ዝነጣው ቀረ ልብሴ አልቆ መሳቀቅ ጀመርኩ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 28 дек 2024
  • This is the story of a woman who has been marginalized.
    In this story, we see her struggle to change her life, the challenges she faced and the success she finally achieved.
    We respectfully invite you to follow it because it is a very interesting and educational story.
    SUBSCRIBE NOW = / @nequheyewet5076
    Telegram ፦ t.me/anqiandeb... , t.me/nequheyewet
    TikTok ፦ www.tiktok.com...
    Facebook ፦ / anqipage
    #anqiandebetoch #life #motivation #motivationalspeech #ethiopianmotivation #training #lifetraining #personaldevelopment #inspiration #inspirationalquotes #success #successmotivation #mindset #positivevibes

Комментарии • 2,3 тыс.

  • @መዲነኝወሎየዋ-ረ1ዀ
    @መዲነኝወሎየዋ-ረ1ዀ Месяц назад +2242

    አንድ ነገር ልንገርሽ እባክሽ ሁል ጊዜም እየመጣሽ አዉሪ 😂❤❤ እንደት እንደምታምሪ ኮንፊደንስሽ + አነጋገርሽ የከለርሽ ዉበት ማሻ አላህ

    • @halimaali4383
      @halimaali4383 Месяц назад +15

      awo

    • @zewdneshzegeye9259
      @zewdneshzegeye9259 Месяц назад +24

      እውነትሽን ነው የኔ ቆንጆ

    • @friayemaryam
      @friayemaryam Месяц назад +1

      😂😂😂😂😂😂

    • @ዙፋንtube
      @ዙፋንtube Месяц назад +6

      ኣዎ እኔም እንድትመጣ እፈልጋለው😂

    • @FafiMohammdOmer
      @FafiMohammdOmer Месяц назад +8

      ለተቀማጭ ሰማይ ቅርብ ነው😂😂😂😂😂😂

  • @BisratGurmamo-ru8dl
    @BisratGurmamo-ru8dl Месяц назад +807

    ት/ ቤት ከስተማረው ሰው ይልቅ ሕወት ያስተማረው ሰው ይበልጣል

  • @MayoshaTa
    @MayoshaTa Месяц назад +437

    እየሳቅኩ ÷እያለቀስኩ ÷ፈገግ እያልኩ÷ በተስፋ ወደፊት ÷በትካዜ ወደኋላ እያልኩ የሰማሁት ምርጥ ታሪክ ❤❤❤❤ጌታ ስሙ ለዘለአለም ይክበር❤❤❤❤

    • @KmUr-xy7ur
      @KmUr-xy7ur Месяц назад

      Amen hale luya yetaredew beg lezelalem ybarek

    • @SamreaMama
      @SamreaMama 29 дней назад +1

      ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @ferdosenuraden
    @ferdosenuraden 29 дней назад +197

    ከዚ ታሪክ የሠው ከሃዲነት እና የአላህ ደጋፊነት በደምብ አይቼበታለው ጥንካሬሽ ግን ለማመን ይከብዳ😢😢 ጀግና ነሽ❤❤❤

    • @LaJs-o9d
      @LaJs-o9d 24 дня назад +1

      በጣም አላህኮ ወላሂ ለኛ ከሁሉሙ ይበልጣል

  • @Tsion952
    @Tsion952 Месяц назад +330

    እንዲ በትእግስት የሰዉ ታሪክ ሰምቼ አላውቅም የማትሰለች ብርቱ እና ለዛ ያላት ሴት

  • @JA_Mikael
    @JA_Mikael Месяц назад +409

    "ለካ ፊቱን ከልክሎኝ አያውቅም፣ እጁንም ጨመረለኝ..." ደስ የሚል አገላለጽ! እምነትሽ ያስቀናል! ቀልድሽ፣ ለዛሽ፣ ሳቅሽ፣ አይንሽ ...በጣም ቆንጆ ነሽ!

    • @MayoshaTa
      @MayoshaTa Месяц назад +7

      በጣም ደስ የሚል አነጋገር ❤❤❤❤❤

    • @peacelove4778
      @peacelove4778 Месяц назад +4

      @@JA_Mikael ይሔ ንግግራ ለኔም ነው አሪፍ አባባል ነው

    • @tigestwoldetsadik4316
      @tigestwoldetsadik4316 Месяц назад +1

      እኔም ተደነቅሁ

    • @Zara90-ew8tw
      @Zara90-ew8tw Месяц назад +1

      ሀበሻ ኡፍፍ ቅናት ሰውሲቀየር አይ ውድ ምትሀት መተት ኡፍፍ ለዚህም ነው እርሱም መሪየታዘዘብን

    • @EthioKenya-vx5bo
      @EthioKenya-vx5bo Месяц назад

      እውነት ነው❤

  • @MasrtiMasrtigeto
    @MasrtiMasrtigeto Месяц назад +1456

    የዝች ልጅ ታሪክ የመጀመሪያዉን ጨርሸዋለሁታሪኳ የተመቸዉ ላዪክጋዪስ

  • @TebestAelaf
    @TebestAelaf Месяц назад +128

    ንግግርሽ ፅድት ያለ የሚያዝናና ቁምነገር አዘል ነው ጠንካራ ኩርት ያልሽ ደሞ ቆንጆ ነሽ 🥰🥰🥰🥰🥰💪💪💪💪💪

  • @danieltekalegn7285
    @danieltekalegn7285 21 день назад +22

    እውነትም መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ህይወት መለወጥ የሚችል ብቸኛ የአእግዚአብሔር ቃል ነው።

