የማቴዎስ ወንጌል ትምህርት 3-ከየትኛው ወገን ናችሁ?-በማሙሻ ፈንታ Matthew Teaching 3-Which Group are you in?- By Mamusha F.

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 2 дек 2024

Комментарии • 76

  • @equipmedia2577
    @equipmedia2577  Год назад +34

    #እነሆ_ንጉሥሽ
    #የማቴዎስ_ወንጌል_ትምህርት
    #ከየትኛው_ወገን_ናችሁ
    📖 ማቴ 2 : 1- 12
    ✔️ ኢየሱስ ሲመጣ ምድር እንዴት ተቀበለችው? የሰዎችስ ምላሽ ምን ነበር? ለተወለደው ህጻን የተሰጡ ምላሾችን በዚህ ክፍል እንመለከታለን።
    ✔️ ኢየሱስ ሲወለድ የነበሩ ምላሾች ዛሬም አሉ፤ ሳይለወጡ። ሰዎቹ ተቀያየሩ እንጂ ምላሾቹ አንድ ናቸው።
    ✔️ ምላሽ ከሰጡ ሰዎች 3ቱን እንመልከት፦
    1) ንጉሥ ሄሮድስ እና መሠሎቹ
    - ሄሮድስ በስልጣኑና በክብሩ የማይደራደር ነበር።
    - ሚስቱንና ልጆቹን ጨምሮ ብዙ ሰዎችን ገድሏል።
    ➲ ምላሽ ➲ ደነገጠ
    - ስልጣኑን፣ ክብሩን የሚያናጋ ስለመሠለው ደነገጠ፤ የተወለደውንም ሕፃን ለመሰየፍ እቅድ አወጣ።
    - እስከመጨረሻ አሳደደ፣ ሕፃናትን በሙሉ አስገደለ። የሄሮድስ ውጤት ግን ሞት ነበር።
    - እነዚህ እየተቃወሙ ሟች ናቸው። እየተቃወሙ ሞታቸውን የሚያፋጥኑ ናቸው።
    - ክብር፣ ስልጣን፣ ዝናንና እኔነትን ፍለጋ ኢየሱስን የተቃወሙ፣ ያሳደዱ መጨረሻ ሞቱ።
    - ስልጣን፣ ዝና፣ እውቀት ክብር አይደለም፤ የሰው ልጅ ክብር ኢየሱስ ነው።
    - እግዚአብሔር ክብር የሚለው ስልጣንን፣ ልብስን፣ እውቀትን አይደለም። ሰው ያለ ክርስቶስ ክብር የጎደለው ነው።
    - ለሰው ክብሩ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው ህይወት ነው።
    - ክብር ላልሆነ ነገር ክብር መግፋት መጨረሻው ሞት ነው።
    2) ኃይማኖተኞች / የኃይማኖት ሊቃውንት
    - በትክክል ተርጉመው በትክክል ምላሽ የማይሰጡ፣ ለሌላ ሰው የሚኖሩ፣ ለሌላ ሰው የሚተረጉሙ፣ ለሌላ ሰው የሚያስረዱ፣ እነሱን የማይነካቸው ናቸው።
    - በትክክል ጠቅሰው በትክክል የማይራመዱ፣ ኃይማኖት ሽባ ያደረጋቸው፣ በኃይማኖት ሰበብ ኢየሱስ ምንም ያልመሠላቸው ናቸው።
    - በቤት ውስጥ ሆነው የጠፉ፣ እያስተማሩ መሪ ያስፈለጋቸው ናቸው።
    - እስከመጨረሻ ለኢየሱስ አገልግሎት እንቅፋት ነበሩ። ኢየሱስን አሳልፈው የሰጡትም እነዚሁ ናቸው።
    📖 ማቴ 21:23
    - የመስቀልና የክርስቶስ ጠላቶች ነበረ።
    - የኃይማኖት ስልጣን እውነትን የመኖር ዋስትና አይደለም።
    - ኃይማኖት ካላንቀሳቀሰ፤ ወደ ኃይማኖቱ ባለቤት ካልመለሰ፣ ካላሰገደ፣ ካላንበረከከ፣ ካላስገረመ ምን ዋጋ አለው? ሙያተኝነት ምን ያደርጋል? ጥቅስ መጥቀስ እንደሙያ፣ ኃይማኖት መምራት እንደሙያ ከሆነ ምን ያደርጋል። የእነዚህም መጨረሻቸው ሞት ነበር።
    3) ሰብአ ሰገል
    - አስደናቂ ነገር ውስጥ የከተታቸው መገለጥ ነበር።
    - ጥርት ያለ ነገር የላቸውም ግን ተገለጠላቸው።
    - ሰው ለመዳን ምንም የተወሳሰበ ነገር አያስፈልገውም፤ መገለጥ ነው የሚያስፈልገው።
    - ያልታሰቡ፤ ግን የተገለጠላቸው አምላኪዎች ናቸው። እግዚአብሔር ሲናገራቸው ምላሽ የሰጡ፣ ወደ መራቸው የሔዱ፣ ለራሳቸው ያመኑ፣ የተሰጣቸውን መገለጥ ይዘው የሔዱ ናቸው።
    - የምንወስነው ውሳኔ መጨረሻ አለው። የእነዚህ መጨረሻ በእግዚአብሔር መጠበቅ ነበር።
    ✔️ በክብር ምክንያት የሚገፉ
    ✔️ በኃይማኖት ሰበብ የማይራመዱ
    ✔️ ያልተጠበቁ አምላኪዎች / የሚሰግዱ
    ➲ ከየትኛው ወገን ናችሁ?
    - ሰው የሰጣችሁን ክብር ለማስጠበቅ መከራ እየበላችሁ ነው?
    - ምስኪን ኩራተኞች ትሆኑ? ያላችሁ ዝናና ክብር የውሸት ነው። ውበት፣ እውቀት ይሻራል፤ አለም ተጠቅማ ነው የምትጥለው።
    - ከክብር የተነሳ የምትገፉ ካላችሁ መመለስ ይሁን።
    - ኃይማኖት ኢየሱስን እንዳይሸፍን ተጠንቀቁ።
    - አምላኪዎች፣ ሰጋጆች፣ ምላሽ የምንሰጥ ያድርገን።
    - እንደ ሰብአ ሰገል አይኖቻችንን ይክፈት። ሰብአ ሰገል ምን አድርጎላቸው ነው እንደዛ የሆኑት? ያሰገዳቸው፣ ያስገረማቸው ምን አድርጎላቸው ነው? ምንም! ለማምለክ ምክንያት አንፈልግ፤ እርሱ እንዲሁ አምልኮ ይገባዋል።

