ዳንኤል 9 ~ 70ኛው ሱባኤ ~ ፓስተር አስፋው በቀለ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 6 фев 2025
  • በከለዳውያን መንግሥት ላይ በነገሠ፥ ከሜዶን ዘር በነበረ በአሕሻዊሮስ ልጅ በዳርዮስ በመጀመሪያ ዓመት፥
    2 ፤ በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት እኔ ዳንኤል የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት፥ እግዚአብሔር በቃሉ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቍጥር በመጽሐፍ አስተዋልሁ።
    3 ፤ ማቅ ለብሼ በአመድም ላይ ሆኜ ስጾም እጸልይና እለምን ዘንድ ፊቴን ወደ ጌታ ወደ አምላክ አቀናሁ።
    4 ፤ ወደ አምላኬም ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፥ ተናዝዤም እንዲህ አልሁ። ጌታ ሆይ፥ ከሚወድዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ጋር ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና የምታስፈራ አምላክ ሆይ፥
    5 ፤ ኃጢአትን ሠርተናል፥ በድለንማል፥ ክፋትንም አድርገናል፥ ዐምፀንማል፥ ከትእዛዝህና ከፍርድህም ፈቀቅ ብለናል፤
    6 ፤ በስምህም ለነገሥታቶቻችንና ለአለቆቻችን ለአባቶቻችንም ለአገሩም ሕዝብ ሁሉ የተናገሩትን ባሪያዎችህን ነቢያትን አልሰማንም።
    7 ፤ ጌታ ሆይ፥ ጽድቅ ለአንተ ነው፤ እንደ ዛሬም ለእኛ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ ለእስራኤልም ሁሉ በቅርብና በሩቅም ላሉት አንተን በበደሉበት በበደላቸው ምክንያት በበተንህበት አገር ሁሉ የፊት እፍረት ነው።
    8 ፤ ጌታ ሆይ፥ በአንተ ላይ ኃጢአት ስለ ሠራን ለእኛና ለነገሥታቶቻችን ለአለቆቻችንና ለአባቶቻችንም የፊት እፍረት ነው።
    9 ፤
    10 ፤ በእርሱ ላይ ምንም እንኳ ያመፅን ብንሆን፥ በባሪያዎቹም በነቢያት እጅ በፊታችን ባኖረው በሕጉ እንሄድ ዘንድ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ምንም እንኳ ባንሰማ፥ ለጌታ ለአምላካችን ምሕረትና ይቅርታ ነው።
    11 ፤ እስራኤልም ሁሉ ሕግህን ተላልፈዋል፥ ቃልህንም እንዳይሰሙ ፈቀቅ ብለዋል፤ በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርተናልና በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ ሕግ የተጻፈው መሐላና እርግማን ፈሰሰብን።
    12 ፤ እጅግ ክፉ ነገርንም በእኛ ላይ በማምጣቱ በላያችንና በእኛ ዘንድ በተሾሙት ፈራጆቻችን ላይ የተናገረውን ቃል አጸና፤ በኢየሩሳሌምም ላይ እንደ ተደረገው ያለ ነገር ከቶ ከሰማይ ሁሉ በታች አልተደረገም።
    13 ፤ በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈ ይህ ክፉ ነገር ሁሉ መጣብን፤ ከኃጢአታችንም እንመለስ እውነትህንም እናስብ ዘንድ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ፊት አልለመንንም።
    14 ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ክፉ ነገሩን ጠብቆ በእኛ ላይ አመጣ፤ አምላካችን እግዚአብሔር በሚሠራው ሥራ ሁሉ ጻድቅ ነውና፥ እኛም ቃሉን አልሰማንምና።
    15 ፤ አሁንም ሕዝብህን ከግብጽ ምድር በበረታች እጅ ያወጣህ፥ እንደ ዛሬም ቀን ዝና ለአንተ ያገኘህ ጌታ አምላካችን ሆይ፥ ኃጢአትን ሠርተናል፥ ክፋትንም አድርገናል።
    16 ፤ ጌታ ሆይ፥ ስለ ኃጢአታችንና ስለ አባቶቻችን በደል ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ላሉት ሁሉ መሰደቢያ ሆነዋልና እንደ ጽድቅህ ሁሉ ቍጣህና መዓትህ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም ከቅዱስ ተራራህ እንዲመለስ እለምንሃለሁ።
    17 ፤ አሁንም፥ አምላካችን ሆይ፥ የባሪያህን ጸሎትና ልመናውን ስማ፤ ጌታ ሆይ፥ በፈረሰው በመቅደስህ ላይ ስለ አንተ ስትል ፊትህን አብራ።
    18 ፤ አምላኬ ሆይ፥ በፊትህ የምንለምን ስለ ብዙ ምሕረትህ ነው እንጂ ስለ ጽድቃችን አይደለምና ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዓይንህን ገልጠህ ጥፋታችንና ስምህ የተጠራባትን ከተማ ተመልከት።
    19 ፤ አቤቱ፥ ስማ፤ አቤቱ፥ ይቅር በል፤ አቤቱ፥ አድምጥና አድርግ፤ አምላኬ ሆይ፥ ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና ስለ ራስህ አትዘግይ።
    20 ፤ እኔም ገና ስናገር ስጸልይ፥ በኃጢአቴና በሕዝቤም በእስራኤል ኃጢአት ስናዘዝ፥ በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን፥
    21 ፤ ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ።
    22 ፤ አስተማረኝም፥ ተናገረኝም እንዲህም አለ። ዳንኤል ሆይ፥ ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ።
    23 ፤ አንተ እጅግ የተወደድህ ነህና በልመናህ መጀመሪያ ላይ ትእዛዝ ወጥቶአል፥ እኔም እነግርህ ዘንድ መጥቻለሁ፤ አሁንም ነገሩን መርምር፥ ራእዩንም አስተውል።
    24 ፤ ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።
    25 ፤ ስለዚህ እወቅ አስተውልም፤ ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል፤ እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።
    26 ፤ ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፤ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፤ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፤ ጥፋትም ተቀጥሮአል።
    27 ፤ እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።

