"እግዚአብሔር ስብራትን ይጠግናል" ፓስተር ዳንኤል መኮንን Pastor Daniel Mekonnen

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 24 ноя 2021
  • ኤርምያስ 8:18-22 ኅዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል። እነሆ። እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ አገር ተሰማ። በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድር ነው? መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንነም። በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ ጠKWreማለሁ፤ አድናቆትም ይዞኛል። በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?
    ኢሳይያስ 40:1-5 አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ። ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ። የአዋጅ ነጋሪ ቃል። የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
    ©Temple of God International Church September 27, 2021

Комментарии • 8

  • @tsehayegetachew4599
    @tsehayegetachew4599 2 года назад +1

    እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርኮት በትክክል ወንጌል ሰለሚስተምሩ።

  • @mamabitu5308
    @mamabitu5308 2 года назад

    ዘመንህ በእግዚአብሔር በረከት ይለቅ።

  • @mercyabs3
    @mercyabs3 2 года назад +4

    Pastor God blessed you!!!

  • @kalekale8217
    @kalekale8217 2 года назад

    Tankyou paster Danial
    God Blsse you and touer family

  • @tsyontesefaye9195
    @tsyontesefaye9195 2 месяца назад

    ተባረክ ዘመንህ ሁሉ ይባረክ

  • @belachewbulto2229
    @belachewbulto2229 2 года назад

    Paster god bless you,,,,,,,,,, you are right

  • @tigestwoldetsadik4316
    @tigestwoldetsadik4316 2 года назад

    Thank your Pastor Daniel Mekonnen.