የፊልጵስዩስ መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 13 сен 2024
  • የፊልጵስዩስን መልእክት እንዴት እናጥና?
    ጳውሎስ ከፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረው ግንኙነት በጣም የጠበቀና የቅርብ ግንኙነት ከነበረው አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ነበር፡፡ በዚህ ደብዳቤውም በባህላቸው ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ የተለዩ እንዲኾኑ በስፋት ይነግራቸዋል ይኸውም የክርስቶስን የትህትና ባህሪ እንዲላበሱ ነው፡፡
    ባህላቸውን ለመረዳትና፣ ባሉበት አለም ውስጠ ኢየሱስን መምሰል የሚያስከትለውን መሠረታዊ የኾነ አስሚታ ለማወቅ፤ ወደ ጥንታዊቷ የፊልጵስዩስ ከተማ ይጓዙ፡፡
    www.thebibleeff...
    FACEBOOK: / experiencethebibleeffect
    INSTAGRAM: / thebibleeffect
    ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
    #ፊልጵስዩስ #የመጽሐፍቅዱስጥናት #የመጽሐፍቅዱስቪድዮ

Комментарии • 7

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic  Год назад +1

    ለተጨማሪ ጥናትና ለሕይወት ተዛምዶ የተዘጋጁ ጥያቄዎች
    1) 1፥1 ጳውሎስ ለቤተ ክርስቲያናት በሚጽፈው ደብዳቤ ኹሉ ራሱን ሐዋርያ ብሎ ያስተዋውቃል፡፡ ይኹን እንጂ ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ራሱን ያስተዋወቀው “አገልጋይ/ባርያ” ብሎ ነው፡፡ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ራሱን ሐዋርያ በማላት ያላስተዋወቀው ለምን ይመስላችኋል?
    - በአስቸጋሪ ኹኔታዎች ውስጥ ስኾን ሌሎችን ወደ ኢየሱስ በመጠቈም በዙሪያዬ ያሉ ክርስቲያኖችን አበረታታለኹ? በዚህ ረገድ ይበልጥ ለማደግ ምን ማድረግ እችላለኹ?
    2) 1፥27 ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ መኖር ማለት ምን ማለት ነው?
    - ስለ መከራና ሥቃይ ያለኝ አመለካከት ከጳውሎስ አመለካከትና ከኢየሱስ ምሳሌ ጋር ሲነጻጸር ምን ይመስላል?
    - 2፥6-8 በሕይወቴ ወስጥ ለሎችን ከማገልገል ይልቅ በራሴ መብቶች ላይ ብቻ የማተኵርባቸው ጕዳዮች የትኞቹ ናቸው? የክርስቶስን የትህትና ምሳሌ በመከተል ውጤታማ ለመኾን ምን ማድረግ እችላለኹ?
    3) 2፥6-11 በዚህ ምንባብ ውስጥ የተዘረዘሩትን የኢየሱስን መገለጫዎች በሙሉ ተመልከቱ፡፡ ከተዘረዘሩት ውስጥ ስለ ኢየሱስ እውነት የኾኑት ነገሮች ምንድን ናቸው?
    - በሕይወቴ ወስጥ ለሎችን ከማገልገል ይልቅ በራሴ መብቶች ላይ ብቻ የማተኵርባቸው ጕዳዮች የትኞቹ ናቸው? የክርስቶስን የትህትና ምሳሌ በመከተል ውጤታማ ለመኾን ምን ማድረግ እችላለኹ?
    4) 3፥20 ጳውሎስ ዜግነታችን በሰማይ ስለ መኾኑ ለፊልጵስዩስ ቤተ ክርስቲያን የነገራቸው ለምንድን ነው? ይህን መንገሩ ምን አይነት አስሚታ በእነርሱ ዘንድ ይፈጥራል?
    - በሕይወቴ ውስጥ ከዘር ሐረጌ ወይም ከስኬቶቼ በመነሳሣት ከእግዚአብሔር ዘንድ የበለጠ በረከት ማግኘት እንደምችል የማስብባቸው ቦታዎች ይኖሩ ይኾን?
    - 4፥4-9 እነዚህን የጳውሎስን ትዕዛዛት አንብቧቸውና አሰላስሏቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የትኞቹን በዐዲስ መንገድ እንድትራመዱባቸው እንደሚፈልግ እግዚአብሔርን ጠይቁት፡፡
    5) 4፥15-18 - በጳውሎስ አገልግሎት ውስጥ የፊልጵስዩስ ሰዎች ምን ዐይነት ሚና የተጫወቱ ይመስላችኋል?
    - ለጋስነት ወይም ልግስና በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ምን ዐይነት ሚና አለው?

  • @_voiceoftheword
    @_voiceoftheword Год назад

    ተባረክ ያምላክ!!!

  • @yonatansimon1994
    @yonatansimon1994 Год назад

    God bless you Yeamlak, it is helpful.

  • @helinaabebe5223
    @helinaabebe5223 Месяц назад

    እግዚአብሔር ይባርካቹ ይህን በአማርኛ ማዘጋጀታቹ።እባካቹ ቀጥሉ ❤❤❤
    from Orthodox twehaedo

    • @thebibleeffectamharic
      @thebibleeffectamharic  Месяц назад

      ስለተመለከቱ እናመሰግናለን፣ እና ስለ ማበረታቻዎ! ለመጽሐፍ ቅዱስ ምንጮች ማቅረባችንን እንቀጥላለን! መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠና እግዚአብሔር ይባርክህ!

  • @tigistsolomon5756
    @tigistsolomon5756 Месяц назад

    ብሩክ ነህ