Комментарии • 157

  • @jerryjerry710
    @jerryjerry710 24 дня назад +2

    ዘመን የማይሽረው ትምህርት ነው ጌታ ኢየሱስ የተባረከ ይሁን ዛሬ ደግሞ ምዕራፍ ዘጠኝ ላይ ነኝ ጌታ እንዲያስተምረኝ አብሬህ ፀልዬ እጀምራለሁ ተባረክ ፓስተር

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +4

    ABSOLUTELY OH YES THE GREAT GOD'S GENERAL HIGHLY ESTEEMED MAN OF GOD SENIOR PASTOR ASFAW BEKELE.

  • @DawitHailemariam-ks3rx
    @DawitHailemariam-ks3rx Год назад +2

    Amen maranata

  • @fekereabkassahun258
    @fekereabkassahun258 Год назад +4

    Pastor Geta yebarkeh
    Bibile Ena mastawesha eyeyazku eyetsafku new memarew

  • @nattymam
    @nattymam Год назад +2

    ፖስተር ተባረክ!!🙏🙏🙏

  • @makbelmillion6534
    @makbelmillion6534 Год назад +3

    በዚ ትምህርት ተባሪኬበት ኣለዉ ፡ ክብር ለኣብ ወልድ መንፈስ ቁዱስ ይሁን ፡
    ጌታ ፀጋ ያብዛልህ ።

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +1

    ABSOLUTELY IT'S TRUE THE GREAT GOD'S GENERAL HIGHLY ESTEEMED MAN OF GOD SENIOR PASTOR ASFAW BEKELE.

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +3

    WELCOME THE GREAT GOD'S GENERAL HIGHLY ESTEEMED MAN OF GOD SENIOR PASTOR ASFAW BEKELE.

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +3

    I RECEIVE.

  • @gadisefita403
    @gadisefita403 2 года назад +2

    Ye tsegaw balabet Egzihabiher yebarak 🙏
    Pastor sila tsalot sitastamir wuste iyatakatale new Ye samawut Geta abzito yebarkih!
    Tselot le hullum nager kulf new.

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +3

    AMEN.

  • @mihret-9876
    @mihret-9876 Год назад +6

    እንደማር እንደወተት የሚጣፍጥ ትምህርት ከኢትዮጵያ ነው እጅግ በጣም ተባርኬበታለሁ።

  • @Ova-7311
    @Ova-7311 Год назад +2

    ፓስተር, ጌታ ይብዛልህ.