  • @mariberihu6562
    @mariberihu6562 Месяц назад +16

    ለመጀመራ ግዜ ውሸት የሌለው እውነተኛ ታሪክ ሰሰማ በጣም ነው ተምስጨ የሰማሁት በጣም ጎቦዝ

  • @mamehika6943
    @mamehika6943 Месяц назад +178

    ንግግርሽ ስብራትን ያክማል፤ ተስፋን ያለመልማል። አገላለጽሽ ደግሞ ሌላ ብቃት! ይጣፍጣል። ከማንም ከንፈር መጣጭ እና አያድን-አይገድል መጽዋች ይልቅ ያንች የአይበገሬነት ተሞክሮ የወደቀን ያነሳል። አመሰግናለሁ ጀግኒት።

  • @tesfahunfeleke01
    @tesfahunfeleke01 Месяц назад +375

    ስታምር። ደሞ በጣም ቀልደኛ ነች። ኢቭን የገጠማት ችግር ላይ ሁሉ ታላግጥበታለች። ዋናው እግዚያብሔርን ማግኘትሽ ነው።

    • @ኤልሳቤጥ
      @ኤልሳቤጥ Месяц назад +2

      ደምሪኝሲ ፍቃድሽ ከሆነ

    • @Sarasara-jz3mg
      @Sarasara-jz3mg Месяц назад +1

      ​@@ኤልሳቤጥደመርኩሽ መልሺ

    • @abebaseyiume8949
      @abebaseyiume8949 Месяц назад

      በጣም

    • @habtamutibebu2947
      @habtamutibebu2947 Месяц назад

      ባስጨነቀሽ ላይ እንደነሐናየሕልቃናቀንዴከፍከፍን፤ተራው የኔነውየኔን ከኤፍሬም፤"እንዴትእንዲያከብርያውቃልእግዚአብሔርንከወርቅነህ ዘምሪበት
      እነዚህን ኪኒን፣ ዋጭበት በቴስቢያዊው ፕሪስክሪፕሽን።
      ለህፃኗ ልጅሽ፣ ጭራሽ የራበው ኤልያስመጣብሽም)ልሽም።ያለወተትእንደወጣቶቹያለፋፋማንሊፋፋ? ፲እጅ በጥራጥሬ ተማምነን ነውኣሉ ተወራረዱበት፤ በሲድራቅሚሳቅአብደናጎም ኣምላክ ተፎካከሩ(ሽ)በት?እናያለና "እስከ ዜሮ ካአደረሥከኝ ከምንምንከዬትእንደምታወጣ? ከየትምአምጪው ዱቄቱንፍጪው? የቅድም ዜሮገበታዋ አሁን ሙሉነዋ?ያቺ ሰራፕታዋ ዊዶ አልቀረችም በባዶ

    • @genet_tube
      @genet_tube Месяц назад

      ​@@ኤልሳቤጥደመርኝ ፕልስ

  • @bizuyetube371
    @bizuyetube371 Месяц назад +224

    አፏ ሲጣፍጥ በጌታ ስም🥰 ዘርሽ ይባረክ!!

  • @redietgezachew9341
    @redietgezachew9341 28 дней назад +57

    እውነትም ሀገር ይሰማሻል👏እንዲ ተመስጬ ሰው አዳምጬ አላውቅም ኡፍፍፍፍ🥺ታድለሽ የኔ ቆንጆ🥰

  • @seblewongelbiruk2435
    @seblewongelbiruk2435 29 дней назад +12

    አወራርሽ፣እርጋታሽ፣ብስለትሽ፣ኮንፊደንስሽ፣እምነትሽ.... ምን አይነት ሰው ነሽ? እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ። ወድጀሻለሁ፣አክብሬሻለሁ፣ከሁሉ በላይ ባንች ውስጥ የእግዚአብሔርን ታላቅነትና ተራዳኢነት አይቻለሁ። እንኳን መጣሽ👏👏👏 u r sooooo perfect.

  • @fufukunfayakun4373
    @fufukunfayakun4373 Месяц назад +127

    በጣም የሚያሳዝንና አስተማሪ ታሪክነው በዛላይ የሀበሻን ተንኮለኛነትና ምቀኝነት እስከጥግ ያየሁበት ነው በጣም ጠንካራ ነሽ አለህ መጨረሻሽን ያሳምርልሽ

  • @በዲልኻናግዜሰብናመልሰልና

    የባለፈው ታሪክሸ አንዴት ተመሰጫ ባልጨርሸ አያልኩ ነው የሰማሁት😊በጉጉት ነው የጠበቅኩት አንካን በሰላም መጣሸ የዚች ልጅ ታሪክ ያሰተማራቹ ኣጋጩኝ😂

    • @dgjhd6774
      @dgjhd6774 Месяц назад +3

      👊👊👊👊😁

    • @DubaiUae-yp9ou
      @DubaiUae-yp9ou Месяц назад +1

      😂

    • @Jiji-ow6iz
      @Jiji-ow6iz Месяц назад

      ሽምካ ክጥዕም ወዲ ዐደይ

    • @KalmeAbra
      @KalmeAbra Месяц назад

      @@Jiji-ow6iz
      2i2l
      you l
      2
      the 9
      Lp
      You
      Il
      998×99th +)

    • @Amsale-sl6ek
      @Amsale-sl6ek Месяц назад +1

      እ/ር ሁሎንነገር ለበጎያደርጋል

  • @elimnoha
    @elimnoha Месяц назад +183

    " ለካስ ፊቱን ከልክሎኝ አያውቅምና እጁንም ጨመረ እግዚአብሔር የማወራለት ነገር ሰጠኝ " 🙌 አስገራሚ ምስክርነት። ጋዜጠኛው እርጋታው ! ምን ይባላል እግዚአብሔር በተለያየ መልኩ እየተናገረ ነውና ሰሚ ልቦና ይስጠን 🙏