    • @rodasgetachew9347
      @rodasgetachew9347 Год назад

      አሜን ...ከየትኛው ወገን እንደሆንን ራሳችንን የምናይበት እውነትና መልእክት ነው ...!!
      ....
      ከኃይማኖተኛነት ከሙያተኛነት ለሌላው ከመጥቀስ ያድነን ይጠብቀን...🙏የተገለጠልን እውነተኛ አምላኪዎች ሰጋጆች ያድርገን እንደ ሰብአ ሰገል ስለተደረገልን ብቻ ሳይሆን ክብሩን አይተን አይኖቻችን ተከፍተው (በፍቅሩ ተይዘን) መስገድ ይሁንልን.. ክብራችን ለሆነው ለኢየሱስ...❤በትክክል ተርጉመን በትክክል ምላሽ የምንሰጥ በትክክል ጠቅሰን በትክክል የምንራመድ ...ኃይማኖት ለጌታ የሚያሰግደን እንጂ የማይሸፍንብን ...እግዚአብሔር ሲናገረን ምላሽ የምንሰጥ ሲመራን የምንመራ በማያልፈው በማይሻረው በእግዚአብሔር ክብር ተሞልተን የተሰጠንን መገለጥ ይዘን እስከ መጨረሻው የምንሔድበትን ጸጋና ህይወት ይስጠን ያብዛልን.....!!
      ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ ጸጋም ይብዛልህ የተወደድህ ወንድማችን ዶ/ር ማሙሻ በጣም ነው የምንወድህ 🙏❤ !!