  • @DawitHailemariam-ks3rx
    @DawitHailemariam-ks3rx Год назад +1

    Asfesh beante temirte bezu awkialhu tebarek

  • @AD-lx3st
    @AD-lx3st 3 года назад +3

    የማንቂያ፣ትምህርት፣እግዚአብሄር፣ይመስገን
    እንዴት ፣የሚያበረታ፣ትምህርት፣የአባቶችን፣ትም
    መስማት፣እንድንችል፣ስለረዳህን፣ፓስተር፣እግዚ
    አብሄር፣ዘመንህን፣ይባርክ፣የአንተ፣የሆነ፣ነገር ፣
    ሁሉ፣ይባረክ ።ማራናታ፣ማራናታ፣ማራናታ፣አሜን

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +1

    በትክክል።

  • @yemanedesta5340
    @yemanedesta5340 3 года назад +2

    ተባረክ ባሰተርበቀለ ትምህርትህ የሚያንጽ ሰለሆነ ተባረክ

  • @martatesfaye7773
    @martatesfaye7773 8 месяцев назад

    ፓስተር አስፋው የምታስተምራቸው እነዚህ በእውቀትና በእውነት የታጨቀ አስተምህሮት ለልጅ ልጆች እና ከትውልድ ትውልድ መተላለፍ አለበት ዘመንህ ይባረክ እግዚአብሔር ለኛ ባስተማርከን እና በሰጠኸን ልክ ብቻ ሳይሆን በመቶ እጥፍ ይባርክህ ❤❤❤❤

  • @hannajesus5594
    @hannajesus5594 3 года назад +2

    Pastor tebarek tsigawon yabezalik holiye Esemalehu tsigawon yesitiki geta yebarek

  • @webitu.tezageraserda7599
    @webitu.tezageraserda7599 4 года назад +18

    እግዚአብሔር ይበርክህ ፓሰተር አሰፋው ይህ ትምህርት መሰማት ለተሳናቸው በምልክት ቋንቋ ብታደርጉት ጥሩ ትምህርት ነው ዝማሬው ሁሉም ተባርኬበታለሁ ተባረክልኘ

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад +11

      selam Wubitu, መስማት ለተሳናቸው የምናደርግበትን ነገር አስቤውም አላውቅም፤ እንኳን ነገርሽኝ፤ የሚረዳን ሰው እንደት እናገኛለን.…? የምታውቁ ሰዎች ብትተባበሩን... እባካችሁ፤

  • @mamityebekeleye7807
    @mamityebekeleye7807 2 года назад +2

    አሜን ቶሎና

  • @zeritumengistu9303
    @zeritumengistu9303 3 года назад +2

    ፓስተር አግዚአብሔር ዘመንክን ይባረክ... በዚህ ዘመን አንዲ የሚያንፅ አና ለ አግዚአብሔር አንድንኖር የምያድረግ ትምርት አንድንማር አንተን የስተን አምላክ ይባረክ::

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +1

    DEFINITELY.

  • @selamtibebe9111
    @selamtibebe9111 3 года назад +2

    ተባረክ

  • @dawitoryonalemu6031
    @dawitoryonalemu6031 2 месяца назад

    ፓስተር እግዚአብሔር ይባርክህ ይህ ትምህርት የተላለፈው 2020 ቢሆንም እኔ አሁን በ2024 ማብቂያ ላይ ትኩስ ሆኖ እየሰማሁት ነው ጠቅሞኛል ተባርኬበታለሁ አንተና አብረውህ ለሚያገለግሉ እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ

  • @TewodrosAyele-fq1dh
    @TewodrosAyele-fq1dh 9 месяцев назад

    Ante sw be eyesus sim tebarek
    ዝም ብለ ቀጥል በኢየሱስ ስም ተባረክ pastor

  • @kebedewakweya8833
    @kebedewakweya8833 3 года назад +2

    ፓ/ር አስፋዉ ጌታ እግዚአብሄር ይባርክህ!

  • @MCEPlus
    @MCEPlus 7 дней назад

    ፓስተር ዘመንህ ይባርክህ!!