  • @Goodthing1009
    @Goodthing1009 22 дня назад +7

    ያቺ ካንሰር ይዟት ሳትፀየፊ ላሳየሻት መልካምነት የመጨረሻ ዘመኗን እንዳሳመርሽላት ያንቺም ያማረ ነው ገና ብዙ ሰው ይሰማሻል በርቺ ሁሌም ነገሮችሽ ላይ እግዚአብሔርን ብቻ ታመኚው እርሱ ብቻ ነው የማይለወጠው የማይቀየመው የማያኮርፍሽ የማይጥልሽ እግዚአብሔር ብቻ ነው ፍቅሩ የማንቀንሰው ተባረኪ ተባርከሽ ቅሪ የብዙዎች እናት ያድርግሽ

  • @seblealemu6098
    @seblealemu6098 Месяц назад +233

    ሰዎች የቁንጅና መስፈርታቸውን መቀየር አለባቸው ከዚህ በላይ ቁጅና የለም በራስሽ ልትኮሪ ይገባል👏👏

  • @AminaMuhammed-i6d
    @AminaMuhammed-i6d Месяц назад +108

    አሁንም ሳልጠግብሽ አለቀ ወይኔ ቆንጆኮ ነሽ ወላህ ስትስቂ ደግሞ ስታምሪ ማሻ አላህ

  • @ageritudemeke1912
    @ageritudemeke1912 Месяц назад +49

    በጣም የሚደንቅ የእግዚአብሔር ጥበቃ እና ቸርነትን የሚያሳይ ታሪክ ነው። ምርየ እወድሻለሁ።

  • @RahelyDeshngll
    @RahelyDeshngll 25 дней назад +16

    ያለፍሺበት መንገድ ሁሉ እግዛብሄር ለምስክርነት ብቻ ሆነ ይገርማል እግዚአብሔር ጥበቃ ምን ያህል እሱ መልካም አባት ነው በህይወቴ አይቼዋለሁ ❤❤

  • @Saron202
    @Saron202 28 дней назад +20

    ለካ ፊቱን ከልክሎኝ አያውቅም እጁንም ጨመረ ድንቅ አባባል እንዴት ጣፋጭ ነሽ አንደበትሽ ተቀብቷል ዝም ብለሽ አውሪ ዘመንሽ ይባረክ 🙏❤❤❤❤❤

  • @MimiShaTube
    @MimiShaTube Месяц назад +72

    አቤት የንግግርሽ መጣፈጥ ፍቅር የሆኖሽ ልጅ ነው ስስቂ ደሞ ውበትሽ የወጣው ምትወደጂ ነገረ ነሽ❤❤❤

  • @hanademelash6673
    @hanademelash6673 Месяц назад +128

    በናፍቆት ነበር አየጠበኩ የነበር ለዛሽ
    ሲያምር ፅናትሽ ደስ ይላል ፈጣሪ ይወድሻል 🙏🙏🥰🥰🥰❤️❤️

  • @sofiamohammed9190
    @sofiamohammed9190 Месяц назад +52

    ውብ ነሽ
    ምሉዕ ነሽ
    ነፃነትሽ ግልፅነትሽ ደስ ይላል
    ትችያለሽ ንፁሕ ልብ ነው ያለሽ
    በሳል ለመሆንሽ ጥያቄ የለውም
    በብዙ ተፈትነሻል :: አሁን ደግሞ ትክክለኛው መንገድ ላይ ነሽ በፈጣሪ ማመን
    ገና ብዙ ታያለሽ ባለ ብሩህ አእምሮ ቆንጆም ነሽ እመኚኝ
    የፊልም ፕሮዲውሰሮች ይችን ልጅ ልብ ብላችሁአታል? ዳይሬክተሮች
    አርቲስቶች ,,,,,,,,,
    የአርት ሰው ናት ፊልም ብታሰሩአት
    ትችላለች
    ባገኝሽ ደስስስስስስስ ይለኛል
    መጨረሻሽን ናፈቅኩ
    ምርጥ ነሽ ምህረትዬ
    እምባሽ ያመኛል
    መፈተንን የደረሰበት ብቻ ነው የሚያውቀው
    ሁሉ ያልፍና ታሪክ ይሆናል

    • @SifanAlemayehu-s7z
      @SifanAlemayehu-s7z 27 дней назад +1

      Bexam hasabish des yilal isu bicha ayidelem agelaletsikim wow new

  • @Goodthing1009
    @Goodthing1009 22 дня назад +4

    ጀግና ሴት ነሽ እግዚአብሔር ይባርክሽ ልበ ንፁሀኖች እድለኞች ናቸው እግዚአብሔር ከእነሱ ጋር ነውና ታድለሽ የማያልፍ የመሰሉ ቀኖችሽን እግዚአብሔር ያሳለፈልሽ ስንቶቹ እኮ በህይወት የሉም ። ላመስግናቸው ክፉ ቀኖቼን የሚል መዝሙር አለ RUclips ላይ ጋብዤሻለሁ ቀሪው ዘመንሽ የዝማሬ የምስጋና ነው ተባረኪ ❤

  • @-Miha-Tech
    @-Miha-Tech Месяц назад +15

    ስታለቅሽ አልቅሼ፣ስትስቂ ደግሞ እየሳቅሁ ነው የጨረስሁት!!! የ አንች ታሪክ ለኔ በጣም ትክክለኛው ሰዓት ነው!!!

