አፄ ሱስንዮስ ቀዳማዊ/Emperor Susenyos I በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብቸኛው ካቶሊክ ንጉስ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 23 сен 2023
  • Fasilides: • አፄ ፋሲለደስ/Emperor Fasil...
    ሱስንዮስ ቀዳማዊ ወይም ካቶሊኩ ሱስንዮስ እ.ኤ.አ ከ1607-1632 ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት እና የሰሎሞናዊ ሥርወ መንግስት አባል ነበሩ።
    የዙፋን ስሞቻቸውም ሥልጣን ሰገድና መላክ ሰገድ ሳልሳዊ ነበር።
    እርሱም አባቱ አቤቶ ፋሲል፣ አያቱ አቤቶ ያዕቆብ እና ቅድመ አያቱ ደግሞ ዳዊት ዳግማዊ ወይም ልብነ ድንግል ነበሩ። በዚህም ምክንያት አንዳንዶች የጎንደር መስመር ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግስትን የመሰረተው ልጁ ፋሲለደስ ሳይሆን አፄ ሱስንዮስ እንደሆነ ይናገራሉ።
    የአፄ ሱስንዮስ የህይወት ታሪክ የታወቀው ጸሐፌ ትዕዛዝ በተባሉ ጸሐፊዎች በተፃፈው ዜና መዋዕሉና ኢየሰሳውያ ኢትዮጵያ ሲመጡ ስለነበራቸው ሁኔታ በፃፉት ጽሑፎች ነው።
    ሱስንዮስ እናቱ ሀመልማል ወርቅ ከወለደቻቸው 5 ወንዶች ልጆች ውስጥ ትንሹ ነበረ።
    በልጅነቱ ወቅት ሱስንዮስ ዘመቻ ባካሄዱ ኦሮሞዎች ተማርኮና አባቱ አቤቶ ፋሲል እና ሌሎች ተገድለው ነበር። ሱስንዮስም ከዓመት በላይ ተማርኮ ከቆየ በኋላ እ.ኤ.አ በ1585 ደጃዝማች አስቦ በአጎቱ አፄ ሰርጸ ድንግል በመመራት ወታደራዊ ዘመቻ በማካሄድ ሱስንዮስን ከምርኮ አወጣው።
    ከዛም ወዲህ ሱስንዮስን እቴጌ አድማስ ሞገሳ ትጠብቀው ነበር፤ ትምህርቱንም ተቆጣጠረች። ንግስቲቱ የአፄ ሠርፀ ድንግል እናት፣ የሟች አፄ ሚናስ ሚስት እና የሱስንዮስ ደግሞ ቅድመ አክስት ነበሩ። ሱስንዮስም ራሱን ይደግፍ ዘንድ ንግስቲቱ አስቀድሞ የአባቱ የነበረውን በጎጃም ይገኝ የነበረውን መሬት ወይም ጉልት መለሱለት።
    አፄ ሠርፀ ድንግል ከሞተ በኋላ ትንሹ ልጁ ያዕቆብ ዙፋን ላይ ወጣ። የንጉስ አማካሪ የነበረችው ንግስት ማርያም ሰና እና የልጆቿ ባሎች እንዲሁም የደምቢያና የወገራ ገዥ እንደ ነበረው እንደ ራስ ዘ ሥላሴ ያሉ ባላባቶች እንደ ሱስንዮስ ያሉ ልዑላንን ዙፋኑን ሊይዙ ይችላሉ ብለው ፈሩ። ሱስንዮስና መሰሎቹም እንዳይጠቁ ተሰደዱ።
    እየተንከራተተ ያለው ሽፍታ ልዑል ሱስንዮስም ከጥቂት ታማኝ ተከታዮቹ ጋር በጎጃምና በሸዋ ተሸሸገ። ከወለጋም በመነሳት ጦርነት መራ። በአካባቢውም ያለው ቁጥጥር ተጠናክሮ ነበር፤ የዚህም ምክንያቱ እ.ኤ.አ በ1595 በወለጋና መርሀ ቤቴ ይኖሩ የነበሩ ከጥንት የክርስትያን ቤተሰብ ውስጥ የተወለደች ልዕልት በማግባቱ ነበር። ከእነዚህም አካባቢዎች በመነሳት ነበር ዙፋኑን ለመያዝና ተፅዕኖ ለመፍጠር ትግሉን የጀመረው። ሱስንዮስም በአባቱ ክፍለ ሀገር በጎጃም ተቀምጦ ከኦሮሞ የሚሰደደውን ጥቃት ይዋጋ ጀመረ።
