የኦሮሞ የዘመቻ ታሪክ/The history of Oromo expansion/Babal'ina Oromoo

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 18 окт 2024
  • የኦሮሞ ዘመቻዎች በ16ተኛውና በ17ተኛው ክፍለ ዘመን በኦሮሞ ማኅበረሰብ የተካሄዱ የመስፋፋት ተግባራት ነበሩ። በ16ተኛው ክፍለ ዘመን ከተደረገው ታላቅ መስፋፋት በፊት የኦሮሞ ማኅበረሰብ ይኖር የነበረው በአሁኗ ደቡብ ኢትዮጵያ እና በሰሜን ኬንያ ብቻ ነበረ። በሂደትም በክፍለ ዘመናት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች በተለይም ደግሞ በሙስሊም አዳል ሱልጣኔት እና በክርስትያን አቢሲንያ ግዛት መካከል የነበሩት ጦርነቶች የሁለቱንም ማለትም የአዳልን እና የአቢሲንያን ወታደራዊ ኃይል ስላዳከመ ብዙ የኦሮሞ ጎሳዎች ዕድላቸውን በመጠቀም በአሁኗ ኢትዮጵያ ማዕከላዊና ምስራቃዊ ክፍሎች ወደሚገኙት አካባቢዎች ተስፋፉ።
    በሉባ ቢፎሌ ዘመን የኦሮሞ ስደት የመጀመርያውን ትልቁን ስኬቱን አግኝቷል። ከዛ በፊት የነበሩት እንቅስቃሴዎች በጎረቤታቸው በሚገኙ ክፍለ ሀገራት ላይ የሚደረጉ ትናንሽ ማጥቃቶች ነበሩ፤ ነገር ግን በቢፎሌ አመራር ስር የአቢሲንያን ቁጥጥር ማዳከም የጀመሩ አዳዲስ ጥቃቶች መከናወን ጀመሩ። የደዋሮ ክፍለ ሀገር ሙሉ በሙሉ ወታደራዊ ዝርፍያ ተካሄደባት፤ ከደዋሮ በሰሜን የምትገኘው ፈጠገርም ለመጀመርያ ጊዜ ተጠቃች። ከዚህ በተጨማሪም ባህሬይ በገለጹት መሰረት የተዘረፉት አካባቢዎች ገባሪ ተደረጉ። አፄ ገላውዴዎስም በእነዚህ ጥቃቶች ምክንያት ወደ ደቡብ ዘመተ። በአፄ ገላውዴዎስ ዜና መዋዕል በተፃፈው መሰረት ንጉሰ ነገስቱ የኦሮሞ ወረራ ጥቃቶችን አሸነፈ፤ የማረካቸውን ደግሞ ለአመራሩ እንዲገዙ አደረጋቸው። ይህም ለጥቂት ጊዜ ያህል ጥቃቶች እንዳይደረጉ አግዶ ነበረ። የመጀመርያዎቹ ጥቃቶች ታላላቅ ስለነበሩ፤ ለአቢሲንያው ሥርወ መንግስት አውዳሚ ነበሩ። ገላውዴዎስ አጸፋዎችን ቢመልስም አደጋ ውስጥ ነበረ፤ በ1550ዎቹ መጀመርያም ተፈናቃዮቹን ከዝዋይ ሐይቅ በሰሜን በሚገኘው በወጅ ከተማ ማስፈር ግድ ሆነበት።
    የኦሮሞ መስፋፋቶች ግን በአቢሲንያ የተገደቡ ብቻ አልነበሩም፤ ወደ አዳልም የሚሄዱ ነበሩ እንጂ። ለምሳሌ ያህል የኦሮሞ ሠራዊት የሀረር አሚር የነበረው የኑር ኢብን ሙጃሂድ ሠራዊትን በሀዛሎ ጦርነት ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ አሸንፎታል።
    በ1710 አካባቢ የሜጫ ኦሮሞ በጊቤ አካባቢ ወደምትገኘው ሺሻፎትቺ በተባለ ንጉስ ወደምትመራው ወደ ጎንጋዋ ግዛት ኢናርያ ደረሰ። የኢናርያ ንጉስም ግዛቶችን በመጠቅለል ጉጉት የተጠመዱትን የሜጫ ኦሮሞዎችን ወደ አመራሩ በማስገባት ነገሩን ለመወጣት ሞከረ። ነገር ግን ይህ ተግባሩ ለጥፋቱ መንስኤ ሆነው። በሥልጣን ቦታዎችም ለኦሮሞ በማድላቱ ምክንያት ንጉሱ ሺሻፎትቺ የራሱ ህዝብ ጠላው። በሥልጣን ቦታ የሚገኙት ኦሮሞዎችም በህዝቡ ዘንድ ያለውን ንዴት ለራሳቸው ጥቅም በማዋል ንጉሱን ከሥልጣኑ አውርደው ግዛቱን በእጃቸው ሥር ከተቱ።
    በተጨማሪም በ18ተኛው ክፍለ ዘመን የሜጫ ኦሮሞዎች የጎጀብ ወንዝን በመሻገር በከፋ ግዛት ላይ ወረራ መሩ። በዛም አዳጋች የሆኑ ተፈጥሮአዊ ኬላዎች ገጠሙዋቸው፤ ወደ ከፋም እንዳይገቡ ከለከላቸው። በተራራማው ጫካም የከፋ ሰዎች ራሳቸውን ለመከላከል ፈጣን የሆነ የፈረሰኛ ጥቃት በሜጫ ኦሮሞዎች ላይ አደረጉባቸው፤ ከዛም ጫካ ውስጥ ከፈረሰኞቹ አምልጦ መሸሽ የማይቻል ጉዳይ ነበረ፤ ዘመቻቸውም በከፊቾ ህዝብ ታገደ። ነገር ግን የሜጫ ኦሮሞዎች ከጎጀብ ወንዝ በሰሜን የሚገኙትን አካባቢዎች የጅማ ከተማን ጨምሮ ተቆጣጠሩ።
    የኦሮሞ መስፋፋት በአሁኗ አፍሪካ ቀንድ ትልቅ ተፅዕኖ አለው። ኦሮሞም በአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆነ። በዚህም የክርስትያን አቢሲንያን በማዳከም የአቢሲንያን የሥልጣን ቦታዎችን በመያዝ ወደ ዘመነ መሳፍንት ከተታት። በዛም በአብዛኛዎቹ የአቢሲንያ ክፍለ ሀገራት ላይ ቀጥተኛ ሥልጣን በማግኘት ንጉሰ ነገስታቱን አቀያየሩ፤ በዘመኑም ንጉሰ ነገስታቱ እንደ አሻንጉሊት የሚቀመጡ ነበሩ።
    ማጣቀሻ(Reference)
    en.m.wikipedia...