  • @haymilemma2797
    @haymilemma2797 Месяц назад +189

    ንግግሯ፣ለዛዋ፣ሳቋ ሁሉም ነገሯ ደስ ሲል❤
    ፍፄ ደሞ ሳቅህ በጣም ነው ደስ ሚለው😅

    • @Yeshi987
      @Yeshi987 Месяц назад +8

      በጣም ማርያምን ባላለቀ ብዬ ነው ያየኋት ደስ ስትል❤❤❤🎉🎉🎉

    • @abayyoutube7148
      @abayyoutube7148 Месяц назад

      ተመስጨነው እኔም የስማሁት​@@Yeshi987

    • @qtrdoh2067
      @qtrdoh2067 17 дней назад

      በጣም ምትገርም ልጅ የንግግሯ አደራደር ሳይዛነፍ 🥰😍

  • @Trhas601
    @Trhas601 Месяц назад +223

    እኔ ግን ከታረክዋ ይልቅ አንደበትዋ ትህትናዋ 🎉❤

  • @haymanothabtemariam6621
    @haymanothabtemariam6621 Месяц назад +71

    አሜን ይሳቅ የቆፈረዉ ዉሃ ቦታዉ ላይ ስላለ ሳይሆን እግዚአብሂር አብሮት ሰለ ነዉ 🙏
    ቀስት መጀመሪያ ወደ ኃላ ነዉ የሚጀምረዉ ❤

  • @selamlema9601
    @selamlema9601 2 дня назад

    በፍቅር ደስ ብሎኝ ያዳመጥኩት ታሪክ❤ ደስ ስትል ስታወራ . ያለፍሽበት ታሪክ ሁፍፍ ጠንካራ ሴት ነሽ

  • @Girumpino
    @Girumpino Месяц назад +14

    እንዳንቺ ታሪክ ተመስጨ የሰማሁት ታሪክ የለም ደስ ምትይ ሰው ነሽ 👏አወራርሽ ስርአትሽ ራሱ አንደኛ

  • @miliardsolomon1769
    @miliardsolomon1769 Месяц назад +37

    If I have a daughter I want her to be exactly like you courageous, beautiful, self aware, confident, articulate, and God fearing women. Oh my God I am so obsessed with you. You make me see my self. Please create your own podcast. You have so much to share. Please Please Fitsum Hire her she is a light in this dark world

  • @አስያአህመድ-ፀ7ለ
    @አስያአህመድ-ፀ7ለ Месяц назад +39

    ማነው አደኔ ክፍል1እስከ2 እስከመጨረሸው ያየው ኮፋደሥሽ አወራረሽ በጣም ደሥ ይላል 🎉🎉🎉

  • @ኢየሩሳሌምዘሚካኤልወገብር

    እውነት ከልቤ ነበር ሳዳምጣት የነበረው እግዚአብሔር በሥራው አይሳሳትም ሊነጋ ሲል ይጨልማል ፈተና መከራ አይነቱ ይለያያል እንጂ ሁላችንም እያሳለፍነው ነው እግዚአብሔር አምላክ ፍፃሜያችንን ያሳምርልን

  • @fetlworkalebachew2358
    @fetlworkalebachew2358 11 дней назад +1

    በህይወት እንደዚህ አይነት ታሪክ ሰምች አላቅም ማሪያምን የኔ ቆንጆ ሳላደንቅሺ አላልፍም ሙሉዉን ታሪክ እያለቀስኩ ነዉ ያየሁት

  • @Hundumak
    @Hundumak 27 дней назад +5

    ይህቺ ልጅ ብዙ ፈተና ያሳለፈች ጎበዝ ና የመናገር ችሎታ አላት። በመንፈሳዊ ህይወት የሚያግዛት ሰው ብገኝና በሃይማኖት ተቋም ድጋፍ መንፈሷ ብታገዝ ትልቅ ደረጃ ትደርሳለች ።🎉🎉🎉

  • @tube7756
    @tube7756 Месяц назад +196

    ልብ ቀጥ የሚያደርግ ታሪክ❤በአንድ ትንፋሽ ሰማሁሽ😂ጠንካራ ነሽ😂❤🥰

    • @zuriashbiremka740
      @zuriashbiremka740 Месяц назад

      ከሚባለው በላይ በጣም ጀግና❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ እንዳንቺ ባረገኝ ፈጣሪ

    • @aminanuredine4278
      @aminanuredine4278 Месяц назад

      😂😂😂😂

  • @SleepyArcticWolf-pm4gn
    @SleepyArcticWolf-pm4gn Месяц назад +89

    በእውነት በህይወቴ ብዙ የንግግር ችሎታ ያላቸውን ሰዎች አውቃለው እራሴንም እንደዝያው ነው የምለው ግን እንዳንቺ አይነት ተናጋሪ አለ ብዬም አላስብም አይቼም ሰምቼም አላውቅም አንደበትሽ ሲጣፍጥ ምንም እንከን የሌለው ብሰማ ብሰማ ልጠግብ አልቻልኩም እንተርቪው ባላለቀ እያልኩ በስስት ነው የሰማሁሽ ጀግና ነሽ ❤

    • @peacelove4778
      @peacelove4778 Месяц назад +5

      በጣም ነው የቀናሁባት በቃላቶቻ ንግግራ እኔ ደግሞ በቃላት ጉድፈት ስንቱን አስቀየምኩ በየዋህነት😢😢

    • @Milkana-d2x
      @Milkana-d2x 29 дней назад

      ​@@peacelove4778me to

  • @hanamehid5214
    @hanamehid5214 Месяц назад +103

    ከሰት አምት በኋላ እረዥም ቪዲዮ በመመሰጥ የሰማሁት ታራክ ❤❤❤❤

  • @genetebrahim5900
    @genetebrahim5900 24 дня назад +1

    ወይኔ እድሏ ግን 😢ስታሳዝን በስማም ግን ደሞ she's such a beautiful and strong soul!

