የልጆቼን በርበሬ አዘጋጅቼ ጨርሻለው! ሙሉ የ በርበሬ አዘገጃጀት| how to prepare Ethiopian spice Berbere

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 31 янв 2025

Комментарии • 520

  • @ejigemoya
    @ejigemoya  2 года назад +167

    ለአንድ ፈረሱላ(17 ኪሎ)
    እርጥብ ቅመም
    ነጭ ሽንኩርት 5 ኪሎ
    ቀይ ሽንኩርት 2 ኪሎ
    ዝንጅብል 1.5 ኪሎ
    በሶብላ የ60 ብር
    ጤናዳም ከነ ፍሬው የ60ብር
    የጥብሰ ቅጠል የ20ብር
    ደረቅ ቅመም
    ኮረሪማ 2 ኪሎ
    ጥቁር አዝሙድ 0.5 ኪሎ
    ነጭ አዝሙድ 1 ኪሎ
    ኮሰረት 1 እፍኝ
    ጦስኘ 1 እፍኘ
    አብሽ 0.5 ኪሎ
    ጨው 1 ኪሎ
    ድንብላል 0.25 ኪሎ
    እኔ በዚህ መልኩ ነው የማዘጋጀው ።ጥያቄና አስተያየት ካላችሁ ፃፉልኝ።

    • @ማሚማሚ-ለ9ጐ
      @ማሚማሚ-ለ9ጐ 2 года назад +6

      እናመስግናለን ስለሺሮ እውቀተወንያጋሩን ቅመምችን

    • @learnamharicforfree4966
      @learnamharicforfree4966 2 года назад +8

      እናመሠግናለን ማሚየ
      የሽሮውንም እንጠብቃለን
      አድሜ እና ጤና ይስጥልን

    • @belayneshsisay3269
      @belayneshsisay3269 2 года назад +2

      Ejot brk yibel enate !!

    • @gulfmuna
      @gulfmuna 2 года назад +3

      በጣም አመሰግናለሁ አክብረዉ ግዜዎትን ወስደው ጥያቄዬን ስለመለሱልኝ አላህ ያክብርልኝ::

    • @bershger5662
      @bershger5662 2 года назад

      First of all Thankyou Ktfech bhuala atkaly kemeoch tchmerw ktfech bhala sint kg meta bgugut new mtbkew yhan mls lgil guday

  • @GAna-iw5ww
    @GAna-iw5ww 2 года назад +28

    እናቴ ከሞተች 6 ወሯ ስታዘጋጅ አግዛታለሁ ግን ልብ አልላቸውም ነበር፤ ሁሉንም በሷላይ ትተን ዛሬ እጅግዬ አንቺን ሳይ ትዝዝ አለችኝ እንዳንቺ ጠንቃቃናት ሁሏንም አጥባ ነው ምትሰራ ነበር፤ በጣም እናመሰግናለን እንዴት አዘጋጃለሁ እያልኩ ስጨነቅ ነበር

  • @mekitekle
    @mekitekle 2 года назад +7

    በጣም አሪፍ ነገር ነው እናመሠግናለን። ለ አንድ ፈረሱላ ምን ያህል ቅመማ ቅመሞች እንደሚያስፈልግ ቢገለጽልን በጣም አሪፍ ይሆናል።🙏🙏🙏👍👍👍

    • @zenebechreggassa6990
      @zenebechreggassa6990 2 года назад

      ሁሉ ነገር ጥሩ ነው ለም ን ባህር ቅመም አልተጨመረም?

  • @bettwascorner
    @bettwascorner 2 года назад +4

    እጅግዬ ሰላምሽ ይብዛልኝ ጥሩ አርገሽ ነው ያዘጋጀሽው የእኛ በርበሬ እኮ ስራው ብዛቱ እናመሰግናለን እጅሽ ይባረክልኝ👍👏👌ሼር❤🙏

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      በጣም አመሰግናለሁ

  • @ሉሉ-ኰ1ጠ
    @ሉሉ-ኰ1ጠ 2 года назад +6

    የማሽኑ ስም በተረፈ እጀወት ይባረክ ማዘር

  • @Hanna-xy8lg
    @Hanna-xy8lg 7 месяцев назад +9

    የእናቶቻችን እድሜ ያርዝምልን የሞቱትን ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያውልልን

  • @muna3074
    @muna3074 2 года назад +2

    እትዬ እጅግ እጆት ይባረክ ረዝም እድሜ ከጤና ጋር ይስጦት ጉልበቷት ይባረክ ሳይሰስቱ ሞያዎትን ስለሚያጋሩን እናመሰግናለን አሑንም የልቦትን መሻት ይስጦት የኛ እናት ኑሩልን አሜን

  • @almazmengistu8400
    @almazmengistu8400 2 года назад +9

    እድሜና ጤና ልእናቶቻን ልእህቶቻችን ይስጥልን;; ለኛ ደፋ ቀና ብላችሁ አዘጋጅታችሁ ትልኩልናላሁ ኑሩልን ስለሁሉም ነገር እናመሰግናለን!

