የማቴዎስ ወንጌል ታሪካዊ ዳራ | የማቴዎስወንጌል ለምን ተጻፈ?

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 13 сен 2024
  • በዚኽ ቪድዮ የማቴዎስ ወንጌልን መጽሐፍ በዐዲስ መልኩ ያጥኑ! ስለ ማቴዎስና ስለ ጻፈው የኢየሱስ መልእክት ታሪካዊ ዳራ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያግኙ፣ ከዚያም መልእክቱን በግል ሕይወትዎና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎ ተግባራዊ ያድርጉ፡፡
    የማቴዎስ ወንጌል በመጀመሪያ የተጻፈው በልዩ መከራ ውስጥ እያለፉና ኢየሱስ
    ተስፋ የተገባለት የአይኹድ መሲሕ መኾኑ ላይ ጥያቄዎችን ያነሡ ለነበሩት አይኹድ ክርስቲያኖች ነው፡፡ ኢየሱስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕና መንግሥቱም ኹሉንም ሕዝብ የምትጠቀልል መኾኗን ለማረጋገጥ ለቀዳሚ ተደራሲያኑም ለእኛም በግልጽ መስክሯል፡፡ ኢየሱስ ሰውን ኹሉ ወደ ርሱ ይመጡ ዘንድ እንደሚጠራ የማቴዎስ ሕይወት ምስክር ነው፡፡
    መጽሐፍ ቅዱስ፣ ታሪኩንና በሕይወታችን ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ በተሻለ መንገድ ሥነ ጽሑፋዊና ታሪካዊ ዐውዱን ለመረዳት በምናደርገው በዚህ ጒዞ ይቀላቀሉን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ ይህ ወሳኝ ክፍል ሲኾን ይህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብና ኑሮ እንዲኖርዎ ያስችሎታል፡፡ የምናዘጋጃቸው
    የመጽሐፍ ቅዱስ ቪድዮዎች ለኹሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሰዎች የሚኾኑ ናቸው፡፡ በእነዚህ ቪድዮዎች የግልና የአነስተኛ ቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችዎችን ያሳድጉ፡፡
    WEBSITE:
    www.thebibleef...
    FACEBOOK:
    / experiencethebibleeffect
    INSTAGRAM:
    / thebibleeffect
    ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ
    ምዕራፎች፡
    0፡00 መግቢያ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል
    0:50 የመጀመሪያው መቶ ዓመት ፍልስጥኤም
    1:50 የኢየሱስ ጥሪ ለማቴዎስ
    2:42 መንግሥተ ሰማይ
    5:13 የማቴዎስ አይኹድ ተደራሲያን
    6:52 ትግበራ፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት ገንቡ
    #የማቴዎስወንጌል #የመጽሐፍቅዱስጥናት
    #ዐዲስኪዳን

Комментарии • 9

  • @thebibleeffectamharic
    @thebibleeffectamharic  6 месяцев назад +1

    የሕይወት ተዛምዶ ጥያቄዎች
    1) ማቴዎስን በምታነብቡት ጊዜ ኢየሱስ ስለመንግሥተ ሰማያት ለተናገረው ንግግር ትኲረት ስጡ፡፡ ኢየሱስ ይህን እነንዴት ገለጸው? ወደዚህ መንግሥት ለመግባት ምን ያስፈልጋል፡፡
    2) የእግዚአብሔር መንግሥት በዓለማችን ላይ እንዴት ልትታይ እንደሚገባ የምትጠባበቁት እንዴት ነው? እነዚህ ጥበቃዎች በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ተሞግተዋል?
    3) የእግዚአብሔር መንግሥት በሥራ ላይ መኾኗን እንድናይ ማቴዎስ ያቀረበልንን ማስረጃዎች ዐስቡ፡፡ በሕወታችኹ፣ በቤተ ክርስቲያናችኹ እና በማኅበረ ሰባችሁ ውስጥ በምን በምን መልኩ ሲሠራ ታዩታላችኹ?
    4) ማቴዎስ ምዕራፍ 5 እስከ 7 አንብቡ፡፡ በዚህ ስብከት ውስጥ ለርስዎ የትኛው ክፍል ትኩረትዎን ሳበው? ይህን በዚህ ሳምንት በምን መልኩ ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ?

  • @getnetgodsoon5684
    @getnetgodsoon5684 2 месяца назад

    ❤❤❤ ጻዲቅ አባት ሆይ ትምህርት በብዙ መረዳት እደበዛልን ቃልህንም መግለጡላይም ሀይልህ ይብዛልን አሜንንን ❤❤❤

    • @thebibleeffectamharic
      @thebibleeffectamharic  2 месяца назад

      አሜን! መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህን ስትቀጥል አምላክ ይባርክህ!

  • @user-bv5lj6dv4j
    @user-bv5lj6dv4j 2 месяца назад

    God bless you ❤

  • @solomonsisay3
    @solomonsisay3 6 месяцев назад

    Keep going

  • @dawitnimani
    @dawitnimani 6 месяцев назад

    God bless u