  • @endashashdebella2441
    @endashashdebella2441 10 дней назад

    በጣም ጠንካራ ሴት ነሽ ትልቁ ነገር እግዘብሔርን ማመንሽ ጠቀመሽ። ቀሠው የታመነ የተረገመ ነው ይላል። አሁን ከሠዎች ጋር ስትቀራረቢ በጥንቃቄ ይሁን። ሁሉ ይከዳል ሁሉ ያልፋል እግዚአብሔር ግን መቼም አይክድም የዘለአለም ነው።

  • @goldbody2836
    @goldbody2836 Месяц назад +21

    የመጀመሪያውን ለመጀመሪያ ጊዜ 3 ጊዜ የደገምኩት ታሪክ ሁለተኛውን በጉጉት ነበር ስጠብቀው የነበር.... ዋው እርጋታሽ አንደበትሽ ይገርማል

  • @BekikabBekikab
    @BekikabBekikab Месяц назад +40

    ላስተዋለው ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ታሪክ ነው በጣም ጠንካራ ሴት ናት❤❤❤❤

  • @AderawDesiybelew
    @AderawDesiybelew Месяц назад +12

    ጥሩ የሐሳብ ባለቤት ነሽ ፣ኮሜዲ ነሽ፣የፅናት ባለቤት ነሽ በጣም ጀግና ፣ጠንካራ እንችን ለመግለፅ ቃል የለኝም።

  • @HamnetSebir
    @HamnetSebir Месяц назад +30

    ቆንጆ እኮ ነሽ አላህ የሰዉ ልጅ ባማረ ሁኔታ እንደፈጠረዉ ይናገራል ዋናዉ የሰዉ ልጅ የተፈጠረበትን አላማ ማወቅ አለበት የዚህ ምድር ሂይወት ያበቃል ዘላለማዊ ደስታ ህይወት የሚገኘዉ በኢስላም ነዉ አንዱንና ያልወለደዉንና ያልተወለደዉን ፈጣሪ አላህ እወቂዉ የዚህ ምድር ፈተና አያበቃም ዘላለማዊ ህይወት ደስታ የሚገኘዉ አላህ በማወቅ ነዉ

    • @hirut2178
      @hirut2178 Месяц назад

      God bless no muselm

    • @Kidus4843
      @Kidus4843 29 дней назад

      Exactly ​@@hirut2178

    • @chhcjcfu9769
      @chhcjcfu9769 27 дней назад

      ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢😢❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

    • @AnasMulat
      @AnasMulat 9 дней назад +1

      አለህ ሂዳያውን (መመራቱን) ይስጣት

  • @girmagossay7127
    @girmagossay7127 Месяц назад +11

    አሳቧን የመግለፅ ድንቅ ችሎታ እግዚአብሔርን የምትገልፅበት ድንቅ አቅም ዋው ስታወራ ብትውል የማትሰለች ጣፋጭ ልጅ
    አቦትችያለሽ 🙏🙏🙏

  • @mesfinteshome2543
    @mesfinteshome2543 Месяц назад +35

    በፈተና የሚፀና የተባረከ ነው ፣፣፣ ምን አይነት ድንቅ ነሽ

  • @ethio4711
    @ethio4711 Месяц назад +37

    ፍፄ እያቀረብክ ያለኸዉ ሰወች የሚገርሙ በብዙ የሚያስተምሩ ናቸዉ በርታልን

  • @FrehiwotAbebaw-i9y
    @FrehiwotAbebaw-i9y Месяц назад +15

    ታሪክሽን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ሰማሁሽ አንደበትሽ እርጋታሽ ቁንጅናሽ አንቺ ለኔ ጀግና ሴት ነሽ በርችልኝ🎉🎉🎉❤❤

  • @mesi16-91
    @mesi16-91 29 дней назад +50

    ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት አንዴ ማልቀስ መሳቅ ደግሞ ወደሃላ በቁጭት መመልከት ደግሞ ወደፊት በተስፋ ማማተት 😢 የእያንዳንዳችንን መናገር ያልቻልናቸውን ታሪኬቻችን ከፍፍ ባለ ድምፅ ስላሰማሽልን እናመሰግናለን 🙏🙌

    • @SeadaAbate-xm6hz
      @SeadaAbate-xm6hz 27 дней назад

      Betam uuuufffff ssk saleks ende drama new yechereskut

    • @SaraKawiso
      @SaraKawiso 22 дня назад

      ስሜቴን ነው የገለፅሽሊኝ

  • @አምላኬሆይያንተእንጂየሰው

    እውነትም ዓለም ይሰማሻል ❤🎉ነገም ከነገ ወድያም አዳምጣለሁ ያልኩ እስከዛሬ አልሰማሁም ዛሬ ግን ተሰካልኝ በዛ ላይ ለእኔ በጣም በከባዱ ቀን 😢 የእውነትን እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው እምነትሽ ጽኑ እኔን ግን በለቅሶ በሳቅ በደስታ በፍገግታ በተስፍ ነው ያዳመጥኩሽ በዛ ላይ በጣም ውብ እና ጠንካራ ብልህ ሴት ነሽ
    🎉 ለመጀመርያ ግዜ ሳይ ሰለቸኝ እንድያም እዳያልቅ በጉጉት የሰማሁትን ለመጀመርያ ግዜ ያንቺን ታሪክ ነው
    ለእኔ በሁሉም ነገርሽ አንደኛ ነሽ#
    ያንቺ ታሪክን በመስማቴ በጣም ደስተኛ ነኝ
    ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።

  • @የሕግአማካሪ
    @የሕግአማካሪ Месяц назад +63

    በጣም የምትገርሚ ደሰ የምትይ ልጅ ነሽ! መጨረሻሽ ናፍቆኛል!

    • @gechtube3308
      @gechtube3308 8 дней назад

      እኔስ ብትሉ መጨረሻው አጓጓኝ

  • @elsaworkayehu382
    @elsaworkayehu382 Месяц назад +50

    ሴት ጓደኞች የተረገሙ ናቸው እንዴት አስበው ሰው እንደሚጥሉ ይጠበባሉ። አንቺ ብሩቱ ሴት ነሽ እግዚአብሔር ይባርክሽ ደግሞ ለብዙ ሰው ያስተምራል።

  • @ezrasamuel6241
    @ezrasamuel6241 Месяц назад +26

    Best Interviewer!
    Best Interviewee!
    She is a good storyteller!
    May God bless you more and more!