  • @etm4603
    @etm4603 2 года назад +21

    😍🥰😘🙏ረጅም እድሜና ጤናውን አብዝቶ ይስጥልን አኡፍፍ እናቶች ኮ መድሃኒት ኮ ናችሁ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад +1

      በጣም እናመሰግናለን

  • @melatTUBE
    @melatTUBE 2 года назад +45

    እውይይይ ስራ ግን ብዛቱ ።በጣም እናመሰግንሻለን እናታችን

    • @etm4603
      @etm4603 2 года назад +3

      Melu I’m in love with mom. I wish if she can be my moms friend 😌

    • @intisarfarah42
      @intisarfarah42 2 года назад +1

      Meluye menaw tafashe yene konjo

    • @melatTUBE
      @melatTUBE 2 года назад

      @@etm4603 weyee yen konjo enem dese yelgnal

    • @melatTUBE
      @melatTUBE 2 года назад +2

      @@intisarfarah42 alew yen konjo telek project yezie new

    • @liyutube6580
      @liyutube6580 2 года назад

      wude demrign emelisalehu pls

  • @lulumohamed1536
    @lulumohamed1536 2 года назад +1

    እጅሽ ይባረክ የሜላት ማም
    የኔ ባለሙያ
    መፍጫሽ ግን የት እንደማገኘው ንግሪኝ ስወድሽ

  • @zulfamohammed207
    @zulfamohammed207 2 года назад

    ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጦት በስደት ተቀምጠን ሞያ ለጠፋብን ብዙ ሞያ እያስተማሩን ነው አመሰግናለሁ ካላስቸገርኩ የመፍጫው ስም ቢያስቀምጡልኝ ምርጧ እናታችን

  • @tsiontsion3938
    @tsiontsion3938 2 года назад +2

    ተግስቶት በስመአም እግዚአብሄር እድሜ ከጤና ይስጦት ። ትክክለኛ እናት ኖት❤❤

  • @marthamog715
    @marthamog715 2 года назад

    እንዴት አንደምወድሽ ልጅሽንም በጣም ነው የምወዳት አንቼ መልካም እናት ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባር ያለው አስተዳደግ እና ባለ ሞያ አድርገሽ ነው ያሳደግሻቸው ልጆችሽን ያሳደግሽው በዜህ ልትመሰገኜ ይገባሻል ሞያሽን እያካፈልሽን ስለሆነም እጅግ በጣም እናመሰግናለን አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ መደለዣሽን የት ገዛሽው እባክሽ ከማውቀው ለየት ያለ ነው ቀላልም ይመስላል ስለሁሉ አለሰግናለሁ በርቼ እግዚአብሔር። ይባርክሽ እድሜና ጤና ይስጣችሁ ከነመላ ቤተሰብሽ

  • @yanitgirma
    @yanitgirma 2 года назад +2

    እናትአለምዬ እኛም እንወድዎታለን በጣም ደስ ይላል እጅዎት ይባረክ እድሜና ጤና ይስጥዎት ❤🙏

  • @Alemtsehay777
    @Alemtsehay777 2 месяца назад +1

    ዋዉ መፍጫዉ አሪፍ ነዉ። ጉልበት ቆጣቢ ነዉ እጆት ይባረክ ማሚ

  • @habtushumoy3875
    @habtushumoy3875 19 дней назад

    This is fantastic video! I like the concept of washing everything!! Some questions: 1) how can i send you private message?
    2) medelez weyim ertibun bekesha afino maskemetu lemin yitekmal? Makatelu yikenisewal way, kehone betam arif

  • @grmaneshgidey945
    @grmaneshgidey945 Год назад

    ቆንጆ ነዉ በጣም ማዘዝ ይቻላል?

  • @HayatHassen-ue7sg
    @HayatHassen-ue7sg 3 месяца назад

    ሁሉም ስራዎችሽ በጣም ነው ምወደው እናመሰግናለን ብዙ ተምሪያለሁ በርቺ

  • @ማሚማሚ-ለ9ጐ
    @ማሚማሚ-ለ9ጐ 2 года назад +2

    እናመስግናለን እዲሜና ጤና ይስጠወት ደረቅ ቅመም ስላሳዩን

  • @saragirma5196
    @saragirma5196 2 года назад +4

    በጣም ምርጥ ነው እግዚአብሔር ይስጥልኝ❤❤❤❤❤❤

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      አመሰግናለሁ

  • @ተስፉነኝየክርስቶስልጅኢየ

    የኔ እናት ጌታ አምላክ ጤናና እድሜ ይስጥሽ ❤❤❤😘😘😘በጣም ዉድድድድ😘

  • @fakiisaa6496
    @fakiisaa6496 2 года назад

    በጣም ጥሩ ይመስላል ከየት ነው ያገኘሽው መፍጪይውን?

