Ahuen yemnorew ferncay new getane yagegnute jibutiy yemibale meder beda weste new yetetmekute 2002 new bezih hulu amete behyewta bezu melkam neger bezu asazagne tariqoch alfewale geta gene beretu melkam new meskrenta betam bezu new ahuenem bezlotesh asbigne eheta tebarekiy
it is the very valuable message for the entire evangelical denominations. Every church leaders should be conscious to safeguard its congregation from loud sound risks. God bless you Pastor and Tg
Very very important and timely discussion. Very common and troubling issue in churches and mosques in Ethiopia. It negatively affects both the neighborhood and the worshippers themselves. I was in Addis Ababa last year for vacation and I was sleeping in a hotel near a mosque. The sound that was coming out of the near by mosque was very scary and devastating. The building was shaking and the dogs were barking everywhere. The same problem is observed in Orthodox and Protestant churches. Thank God there is sound restriction in western countries and the sound that comes out of religious centers does not usually affect the neighbors. But Protestant church worshippers in particular are suffering everywhere - be it Ethiopia or America. There are some believers who stopped going to church because of the issue. Everyone has a right to worship whatever he or she likes but it should not be in a wrong and messy way. The sound pollution problem requires big attention. May God open our eyes!
It is true fact continual exposure to noise can cause stress, anxiety, depression, high blood pressure, heart disease, and many other health problems. Some people are at higher risk for hearing loss, including those who: are exposed to loud sounds at home and in the community.God Bless You!
haile.emiru@gmail.com
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😊❤❤❤😊❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😊❤❤❤😊❤😊❤❤❤❤😊❤❤❤❤😊❤😊❤😊❤
❤❤😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
❤😊😊😊😊😊😊❤😊😊😊😊😊😊❤😊😊😊😊😊😊😊
😊😊😊😊😊
Ahuen yemnorew ferncay new getane yagegnute jibutiy yemibale meder beda weste new yetetmekute 2002 new bezih hulu amete behyewta bezu melkam neger bezu asazagne tariqoch alfewale geta gene beretu melkam new meskrenta betam bezu new ahuenem bezlotesh asbigne eheta tebarekiy
ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ስውር በሆነ የጠላት ክፉ ስራ በመግለጥ ብዙዎች እንዲጠነቀቁ በማድረገዎት አመሰግናለሁ ። ትግስት አዘጋጅዋን ጌታ ይባርክሽ።
ቲጂ ደፋር እውነተኛ ንግግር አዋቂ እኛ መናገር ያቃተንን በውስጣችን ያለውን ሀሳብ ባማረ ቋንቋ የምታወጪልን የተባረክሽ እህት እግዚአብሔር የበለጠ አብዝቶ ይባርክሽ
ተባረኩ ትልቅ ትምህርት:: ሁሌ በቤ/ክ ውስጥ ያለ ጩኽት ይጨንቀኝ ነበር:: ፓስተሩ ይጮሃል ሙዚቃው ይጮሃል: ህዝቡ በልሳን እየጸለየ ይጮሃል::
እግዚያብሄር እባክህ አይኖቻችንን ክፍትልን:: አሜን
የጩኸት ነገር በጣም ከብዶናል፣ ከምንም በላይ የልጆችን ጤንነት ያውካል።
በጣም የተማርኩበት ፕሮግራም ነው ይህ ጠቃሚ ሀሳቦች ለሁሉም እንዲዳረስ ምኞቴ ነው ለመጋቢ ጌታ ጸጋውን ያብዛለት
በአረብ ሀገር በጣም የሰላቸኝ የአረቦች ጩሃት ነው ከልክ በላይ ይጮሃሉ እኔ ጩሃት አልወድም ይጫንቃኛል በጣም ስጮሁ
ጌታ ይባርኮት
እጅግ ልዩ እውቀት ነው ያገኘሁት ጌታ ኢየሱስ ይባርክዎት የኔ ወንድም።
አምልኮን በተመለከተ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤ/ያን ያላትን አቁዋም አከብራለዉ። በተጨማሪ በእግዚያብሔር ህግ ላይ ያላት አስተምሮት እና ስነስርአት ክብር ይገባዋል።
በትክክል ፓስተር ጌታ ይባርክህ ለሁሉም አብያተ ክርስትያን ሁሉ አስፈላጊ ነው በጣም ግሩም የሆነ ትምህርቶች አግተናል ትግዬ ተባረኪ
እግዚአብሔር ያከበሩት ልጆቹን እንደዚህ በእድሜያቸዉ ያለመልማቸዋል::ይገርማል እኔ በህይወቴ ቸርች ዉስጥ መጨረሻ ወንበር ላይ ሆኜ እንጂ የማመልከዉም ሆነ ቃሉንም የማዳምጥበት ምክንያት ቸርች ዉስጥ ከፊት ተቀምጬ የስፒከሩ ጩኸት እራሴን ልስት ስል ቶሎ ብዬ በወጣሁበት ቀን ምክንያት ነዉ::
እግዚአብሔር ይባርካችሁ! የተማረርኩበት ነገር ስለ ሆነ እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ፣ ለጥቂት መጋቢዎቼም share ማድረግ አይቀርም።
እግዚአብሔር ይባርካችሁ! አሜሪካ ስኖር ፫፫ አመት ነው እንደዚህ አይነት ትምህርት ሰምቼ አላውቅም። ቤተ ክርስትያን ሔጄ በድምጽ በጣም ታውኬ አውቄአለሁ። ካልተሳሳትኩ ጥዬ የወጣሁበት ቀን አለ። ጩኸት በመንፈስ ቅዱስ ተተክቷል። የአሁን ወጣት ዘማሪዋችም መሐል ላይ ሲጮሁ በእልልታ ፈንታ እጅግ በጣም ይረብሻል! ጌታ እየሱስ በራእይ ፪ & ፫ ደጋግሞ እንደተናገርው "መንፈስ ቅዱስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ" !!!