    • @betheldalocha7196
      @betheldalocha7196 Год назад

      ይህን ሰምቶ አለመባረክ(ጠብቆ)፤ አለመባረክ (ላልቶ) አይቻልም .....ዘመንህ ሁሉ እንዲህ ክብሩን በመግለጥ ይጠቅለል።ብዙ ብዙ ብዙ....... ተባረክ።

    • @mahedr7075
      @mahedr7075 Год назад

      ❤❤❤❤❤❤

  • @tagesechtesema6195
    @tagesechtesema6195 Год назад +2

    አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ሆይ በየትኛው የከፍታ ጥግ ብወጣም አንተን እንዳልለምድ
    በእኔ ቤት በእኔ ልብ ቦታ እንዳልከለክልህ እርዳኝ

  • @haimanotbekana2971
    @haimanotbekana2971 Год назад +8

    እግዚአብሄር ሁሌም በየዘመኑ የራሱ የሆኑ ሰዎች አሉት በዚህ ዘመን እናንተን ለእኛ ሰጠን ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን።

  • @eteruhabteyes9764
    @eteruhabteyes9764 Год назад +1

    አግዛብሔር ዘመንህን ይባርክ ዶ/ሮ ማሙሻ እና ዶ/ር አብርሃም በሕይወቴ እንድ በረታ የእግዛብሔር ቃል በፍቅር እዳጠና ከእግዛብሔር ቃል ጋር ልዬ ፍቅር እንዳኖረኝ ስለረዳችሁኝ እግዛብሔር ይባርካችሁ ማለት እወዳለሁ ተባረኩ

  • @BirukGuta-jn5up
    @BirukGuta-jn5up 3 месяца назад

    Thank you lord Jesus. Its all your hand work❤❤❤

  • @hiwigelaye6509
    @hiwigelaye6509 Год назад +19

    እግዚአብሔር ሆይ ቃልህ እንደ ማር እየጣፈጠኝ እየተማርኩ ሰለሆነ አመሰግንሃለሁ ሰለ ማሙሻ ተመሰገን ባርከዉ ፀጋህን አብዛለት የሰማነዉን ቃል ከህይወታችን ጋር አዋህድልን አሜን🙏

  • @tsegaabamare7052
    @tsegaabamare7052 Год назад +5

    ብዙ ክብር ለነገስታት ንጉስ፣ ለጌታዎች ሁሉ ጌታ፡ ለአምላካችን ለእየሱስ ክርስቶስ ይሁን።

  • @URIMAGAPE
    @URIMAGAPE 3 месяца назад

    የህይወታችንን ጌታ በዚህ መልኩ መማር ምንኛ ደስስስ ይላል😊 ተባረክ ዶ/ር

  • @heldanatekola7129
    @heldanatekola7129 Год назад +3

    አሜንንንንንንንንንንንን ዶክተርየየየየየ እግዘብሔርን አመሰገንኩት ሆድ ብሶኝ እምባ እምባ ብሎኝ እንዳልቀር ጌታ በዘመናት ሰወ አለወ በቃ እየሱስየየየየየየየየየየ ሲደነቅ ሲሞካሽ በእምባ አደመጥኩት የማይገባኝን ወገን አደረገኝ በቃ እሔ እወነት ምድሪቱን ይሸፍን

  • @lidutigech2164
    @lidutigech2164 Год назад +1

    ሁሌም በምታስተምረው ትምህርት እመከርበታለሁ፣ እገሰጻለሁ ደግሞም እባረክበታለሁ በርታ! በአንተ አልፎ ስለሚደርሰኝ ጤናማ አገልግሎት ጌታ ክብሩን ይውሰድ፡፡

  • @ምህረትየበዛላት
    @ምህረትየበዛላት Год назад

    የምወድህ የእግዚአብሔር ሰው ዶክተር ማሙሻ ተባረክልኝ። ውድ ስጦታችን።

  • @shumeyetessema819
    @shumeyetessema819 Год назад +6

    "Being in a higher position in a religious organization is not a guarantee for living a truthful life." I like this.