  • @eimaneiman8850
    @eimaneiman8850 Год назад

    በጣምጎበዝባለሙያነሽ እኔኳ አዘጋጅቸአላውቅም በርበሪምሽሮም ያለሁት ስደትነው ሀገር ስገባ አሁን በደብ ሙያልልመድና እሞክረዋለሁ ገናመጀመሪያየ ውነት ሀሳብይሆነኝነበር ቀላልነው እደማየውከሆነ. እሲደሞ የሹሮ አዘጋጃጀት አሳይን ለመረጃሽከልብ አመሰግናለሁ

  • @hayathmuhammad864
    @hayathmuhammad864 Месяц назад

    የኔ እናት ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ግን እኔ ውጪ ሀገር ነው አገር ልገባ ገንዘብ ብልክልሽ እንደዚህ ማዘጋጀት ትችያለሽ ይመችሻል ❤

  • @jiromyohahannes5021
    @jiromyohahannes5021 2 года назад

    Yeni e biruk ihit tebareki gin timiz , camon ina 7 kimem kundo berber kirunfidina kerefa malet ye mekelesha kimemoch anasgebam wey? Tebarekilign

  • @bereketdebeleT87
    @bereketdebeleT87 16 дней назад

    Wow ejish yebarek

  • @beautifuloromiya4288
    @beautifuloromiya4288 2 года назад +3

    ማዘርዬ ስራው ግን በጣም አድካሚ ነው እድሜና ጤና ይስጦት እንግዲህ ሜሊ እንድታስቀምሽኝ ድካሙ በጣም ብዙ ስለሆነ ሜሊ ወጥ ስትሰሪ በርበሬ እንዳታበዥ😆

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      አዎ። በጣም አመሰግናለሁ

    • @EndrisYimam-e5c
      @EndrisYimam-e5c 2 месяца назад

      ማዘርየ እጀወ ይባርክ መፍጫው የትነውሚገኝ

  • @ሰኒሰኒ-ጀ4ረ
    @ሰኒሰኒ-ጀ4ረ 2 года назад +3

    ማምዬ በጣም እናመሰግናለን ያምራል እንዳለው የማሽኑን ዋጋና ኬት እንደሚገኝ ብትነግሪኝ ልግዛ????

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      ማሽኑን የገዛሁት ከሰው ላይ ነው ግን ተመሳሳይ ፈልጌ አድራሻ አስቀምጣለሁ በቅርቡ

  • @BhCus-i3p
    @BhCus-i3p 11 месяцев назад +1

    እጅሽ ይባረክ እናቴ

  • @lovehelinarecipe9932
    @lovehelinarecipe9932 2 года назад +2

    አቤት ሙያ መፍጫሽ ደሞ ገላግሌ ነው እጅሽ ይባረክ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      አሜን እውነት በጣም እንጂ

  • @ዘይነብትዩብ
    @ዘይነብትዩብ 2 года назад +2

    ማዘርየ እጂሽ ይባረክ ቆንጆ አዘገጃጀት ነዉ እስከመጨረሻዉ በጉጉት ነዉ ያየሁት

  • @be8cab
    @be8cab 2 года назад +10

    ጥቁር አዝሙድ አጥቤ ሳሰጣ ያየች ልጅ ልክ ሙያ እንደሌለን የቆጠረችኝን አልረሳውም ይህው ግን ምን ያህል ቆሻሻ እንዳለው አየን ። ማዘርዬ ኑሪልን

  • @senayetzeethiopiatube8632
    @senayetzeethiopiatube8632 2 года назад +3

    ዋው ዋውእናታችን በጣም ነው የሚያምር እጅሽ ይባረክ በእውነት ፅድት ያለ አዘገጃጀት ነው ግን ማሚዬ የኤሌክትሪክ እቃወችሽን የት እንደሚገኙ በዛው ብትነግሪን አዳዲስ እቃዎችን ነው የማየው ካንችጋ በተረፈ ሱሴ ነሽ ማሚዬ በጉጉት ነው የምጠብቅሽ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад +3