እግዚአብሄር እኮ መልካም ነው በዘመናት መካከል እያስመለጠ እያስዋበ ክብር ለእግዚአብሄር በፀሎት ቤት አስቸጋሪና ሰው ወደጌታ ዞር እንዳይል በጣም መወገድ ያለበት ጩኸት ፣በመዝሙር የሚደነሰው ብሄር ብሄረሰብ ጭፈራ ፣ከለር ያለው ሃይሉ ከፍተኛ ጨረር ያለው መብራት ቸርቹ ናይት ክለብ እስከሚመስል እንዲህ መቀየሩ ያሳዝናል ብቻ በስመ ክርስትና የሚሰራው ስራ ግን አይደለም መንግስተ ሰማይ ከደመናውም ላይደረስ ይችላል ጌታን መቀበል ከቅድስና ጋር ሲሆን መልካም ይሆናል ብቻ ጌታ የራሱን ሰው ይሰበስባል
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ይህን ምስክርነት በመስማቴ በጣም ደስ ብሎኛል ሰው ሁሉ ሊሰማው ይገባል ክብሩ ለጌታ ይሁን።
How a person be humble like this? I really saw God's spirit in him. WOW....Stay Blessed.
ቀሺ ሃይሌ ጎይታ ይባርኽኩም ሎሚ መዓልቲ ናይ ዓመታት ሕቶይ ተመሊሹለይ።ብጣዕሚ ጽቡቕ ትምህርቲ።
በጣም ጠቃሚ ትምህርት ጌታ የሱስ ክርስቶስ በሁሉ ሁሉ ግዜ ጸጋው ያብዛላቹ. ከ 20 ዓመት በፊት የቤ/ክ'ኑ ማይ ክሮፎን እንዳንጠቀምበት እደብቀው ነበር. ከመጮህ በስተቀር ጥቅም ስላልነበሮው. ህንጻው ያከራዩንም ይከሱን ነበሩ. በዙሪያው የሚኖሩ ፋሚሊ ይረበሹ ስለ ነበረ. ፓስተር ሃይሌ'ና እህታችን ትእግስት እግዚአብሄር ይባርካቹ.
በጣም በጣም ተጠቅሜአለሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ልብ ማለት ያስፈልጋል። የጩኽቱ ጋጋታ ጤናን ነው ይሚያሳጣ ሌላ ምንም ፋይዳ የለውም። አንዲት የእግዚአብሔር ቃል ግን ታረሰርሳለች። ሁለት መጽሐፍትን ማግኘት እሞክራለሁ።አመስግናለሁ።
Uffff... ከወንድሞች ጋር በሰላም ማምለከ አልቻልንም እኮ ! "ግልባጭ ለኢትዮጲያ ቸርቾች " አድርሱልን .
