እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እምነት - ጳውሎስ ፈቃዱ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 18 окт 2024
  • የእምነት ግቡ ምንድን ነው?
    ሁሉስ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል?
    ታዲያ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው እምነትስ የትኛው ነው?
    ዕብራውያን 11 የእምነት አባቶችንና እናቶችን ግለ ታሪክ በየፈርጁ እየዘረዘረ እግዚአብሔርን ስለሚያስደስተው እምነት ምንነት ማስረጃና ድንቅ ትንታኔ ያቀርባል።
    ዘመናችን በእምነት ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ በርካታ እሳቤዎች በየቤተ ክርስቲያኑ ምስባክ ሲሰራጩ ይገጥመናል፤ በዚህ ዐይነቱ ሁናቴ ውስጥ የዕብራውያን 11ኛ ምዕራፍ አስደናቂ መልእክት አለው።
    እምነት ሲተነተንና ሲተገበር ምን እንደሚመስል ከዚህ ስብከት ባሻገር ተጨማሪ ትምህርት ለማግኘት ቢሹ፣ “የእምነት ኀይል” በሚል በጳውሎስ ፈቃዱ ወደ አማርኛ የተመለሰውን መጽሐፍ ቢያነቡ ይጠቀማሉ። ይህንንም መልእክት እዚያ ውስጥ ያገኙታል።

Комментарии • 113

  • @eysusyadinaleysusgetanew4992
    @eysusyadinaleysusgetanew4992 4 года назад +3

    አሜን አሜን እግዚአብሔር እኛን የጠራ ወደ እሱ ነው

  • @netsanetzegeye5884
    @netsanetzegeye5884 2 года назад +1

    ንጹህ ትምህርት ጌታ እንዲህ ያለውን ያብዛ ለእርስዎ ጤና ከእድሜ ይስጥ በኢየሱስ ስም።

  • @Ewneta-p1p
    @Ewneta-p1p 3 года назад +3

    አሜን አሜን
    ገብቶንና ተረድተን የበለጥከውን አንተን እንድንፈልግ ፍለጋችን አንተን ብቻ እንዲሆን እርዳን አባት ሆይ🙇‍♀️

  • @eysusyadinaleysusgetanew4992
    @eysusyadinaleysusgetanew4992 4 года назад +2

    እግዚአብሔር ሆይ ከአንተ ጋር መኖር መታደል ነው ወደ አንተ አሰጣጋኝ

  • @mulualembaye6127
    @mulualembaye6127 3 года назад +3

    እግዚአብሔርን ራሱን መውረስ ከምንም ጋር አይወዳደርም አሜን አሜን አሜን ይሁንልን

  • @AmanuelTesfaye-fv1mn
    @AmanuelTesfaye-fv1mn 3 дня назад

    በብሉይ ኪዳን የኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ነው ተብሎ ስለሚታመነው ስለ መልአከ ያህዌ(የእግዚአብሔር መልአክ)በወንጌላውያንን፣በኦርቶዶክስ አና በካቶሊካውያን ዘንድ ስላላቸው ምልከታ አስተምረን 🙏

  • @iftuabdissa6171
    @iftuabdissa6171 3 года назад +3

    እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ

  • @yayena123
    @yayena123 10 месяцев назад +1

    አሜን አሜን🙏❤🙏

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  10 месяцев назад +1

      God bless

    • @yayena123
      @yayena123 10 месяцев назад

      Amen amen🙏🙏🙏 በጣም ተባርኪለሁ በትምህርትዎ ወንድሜ ጳውሎስ እግዚአብሔር አባታችን እድሜዎን ያርዝምልን አሜን🙏
      ግን በጣም ተይቅርታ ጋር አንድ ጥያቄ ልጠይቆት ነው!
      በትምህርቶ መጨረሻ ላይ የጸለዬት ጾለት ላይ የሆነ ቃል ሲጠቀሙ ሰማሆት
      ምንድነው እርሱ፦ #በደላችንን መተላለፋችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይቅር በለን የሚል ነበር።
      -በኢየሱስ እያመንሁ እስካሁን #በደሌ መተላለፌ ይቅር አልተባለልኝም ማለት ነው?
      የዳነ ሰው የምን በደልና የምን ሀጢያት ነው ይቅር የሚባልለት የክርስቶስ ስጋ አንድ ግዜ በማቅርበን አልተቀደስንም እንዴ?
      እስኪ ለጥያቄ መልስ እፈልጋለሁ።