      አመሰግናለሁ በጣም። የብዙዎች ጥያቄ ስለሆነ አንድላይ እመልሳለሁ

  • @ኢቲዮጲያየሰላምሽይብዛልኝ

    እናመሰግናለን እናታችን

  • @emugedefe2860
    @emugedefe2860 2 года назад +4

    እድሜና ጤናን አብዝቶ ይስጥልን እናታችን

  • @adiamgebre8039
    @adiamgebre8039 2 года назад +11

    የ ሚሉዬ እናት በጣም በጣም እናመሰግናለን። በጣም አስተማሪ ነው ከቻሉ ኮሜንት ላይ ዝርዝሩን ቢፅፉልን ደስ ይለኛል , ለ አንድ ፈረሱላ ምን ምን እደተጠቀሙ እና ምን ያህል እንደሚያስፈልግ።❤❤❤

    • @nejatumuayub6232
      @nejatumuayub6232 2 года назад +7

      እንደበርበሬው ብዛት ነው ቅመሞቹን እምትጠቀሚው
      ከእርጥብ ቅመሞች ስንነሳ
      ነጭ ሽንኩርት
      ዝንጅብል
      በሶ ቢላ
      ጤና አዳም
      ቀይ ሽንኩርት
      የስጋ መጥበሻ ቅጠል ሮዝመሪ ናቸው በነዚህ እርጥብ ቅመሞች በርበሬውን ከደለዝሽ በኋላ ለሶስት ቀን ሽፍን አድርገሽ ታቆይውና ከሶስት ቀናት በኋላ ታደርቂዋለሽ
      በርበሬ ከደረቀ በኋላ ወደ ደረቅ ቅመሞች ስንመጣ እሚያስፈልጉን ግዕባቶች
      ገውዝ የፈረንጅ ኮረሪማ
      ስናፍጭ
      ጎመን ዘር
      ተንገርግቦ ደርቆ የተቆላ አብሽ
      ነጭ አዝሙድ
      ጥቁር አዝሙድ
      ጦስኝ
      ደረቅ በሶቢላ
      የድንብላል ፍሬ
      ኮረሪማ
      ጨው
      ኮሰረት ናቸው
      እኔ ግን በግሌ
      ቀረፋ
      ቅርንፉድ
      ጥምዝ
      ቁንዶ በርበሬ
      ሄል
      እጨምርበታለሁ
      በውጪው ዓለም ስለምኖር በርበሬው እንደ ሃገራችን በርበሬ የማቃጠል ጣዕም ስለሌለው የሚያቃጥለውን ቃሪያ ወይንም ከሳምስ ክለብ ሱፐር ማርኬት ውስጥ የሚሸጥ ትንሽ የማቃጠል ጣዕም ያለው የተሸከሸከ በርበሬ አለ እሱንም እጨርበታለሁ ያው አንድ አማራጭ ነው እምጠቀመው ከሁለት አንዱን ወይ ቃሪያውን ቃሪያው ከሌለኝ ደግሞ የተወቀጠውን በርበሬ አንድ ላይ ከበርበሬው ጋር አድርጌ ነው እምደልዘው በኢትዮጵያ 🇪🇹 ለምትኖሩ ኢትያኖች ግን ሌላ እሚያቃጥል ቃሪ መጨመር አይጠበቅባችሁም
      እንግዲህ የፃፍኩላችሁ ግዕባቶች ለሁላችሁም ይጠቅማችዃል ብዬ አስባለሁ ደህና ሁኑ

    • @adiamgebre8039
      @adiamgebre8039 2 года назад +1

      @@nejatumuayub6232 አመሰግናለሁ !!