ኡፍ ወሳኝ ነገር አነሳችሁ,,,,,,,,,,,,, የጆሯችን ጤንነት ችግር ውስጥ የገባበት ጉዳይ
እኔ በዚህ የተነሳ ቸርች ሁሉ ለመሄድ ፍላጎት አጣሁ ለምን ጩኸት ጫጫታ ሁካታ ይረብሸኛል እቤት እንኳ ቲቪ ጮክ ካለ ይጨንቀኛል። ድምፅ እና መጥፎ ሽታ አንድ ናቸው ለኔ👌 ተባረኩ ስላነሳችሁት🙌
እሚገርም ነው አንዳንዴ ኮ የማያምኑ ሰወችን እንዲመጡ ለመጋበዝ እንኳን ያሳፍራል በተረጋጋ መንፈስ እግዚአብሔር ን አምልኮ ቃሉን ሰምቶ መሄድ መታደል ነበረ በዕውነት እግዚአብሔር ያድሰን እውነት ያለባት እውነት የሚሰበክባት ቤቴ ክርስቲያን
ከጩኸት እና ከብዙ ዲምላይት የተነሳ ብዙ የሌላ እምነት ተከታዮች ጭፈራ ቤት ነው ይላሉ 😢😢😢 እግዚአብሔር ይባርካችሁ ወድ አባታችን እና ቲጅየ ❤❤❤
ትክክል፣ ሌላ ሃይማኖት ውስጥ ገብተናል። አቤቱ መልሰን❤❤❤
እባክሽ ለአጥቢያዎች ብታደርሺልን ብዙ ህዝብ እየተጎዳ ነው ።
ተባረክ ወንድማችን እኔ ከቅርብ ጊዜ ወድህ ከቸርች ስወጣ ደክሞኝ ነው የሚወጣው ስለዚህ ከሰማሁት ምንም አላስተዊስም አንዳንድ ሰባኪዎች ከመጮኻቸው የተነሳ ልብሳቸውን አውልቃሉ በለብ ይጠመቃሉ የእነሱ ከፍተኛ ድምፅ መጠቀም ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን ጩኽ እያሉ ያስገድዱናል ።
እስራኤላውያን የኢያሪኮን ግንብ ሊያፈርሱ ሰባቴ ዞረው ነው ጩሁ የተባሉት። ሰባኪው በጩኸቱ እኛን አፈራረሰን እኮ።
ድንቅ ትምህርት መጋቢ ሃይሌሉዑል ተፈራ ዘመኖት ይባረክ❤🙏
Wow እጅግ በጣም ጠቃሚ ነገር ነው ያጋሩን። ብዙ ተምሬበታለሁ። በዚህ አቅጣጫ ከእንተርቪ በላይ ትውልድን የማስመለጥ ስራ መሬት ላይ ወርዶ ቢተገበር መልካም ነው። ስላጋሩን እውቀት እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርኮት።
ቲጂዬ በብዙ የምንማርበትን እና የምንጠቀምበትን፣ ቃለ መጠይቆች፣ አስተምሮቶች፣ ምስክርነቶች ስለምታቀርቢ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ። ስለ አንች ጌታን በጣም አመሰግናለሁ። እንኳን የክብሩ መገለጫ ሆንሽ ! እወድሻለሁ ተባረኪ❤
ይህን በመስማቴ ተገርሜአለሁ
ይህን pastor በጣም :አደንቀዋለሁ !!!!!! የድምፅ :ጉዳይ :ሁሌም :እያሸገሸገ ን :ያለው ነገር ነው ።
ቲጂ በእውነት ተባረኪ ብዙ እንግዳ የምትጋብዥው እየተባረክን ነው ጌታ ቢረዳሽ ደግሞ ጥበበ ወርቅዬን ብታቀርቢው ምስክርነት የሚሠራ ብዙ ነገር ስላለ ተባረኪልን ፀጋው ይብዛልሽ🙏
ቲጅዬ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር እየሰራሽ ነው እግዚአብሔር አምላክ ዘመንሽን አገልግሎትሽን ትውልድሽን ይባርክ
ቲጅ እምታቀርቢያቸው አሰተማሪ ናቸው እናመሰግናለን ተባረኩ
it is the very valuable message for the entire evangelical denominations. Every church leaders should be conscious to safeguard its congregation from loud sound risks. God bless you Pastor and Tg
ትጊ ተባረኪ እና ቄስ ትግስቱ ሞገስ የሃያት ቃለ ሂወት ቸርች እባክሽ ኢንተርፌ አድሪጊልን በጣም የተባረኩና የምባርኩ ቄስ ናቸው፡፡