  • @eyerusalemnaizghi7791
    @eyerusalemnaizghi7791 2 года назад +2

    Amen God bless you Pastor

  • @adebe4130
    @adebe4130 2 года назад +2

    I love all old songs. May God bless pastor

  • @ሳራእግዚአብሔርአባቴነው

    አሜንንን 🙏GOD bless you paster

  • @lidyaghrmay851
    @lidyaghrmay851 3 года назад +3

    ትምርቱ ኣይጠገብም ጳስተርዬ በብዙ ይባርክህ አንተ በረከታችን ነህ❤❤❤❤🌹🌹🌹🌹

  • @bettymehari3768
    @bettymehari3768 Год назад +1

    Amen 🙏 Jesus is coming, Maranata.

  • @natnaeltilahun5694
    @natnaeltilahun5694 2 года назад +2

    God bless you pastor 🙏🙏🙏

  • @11223h_v
    @11223h_v 4 года назад +2

    ጌታ እየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ፓስተር አስፋው እማትጠገብ የጌታ አገልጋይ ፀጋውን ያብዛልህ

  • @abrahambezabih5122
    @abrahambezabih5122 Год назад +1

    አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!

  • @husseinabdi527
    @husseinabdi527 4 года назад +4

    ፓስተርየ ጌታ ዘመንህን ይባርክ
    እኔ ምን ጊዜም ስለ አንተ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
    በዚህ ዘመን ከትውልድ መካከል የጠፋውን ትምህርት ነው የጀመርከው በርታ

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад +2

      ተባረክ ወንድም ሁሴን አልፎ አልፎ በእስልምና ዙሪያ የምታስተምረውን አያለሁ። በርታ ብዙዎችን መድረስ ያለብን ዘመን ነው። ዘመኑ አልቋል፤ ሙስሊሞች ለኢየሱስ ሊሆኑ ይገባል።

    • @husseinabdi527
      @husseinabdi527 4 года назад

      @@asfawBekelepastor
      ያለሁት አፍርካ በመሆኑ ለልጆቼ ስል ብዙ ማገልገል አልቻልኩም

    • @husseinabdi527
      @husseinabdi527 4 года назад +4

      አዎን ፓ/ር ጸልይልኝ ጌታ ይረደኛል እንደምንም ብየ ቤተሰቦቼ ከአፍሪካ ብወጡልኝ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ት/ ቤት ገብቼ መማር እፈልጋለሁ ።
      እንደዚሁም ያለሁበት ናይሮቢ በሶማሌዎች እና አጉል አክራሪዎች የተሞለች በመሆኑ እንደ ልቤ ወጥቼ ለማገልገል አልቻልኩኝም
      ልክ እንደ ጳውሎስ በውስጥም በውጭም ፈተና( ስጋት ) አለብኝ
      ጌታ ግን ከሁሉ አድኖኛል

  • @nurobetselotzeleke7585
    @nurobetselotzeleke7585 Год назад

    ሁልጊዜ በአንተ ውስጥ ክርስቶስን አያለሁ። እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜው ያጽናህ። ተባረክልን።

  • @TruemanAyalew
    @TruemanAyalew 8 месяцев назад

    ፓስተር ዘመን ይባረክ።

  • @muluwoldemichael5439
    @muluwoldemichael5439 3 года назад +1

    ጌታ አብዝቶ ይባረክህ ፓስተር በጣም አስፈላጊ ትምህርት ነው የሚያነቃቃ ጸጋው ይጨመርልህ።

  • @SolomonAlemu-ur5fo
    @SolomonAlemu-ur5fo 22 дня назад

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ተባረክልን ዘመንህ ይባረክ ጋሼ

  • @amenamen9497
    @amenamen9497 4 года назад +2

    Amen 🙏🏽 Maranata geta Jesus hoy tolona 🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙌🏽🙌🏽🙌🏽🙌🏽🙌🏽🙌🏽 pastor geta Jesus yibarkih tsegawin yabzalih

  • @Tamgn
    @Tamgn 9 месяцев назад

    ፓስተር እናመሰግናለን በጣም ጥሩ ትመለከታለህ ሕርችዠት ነው

  • @thitinabirhanu1351
    @thitinabirhanu1351 4 года назад +7

    ወንድሜ ተባረክ ዘመንህ ይባረክ ከዚህም በላይ የጌታ ጸጋ ይብዛልህ በዚህ ዘመን ለዚያውም በዚህ ጊዜ እንዴት መታደል ነው የጌታን ቃል መማር ተባረክ እኔም ቤተስቦቼም በጣምምምምምምምም እንወድሀለን ጌታ ይባርክህ።

  • @proudsemayawi9052
    @proudsemayawi9052 2 года назад +3

    ጌታ ኢየሱስ ይመጣል!!!