  • @srms7403
    @srms7403 Месяц назад +15

    ብዙ ጊዜ ረዘም ያለፈ ኢንተርቪው ሙሉውን እያስኬድኩ ነበር አንቺን ግን እየጣፈጠኝ ነው ያዳመጥኩሽ የኔ ጣፋጭ እህት የውም የሀገሬ ልጅ ደግሞ የማቅሽ መሠለኝ ወላሂ ከሀገር ከወጣሁ ቆየው ከአንቺው እኩል 2004 ላይ የኔ ጠንካራ❤❤❤

  • @MgdsMgds
    @MgdsMgds Месяц назад +16

    የእዉነት አንችን ለማበረታታት አይደለም ወይም ላስመስል አይደለም የሆነ የሚስብ ዉብት ግርማ ሞገስ ጥፍጥና አለሽ የኔ ዉድ ምርጥ ማራኪ ነሽ❤❤❤❤

  • @KalkidanTeshale-b3c
    @KalkidanTeshale-b3c Месяц назад +121

    All this because her parents didn't give her care&love It's so sad we ran away from our childhood and still follow us may God heal us all

    • @Mindfulconsience
      @Mindfulconsience Месяц назад +3

      Amiin!

    • @amytk6095
      @amytk6095 Месяц назад +2

      Thank you this was exactly what I was thinking, our upcoming has everything to do with our adulthood life.

    • @bonofienrobaa3637
      @bonofienrobaa3637 27 дней назад

      Ehmmmm😢

  • @ኡምሪማሥ
    @ኡምሪማሥ Месяц назад +81

    ፈገግታዋ እራሱ ድፍት ነው የሚያደርገው. ❤❤

  • @mishomishomeseret8863
    @mishomishomeseret8863 Месяц назад +15

    የኔ ቆንጆ አነጋገርሽ ከማር ይጣፍጣል ቀሪውን ዘመንሸን ሁሉ ይበርክልሽ አይዞሽ ማርዬ ❤

  • @Alemtsehay777
    @Alemtsehay777 19 дней назад +1

    ታሪክሽ በጣም ነዉ የደነቀኝ። ድንገት ገብቼ ነዉ የሰማሁት ጠንካራ ሴት ነሽ በእዉነት

  • @melekeKetema
    @melekeKetema 29 дней назад +4

    ፈገግታሽ በጣም ነው ደስ የሚለው ቲክቶክ የተቆረጠ አይቼ ሙሉ ታሪክሽን የሰማሁት

  • @zabebahmed7095
    @zabebahmed7095 Месяц назад +20

    ወዝ ያለው ታሪክ ታሪክሽ ያሳዝናል ግን አንች እያሳቅሽን ፈታ ነው ያደረግሽን አይዞሽ ሁቢ ጀግና ታጋሽ ሴት ነሽ ያሰብሽወን ያሳካልሽ

    • @M_52-l1y
      @M_52-l1y Месяц назад

      Amen 🙏🙏

  • @kidesttadel
    @kidesttadel Месяц назад +27

    እጅግ ድንቅ ንግግር ታሪክሽን ስትተሪኪው ለልብ ይመቻል ለጄሮ ይጥማል ተባረኪ

  • @raconwon
    @raconwon Месяц назад +8

    my goodness, ምን አይነት አንደበት ምን አይነት ጀግንነት ነው ?
    በእውነት በአንድ ሰው ዕድሜ የተከናወነ የሕይወት ታሪክ አይመስልም ።
    እኔ ትንሽ ዘመም ሲልብኝ እኮ ዓለም በአፍጢሟ የተደፋች ነው የሚመስለኝ።
    ጀግና ልጅ ነሽ።

  • @Abeba23-e7u
    @Abeba23-e7u 25 дней назад +4

    የድምፅሾ ቅላፄ ቃላቶች ምርጫ አስተዋይነትሽ ደስ ይላል ግን በእየንዳንድ የሕይወት ገጠመኝ እግዚአብሔር አትርፎሻል በተለይ ፍተሻው ላይ ፈጣሪሽን አመሥግኚ በተረፈ አስተማሪ ታሪክ ነው ሰዓት ዕላፊ ማንበብሽ ጠቅሞሻል ምንም ቢሆን ግ ቤተሠብ ቤተሠብ ነው ቂም አያዝም እግዚአብሔር አትርፎሻል በርቺ

  • @Meron-o9z
    @Meron-o9z Месяц назад +32

    በ youtube እንደዚህ አዳምጨ ጨርሸም አላውቅም እንዴት ይስባል አነጋገራ ብዙ ነገር ተማርኩበት ስለኔ የምታወራ መሰለኝ ❤❤❤❤

  • @WednshLakew
    @WednshLakew Месяц назад +30

    ልጄ በጣም አሳዘንሺኝ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ይሁን እግዚአብሔር ይርዳሽ

  • @tamirukidus811
    @tamirukidus811 Месяц назад +44

    ጀግና ሴት ነሽ ፊልም ቢሆን ሁለት ፖርት ይሆነዋል ምናልባት ብዙ ሴቶች እንዲሰሙት በቴሌቭዥን ፕሮግራም ሙሉው ቢተላለፍ እራሳቸውን የሚጠሉ ባማንነታቸው የማይደሰቱ እራሳቸውን ሊያጡ የተዘጋጁ ገንዘብ ማጣት የዓለም መጨረሻ ለሚመስላቸው ሰዎች (ሴቶች) እራሳቸውን እንደሸቀጥ በማቅረብ በማይሆን ስራ በመስራት ለሚኖሩ አንቺ ሞዴላቸው ትሆኛለሽ እግዚአብሔር ማወቅ ትልቁ ሀብትን ይዘሻልና እመኝኝ ነገሽ የጣሉሽ ከፍታሽን ያያሉ