በጬኸት Hypnotize ማድረግ በአሁን ሰዓት በተለይ አብዛኛውን የግለሰብ ትንንሽ ቸርቾች የሚጠቀሙት ይሄን መንገድ ነው ፈጣሪ ይባርኮትአባቴ የመጀመሪያ አውነቱን የተናገሩ ሰው ኖት
የድምጽ ነገር በጣም እቸገርበት ነበር ? የኔ መንፈሳዊነት ማነስ ይመስለኝ ነበር ? ዛሬ ጌታ አርነት አውጥቶኛል 🙏🙏🙏 ቲጂ ጌታ በነገር ሁሉ ባርኮሻል 🙏🙏🙏
ስሚ አጥቼ ነበር ብዙ ጊዜ ስለሙዚቃ መሳሪይ ተናግሬ
መንፈሳዊነት የጎደለኝ ይመስላቸዋል
እባካችሁ በተልይ ለህጻናት እናስብ
ጌታ ይባርክዎት ወንድሜ፡፡ በቤተክርስትያን ያለው የጩኸት ነገር መስመር በሳተ መንገድ ላይ መሆኑን ሁሉም እንዲያስብበት በማስተማርዎ ደስ ብሎኛል፡፡ እኔ በግሌም ብዙ የምቸገርበት ጉዳይም ስለሆነ መፍትሔ የሚሆን ነገር በመስማቴ ደስ ብሎኛል፡፡
ኢያሪኮ የፈረሰዉ በጭሆት ነው ይላል ይሄ እንዴኤት ነው እኔ በእግዚያብሄ ማዳን በጣም ደስ ስለሚለኝ ሳመልክ በጣም ነው እልል የምለዉ ወድጄ ሳይሆን ፍቅሩ ከአይምሮዬ በላይ ስለሚሆንብኝ የማመሰግንበት ቃል ስለማጣ አንዳንዴ መቆጣጠር ባቃተኝ ሀይል በጣም ጮክ ብዬ ነው እልል የምለዉ ጉሮሮዬ እስከሚሰማኝ እንባዬ ከአይኔ ይፈሳል ግን ወድጄ አይደለም የአባቴ ፍቅር ከባድ ሆኖብኝ ነው በምድርም በሰማይም አባቴ አቅሜ ጉልበቴ እረዳቴ ጠባቂዬ መከታዬ ጋሻዬ አቤት ቃላት አጣሁለት እግዚያብሄር አምላክ እና አባቴ አንተ ጠብቀኝ ጌታ ያዉቃል ላለፈ ስለነገዉም እሱ ያዉቃል
ኧረ የትእንድረስ? ጩኸት : አሜን በሉ : ኧረ እዚህ ቤት ሰው የለም እስቲ አንድ ሰው አሜን ይበል መባል ደከመን
የሚገርም ውይይት ነው! እጅግ ጠቃሚ!!!
ጌታ ይባርካችሁ
ተረጋግቶ ማምለክ እንዳለመፈታት እየታየ
በመካከላችን ላሉ ህፃናት እና አዛውንት እንኳን አይገደንም
ስሜትን የሚኮረኩር እና ጆሮን የሚያደንቂር ካልሆነ ይተፈታ አምልኮ የማይመስላቸው አሉ
አንዳንዶች የዝማሬ ጊዜ ካለፈ የሚመጡ ሰዋች አምልኮ ጠልተው ሳይሆን ድምፅ እየረበሻቸው ይመስለኛል
ትግስትየ ቆንጆ በጣም ደስ ትያለሽ እርጋታሽ ኣጠያየቅሽ የማዳመጥ ትዕግስትሽ ሁሉ ልዩ ነው ለኣድማጭ ተመልካች በሚገባ እና በሚረዳ መልኩ ስለሆነ የምታቀርቢው እጅግ ተወዳጅ ኣድርጎታል ግልታ ጸጋውን ያብዛልሽ ይጨምርልሽ ትግስትየ ሽኮር
Sis Tigist ከአንቺ ፕሮግራም ምን ያልተማርነውና እውቀት ያላገኛውን ነገር አለ ጌታ ይባርክሽ። የኢትዮጵያን ቸርች ጌታ ይታደጋት ከፍተና ድምፅ አሁን አሁንማ ካልተጮህ ስው የማይስማበት ዘመን ላይ ስላለን normal እስከ የሚመስል ደርስናል ይህንን መልእክት ሁሉ ቸርች ቢስማው እንዴት መታደል በሆነ ጌታ ይርዳን ጌታ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርኮት ፓስተር ጥሩ ማስተዋል ነው።
Amen my diligent and committed sister 🙏
ተባረክ ፓስተር እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነና በብዙ አብያተ ክርስቲያናት ላይ ተቃራኒ ተፅእኖ የፈጠረና ብዙዎችን ካስቀረዉ ነገር
አንዱ ምክንያት ነዉ።
ይሄን የሚሰሙ የቤተክርስትና መሪዎች ሰምተዉ በቶሎ ያስተካክላሉ ብየ አምናለሁ።
ተባረኩ!