    የአንድ ወቅት ተባባሪውና የአጎቱ ልጅ የነበሩት አፄ ዘ ድንግልም በሞቱ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1604 በራስ አትናቴዎስ ቡድን ሱስንዮስ ንጉስ ሆነ፤ ነገር ግን የዘ ሥላሴ ቡድን የአጎቱን ልጅ ያዕቆብን ወደ ዙፋኑ መለሰ።
    ሱስንዮስም ዘ ሥላሴን ካሸነፈ በኋላ ንጉሰ ነገስት ሆነ፤ እ.ኤ.አ በ1607ም በደቡብ ጎጃም በተካሄደው የጎል ጦርነት ያዕቆብን አሸነፉ። ከሽንፈቱ በኋላ ዘ ሥላሴ የሱስንዮስ ተባባሪ ሆነ፤ ነገር ግን በሱስንዮስ ዘመን መጀመርያ ከንጉሱ ጋር አለመግባባት ገጥሞት በጎዛም በሚገኘው አምባ ታሰረ። ከዓመት በኋላ ዘ ሥላሴ ከእስር አምልጦ ሽፍታ ሆኖ መኖር ጀመረ፤ ነገር ግን አንድ ገበሬ ዘ ሥላሴን ገደለውና ጭንቅላቱን ለሱስንዮስ ላከላቸው። በመሪነታቸው የመጀመርያ ዘመኖች ሱስንዮስ በሲዴ መሐመድ የሚመራውን የሀድያ ጦር ገጥሞ በሀድያ ጦርነት ተሸንፏል።
    እ.ኤ.አ በ1608 በደብረ ብዜን አማፂ ተነሳ። በጎል ጦርነት ወቅት የያዕቆብ አስክሬን አልተገኘም። ስለዚህም በህዝቡ ዘንድ ያለፉት ንጉሰ ነገስት ይሙቱ አይሙቱ አከራካሪ ጉዳይ ነበረ፤ ታድያ ይህንን ክፍተት በመጠቀም አማፂው ሞተ ብለው የዋሿችሁ አፄ ያዕቆብ ነኝ ብሎ ተነሳ። ህዝቡም ፊቱን አይተው አንተ አፄ ያዕቆብ አይደለህም እንዳይሉት ፊቱን ይሸፍን ነበረ፤ ፊቱንም የማያሳያቸው በጦርነቱ ወቅት በጥርሶቹና ሙሉ ፊቱ ላይ ከባባድ ቁስል ስለገጠመው ለመሸፈን እንደሆነ ይነግራቸዋል። የትግራይ ገዥ ሰላ ክርስቶስም ስለዚህ አመፅ ሰማ፤ እርሱም በቤቱ ያሉ ወታደሮችን እና ከ60 ዓመታት በፊት የቫስኮ ዳጋማን ልጅ ክሮስቶቮ ዳጋማን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የፖርቹጋል ወታደሮችን የልጅ ልጆች ይዞ ተነሳ። ሰላ ክርስቶስ አማፂዎቹን ሦስት ጊዜ ቢያሸንፋቸውም አፄ ያዕቆብ ነኝ ብሎ ያስመሰለው ሰው ከእያንዳንዱ ጦርነት እያመለጠ በሀማሲን ተራሮች ይደበቅ ነበር።
    በተመሳሳይ ጊዜም አፄ ሱስንዮስ ከዘማች ኦሮሞዎች ጋር በመዋጋት ተጠምደው ነበር። ለረብ ወንዝ ቅርብ የሆነ ቦታ ላይ ከመረዋ ኦሮሞዎች ጋር በተደረገው የመጀመርያ ውግያ የሱስንዮስ ወታደሮች ተሸነፉ። ሱስንዮስም ወታደሮቹ እንዲያገግሙ ካደረጉ በኋላ አጥቂዎቹን በማጥቃት እንዲበተኑ አደረጋቸው። መረዋዎችም ከሌላ የኦሮሞ ጎሳዎች ጋር ሕብረት በመፍጠር ሽንፈቸውን ለመበቀል ወደ በጌ ምድር ገቡ። ንጉሰ ነገስቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ አማቻቸውን ቀኝ አዝማች ጁልየስን እና ክፍለ ክርስቶስን ከሰራዊቱ ጋር እንዲቀላቀሉ በማድረግ በጦርነት ሊያሸንፉ ችለዋል። አፄሱስንዮስም አፄ ያዕቆብ ነኝ ያለውን ሰው መያዝ ስላልቻሉ ተግባሩን ለአገልጋያቸው አምሳለ ክርስቶስ ተዉለት። አምሳለ ክርስቶስም የአማፂውን አመፅ የተቀላቀሉትን ሁለት ወንድማማቾች አሳምኖ አስመሳዩን ያዕቆብ እንዲገድሉት በማድረግ የሟቹን ራስ ለሱስንዮስ ላከለት። ፊቱም ላይ ምንም አይነት ቁስል አልነበረም፤ ጥርሱም ሆነ አገጩም አልተሰበረም ነበር፤ ፊቱን የሸፈነው ሟቹን ያዕቆብ እንዳልሆነ እንዳይነቃበት ነበር።
    ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የሱስንዮስ ዘመን በይበልጥ የሚታወቀው የካቶሊክ ክርስትናን የኢትዮጵያ የግዛት ሐይማኖት በማድረጉ ነው። ንጉሰ ነገስቱ ካቶሊክ ሐይማኖት ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉት በፔድሮ ፓኤዝ ስብከት በመሳባቸው እና በወቅቱ አንድ ከነበሩት ከስፔን እና ፖርቹጋል የሚያገኙትን ወታደራዊ እርዳታ አስበው ነበር። ሱስንዮስ ታጣቂ የአውሮፓ ወታደሮች መጥተውለት ቋሚ አመፆችን እንዲያቆሙለት ይመኝ ነበር። ሁለት ደብዳቤዎችንም ወደ አውሮፓ ልኳል፤ አንዱን ለፖርቹጋል ንጉስ አንዱን ደግሞ ለሮም ጳጳስ ነበረ፤ ሁለቱም ላይ ሐይማኖቱን እንደቀየረ አይናገርም፤ ሁለቱም ግን ወታደሮች ይጠይቁ ነበር።
    እ.ኤ.አ በ1613ም ሱስንዮስ መልዕክተኞችን ወደ ሮምና ማድሪድ ላከ። አላማውም ኦቶማኖች በግዛቱ ሰሜን በኩል ወደብ ለመጠቅም ስላላስቻሉት በአሁኗ ኬንያ ደቡብ በኩል የሚገኘውን የማሊንዲን ወደብ በመጠቀም ከለላቸውን ለመስበር ነበር፤ ነገር ግን ወደ ማሊንዲ መድረስ አልቻሉም።
    አፄ ሱስንዮስ ካቶሊክ መሆናቸውን በግልፅ ያወጁት እ.ኤ.አ በ1622 ነበረ፤ ይህም ከመጀመርያ ሚስታቸው በቀር ከተቀሩት ሚስቶቻቸው እና ቁባቶቻቸው ለያቸው። ነገር ግን ሌሎች ሐይማኖታቸውን ሲያካሂዱ የማይናደደው ፔድሮ ፓኤዝ በሞተ ጊዜ እ.ኤ.አ በ1624 አልፎንሶ ሜንዴስ በምፅዋ በኩል መጥቶ ቦታውን ተካው። እ.ኤ.አ በ1626 ሜንዴስ በግድ ለውጦችን ማካሄድ ጀምረ፤ ሮምም የበላይ እንደሆነች፤ ቅዳሜም ሰንበት አትሁን አለ፤ ብዙ መፆምንም ተቃወመ። ነገር ግን ብዙ ኢትዮጵያውያን ካቶሊክ ሆኑ፤ Richard Pankhurstም እንዳለው በደምቢያና ወገራ ብቻ 100000 ሰዎች ሐይማኖታቸውን ቀይረው ነበር። ከብዙ ችግሮችም በኋላ ሱስንዮስ ህዝቡ ሐይማኖቱን እንዲቀይር ማስገደድ ተዉ። እንዲህም ብለው አዋጅ አወጁ፦ "ካቶሊክ ሐይማኖትን መከተል የሚፈልግ ተፈቅዶለታል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ማንም አይገደድም"። በዚህም ካቶሊክ ኢትዮጵያ የሚለው ነገር ቆመ።
    ሱስንዮስም ካቶሊክ እንደሆኑ ነበር የሞቱት፤ ልጃቸው ፋሲለደስም ዙፋኑን እንደያዘ ወድያውኑ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን የነበራትን የግዛት ሐይማኖትነት ቦታ አስመለሰ።
    ማጣቀሻ(Reference)
    1. en.wikipedia.org/wiki/Susenyos_I
    2. en.wikipedia.org/wiki/Fasilides

Комментарии • 9

  • @tsege9049
    @tsege9049 10 месяцев назад +7

    አሪፍ አሪፍ ታሪክ ነው የምታቀርብልን እናመሰግናለን

  • @HannaMersha-tx1kh
    @HannaMersha-tx1kh 10 месяцев назад +6

    Bertalegne yenea gobz

  • @AsuSa-uu4hm
    @AsuSa-uu4hm 7 месяцев назад +3

    አፀሆች የራሳቹሁ ታሪክ ሲሆን እሰከ ቅድመ አያት ድረሰ ትፀፍላቹሁ የኦሮሞ ታሪክ ሲሆን ሰሙን ብቻ ትፀፍላቹሁ