    • @adiamgebre8039
      @adiamgebre8039 2 года назад +1

      @@nejatumuayub6232 ምጥን ሽሮስ ለማዘጋጀት እርጥብ እና ደረቅ ቅመሞች ዝርዝሩን ብትልኪልኝ ደስ ይለኛል

    • @nejatumuayub6232
      @nejatumuayub6232 2 года назад +4

      @@adiamgebre8039 ምጥን ሽሮ ለማዘጋጀት እሚያስፈልጉን እርጥብ ቅመሞች
      ነጭ ሽንኩርት
      ቀይ ሽንኩርት
      ዝንጅብል
      ታጥቦ የተዘፈዘፈ አብሽ በጣም በትንሹ ሳይበዛ
      በሶቢላ
      ጤናዳም
      ጦስኝ
      የተወቀጠ በርበሬ ያስፈልጋል
      ልክ በርበሬ እንደምንደልዘው መጀመሪያ ቅመሞቹን ካደቀቅሽ በዃላ
      ለቅመሽ ቆልተሽ አጥበሽ ያደረቅሺውን የሽሮ እህል ከእርጥብ ቅመሞቹ ጋር አብረሽ መደለዝ ነው ማሽን ካለሽ በማሽኑ ታዋኽጂዋለሽ በሙቀጫ ከሆነ እምትጠቀሚው ቀስ ብለሽ ነው ሸክሸክ ሸክሸክ እምታደርጊው እኔ ግን በሽንኩርት መፍጫ ማሽን ነው እምጠቀመው ለበርበሬም ለሽሮም
      ሽሮውን ከእርጥብ ቅመሞቹ ጋር ከደለዝሺው በዃላ ክዳን ባለው ኮንቴነር ክድን ሽፍን አድርገሽ ለሶስት ቀናት ታቆይውና ከሶስት ቀናት በኋላ ታደርቂዋለሽ የሽሮው እህል ከደረቀ በኋላ ወደ ደረቅ ቅመሞች ስንመጣ
      ደረቅ በሶባላ
      ደረቅ ጤናዳም
      ደረቅ ቀይ ሽንኩርት
      የተቆላ አብሽ
      ደረቅ የስጋ መጥበሻ (ሮዝመሪ)
      ደረቅ ጦስኝ
      ኮረሪማ በትንሹ
      ጨው
      ጥምዝ በትንሹ
      ድንብላል
      ነጭ አዝሙድ
      ጥቁር አዝሙድ
      ቁንዶ በርበሬ በትንሹ
      እነዚህን ቅመሞች ነው እኔ እምጠቀመው የሁሉም ሰው ሙያው ይለያያል ቀረፋ የሚጨምሩ ሰዎች አሉ እኔ ግን አልጨምርም ከኔም ሙያ በበለጠ እዚሁ ዩቱብ ላይ ገብተሽ የምጥኝ ሽሮ አዘገጃጀት ብለሽ ሰርች አድርጊና ማየት ትችያለሽ መልካም ጊዜ ይሁንልሽ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      እሺ

  • @jembia7857
    @jembia7857 2 года назад

    It’s nice. How much berebere medelezaw? Yetnew yemigezawg mother?

  • @selamhailu1990
    @selamhailu1990 Год назад +1

    WOW እጅግ በጣም ባለሙያ

  • @nejatumuayub6232
    @nejatumuayub6232 2 года назад +1

    እሰይ የኔ ባለሙያ 😍❤️ እናት በጣም ነው እምወድሽ ❤️ ደስ ትይኛለሽ እጅሽ ይባረክ እንዲህ ነው እንጂ ሙያ ምርጥ የበርበሬ አዘገጃጀት እኔም ልክ እንዳችው አድርጌ ነው እማዘጋጀው ከገበያ አልገዛም

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      በጣም አመሰግናለሁ

  • @genetdebele7702
    @genetdebele7702 2 года назад +4

    መቼም መፍጫሽ ከድካም በጣም ይረዳል
    መውቀጥ ያደክማል በርቺ ጎበዝ እናት ልጅሽም
    ሜላትዬ ባለሙያ ነች እናመሰግናለን::

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      በጣም አመሰግናለሁ

  • @mominaahmed1784
    @mominaahmed1784 2 года назад

    Mashaallah tena yaderegelachu mefechawan le enati megezate felegi nebere betam enamesegnalen 👍👍👍👍

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      ማሽኑን የገዛሁት ከሰው ላይ ነው ግን ተመሳሳይ ፈልጌ አድራሻ አስቀምጣለሁ በቅርቡ

    • @mominaahmed1784
      @mominaahmed1784 2 года назад

      @@ejigemoya eshe amesegenalewu

  • @yidubeyene6994
    @yidubeyene6994 2 года назад +2

    Gobez enat enameseginalen!!!!

  • @tezetaafework5479
    @tezetaafework5479 2 года назад

    ተባረክልን እናመሰግናለን ወደአሜሪካ ብትልኪ ልንኣርደር እናረጋለን ስልክሽን አስቀምጭልን ፌላጋቱካለሽ

  • @selamealemu6688
    @selamealemu6688 2 года назад

    እናመሠግናለን ማዘር ማሽኗን ከየት አገኝዋት

  • @sosojed416
    @sosojed416 2 года назад +4

    እጅዎት ይባረክ ኑሩልን የጤና ምግብ ያድርግልዎት

  • @zahraasiri8953
    @zahraasiri8953 2 года назад

    ጤናሽን ይስጥሽ ማማዬ ውይ ግን ማሽኑ በጣም ያግዛል ።

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      አመሰግናለሁ

  • @ninjago9518
    @ninjago9518 2 года назад +1

    እግዚአብሔር ይስጥልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን እናታችን እንደእርሶ አይነት ደግ ደግ የመጨረሻ ደግ እናት አያሳጣን አሁንም በድጋሚ እድሜ ከጤና አብዝቶ ይስጥልን እግዚአብሔር ልጆቾን ይባርክልን አሜን🙏🙏🙏❤❤❤