ተባረኪ ቲጂ , የምንታነፅበትን እንግዳ ስለምታቀርቢ .. ጌታ ይባርክሽ !
በእውነት ጌታ ይባርኮት ፓስተር እደእርሶ ያሉ ብዙ አባቶችን ጌታ ይጠብቅልን በጣም እንወዶታለን❤❤
Thank you pastor, and Tigist. God bless you.
የሚገርም ትምህርት ነው ያገኘነው እግዚአብሔር ይባርካችሁ! ይገርምሻል የሆነ ጊዜ ላይ አንዲት ልቧን የሚያማት እህት የሚኖሩበት ጊቢ የብየዳ ስራ ይሰራ ነበርና ልቤን እያሳመመኝ ያለው ይሄ ከጠዋት እስከ ማታ የሚጮህ የብየዳ ድምጽ ነው ትለኝ ነበር እና አሁን ነው የገባኝ ምን ለማለት እንደፈለገች።
በሕግ አምላክ አጠገብህ ያለውን ሰው እንዲህ በለው የሚባለውን ፈሊጥ ከቤ/ክ አስወግዱልን ።
እንደኔ ዝም ማለት
እኔ ቀናም ብዬ አላይ እነሱም አይደግሙም ..ክፉ ልማድ
እግዚአብሄር ይበርክሽ የኔ እህት❤❤
ይህ ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰና ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። እባካችሁ የቤተ/ክ መሪዎችና የህክምና ሙያተኞች ለህዝባችን ግንዛቤ መስጠት አለባችሁ!!!
Thank you very much. This is very important agenda.
ፖስተር ጌታ ይባርክህ እንደውስ የኢያሪኮ ግንብ በጩኸት መፍረሱ የጩኸትን ሃይለኛ አቅምና የጉዳት መጠን ያሳያል ስለዚህ ተደጋጋሚ የድምፅ ብክለት በሰፊው ቢነገር መልካም ነውና እባክሽን ትግስት በሌላም ፕሮግራም ብታመጪልን ተባረኪ
ኢያረኮማ እግዚአብሔር ስለተናገራቸው ጮኸው ነው የፈረሰው።። አሁን እኮ እኛኑ አፈራረሱን።
እግዚአብሔርን ስለ አባቶች አመሰግናለሁ 🙏🙏🙏🙏
God bless you pastor Haile.
በጣም ጠቃሚ አስተማሪ ፕሮግራም ነው:: ጌታ ይባርካችሁ !! የድምፁ ጉዳይ አሳሳቢ ነው::
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ትልቅ መልእክት ነው። ጌታ ይርዳን በእውነት
Very very important and timely discussion. Very common and troubling issue in churches and mosques in Ethiopia. It negatively affects both the neighborhood and the worshippers themselves. I was in Addis Ababa last year for vacation and I was sleeping in a hotel near a mosque. The sound that was coming out of the near by mosque was very scary and devastating. The building was shaking and the dogs were barking everywhere. The same problem is observed in Orthodox and Protestant churches. Thank God there is sound restriction in western countries and the sound that comes out of religious centers does not usually affect the neighbors. But Protestant church worshippers in particular are suffering everywhere - be it Ethiopia or America. There are some believers who stopped going to church because of the issue. Everyone has a right to worship whatever he or she likes but it should not be in a wrong and messy way. The sound pollution problem requires big attention. May God open our eyes!
May the Lord bless you and may the Lord bless everything you touch Tigiye 💜
Very interesting and teachable lesson.
Waw yemegerem meleket yenem tiyake meles agechalu tebarekuu be bezuuu bezu churchercho iko xouhet yebezal enem terebeshe akaleu tibebina masetwalu geta yabezalen!😥🤲🙏❤️❤️❤️
የሚገርማቹህ ነገር ብዙ ሰው የሚጮህ ሰባኪ ይወዳሉ🤣🤣🤣ድምፁ ከአቅም በላይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ይመስላቸዋል🤣🤣 ድምፅ ከፍ አርጎ መናገርና ጩሀት የተለያዩ ናቸው። ቲጂዬ ብሩክ ነሽ። በብዙ ጠቅመሽናል። ያንቺ ፕሮግራም የማያይ ሰው ከስሯል።
Kehulu belai hixanoch eyedenegetu gena jorachew eyetegodu new tebareku tigi 🎉
እግዚአብሔር ይባርካችሁ ።
Such a blessing discussion and be blessed Pastor and Tigest
What a wonderful and important message and interview time
God bless you.