  • @merhawitgebremeskel
    @merhawitgebremeskel 4 года назад +2

    ተባረክ ፓስተር አስፋው ጌታ ኢየሱስ ፀጋውን ያብዛልህ ።
    አሜን ማራናታ ጌታ ኢየሱስ ይመጣል ተስፋችን እርሱ ነው ።

  • @Neb-w9n
    @Neb-w9n 7 месяцев назад

    እንዴት ድንቅ አውቀት ነው

  • @ሳሚቱዩብ
    @ሳሚቱዩብ 4 года назад +6

    ፓስተር ጌታ ዘመንክ ያለምልም እንዴት ደስ የሚሊ አስተምሮት ተባረከ በብዙ!!

  • @ramayouns9321
    @ramayouns9321 4 года назад +2

    Amen amen thank you so much pastor God bless you all the family

    • @ሃሊሉያቲቪ
      @ሃሊሉያቲቪ 4 года назад

      ፓስተር ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክ ተበራክ ሁሉንም ትምህረቶችን እከታተላለሁ እበራከለሁ
      ከግርክ ደዊት GBU

  • @ዓለምአየለ
    @ዓለምአየለ 4 года назад +2

    እግዚአብሔር ይጠብቅህ እስከነ ቤተሰቦችህ
    እግዚአብሔር ይመስገን እናመሰግናለን

  • @hailemichaeldebalke2403
    @hailemichaeldebalke2403 3 года назад +2

    God bless you brother. I glorify our father for his mercy and love for us.

  • @abebatanga7958
    @abebatanga7958 4 года назад +3

    God bless you pastor. Thank you so much.

  • @tirsitthomas4535
    @tirsitthomas4535 4 года назад +5

    ፓስተር አስፋው ጌታ አብዝቶ ፅጋውን ያብዛልህ ተባረክ በጣም ተጠቅሜለሁ ጌታ ክብሩን ይውሰድ።🙏🙏🙏😇😇😇😇😇😇😇

  • @ሰላምለኢትዮጵያ-ዐ7ፈ
    @ሰላምለኢትዮጵያ-ዐ7ፈ 4 года назад +10

    God bless you I love Danial teaching amazing!!!

  • @zewudekia7473
    @zewudekia7473 2 года назад +3

    God bless you pastor, I'm one of beneficiary from your teaching

  • @aderamillo4576
    @aderamillo4576 2 года назад +1

    Dear brother God bless you very much.

  • @tesfutilahun808
    @tesfutilahun808 2 года назад +1

    Tebark

  • @almazlemmahabte6053
    @almazlemmahabte6053 4 года назад +2

    ጌታ እንደ ባለፀግነቱ መጠን ይባርክህ ፓስተር ተጠቅሜአለሁ

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 года назад +3

    Amen God bless you Pastor Asfaw this is my daily prayer the body of Christ to build the Altar of Prayer as individual ,family and us church union

  • @yohanneskantibaayana2784
    @yohanneskantibaayana2784 11 месяцев назад

    እግዚአብሔር ይባርክህ!!!

  • @destayonas6613
    @destayonas6613 4 года назад +4

    ጌታችን በእውነት ዘመን ህን ይባርክ ይቀድስ አሜን በኢየሱስ ስም።

  • @frehiwotfitamo7548
    @frehiwotfitamo7548 Год назад

    Amennnnn Maranta

  • @asterdegu9426
    @asterdegu9426 8 месяцев назад

    ተባረከ❤

  • @OzenOffie
    @OzenOffie Месяц назад

    Pastor God bless you and your service Ozen from Gofa bulki

  • @AbebawuPawulosBelete
    @AbebawuPawulosBelete 9 месяцев назад

    pastor be timrtih eytebareku nw eg/r yibarkih

  • @tirsitthomas4535
    @tirsitthomas4535 4 года назад +3

    አሜን አሜን እውነት ነው ፀሎት ሀይል አለው 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @dawitdefaru1639
    @dawitdefaru1639 3 года назад +1