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  10 месяцев назад

      @@yayena123 በየቅኑ የምንሠራው ኀጢአት ይቅርታ አያስፈልገውም?

    • @yayena123
      @yayena123 10 месяцев назад

      @@PaulosFekadu
      በየቀኑ ምንሰራው ሀጢያት#የአለም ሀጢያት ይባላል#የአለምን ሀጢያት ሆነ የውርሱን ሀጢያት ሳላለፈው#ሀጢአት ሆነ ስላሁኑ #ሁሉንም ሀጢያት የኢየሱስ #ስጋ ሀጢያቶቻችንንን ሁሉ አንድ ግዜ #ቅዱስ ስጋውን አቅርቦ ለዘላለም ከሀጢያቶቻችን ሁሉ ዋጅቶናል።
      የትኛውን ሀጢያት ነው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቅርታን የምንጠይቀው?
      ጥያቄ ግልጽ ይመስለኛል እርስዎ እያስተማሩና እየጸለዬ ያሉት በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን ለዳንን ክርስቲያኖች ከሆነ
      ለምን በደላችን ሀጢያታችን ይቅር በለን ብለን እንጸልያለን?
      የዳነ ክርስቲያን የትኛውን በደል ነው ይቅር የማባልለት #ስንት ግዜ ነው ኢየሱስ ስለኛ ሀጢያት መስዋት የሚሆንልን?

  • @efremtilahun2323
    @efremtilahun2323 3 года назад +3

    እጅግ በጣም ድንቅ ነው ፖል የዘመናችን ሀዋርያ በርግጥ እግዚአብሔር እኛን የወደደበት ፍቅሩን የተለየ ያደረገውን ምክንያት ሸላሚው ና ሽልማቱ እራሱ መሆኑ ይገርማል ዘፍ 15:1 እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ ታላቅ ዋጋህም እኔው ነኝ አለው ጌታ አምላካችን የአንተንና የቤተሰብህን ዘመን በእርሱ ዋጋ ይባርክልህ

  • @yewobdardemissie5236
    @yewobdardemissie5236 2 года назад +1

    ተባረክ

  • @sarabeatay8253
    @sarabeatay8253 3 года назад +2

    ኡፍፍፍ የክርስትና ጣእሙን እምነትን አብራራህልን
    ጌታ ይባርክህ አመሰግናለሁ

  • @PerfectGRACEMinistries-2023
    @PerfectGRACEMinistries-2023 7 месяцев назад

    ተባረክ ጌታ ፀጋውን ያብዛልክ

  • @መቅደስላኔህይዎትክርስቶስ

    የፀጋው ባለቤት እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ አሜንንንንን እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @habtishjenbola367
    @habtishjenbola367 9 месяцев назад

    የሚገርም ትምህርት ነው...ደጋግሜው መስማት ይኖሮብኛል...ትንሽ ብልጭ ያለ ነገር አለ...ደጋግሜ ሰማዋለው.....ፀጋ ና ሰላም ይብዛልህ

  • @boshabombe8036
    @boshabombe8036 4 года назад +2

    Amazing teaching . Am blessed and got new insight . May God bless you!