አባታችን ተባረኩ
በእውነት በጌታ ይባርክሽ
May God bless you pastor
blessing ❤ both
እኔ በግሌ በጣም የተቸገርኩበት ጉዳይ ነዉ ቤተክርሥቲያን መሄድ እሥከመቸገርና ጆሮዬን እሥከመታመም ደርሻለሁ ተባረኩ ወሳኝ እርእሥ ነው
መስማትና ድምፅ የመጽሐፉ ርዕስ
God bless you Pastor for the wise and godly advice to the current body of Christ. sister Tiges tGod bless you
የፅሞና ቤተክርስቲያን እናፍቃለሁ
Pastor Eyasu Tesfaye
Kes Tigestu Moges
nice advise,God bless you.
በጣም በመንፈሰ ቅዱሰ የተረጋጋሽ እህቴ ተባረኬ ቴጄ
አንቺ የተባረክሽ እህቴ ! አመሰግናለሁ🙏
እዉነት ነዉ ቤተክርሰቴን መሄድ እሰክጠላ ጆሮዬን እየሱሰ እላለሁ ዋዉ ቤነገራቸዉም አይሰሙም በጣም ያሳዝናል።
ጌታ እየሱስ ክርስቶስ አብዝቶ ይባርኮት ለጥያቄዬ መልስ አግኝቻለሁ!!!
በጣም ይገርማል እኔ ማዳም ምን ሁኖ ነው እንዲህ በቁጣ የሚጮህ ስትል በመንፈስ ቅዱስ እንዳልሆነች አስብ ነው ጌታ ሆይ ምህረት አድእግልኝ
Thank you for this very important issue!
አረ ጩኧት ያለው ፉጨት ያለው እየተባለ ነው የሚጨፈረው ከኢትዮጵያ አገልጋዮች ሲመጡ እባካችሁ ድምፅ ቀንሱልን ስትሰብኩ ተብለው ቀድመው ተነግረው ነው ። ኢትዮጵያ ውስጥ በራሱ ታክሲ ውስጥ መንገድ ላይ የት ቦታ ነው ድምፅ የሌለው እግዚአብሔር ያስበን🙏
Thanks a lot!!
It is true fact continual exposure to noise can cause stress, anxiety, depression, high blood pressure, heart disease, and many other health problems. Some people are at higher risk for hearing loss, including those who: are exposed to loud sounds at home and in the community.God Bless You!
ልጆቻችንን እንዴት ማናገር እንዳለብን ጭምር ተምሬበታለሁ አመሠግናለሁ❤
yemgerm tark geta ybarkachu
Thanks very much! betam temirebetalewu🥰🥰🥰
WOW!!.🙄
May God Bless You!
ፓስተር ኃይለልዑልን ከኢትዮጵያ ከመውጣቱ በፊት በባቲስት ቤተክርስቲያን ወስጥ በመጋቢነት ሲያገግል ደርሼበታለሁ ተወዳጅ እና መልካም ስም የነበረው አገልጋይ ነበር።ከረጅም አመት በኋላ በኒቆዲሞስ ሾው ላይ በማየቴ በጣም ደስ ብሎኛል።
በዚህ ቃለመጠይቅ ላይ ከጩኸት እና ድምጽ ጋር ያስተላለፈው ሳይንሳዊ ትንታኔ ጠቃሚ ቢሆንም ከአምልኮ ጋር አገናኝቶ የሠጠው ድምዳሜ ግን የግል ዕይታ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብሎ ለመቀበል ትንሽ አስቸጋሪ ይመስለኛል ምንም እንኳን መጽሐፉን አግኝቶ ማንበብ ቢጠይቅም ምክንያቱም ስለ ጩኸት መጽሐፍ ቀዱስ በተለያየ ሥፍራ ጌታችን ኢየሱስን ጨምሮ በእግዚአብሔር ማኀበር ውስጥ ይደረግ የነበረ ስለሆነ ለምሳሌ፦
1ኛ “ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱንም ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ይገባባታል።”
- ኢያሱ 6፥5
ታላቅ ጩኸት ይጩኹ
“ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ
በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ወደ ፊቱ ወደ ከተማይቱ ወጣ፥ ከተማይቱንም ወሰዱ።”
- ኢያሱ 6፥20
ሕዝቡም ጮኹ ...በታላቅ ጩኸትም ጮኹ ይለናል
2ኛ “ደግሞ፦ ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እያሉ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በእርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት ስለ ተመሠረተ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ።”
- ዕዝራ 3፥11
በታላቅ ድምጽ እልል አሉ የሚለውን በእንግሊዝኛው ጮኹ ነው የሚለው
“And they sang together by course in praising and giving thanks unto the LORD; because he is good, for his mercy endureth for ever toward Israel. And all the people shouted with a great shout, when they praised the LORD, because the foundation of the house of the LORD was laid.”