  • @getachewselassie7137
    @getachewselassie7137 2 года назад +1

    ጎበዝ፡ባለሙያ፡ኖት። እግዚአብሔር፡ይባርኮት። ባህላችንን፡በተቀናጀና፡በአማረ፡መልኩ፡በማቅረቦ፡ኢትዮጵያ፡ትኮራበታለች።

  • @abeeraldrany9487
    @abeeraldrany9487 2 года назад +1

    እግዚአብሔር ይሰጥልን እድሜና ጤና ይሰጥለን እናቲየ

  • @גנטלמה
    @גנטלמה 2 года назад

    Gobez enat neshe
    Lek endzh new Enata yemtazegagew
    Yeswan berbera lemga yelal aitafetgnm
    Egeshe yebarek

  • @aberashdebela8327
    @aberashdebela8327 2 года назад

    ትክክለኛ በርቤሬ ማለት ነው ከባልትና የምገዛው ቤርበሬ ሰውን በሽተኛ አደረገው ምን ጨምረው እደምያስፈጩ አይታወቅም የእርሶ በርቤር ወደ አክቤት መሄድ አያስፈልግም ከመዳኃንት በላይ ነው ሁሉንም አጥበው ለቅሞውህ ዋው ሺህ አመት እድሜ ተመኝሁሎት እድለኛ ናቸው የእርሶ ልጆች

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      እውነት ነው በጣም አመሰግናለሁ

  • @Tube-im6us
    @Tube-im6us 2 года назад

    ማሻአሏህ በጣም ጎበዚነሺ እኔ ማሺኑን እፈልጋለሁ የትነውየሚገኘው እባክሺ የትእዴሚገኘ መልሺልኙ

  • @BamlakAsres
    @BamlakAsres 4 месяца назад +4

    እናመሰግናለን ለ5 ኪሎ በርበሬ ለመደለዝ ምን ያህል ቅመም ያስፈልጋል?? ላዘጋጅ ነዉ

  • @lemlembeleteyoutube
    @lemlembeleteyoutube Год назад

    ዋዉዉዉዉ በጣም ምርጥነዉ❤💛💚❤💛💚

  • @merontesfaye152
    @merontesfaye152 2 года назад +1

    ዎው በጣም ጥሩ ሙያ ነው ያክፍሎን ዕድሜ ከጤና ጋር ይሰጠልን እናመሰግናለን ሺር ላይክ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      አመሰግናለሁ

    • @akiserikitchen6290
      @akiserikitchen6290 2 года назад

      በጣም በጣም ትህትና ያለሽ አናት ሁሌ ነው ይምከታተልሽ ከጀመርሽ ጀምሬ ለካ ለዛ ናትሚላት ድምጽዋ ደስ ይምል አድሜና ጤና ይስጥልኝ መቆጫው ግን ከየት አደገዙት ቢነግርን ደስ የለኝ ነበር ❤🇪🇷

  • @aqoonqaate8109
    @aqoonqaate8109 2 года назад +1

    im from Somalia and i love this ❤😂

  • @ethiopia9573
    @ethiopia9573 2 года назад +1

    እጅሽ ይባረክ ። መፍጫው ከየት ይገኛል? የብዙ ሰው ጥያቄ ነው።

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад +1

      ማሽኑን የገዛሁት ከሰው ላይ ነው ግን ተመሳሳይ ፈልጌ አድራሻ አስቀምጣለሁ በቅርቡ

  • @hayatseid6279
    @hayatseid6279 2 года назад

    ባለሙያ ነሽ ማሻአላህ ጠንክሪ😍😍😍😍

  • @kidistmogesie3702
    @kidistmogesie3702 2 года назад

    አመሰግናለሁ እድሜሽን ያርዝምልኝ።

  • @nebaitmana528
    @nebaitmana528 2 года назад

    Wow you are very clean and took you time.

  • @gitigiti4447
    @gitigiti4447 Год назад

    Thank you so much. God Bless you more. Very helpful!

  • @dinabereket8561
    @dinabereket8561 2 года назад

    Egesh yebarek ema edemena tena yestesh mefechawen keyet newe tsafelene

  • @abebechmekebib3710
    @abebechmekebib3710 2 года назад +3

    ስለመጣፈጡ ጥርጥር የለውም። ሙያ ብሎ ዝም 😚 😍

  • @aynalemtigashaw3442
    @aynalemtigashaw3442 Год назад

    መፍጫው ማሽን በጣም አሪፍ ነው ስንት ይገኛል?