  • @eysusyadinaleysusgetanew4992
    @eysusyadinaleysusgetanew4992 4 года назад +1

    Zamanhe yibareke tabareke
    Amen egzabern dase yemyasange rmunate yisatan

  • @almazabebayehu7483
    @almazabebayehu7483 4 года назад +1

    Amennn amenn geta hoy anten mefeleg abzalng amennn tebarekk wendme pawlos

  • @damtewtesfaye9149
    @damtewtesfaye9149 2 года назад +2

    It is an amazing message. I listened from start to finish. It has helped me in soul searching. You have been a huge blessing. May the Lord bless you even more

  • @danielhailemelekotambaye5563
    @danielhailemelekotambaye5563 4 года назад +1

    Godblessedyou

  • @משהאדגו-כ6ו
    @משהאדגו-כ6ו 2 года назад

    תודה

  • @yoditalemayehu9930
    @yoditalemayehu9930 4 года назад +1

    God bless u

  • @fitsumgetahun2749
    @fitsumgetahun2749 2 года назад +1

    ዋው!

  • @selam2229
    @selam2229 4 года назад

    "ሸላሚው እግዚአብሔር ነው ሽልማቱ እግዚአብሔር ነው"!! በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ተባረክ poዬ!!!

  • @mulualembaye6127
    @mulualembaye6127 3 года назад +1

    አንተን ማትረፍ ይሁንልን

  • @emuye10
    @emuye10 4 года назад +2

    TEBAREK ,GETA YERDAN.

  • @lydiahana5616
    @lydiahana5616 3 года назад +1

    ተባረክ ወዳጄ 🙏🙏🙏🌻🌻

  • @habtehyimermesfin796
    @habtehyimermesfin796 4 года назад +1

    Paulo's God bless you.

  • @abewada4784
    @abewada4784 Год назад

    Amen amen

  • @AMLIKOMISGANAPRODUCTION
    @AMLIKOMISGANAPRODUCTION 4 года назад

    እውነተነኛው እምነት እግዚአብሄርን በማስደሰት መኖር!!!!!! ተባረክ ፖል ቆንጆ ስብከት ነው፡፡

  • @idriskolsawala4291
    @idriskolsawala4291 2 года назад

    እግዚአብሔር ይባርክህ በረከታችን ነህ❤️

  • @blenberhanmamoye5801
    @blenberhanmamoye5801 4 года назад

    Amen tebareke

  • @martatberkealhamed2015
    @martatberkealhamed2015 4 года назад

    ዋው ዋው ጌታ ሰው አለው ለካ ተባረክ

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад

      ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን።

  • @abenezerkebede9429
    @abenezerkebede9429 8 месяцев назад

    Thank you brother! We are waiting for a new book!

  • @zekariaszeko1377
    @zekariaszeko1377 2 года назад

    ፍቄ ወዳጄ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርከው።

  • @vengeanceismineiwillrepays9016
    @vengeanceismineiwillrepays9016 4 года назад +1

    Wonderful message! Keep fighting the good fight!

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад

      I will, but keep me in your prayers

  • @jameela3971
    @jameela3971 4 года назад

    አተ የግዛቤር ሠው ፀልይልኛ እኛበሠዋገሪ መፈሥ እየአሣደደንነው ዘመናችነን እየበላ ያለትዳር ለወድሜም ለሆቴም እያሥጨነቀን ወድሜ ያለሥራ ያለትዳሪ ከሠውጋሪ እድአንሥማማ አደረገን አደረገን 2013 የመለወጥ አመት እድሖንልን በየሡሥምፀ ፀልይልን

    • @lovewin1582
      @lovewin1582 3 года назад +1

      ጌታ ፍፁም አርነትን ይስጣችሁ!🙌

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  5 месяцев назад

      God bless

  • @fitsumabaruda1643
    @fitsumabaruda1643 4 года назад

    አሜን ፖዬ ተባረክ

  • @sabam473
    @sabam473 4 года назад +1

    Birik bel, Poyé!

  • @eyesusyadinale4048
    @eyesusyadinale4048 4 года назад

    አሜን።ተባረክ።🙏

  • @genethabdi2647
    @genethabdi2647 4 года назад

    Amen ! tebarek !

  • @netsyabebe1484
    @netsyabebe1484 4 года назад

    ፖዬ ዘመንህን ጌታ ይባርከው!
    More grace be up on you!