- Ezra 3:11 (KJV)
Shouted with a great shout!!
3ኛ ኢሳይያስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።
³ አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር።
⁴ የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።
4ኛ “ጩኽ የሚል ሰው ቃል፤ ምን ብዬ ልጩኽ? አልሁ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።”
- ኢሳይያስ 40፥6
ስለ መጥምቁ ዮሐንስ የተነገረ ትንቢት ነው
“እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥”
- ማርቆስ 1፥2-3
5ኛ ዮሐንስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁷ ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።
³⁸ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ።
ጌታቸን ኢየሱስ...ጮኸ ብሎ ይነግረናል
“እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ።”
- ራእይ 1፥15
ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ
6ኛ ራዕይ 1:10፣5:2፣5:12፣6:10፣7:2፣7:10፣8:13፣10:2፣11:12፣12:10፣14:7፣14:9፣14:15፣14:18፣16:1፣18:2፣19:1-2 እና 21:3
ታላቅ ድምፅ፣ብርቱ ድምፅ ይለናል
ከእግዚአብሔር የሆነ ጩኸት ያለና አስፈላጊ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳችን ቢገልጽልንም ጩኸት ሁሉ ደግሞ ከጌታ ነው ማለት ግን እንዳልሆነም ይነግረናል ምክንያቱም እግዚአብሔር ያልነበረባቸው ጬኸቶች ከሰው እና ከልላ አምልኮ ጋር የተገናኙ ደግሞ ተጽፈው እናገኛቸዋለን ለምሳሌ፦
1ኛ ዘጸአት 32
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ኢያሱም እልል ሲሉ የሕዝቡን ድምፅ ሰምቶ ሙሴን፦ የሰልፍ ድምፅ በሰፈሩ ውስጥ አለ አለው።
¹⁸ እርሱም፦ ይህ የድል ነሺዎች ወይም የድል ተነሺዎች ድምፅ አይደለም፥ ነገር ግን የዘፈን ድምፅ እሰማለሁ አለው።
2ኛ “የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ እስራኤል ሁሉ ታላቅ እልልታ አደረጉ፥ ምድሪቱም አስተጋባች።”
- 1ኛ ሳሙኤል 4፥5
“በታላቅም ቃል ይጮኹ፥ እንደ ልማዳቸውም ደማቸው እስኪፈስስ ድረስ ገላቸውን በካራና በቀጭኔ ይብዋጭሩ ነበር።”
- 1ኛ ነገሥት 18፥28
ከዚህ አኳያ ፓስተር ኃይለ ልዑል ያቀረበው ትንታኔ ሙሉነት የጎደለው እና የእግዚአብሔር የሆነውን ካልሆነው በመለየት አቅጣጫ ማብራሪያ የሚያስፈልገው እንደሆነ አስባለሁ።
እህታችን ትዕግስትም በዚህ አቅጣጫ የመወያያ ሃሳቦችን ታቀርቢያለሽ ብዬ ብዙ ተስፋ አድርጌ ነበር ለሌላ ጊዜ የምንወዳቸው እና የምናከብራቸው ሰዎችም እንኳን ቢሆን ውይይታች አንድ ጽንፍ ያልያዘና ሰዎች ሊጠይቋቸው ይችላሉ ብለሽ የምታስቢያቸውን ጥያቄዎች አክለሽ ብትጠይቂልን የበለጠ እንጠቀማለን።ሁላችሁንም እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
አሜን
😮😂😂😂በመሰረቱ የጠቀስካቸው ጥቅሶች አንተ ራስህ ልብ ብለህ ማንበብህን ተጠራጠርኩ ወንድሜ 🤔🤔😳
1. የመጀመሪያው የጠቀስከው የኢያሪኮ ቅጥር እንዴት በጩኸት እንደፈረሰ ያሳያል ይህም ፖስተሩ ከገለፁት ነጥብ የጩኸትን ሃይለኛነት የሚያሳይ ነው ድምፅ ኢያሪኮን ግንብ ካፈረሰ እንዴትስ አብሶ ጤናን አያፍርስ 😂😂😂😂ይበልጥ ሳይሱንና ፖስተሩ የተናገሩትን ይድግፋል
2. ከዛ በታች የገለፅካቸው ጥቅሶች በሙሉ ከአውዱ ውጪና አንዴ ብቻ የሆኑ ንገሮችን ነው ፖስተሩ ግን በተከታታይ ስለሚድረግ የጩኸት አምልኮ ነው የጠቀሱት : እስኪ በርጋታ ምእራፎቹን አንብባቸው
3. በጣም ግን የሚያስተዛዝበው 😮😢😮😮 በመጨረሻ የጠቀስከው 1ኛ ሳሙ 4:5 እና ነገስት 18 የጣኦት አምልኮን የጩኸት ድርጊት ነው ይህንን ደግምኢ ፖስተሩ ከኤልያስ ፀሎትጋር አነፃፅረው ሲናገሩት ሰማሁ ምናልባት ወንድሜ ጩኸት የሚል ብቻ ቃላት መርጥህ ይሆን ኮሜንት የሰጠኸው ? 🤔ወይስ ጨርሰህ በትክክል አላዳመጥክም ???? ለማንኛውም ቃሉን በአግባቡ አንብበህ ብትተች መልካም ነው በተረፈ ፖስተሩ እንዳሉትም እግዚአብሔር በጩኸት ብዛት የሚሰማ አምላክ አይድለም ስለዚህ ስሙ ይመስገን
@@hhttEthioለምን ይመስልሃል(ሻል) የኢያሪኮን ግንብ ያፈረሰው ጩኸት ሕዝቡን ያላፈረሰው?