  • @kemeriakela-xs7um
    @kemeriakela-xs7um Год назад

    ዎው በጣም ጎባዝ ነሽ 🥰🥰🙏🙏ስንት ኪሎ ነው በርበሬ እና ቂመማ ቂማሞች?

  • @tesfayemarimadlen4506
    @tesfayemarimadlen4506 2 года назад

    Betame Gobez, we de wech melake yechalal wey???🙏🏻💐❤️👏

  • @cucinaitalianaa
    @cucinaitalianaa 2 года назад

    ስራው በጣም ብዙነው እናቶቻችን እግዚአብሔር ያኑርልንንን 🙏 ይይጠብቅልንንን 🙏🙏🙏

  • @TransformYourMind8860
    @TransformYourMind8860 2 года назад +1

    blessed mother tanks

  • @tgtgste5403
    @tgtgste5403 2 года назад

    Enatachin fetari yibarkot andi tiyake aleng mashinun yet new yegezut medelezha betam techegiralew ebakot mashinun yet new yegezut

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      Yene kewsew lay new gn megenagn marathon building yenoral

  • @zebebalalemeda9675
    @zebebalalemeda9675 2 года назад

    Betam enamsegnalen bezu yemnawkewen neger temrenal bertulen 👍🏻👍🏻👍🏻👍🏻👍🏻😍😍😍😍😍

  • @devoramellesse2326
    @devoramellesse2326 10 месяцев назад

    ወይዘሮ እጅጌ በጣም አድናቂሽ ነኝ ። ሲበዛ ባለሙያ ነሽ። እኔ የምኖረው እስራኤል ሀገር ነው እና አንዳንድ የባልትና ውጤቶችሽን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

  • @fatum1999
    @fatum1999 2 года назад +1

    አይኔ ላየው ደከመኝ እረ ጉድ ኢትዩጱያ ሂጀ የምኖረው እደት ነው እድህ እያደረኩ ሆ ብቻ እጂሽ ይባረክ

  • @BamlakAsres
    @BamlakAsres 4 месяца назад

    እናመሰግናለን ግን ለ1ኪሎ ምን ያህልቅመም እንደሚያስፈልግ ፃፊልን

  • @misteregebeyehu8064
    @misteregebeyehu8064 2 года назад

    Betam enamesegenalen Ejige muyashen selakafeleshen tebarekilene😘🙏

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      Enem betam amesegnalew

  • @اللهمارحمني-ص6ض
    @اللهمارحمني-ص6ض 2 года назад +1

    ዋዉ ሲያምር 👍👍👍😍

  • @mekiyayoutube5974
    @mekiyayoutube5974 2 года назад

    ማሻአላህ እጅሽ ይባረክ የኔ እናት እመሰግናለን

  • @bcbc8854
    @bcbc8854 Год назад +1

    እናትዬ አድ ጥያቄ አለኝ ቁዶ በርበሬ ጥምዝ ኩሞን አይደረግም በርበሬላይ????????