  • @selamawitderibe1244
    @selamawitderibe1244 Год назад +1

    እግዚአብሔር አምላክ ጨምሮ ጨምሮ በሰማያዊ ቃሉ ይባርክህዘመንህ ዘርህ ይባረክ

  • @habatamhabatam8769
    @habatamhabatam8769 Год назад +3

    ፀጋው ይብዛላችሁ ወገኖቸ 💚

  • @tensumamush9918
    @tensumamush9918 Год назад

    Amennn Amennn.geta yibarek yemeretegn.geta liju beliju liju yaregegn.geta yibarek🙏🙏🙏🙏 dr mamusha tebarek

  • @tayechefo6312
    @tayechefo6312 Год назад +2

    እናመሰግናለን ዶክተር ማሙሻ፤ ሁልጊዜ የሚገርም ቃል በተለየ መገለጥ ስለምትመግበን የቃሉ ፍቅር እንዲኖረን እያበረከትክ ያለሀው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚነገር አይደለም ። ህይወትህ፥ ትዳርህ፥ ልጆችህ፥ ዘርማን ዘርህ ከዛሬ እስከመጨረሻው ይባረክ። አንተንና መሰሎችህን የሰጠን እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን ። አሜን።

  • @milliongelan3490
    @milliongelan3490 Год назад

    እግዚአብሔር ሰላዘጋጀልን ቃል ይመስገን። መልእክቱንም እንዲያሰተምሩ ስለሰጠኸን ባሪያዎችህ ተመስገን። ቃልህን እንደሚገባ እንዲናገሩ ፀጋን አብዛላቸው።

  • @maledaadane2519
    @maledaadane2519 Год назад

    ሁሌ አዲስ የእግዚአብሔር ቃል

  • @waynaphonetastic9887
    @waynaphonetastic9887 Год назад

    Taberekileghe mamushaa sagewen yabezalehee babezuu tatekimalewe

  • @mimi-gu3fy
    @mimi-gu3fy Год назад

    Ufffffte haleluya elelelelel elelelelel elelelelel elelelelel iyesusi yadinali 🙇‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️🙇‍♂️👏🙏👏🙏👏🙏👏

  • @DulumeRobi
    @DulumeRobi 11 месяцев назад

    ፀጋውን፡ያብዘልህ።

  • @Ebenezer2011
    @Ebenezer2011 Год назад +2

    እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቹሁ

  • @thomlimoservice
    @thomlimoservice 5 месяцев назад +1

    እናመሠግናለን

  • @kaneyEN2005
    @kaneyEN2005 Год назад

    Betam des yemil kal ❤❤❤❤

  • @merhawitgebremeskel
    @merhawitgebremeskel Год назад +1

    ተባረክ ወንድሜ ሁላችሁም የዚህ ፕሮግራም አስተቤሪዎች ተባረኩ ፀጋ ይብዛላችሁ።

  • @fadillamarkosi9137
    @fadillamarkosi9137 Год назад

    Uuuuuuu geta newo Eyesuse haleleuyyyaaa
    Wooowwwwow kebr eyehunilete
    Essyyyssseee ke Eyesuse wogenege ene anemeennneenen mamausha zemenike yebrke

  • @helenawonde9771
    @helenawonde9771 Год назад

    አቤት እግዚአብሔር ስምህ ይባረክ

  • @aboneshayalnesh8408
    @aboneshayalnesh8408 Год назад

    Abetu sele ante sele wede leju keberune yewesed tebatek

  • @pawlosfeleke6584
    @pawlosfeleke6584 Год назад +1

    ጸጋ ይብዛላችሁ !🙏

  • @tsegayemesele9031
    @tsegayemesele9031 Год назад +2

    Brother in one word thank you for your faithfulness for the scripture!

  • @zinashmamo9676
    @zinashmamo9676 Год назад

    አሜን ክብር ለእግዚአብሔር ይሆን ያስተማረን በቅዱስ አጠራሩ የጠራን ያበራልን ጌታ ይባረክ ክብር ለእግዚአብሔር አሜን ተባረክ ዶክተር

  • @Savedbygrace952
    @Savedbygrace952 10 месяцев назад

    God bless you dear brother

  • @selamtewolde8044
    @selamtewolde8044 Год назад

    Our big brother Mamusha Geta ahunm Tsega yabzalh, ychemrlh. Wstachin eske mineka bareken.

