የማርቆስ ወንጌል ታሪካዊ ዳራ | ማርቆስ ወንጌልለምን ተጻፈ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 29 окт 2024

Комментарии • 1

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic  6 месяцев назад

    የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች
    1. ማርቆስን ስታነብቡ ሁሉንም ታሪኮች ከጴጥሮስ አንጻር ዐስቡ። ይህ ይሁዲ የገሊላ ዓሣ አጥማጅ እነዚህ ከኢየሱስ ጋራ ያሳለፋቸው ተመክሮዎች ሕይወቱን የሞገቱት እንዴት ነው? ስለ መሲሑ
    ይጠብቀው የነበረው ነገር በመጽሐፉ ውስጥ እንዴት የተለወጠ ይመስላችኋል?
    2. በማርቆስ ውስጥ ኢየሱስ በትምህርቶቹ መሪነትን እንዴት እንደቀረጸ፣ ከሌሎች ጋራ ያለውን ግንኙነትና የቅርብ ሰዎቹን ደቀ መዛሙርት ያደረገበትን መንገድ በትኩረት ተመልከቱ።
    የትኛው ነው ትኩረታችሁን የሳበው? በዙሪያችሁ ካሉ ሰዎች ጋራ ባላችሁ ግንኙነት ውስጥ የርሱን ምሳሌ በመከተል እንዴት ተግባራዊ ማድረግ ትችላላችሁ?
    3. በማርቆስ 1፥15 ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ከመልካም ዜና (ወንጌል) ጋራ አስተካክሎ አቅርቧል። በማርቆስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ እግዚአብሔርን መንግሥት እንዴት ነው የገለጸው? ይህ መንግሥት እንዴት “የምሥራች” ሊሆን ቻለ። የዚህን መንግሥት መልካም ዜና በተመለከተ የእኛ ኀላፊነት ምንድን ነው?