Комментарии • 23

  • @nugusaethiopia
    @nugusaethiopia Месяц назад +1

    ይሄ የአማራ ታሪክ ነው የኦሮሞ ታሪክ እንደዛ አይነት አይደለም

    • @sabelfayeza9921
      @sabelfayeza9921 Месяц назад +1

      አይ እኔ ብቻ ማለት ።ልማዳችው ነው😅😅😅😅 የሠው ታሪክ መስረቅ መቼ በመቶኛ አመትም አትነቁው😅😅😅

  • @habeshamereja9267
    @habeshamereja9267 5 месяцев назад +1

    emegerm ecko nw bzu sltane teftwal malet nw bezi werera bcha

  • @meharimena8093
    @meharimena8093 6 месяцев назад +4

    They are not indigenous people .

    • @tarikhistory
      @tarikhistory  5 месяцев назад

      They are Indigenous people

    • @qwertyuiop23916
      @qwertyuiop23916 3 месяца назад +1

      ​@@tarikhistorythey indigenouse to kenya

    • @qwertyuiop23916
      @qwertyuiop23916 3 месяца назад

      Only borena is oromo

    • @Rufo243
      @Rufo243 3 месяца назад

      Oromo peoples were live in Northern. In today, around Egypt, Sudan, and Aksum. Thoughts a time migrate to the southern and western parts of Africa. In the 16th century, they stated expansion to northern parts of to day Ethiopia. So, Oromo is one indigenous Kush nation.

    • @الحمدالله-ش6غ3ض
      @الحمدالله-ش6غ3ض 2 месяца назад +1

      ​@@Rufo243😂😂😂😂😂😂ኦሮሞ ኬኒያዊ ነው🎉

  • @brehanbekele1345
    @brehanbekele1345 25 дней назад +1

    የኦሮሞ የወረራ ታሪክ ተብሎ ይስተካከል

    • @be-liever
      @be-liever 6 дней назад

      ጀግና ሃያል ህዝብ ስለሆነ ነዋ አይሎ ወሮ የያዘው።

  • @MetiTole
    @MetiTole 6 месяцев назад

    ይገርማል

  • @Muzeyen-bi5tp
    @Muzeyen-bi5tp 4 месяца назад +2

    Some Ethiopians who consider oromos inferior to them based on false debtera history should laearn from this.oromos never defeated when they were united even susinoyos whom debtera claims is amhara was crowened with help of oromo soldiers.fasil was susinoyos son he himself was protected by oromo soldiers
    .

  • @girumbelay5997
    @girumbelay5997 2 месяца назад

    😂😂

  • @gutemaguutuu5117
    @gutemaguutuu5117 2 месяца назад

    Gosh 😮😂🎉😅

  • @sabelfayeza9921
    @sabelfayeza9921 Месяц назад

    ታሪክ ይፋቅም የኦሮሞው ህዝብ ለዚቻ አገል አጥቱን ነብሱን።።ሠቶው አኑሮታል በዛበጨለማ ዘመን ።። የነቃ ህዝብ ነው

  • @الحمدالله-ش6غ3ض
    @الحمدالله-ش6غ3ض 2 месяца назад

    ትክክል ነው ኦሮሞ ከኬኒያ እንደመጡ የውጭ ዜጎች ታሪኩን ፅፈውታል እነዚህ አራጆች የሸዋን ህዝብ ወረሩት😅

    • @be-liever
      @be-liever 6 дней назад +1

      ጀግና ሃያል ስለሆኑ ነው አይለው የወረሩት😂😂😂

  • @DawitKibbi
    @DawitKibbi 2 месяца назад

    History endagabak bicha atawura

  • @Ethio-One1
    @Ethio-One1 2 месяца назад

    Why are you living lies 🌎 Oromo one 🕐