  • @jesuschrist15111
    @jesuschrist15111 Год назад

    ✞ክብር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።✟❤
    “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
    - ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

  • @amanuelbaze3004
    @amanuelbaze3004 Год назад +1

    ወንድም ማሙሻ ጌታ ይባርክ

    • @dahlaksiceland6162
      @dahlaksiceland6162 Год назад

      Egziabher yebarkesh sele qedus yehonew qalu tebarek egnam enbarkebtalen and neger gen lebelh ye demtse guday genn mejemerya lay teru neber ke 40 deqiqa behuala betam qensual ena studyiowoch leberketu tebaberun

  • @BetiAbera-op5dx
    @BetiAbera-op5dx 5 месяцев назад

    Geta eyesus yebarkhe

  • @yosefabeje9129
    @yosefabeje9129 Год назад

    በጣም በመገረም ጌታ እያስገረመን ነዉ

  • @aep.ronaldoedits
    @aep.ronaldoedits Год назад +1

    Thank you for your grace God!!!❤

  • @loinofjudahjesusint.hotels7710
    @loinofjudahjesusint.hotels7710 3 месяца назад

    It is nice❤

  • @redietcheru
    @redietcheru Год назад

    እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ

  • @aynalemh9590
    @aynalemh9590 Год назад +1

    ከእየሱስ ወገን ነኝ

  • @mulukenmihretu8711
    @mulukenmihretu8711 Год назад

    አሜንንንን ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርካችሁ ❤️❤️❤️🙏🙏🙏

  • @mesertkebede4115
    @mesertkebede4115 Год назад +1

    God bless you and your family 🙏

  • @desta5885
    @desta5885 Год назад

    ተባረክ ወንድሜ።

  • @Milliblackcreativities-pi1ms
    @Milliblackcreativities-pi1ms Месяц назад

    በቀን ሶስት ክፍል ብመለከት በ አንድ ወር 90 ክፍል አይቼ እደርስባችኋለሁ።
    ተባረኩ!

  • @aynalemh9590
    @aynalemh9590 Год назад

    Amen Amen 🙏 🙌 👏 ❤️ God bless you

  • @kumeinkosagalata8195
    @kumeinkosagalata8195 Год назад

    Ameen ameen tebrk wondme

  • @genetkalata9710
    @genetkalata9710 Год назад

    Egziaber tsegaw yechmreleh

  • @tsigetekalegne771
    @tsigetekalegne771 Год назад

    Amen eyesus kibera new

  • @naninani-bp7sn
    @naninani-bp7sn Год назад

    Haleluya Ke Eyesus wegen kiber lengusu

  • @samrawitamare2248
    @samrawitamare2248 Год назад +1

    Enate legna #berketoch nachu #lemelmulen

    • @mikoandsow2930
      @mikoandsow2930 Год назад

      אמן אמן תבורך אח שלי 🙌🙌

  • @genetkalata9710
    @genetkalata9710 Год назад

    Amen

  • @habyeab4210
    @habyeab4210 Год назад

    Oooo my God 💚👀✍

  • @BirtukanKebededemise
    @BirtukanKebededemise Год назад

    💖🕊🦅

  • @jakovmussie9505
    @jakovmussie9505 Год назад

    አሜን መመለስ ይሁንልን 🤭🤭🤭

  • @jakovmussie9505
    @jakovmussie9505 Год назад

    ❤️❤️❤️

  • @kokebetadesse6026
    @kokebetadesse6026 Год назад

    Geta tesgawin ybzalh..

  • @addiss5360
    @addiss5360 8 месяцев назад

    መዝሙረ ዳዊት 131
    2፤ ነፍሴን አሳረፍኋት፥
    የእናቱንም ጡት እንዳስተውት ዝም አሰኘኋት፤
    ነፍሴ የእናቱን ጡት እንዳስተውት በእኔ ውስጥ ናት።

  • @abramabram4828
    @abramabram4828 Год назад

    👍

  • @selamugenetu9253
    @selamugenetu9253 Год назад

    አምልኮ ይገባሀል፤ተገብቶሐል በክብር

  • @genetkalata9710
    @genetkalata9710 Год назад

    You Tube balnebrebet Zemen ke Ehtiopia CD eytlaklegn temhrteh eketatel neber tebarek

  • @yonasnegasa4493
    @yonasnegasa4493 Год назад +1

    Galata kee Waaqayyoo koo baroota keessatti nama dhugaaf hafuuraan si tajaajiluu qabdaa!!!!

  • @mandelaafework9213
    @mandelaafework9213 Год назад

    Amen

  • @jakovmussie9505
    @jakovmussie9505 Год назад

    ❤️❤️❤️

  • @abramabram4828
    @abramabram4828 Год назад

    Amen