    Nice mlikity

  • @raheltadsse789
    @raheltadsse789 4 года назад +1

    Betikikil Paster endeferanew ayidelem betam endiniwedew argenehal Paster geta yibarek antem tebarekilin

  • @TsiYon-h1q
    @TsiYon-h1q Год назад

    🎉ተባረክልኘ

  • @J2E0S1U3S
    @J2E0S1U3S 4 года назад +1

    ተባረክ ፓ/ር

  • @loveworld1111
    @loveworld1111 3 года назад +1

    geta abzto ybarkh pastor.....betam iwedhalew

  • @danielbelay8110
    @danielbelay8110 6 месяцев назад

    Amazing

  • @sosenanaser8565
    @sosenanaser8565 4 года назад +1

    ቅሪት ያስቀረልን ጌታ ይባረክ ጌታ ዘመንህን ቤተሰብህን ይባርክ ፀጋውን ያብዛልህ pastor

  • @mengistuayele2707
    @mengistuayele2707 4 года назад +2

    Amen Glory to God.

  • @christiantsegaytewelde450
    @christiantsegaytewelde450 4 года назад +1

    "Tselot yemiwedu sewoch tienegnoch nachew " oh God! Lik neh pastor tebareklin

  • @raheltadsse789
    @raheltadsse789 4 года назад +1

    God bless you Paster zemenik yibarek egna geta ke mitebikut gar nen berta egzabihar kante gar new be strong Paster be Tselot enkomalen kante gar

  • @messelefanta
    @messelefanta 10 месяцев назад

    Stay Blessed!

  • @memeelmemee5123
    @memeelmemee5123 Год назад

    Amen 🙏🤲

  • @helengm2977
    @helengm2977 3 года назад +1

    May God Bless You Abundantly Pastor!

  • @mebrateasaminew8030
    @mebrateasaminew8030 4 года назад +1

    ፓስተር ጌታ በነገር ሁለ ይባርክህ ፀጋ ይብዛልህ።

  • @yigeremuyoelyoola5282
    @yigeremuyoelyoola5282 Год назад +2

    I AM CONNECTING FROM HAWASSA ETHIOPIA.

  • @betels5161
    @betels5161 4 года назад +2

    God bless you Pastor

  • @tayeterefe779
    @tayeterefe779 4 года назад +1

    AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN AMEN

  • @ribikadaniel3847
    @ribikadaniel3847 4 года назад +4

    Shalom Shalom Pastor, God Bless You and Your Family

  • @meseretworkureta8723
    @meseretworkureta8723 4 года назад +1

    You are blessed

  • @fimt448
    @fimt448 2 месяца назад

    Tebarek!

  • @haimanottadessekassa7414
    @haimanottadessekassa7414 4 года назад +1

    ጌታ አብዝቶ ይባርክህ.ፀጋ ያብዛልህ.

  • @yeshezewedie6287
    @yeshezewedie6287 4 года назад +1

    God Bless you 🙏

  • @selamawitwendmu8066
    @selamawitwendmu8066 4 года назад +1

    Paoster betam new menwedhe zemenhe yebark ke jemma new meketatelhe

  • @meseretworkureta8723
    @meseretworkureta8723 4 года назад +1

    Amen

  • @yot8138
    @yot8138 4 года назад +1

    Pastorya God bless you

  • @selam.m6744
    @selam.m6744 4 года назад +2

    ሰላም ነው። ስብከቱ በጣም ደስ ይላል። እኔ ወድጀዎለው

  • @Luna23official
    @Luna23official 4 года назад +1

    አሜን

  • @masetewalyenuren4078
    @masetewalyenuren4078 4 года назад

    Bebzu tebarek yabzalib

  • @samuelkassa192
    @samuelkassa192 4 года назад +2

    God bless you. Pastore Asfaw

  • @tesfayemokonen7281
    @tesfayemokonen7281 4 года назад +3

    እግዚአብሔር ይባርክህ

  • @happydm3382
    @happydm3382 4 года назад +1

    Tabraki p s

  • @hananpfister5708
    @hananpfister5708 4 года назад +1

    Amen! Maranatha!

  • @seblewongelwondifraw8673
    @seblewongelwondifraw8673 4 года назад +1

    ጌታ ይባርክህ

  • @tayeterefe779
    @tayeterefe779 4 года назад +1

    waw GODBLESS brother