  • @KattofTelecom-hr7zd
    @KattofTelecom-hr7zd Месяц назад +6

    የሰው ቤቱ ቢፈተሽ በጣም አስተማሪ ታሪክ ይገኛል አንቺ የሁሉም ተምሳሌት ነሽ ፈጣሪ አውንም ያበርታሽ

  • @deboamare5171
    @deboamare5171 19 дней назад

    ኡፍ Unconditional love ዋው ስለ ጌታ ስታወሪ ልቤን እየሰነጠቀ የሚያልፈው የርሱ ምህረትን ሳስብ አይኔ ሳይሆን ውስጤ በደስታ እያለቀሰ ነው በጣም ሁሌ ነይና አውሪን የማትሰለቺ ቆንጅዬ ነገር ነሽ ማሬ ጥንካሬሽ , ኮንፊደንስ , ደስተኝነታሽ ዋውውውውውውውውውውውውውው🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

  • @umikelsumajib7858
    @umikelsumajib7858 Месяц назад +29

    ወላሂ እያለቀስኩ እየሳኩ ነው የሰማኋት 🥰 the way she telling the story is Amazing ....can't wait the last part 😌

  • @ElsabetAbrar
    @ElsabetAbrar Месяц назад +6

    ኸረ የምትገርሚ መፅሀፍ ነሽ ደግሞ ስታወሪ ውስጥሽ የእውነት ነው ለፈጣሪ የሚመች ዓይነት ሰው ነሽ ዘመንሽን ይባርክልሽ

  • @lamrotweldemichael7777
    @lamrotweldemichael7777 Месяц назад +17

    ወይ የኔ ቆንጆ እኔ ያንቺ አስቀያሚነት በፍፁም ሊገባኝ አልቻለም !!! ግን you are amazing❤ጥንካሬሽ፣ ተስፋ አለመቁረጥሽ Wawuuuu🎉ታሪክሽ እኮ ታሪክ ቀመስ ልብወለድ ነው ፃፊው !
    ከልቤ ነው። በጌታ ላይ ያለሽ ተስፋ፡-አቋም ተባርከሻል❤

  • @mesialex9330
    @mesialex9330 18 дней назад

    እንዴት ደስ የምትይ ሴት ነሽ አነጋገርሽ ለዛ አለው በጣም ጠንካራ ሴት ነሽ❤

  • @betieltsegaye4315
    @betieltsegaye4315 22 дня назад +4

    Who says she's not Beautiful... እንዴዴዴ! እናቴ፡ትችያለሽ፤ ሁሌም፡እግዚአብሔር፡ካንቺ፡ጋር፡ነው!

  • @saratadesse6434
    @saratadesse6434 Месяц назад +16

    እንዴት አይነት አስገራሚ ታሪክ ነው ያለሽ 😮አንደበትሽ ፥ለዛሽ፥ጥንካሬሽ፥ወላሂ በጉጉት ነው የሰማሁሽ❤ በሰዎች መገፋትን እኔም በደንብ እውቀዋለው 😢 አላህ ይጠብቅሽ የኔ ውድ❤

    • @SSna-m9i
      @SSna-m9i Месяц назад

      እኔስ ብትዬ😢

  • @Sara-g4o2d
    @Sara-g4o2d Месяц назад +54

    በስመአብ አንደየ እስቃለሁ አንዴየ አለቅሳለሁ የሚገርም ታሪክ ነው እኔም አለኝ ግን እግዚአብሔር ይመሰገን እግዚአብሔር እኮ ከኛ ጋር ነው ክብር ለእግዚአብሔር
    ክብር ለሚገባቸውም ለድንግል ማሪያም ለጭንቅ አማላጇ ክብር ለመላእክት ለሳድቃን አሜን 😓🙏🙏🙏

  • @MeseretMamo-si6sw
    @MeseretMamo-si6sw Месяц назад +23

    በናትህ ፍፄ ቀጣዩን ቶሎ ልቀቅልን❤ በጣም አስተማሪም አሳዛኝም ነው ። የኔ ቆንጆ ተባረኪ ❤❤

  • @HanaTemesgen-ze5jp
    @HanaTemesgen-ze5jp 20 дней назад +2

    ንግግርሽ ሰብራትን ያክማሉ ተስፋን ያለመልማል ደሞ ስታምር የኔ ቆንጆ አገላለፅሽ በጣም የሚያሳዝንና አስተማሪ ታሪክ ነዉ በዛላይ የሀበሻን ተንኮለኛነትና ምቀኝነት እስከ ጥግ ያየሁትነዉ በጣም ጠንካራ ነሽ ያለፍሽበት ምንገድ ሁሉ እግዚአብሔር ለምስክርነትሽ ሆነ እግዚአብሔር ጥበቃ ምን ያህል መልካም አባት ነዉ በህይወቴ አይቸዋለሁ ምን ይሳንሀል እግዚአብሔር ሆይ ❤❤❤❤❤❤ ❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🙏🙏🙏

  • @yousifmohammad9627
    @yousifmohammad9627 19 дней назад

    በጣም ጠንካራ ነሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ታሪክዋ እየማረከኝ የሰማሁዋት አንቺ ነሽ እና ሁሌ ፋጣሪ ካንቺጋ ይሁን ❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @amefke2069
    @amefke2069 Месяц назад +6

    እህቴ ገራሚ ታሪክ አስተማሪ አድርጎ ፈጣሪ አስተማረሽ ጎበዝ ነሽ ታሪክሽን በመፃሐፍ አሳትሚው ድንቅ ነው

  • @geniaimiro1414
    @geniaimiro1414 Месяц назад +15

    እስከዛሬ ከሰማኋቸዉ እጅግ መሳጭ ታሪክ

  • @kelemeuagatukelemeuagatu4701
    @kelemeuagatukelemeuagatu4701 Месяц назад +7

    👌🏾👌🏾👌🏾🤣🤣 ላዳምጠው ሰደተኛ እህቶች ጥሩ ትምህርት ነዉ እግዚአብሔር መጭርሻሸን ያሳምርልሽ 👍🏾👍🏾🙏🏾

  • @አመለወርቅጥላሁን
    @አመለወርቅጥላሁን 11 дней назад

    እግዚአብሔር ታላቅ ነው አንዳንድ ነገሮች በእራሱ ጊዜ ሰአት ያደርጋል ህይወት ይቀጥላል ህይወት ህመም ችግር በጣም መራራ ነው
    ተመስገን ደስ የሚል
    ምክር ከአንደበትሽ የሚወጣው ቃል ብርክ በይልኝ 🙏🙏🙏

