጋ ይብዛልህ ስላንተ ጌታን አመሰግናለው

  • @marthamule9997
    @marthamule9997 Год назад +1

    እግዛብሔ ይመስገን ስለቃሉ ጌታ እረዳኝ የእውነት እንድኖረልህ ❤❤ዘመንህ ዘረህ ይባረክ

  • @serguttilahun2443
    @serguttilahun2443 Год назад +1

    እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን ልባችን ረሰረስ በሚመቸን መልኩ ቃሉን እየተጠቀምን ራሳችንን አማኝ አድርገን ከፍ ያለ ወንበር ላይ አስቀምጠን የእግዚአብሔር እስራኤል መባላችንን ዘንግተን ልክ እንደ አይሁድ መመረጣችንን እንደ privilege ወስደን መብራት መሆናችን ቀርቶ እንቅፋት እንዳንሆን ማንቂያ ደውል የሆነ መልእክት ነው እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ ወንድም ማሙሻ እግዚአብሔር ሆይ አግዘን 📢📢📢🔊🔊🎺🎺🎺🔔🔔🔔

  • @hanatesseme9170
    @hanatesseme9170 9 месяцев назад +1

    የዘላለም አምላክ ጌታ እግዚአብሔር ይባርክህ ዶክተር ማሙሻ ለሰማነውና ለምንሰማው በሰማነው እንድንኖር ጌታ ይርዳን

  • @user-xf5dy8oi6n
    @user-xf5dy8oi6n Год назад +1

    ♥♥♥♥♥♥♥♥♥

  • @user-ek2tw9fh3p
    @user-ek2tw9fh3p Год назад +1

    ጌታ ኢየሱስ ዘመንህን ይባርከው

  • @yodittezaz1419
    @yodittezaz1419 3 месяца назад

    ተባረክ

  • @Ethiopiatomorrow
    @Ethiopiatomorrow Год назад +1

    Be blessed!

  • @yamrotyammer9960
    @yamrotyammer9960 Год назад +1

    ጌታ ይባርክህ ዶከተር ማሙሻ

  • @zewditesfatsion693
    @zewditesfatsion693 Год назад +1

    🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @kali2839
    @kali2839 Год назад +1

    ተባረኩ ወንድሞች

  • @jesuschrist15111
    @jesuschrist15111 Год назад +1

    ምሕረትና ጸጋ፣ ሰላምና ፍቅር ይብዛልን፤ ሃሌ ሉያ አሜን።✞❤
    ✞ክብር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።✟❤
    “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።” - ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

  • @Rosei870
    @Rosei870 Год назад +1

    Egziabher Yimesgen

  • @bereketalemayehu
    @bereketalemayehu Год назад

    ❤❤❤

  • @Newaccountbunnimeow
    @Newaccountbunnimeow Год назад

    God bless you

  • @Aki-rl2wz
    @Aki-rl2wz Год назад +1

    Woww wonderful teaching God bless you more ❤❤️🙏

  • @getinettafesetucho7999
    @getinettafesetucho7999 5 месяцев назад

    እረጂም ጊዜ ሆነኝ እንዲህ ያለዉን ስብከት ከሰማሁት። ተባረኩ ዶ/ር ማሙሻ የእግዚአብሔር አገልጋይ። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን 🙏

  • @netsanetgood992
    @netsanetgood992 Год назад +1

    ተወዳጅ ወንድሜ ጌታ አብዝቶ ጸጋውን ያብዛልህ 🙌 ብዙ ነገር ተምሬአለሁ አመሰግናለሁ❤️🙏

  • @rodasgetachew9347
    @rodasgetachew9347 Год назад +3

    ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ ማሙሻዬ በጣም ነው የምንወድህ ጸጋም ይብዛልህ ያንተ የሆነው ሁሉ ይባረክ ይጠበቅ❤❤❤

  • @frehiwotkelelaw5401
    @frehiwotkelelaw5401 Год назад +1

    ሁላቹሁንም እግዚአብሔር ይባርካቹሁ።❤❤❤❤

  • @taaadu9514
    @taaadu9514 Год назад +3

    ለዚች ቅብ ለሆነች አርቴፊሻል ለሆነች አለም እውነት ነው ለእርሡ እንኑር👏👏

  • @jamanolach5220
    @jamanolach5220 Год назад

    I am christian, but not pente or religions . You r a good christian preacher. God bless u.

  • @mesertkebede4115
    @mesertkebede4115 Год назад

    Geta Eysus hoye temsgm 🙏
    GoD bless you all 🙏

  • @selamugenetu9253
    @selamugenetu9253 Год назад +1

    ማብራሪያ ለምን እደቀረ ብታሳውቁ መልካም ነው።
    እኔ ግን ከምዕራፍ 1-5 እየተከታተሉኳችሁ ነው።በዚህም ትምህርት ተማርኩ ተማርኩ ተማርኩ እንጂ አልከሰርኩም።
    ስለዚህም ማብራሪያወ ይቀጥል

    • @equipmedia2577
      @equipmedia2577  Год назад

      አልቀረም ሼር እናደርጋለን

  • @RACH-leah
    @RACH-leah Год назад

    Can someone send me the address of this program? Also the the days and the times of the program?

  • @BirtukanKebededemise
    @BirtukanKebededemise Год назад +1