  • @mesaygebereyes950
    @mesaygebereyes950 4 года назад

    Geta yebarekeh brother

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад

      አሜን። አብሮ ይባርከን።

  • @dawitbelete8292
    @dawitbelete8292 4 года назад

    ወንድሜ ተባረክ

  • @hanaberhaneyesus7502
    @hanaberhaneyesus7502 4 года назад

    God bless you brother paul🙌🙌🙌🙌🙌🙌

  • @girmachewhabtie7873
    @girmachewhabtie7873 4 года назад +1

    ፖል ቡሩክ ነህ!

  • @binisadeba7176
    @binisadeba7176 8 месяцев назад +1

    ፖል አንተኮ ብሩክ ነህ!!!

  • @zozotadesse7230
    @zozotadesse7230 4 года назад

    Esey tebarek brother

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад

      አሜን። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

  • @amenamen9497
    @amenamen9497 4 года назад

    Egzabher yibarkih 🙏🏽🙌🏽

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад

      አሜን። ሁላችንንም ይባርከን

  • @yeruksewmerid3973
    @yeruksewmerid3973 4 года назад

    God bless you

  • @enlightedbyHim
    @enlightedbyHim 4 года назад

    Thank you for the unadulterated exposition of the Word. I have been blessed by your ministry. Keep it up!

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад +1

      I'll. Keep me in your prayers.

  • @mahederbiltibo2749
    @mahederbiltibo2749 4 года назад

    May the Lord bless you in abundance dear brother. This is from God!

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад +1

      አሜን። ለሚሰሙኝም ጸጋ ይብዛ

    • @jesusislord9447
      @jesusislord9447 4 года назад

      Paulos Fekadu Amen yibzalen! Pray for us😊

  • @surafelbayu6990
    @surafelbayu6990 3 года назад

    geta yebarkeh wendme

  • @amsalberehanu5535
    @amsalberehanu5535 3 года назад

    ጳውሎስ የጌታ ሠላም ይብዛልህ ባለፈው ኢትዮጵያ የመጣህ ጊዜ ስነ ክርስቶስ Christology / እየጻፍክ እንደነበረና በቅርቡ ገበያ ላይ እንደሚቀርብ የነገርከኝ መስሎኛል አ.አ. ጠይቄ ነበር አላገኘሁትም ገና ነው ወይስ?

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  Год назад

      አላገኘኸውም እስካሁን?

  • @chunafitness4128
    @chunafitness4128 4 года назад

    ፖል በ20-21 ደቂቃ ላይ ቢሆንም ባይሆንም እሚል ልብ እግዚአብሔርን አያገኘውም ስትል በግማሽ ልብ ለማለት ነው? ምክንያቱም በትንቢተ ዳንኤል ላይ ሶስቱ ወጣቶች ባያድነንም እንኳ ብለዋል እናም አንዳንዴ ነገሮች ቢሆኑም ባይሆኑም እግዚአብሔር ግን ፃድቅ ነው እንላለን ታድያ ይህ ሁለት ልብ ነን ማለት ነው?

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад +3

      አዎን፤ በግማሽ ልብ ማለቴ ነው፡፡ ዳንኤልና ጓደኞቹ ቢያድነንም ባያድነንም አንሰግድም በማለታቸው እንዲያውም እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ ማመናቸውን ነው የሚያሳየው፡፡

  • @chunafitness4128
    @chunafitness4128 4 года назад

    ፖል 8ኛው ደቂቃ ላይ ያነበብከው ጥቅስ ዕብ 11:32 ላይ ያለ ነው እንዴ ግራ አጋባኸኝ? 39 ነኛውም ላይ ያለው ጥቅስ ከየትኛው ምዕራፍ ነው?

    • @PaulosFekadu
      @PaulosFekadu  4 года назад

      ይቅርታ። ምዕራፍ 10 ነው።

    • @chunafitness4128
      @chunafitness4128 4 года назад +1

      Paulos Fekadu bless you Paul መቼም እንዴት ደጋግሜ እንደሰማሁ