  • @aminaseidfrom3725
    @aminaseidfrom3725 2 года назад +7

    ረጅም እድሜና ጤና ይስጥሽ እጅግዬ ይሄን መሽን ግን ለእህቴ መግዘት ፈለኩ ኢትዮ ውስጥ ይኖር ይሁን

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад +2

      ማሽኑን የገዛሁት ከሰው ላይ ነው ግን ተመሳሳይ ፈልጌ አድራሻ አስቀምጣለሁ በቅርቡ

    • @aminaseidfrom3725
      @aminaseidfrom3725 2 года назад

      @@ejigemoya እሺ እጅግዬ❤🙏

  • @desalechkuma-vm8rm
    @desalechkuma-vm8rm 5 месяцев назад

    Mami Ejish yibarek 🥰🥰🙏

  • @tewabechbale4784
    @tewabechbale4784 Год назад

    አመሰግናለሁ ማምዬ እጆት ይባረክ

  • @emugedefe2860
    @emugedefe2860 2 года назад +7

    የበርበሬ መደለዣዋን ማሽን የት እንደገዟት ቢነግሩን እማየ እናመሰግናለን

    • @yashidata7934
      @yashidata7934 2 года назад

      የኔም ጥያቄ ነዉ የት እንደገዙ ንገሮን ተባበሮን

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад +4

      ማሽኑን የገዛሁት ከሰው ላይ ነው ግን ተመሳሳይ ፈልጌ አድራሻ አስቀምጣለሁ በቅርቡ

  • @adona21adona16
    @adona21adona16 2 года назад +1

    እጅግዬ እናቴ ሰላምሽ ይብዛልኝ ዋው ዛሬ ዝግጅት ነው በጣም ደስ የሚል አዘገጃጀት ነው የበርበሬው ቅላት በጣም ደስ ይላል

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      አመሰግናለሁ በጣም

    • @liyutube6580
      @liyutube6580 2 года назад

      wude demrign emelisalehu pls

  • @mesaylala8285
    @mesaylala8285 2 года назад

    ደሰ ይላል ቀጥይበት መፈጫሸ የት ይገኛል

  • @ferehiwotmekonnen7908
    @ferehiwotmekonnen7908 2 года назад +1

    እጅግየ ደሕና ነወት የአሜሪካ ሕይወት እንዴት ነው መቸም ዘግይቼም ብጠይቅዎትም መልስ እንደሚሠጡኝ ተስፋ በማደረግ ነው እና እባክዋ የደለዙበትን ማሽን የት ገዙት አመሠግናለሁ ተባረኩ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      ከሰው ላይ ነው የተገዛው ግን መገናኛ አከባቢ አለ

  • @mekiyamohammed2785
    @mekiyamohammed2785 2 года назад

    መፍጫውን አሳይን እኔም መግዛት እፈልጋለሁ የሚገኝበትንም ንገሪኝ የኔ ቆንጆ እጅሽ ይባረክ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      ከሰው ነው የገዛሁት ግን እፈልጋለሁ እስቲ

    • @mekiyamohammed2785
      @mekiyamohammed2785 2 года назад

      @@ejigemoya እሺ ያው ጠይቀሽ መልስ እዴም ሰጭኝ አምንብሻለሁ ወሎ በጣም አስቼጋሪ ነው በሙቀጫ አልተቻለም

  • @ልጂደሞዝ
    @ልጂደሞዝ 2 года назад +2

    የኔ እናት የኔ ባለሙያ ፈጣሪ ሠላምሽ ይብዛወ እናት ፈጣሪ ለልጆችሽ እድሜ ልክ ያኑርሽ ምኞቴ ነው እማ 🌷🌷🌷🌷🌷🙏🙏🙏🙏💔💔🥰

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      አሜን በጣም አመሰግናለሁ

  • @marthatady8192
    @marthatady8192 2 года назад

    Shalom mother God be with you all. Mother Please Please can you tell me where do you buy the mixer?? Please I will wait your answer. More blessing upon you all.

  • @genetlhenaff8511
    @genetlhenaff8511 2 года назад +1

    Betame bekonjo newe yemetazegajiw !!!
    Bewesete mesemer manegare yechalale?

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      Yechalal you can contact me on Instagram at እጅግ ሞያ

  • @addishiwottaklu6841
    @addishiwottaklu6841 2 года назад +1

    እናመሰግናለን ማሚ

  • @አነስ
    @አነስ 2 месяца назад

    በጣም እናመሰግናለን

  • @selamtsegay-r6v
    @selamtsegay-r6v Год назад

    ehtye enamesegnaln gin
    komun anasgebam weys ayasfelgm malet new

  • @abzx8743
    @abzx8743 2 года назад

    ውይ የኔ እናት በቅድምያ እጅሁ ይባረክ በመቀጠል አንድ ጥያቄ አለኝ ለ50ኪሎ በርበሬ ለማዘጋጀት ምን ያህል ቅመማቅሞች ያስፈልጋል ሰለቀና መልሶ አመግናለሁ

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      ለ1 ፈረሱላ ማለትም ለ 17 ኪሎ ያስቀመትኩት አለ ከላይ እሱን በ3 ማብዛት ነው

  • @markoriosadafre673
    @markoriosadafre673 Год назад

    Excellent job. This is what call Ballemoya !!

  • @ellenihagos1944
    @ellenihagos1944 2 года назад

    bemejemeria fetary ejochshn ybark bemeketel yene enat yhen aynet medeleza yet ygegnal.

  • @alipppalippp8628
    @alipppalippp8628 8 месяцев назад

    እናመሰግናለን ሀቢብቲ ግን ስንት ኪሎ ነው በርበሬው

  • @jesusislord6649
    @jesusislord6649 2 года назад

    እናመሰግናለን!!
    የምጥን ሽሮ አዘገጃጀት ብታሳይን ?

    • @ejigemoya
      @ejigemoya  2 года назад

      ruclips.net/video/XZMSTOfrp-Y/видео.html እዚ ላይ አለ

  • @mememe1367
    @mememe1367 2 года назад +1

    እናታችን ምፍጫውን የት እናገኘዋለ አገር ውስጥ አለ ቢያሳውቁን።

  • @Tube-nv4el
    @Tube-nv4el 8 месяцев назад

    አሪፍ ነው መፍጨዋ የት ነው እምትገኘው????

  • @mafifikadu1074
    @mafifikadu1074 4 месяца назад

    አጆት ይባረክ m🙏🙏🙏🙏🙏🥰