*ሳይንሱን አልተቃወምኩም
*Spurgen ለ6,000 ሰዎች Wesly ለ40,000 ሰዎች ለመስበክ መጮኽ አይኖርባቸው ይሆን?
*1ኛ ሳሙ 4 እና 1ኛ ነገ 18ን ጥቅሶች የጠቀስኳቸው እግዚአብሔር ከሌለባቸው ጩኸቶች ወይም ከሌላ አምልኮ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ልብ ይሏል!
*ሚዛኑን የጠበቀ የድምጽ መስተጋብር አሰፈላጊ መሆኑን አምንበታለሁ
*ጩኸት ሁሉ ግን ከመንፈስ ቅዱስ አይደለም ብሎ መፈረጅ ግን ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም
*Genocidal ነው ብሎም መፈረጅ እንዲሁ
ለእኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የድምጽ አጠቃቀም ከእውቀት ማጣት ጋር የተገናኘ ነው የሚለው አሳማኜ ነው።
ተባረክ (ኪ)
@@mesfintadewos7581ጩኸት ሁሉ አላለም እኮ ሲናገር ለዛም መሰለኝ ስለነ ስፐርጀን የጠቀሰው ግን ባግባቡ ካልሆነ ጉዳት አለው ነው መልክቱ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በጩኸት የሚሰራ አምላክ አይደለም ቆሮ 14 ላይ ሁሉም ባግባቡ እንዲደረግ በጉባኤ ተነግሮናል ታድያ አምልኮ ላይ ጩኸት ነበር የሚል የታለ? መፃፍ ቅዱስ ላይ? በጩኸት አምልኩ የሚል ጥቅስ ብታሳየኝ ደስ ይለኛል የጠቀስካቸው ግን የጩኸትን ሀይለኛነት የሚደግፉ ናቸው. ተባረክ እህት ነኝ
@@hhttEthio ❤🙏
እውነተኛ አምልኮ “በእውነትና በመንፈስ” መሆኑ ቀርቶ “በጩኸት” እንበለዋ? ኧረ ስህተት ነው።
አልፎ አልፎ የተደረገውን የየዕለቱ ድርጊት አናድርገው።
Kerehu eko enem kechurch. This is one of the reasons. The main one.
This is indeed shocking and needs an immediate action . It’s so sad
Thank you so much my question was answered, I had a question allways about that. We should learn from this.
ይህ እንደለ ሆኖ ግን ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል የምለው ወሳኝ ነገር ነው ።
# ኢየሱስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ...
# የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ እያለ ይጮህ ነበር..
# ወደ እኔ ጩህ .. ወዘተ
መጽሐፍ ቅዱስ ከድምፅ ጋር ተያይዞ ይህንን እና ሌሎችንም ይነገራል ከነዚህ አንጻር ምን አይነት መልስ ይኖራል ...
ፓስተር ጌታ ይባርክዎት ይህንን ሀሳብ ለቤተክርስቲያን መሪዎች በስልጠና መልክ ቢሰጥ ምን ይመስላችኋል ቲጂዬ ብታስቢበት።
I was thinking same as you. It needs to give some training and awareness .
Dinik mastenikekia New Gata ybarikachu Meriwoch Ermija ywsedu Fetinew
God bless You ❤
wowowo tabarakuuu
GBU more and more