  • @DiaCell-r8d
    @DiaCell-r8d 18 дней назад

    እውነት በጣም የሚያስተምር ታሪክ ነው እህቴ እግዚአብሔርን መያዝ እንደሚጠቅም ተረድቻለሁ 😔😔😔😔😔😔♥️♥️♥️♥️♥️ተባረኪ የመጨረሻ ክፍልን ማየት ናፍቂያለሁ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰

  • @HsksnsHaovs
    @HsksnsHaovs Месяц назад +54

    ቪዲዮ ስትለቁ ሰዓት አስተካክሉ እይታ እንዲኖረው ❤❤🎉🎉
    ክፍል ሁለት ልክ እንድኔ በጉጉት ሲጠብቅ ይነበረ ማነው ካላቹ በ like👍👍

  • @mercyba2060
    @mercyba2060 Месяц назад +8

    I love how the way she talked and explained herself,makes me to learn how the way to talk show your confidence,she is smart ,trust God is more than anything ,I'm sure she is gonna be successful women not only in ethiopian all over the world, I wish I can meet her i will love to have like this women in my life to be my friend or sister,🎉🎉🎉

  • @ማርያምጽዮንኣደይብርሃንና

    እርጋታሽ የቃላት አጠቃቀምሽ የእምነትሽ ፅናት ይደንቃል የፈጣሪ ስራ ድንቅ ነው ትሞታለች በሽተኛ ናት የተባለች ጤነኛ ወሀም አንተከባረከው ወተት ይሆናል ብለሽ የአንድ ወር ህፃን በወሀና ስኳል በጥብጠሽ ስትሰጭያት ከወተት በላይ ለጤና ንመፋፋት ያደረሳት አምላክ ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን😢😢😢❤❤❤የንቺ ፅናትና እምነትም ይደንቃል😢😢😢❤❤❤ ጠንካራ እናት የዋህ ልበቀና ግን በሰው ልጅ ምትከዳ ምትሳቃይ ነሽ ታሪክሽ በጣም አስተማሪና አሳዛኝ ነው ግን ከማንም በላይ ፈጣሪ ይወድሻል ❤❤❤❤❤ እስኪ አሁን ደክሞኛልና ራሴ ከማጠፋ አንተ ግደለኝ😢😢😢😢😢😢 አሁን ሁሉ አጥቼ አለው እና ምን እንደ ምትሰራ አያለሁ የኔ ማር አይይይ❤❤❤❤❤😢😢😢
    በሰላ አለኝ በስደት እኔም ፈተናየ ገና አላለቀም ግን እንደ አንቺ ሁሉ ለፈጣሪ ሰጥቼው አለው የሰው ልጅ ፈተና በየ አይነቱ ተነግሮ አያልቅም 😢😢😢😢😢😢

  • @betlihemzerihun6017
    @betlihemzerihun6017 Месяц назад +2

    የኔ ቆንጆ ❤እኔ የሁሉም ነገር ውበት ነው ያየሁብሽ😍 እግዚአብሔርን አከበርሽው ❤ እንደስብከት ሰማሁሽ ❤ ተባረኪ

  • @vibvib45
    @vibvib45 18 дней назад

    እውነት ታሪክሽን በመፃፊው እናም ሰው ያንባዋል በጣም ጎበዝ ነሽ ጠንካራ ❤

  • @RozRoz-nh3vy
    @RozRoz-nh3vy 25 дней назад +3

    ስታወሪ እንዴት እንደምትጥሚ😁
    አሁን ካለሽበት ሁኔታ ያለፈ ...
    የታመንሽበት ጌታ እግዚአብሔር ትልቅ ቦታ ያድርስሽ በእርሱ ላይ መታመንሽ
    ይፅና😇🙌

  • @alamaetaddesse6198
    @alamaetaddesse6198 Месяц назад +6

    እኔ ያንተን ስራ ተመኝሁ ፍፁም በጣም ይምትገርም ስው ነህ እግዚአብሄር ይባርክህ ብትዕግስት ታዳምጣትአለህ ትስቃለች እየህ ልቦ ንፁህ ነው ተፈተነች አምላኮን ሙጥኝ ብላለች አይትዋትም ትምህርት እየስተማራት ነው ታላቅ ነው አይዞሽ የኔ እመቤት አንተ እንደ ስምህ ፍፁም ነህ ይባርክህ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ❤❤❤

  • @rediethailu8262
    @rediethailu8262 Месяц назад +3

    የኔ ውብ የምር እደዚህ ሳይሰለች እሚሰማ ታሪክ❤አተራረክሽ❤ኡፍፍፍፍፍ በቃ ቃል የለኝም ላቺ😍

  • @bu-ze3326
    @bu-ze3326 21 день назад +1

    አቤት እንዴት ጣፋጭና በብርታት የተሟላ ደስ የሚል ታሪክ ነው🥺😍

  • @HeluBura
    @HeluBura 28 дней назад +1

    እውነት ነቁ ሕይወት በጣም ሚገርም ታሪክ ነው የኔ ውድ ተባረኪ❤❤❤❤

  • @መሳይአስራት
    @መሳይአስራት Месяц назад +63

    አንቺ ልጅ መጣሽልኝ😘😘😘

  • @laveleable
    @laveleable Месяц назад +30

    አንተን አምኖ ያፈረ ማን አለ? ጌታ እየሱስ ተባረክ !🙏✝️🙏✝️

    • @MayoshaTa
      @MayoshaTa Месяц назад

      አሜን❤አሜን❤አሜን❤❤❤❤❤