የዓመት ፈቃድ በገንዘብ How to calculate ANNUAL LEAVE & Tax የሕመም ፈቃድ የቤተሰብ ጉዳይፈቃድ
HTML-код
- Опубликовано: 22 дек 2024
- ዓመት ፈቃድ መጠን
ሀ) ለመጀመሪያ የ1 ዓመት አገልግሎት 16 የሥራ ቀናት፤
ለ) ለአሠሪው ከ1 ዓመት በላይ ለተበረከተ አገልግሎት ለእያንዳንዱ 2 የአገልግሎት ዓመታት 1የሥራ ቀን እየተጨመረ ይሰጣል፡፡
አንድ ሠራተኛ ያገለገለበት ጊዜ ከ1 ዓመት በታች ከሆነ በአገልግሎት ዘመኑ ልክ ተመጣጣኝ የሆነ ዕረፍት በዚያው በአገለገለበት ዓመት ይሰጠዋል፡፡
አመት ሳይሞላው የስራ ውሉ ከተቋረጠ በገንዘብ ተቀይሮ የሰጠዋል
ምሳሌ፡- ደመወዝ 25,000 95days
365=16
95 ?
365X=95*16
X=1,520/365 days
X=4.16 ~4 Days leave
የዓመት ፈቃድ መከፋፈልና ማስተላለፍ
አንድ ሠራተኛ ሳይከፋፈል የሚሰጥ የዓመት ፈቃድ ከክፍያ ጋር ያገኛል፡፡
ሠራተኛው የዓመት ፈቃድ ተከፋፍሎ እንዲሰጠው ሲጠይቅና አሠሪውም ሲስማማ ለ2 ተከፍሎ ሊሰጠው ይችላል፡፡
የዓመት ፈቃድ ሠራተኛው ሲጠይቅና አሠሪውም ሲስማማ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
አሠሪው የሥራ ሁኔታ ሲያስገድደው የሠራተኛውን የፈቃድ ጊዜ ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡
የተላለፈው የዓመት ፈቃድ ከሚቀጥለው 2 ዓመት በላይ ሊራዘም አይችልም፡፡
አንድ ሠራተኛ በዓመት ፈቃድ እያለ ቢታመምና በህክምና ተቋም እንዲተኛ ለተደረገበት ጊዜ ብቻ የዓመት ፈቃዱ ተቋርጦ የህመም ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
በፈቃድ ላይ ያለ ሠራተኛን መጥራት የሚቻለው ቀደም ብሎ ሊታወቅ በማይችል ምክንያት ሠራተኛው በሥራ ላይ መገኘት ያለበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡
ሠራተኛው ከፈቃዱ በመጠራቱ ምክንያት የደረሰበትን የመጓጓዣና የውሎ አበል ወጭ በአሠሪው ይሸፈናል፡፡
ሠራተኛው ከፈቃድ ሲጠራ በጉዞው ያጠፋው ጊዜ ሳይቆጠር የቀረው የዓመት ፈቃድ በገንዘብ ተተምኖ ይከፈለዋል፡፡
Annual Leave Payment & Tax Amount
Salary 45,000 40 day annual leave
Annual leave amount=45,000/30=1,500
1,500*40=60,000
60,000/12=5,000 or
45,000/12=3,750
3,750/30=125
125*40=5,000
Taxable amount 45,000+5,000=50,000
50,000*0.35*-1,500*0.35=16,000
45,000*0.35-1,500=14,250
Per month tax amount 16,000-14,250=1,750
Annual tax amount 1,750*12=21,000
Net pay/after tax 60,000-21,000=39,000
የሕመም ፈቃድ
አንድ ሠራተኛ የሙከራ ጊዜውን ከጨረሰ በኋላ በሥራ ላይ በሚደርስ ጉዳት ሳይሆን በሌላ ሕመም ምክንያት ሥራ መሥራት ካልቻለ የሕመም ፈቃድ ያገኛል፡፡
ማንኛውም ሠራተኛ በሕመም ምክንያት ከሥራ ሲቀር አሠሪው ስለሁኔታው ሊያውቅ የሚችል ወይም ሠራተኛው ለማስታወቅ የማይችል ካልሆነ በስተቀር ከሥራ በቀረ እጅግ ቢዘገይ በማግስቱ ለአሠሪው ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
ሕመሙ ከደረሰበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ባለው የ12 ወር ጊዜ ውስጥ በተከታታይ ወይም በተለያዩ ጊዜያት ቢወስድም በማንኛውም ሁኔታ ከ6 ወር አይበልጥም፡፡
የሕመም ፈቃድ ቀጥሎ በተመለከተው ሁኔታ ይሰጣል:-
ለመጀመሪያው ወር ከሙሉ ደመወዝ ክፍያ ጋር፣
ለሚቀጥሉት 2 ወራት ከደመወዙ 50% ክፍያ ጋር፣
ለሚቀጥሉት 3 ወራት ያለክፍያ፡፡x3
ለቤተሰብ ጉዳይ የሚሰጥ ፈቃድ
ሕጋዊ ጋብቻ ሲፈጽም፤
የትዳር ጓደኛ፣ ወላጅ፣ ተወላጅ፣ ወንድም፣ እህት /አጎት፣ አክስት የሆነ የሥጋ /የጋብቻ ዘመድ ሲሞትበት፤ ከክፍያ ጋር ለ3 የሥራ ቀናት ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
የሠራተኛው የትዳር ጓደኛ ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 3 ተከታታይ ቀናት ፈቃድ ከክፍያ ጋር ይሰጠዋል፡፡
ሠራተኛው ልዩና አሳሳቢ ሁኔታ ሲያጋጥመው እስከ 5 ተከታታይ ቀናት ያለክፍያ ፈቃድ የማግኘት መብት አለው፡፡ ሆኖም በዚህ ረገድ የሚሰጠው ፈቃድ በበጀት ዓመቱ ከ2 ጊዜ ሊበልጥ አይችልም፡፡
#Severancepay
#annualleave
#incometax
#microsoft
#Windows
#BonusPay
#Bonus
#PENSION
#NETSALARY
#OVERTIME
#TransportationAllowance
#BedAllowance
#Perdiem
#MicrosoftWord
#MicrosoftExcel
#MicrosoftAccess
#MicrosoftPowerPoint
ETHIOPIA
question- le 30 new weys le 26 mekafel yalebet?
ቆንጆ ትምህርት ነው።።😍😍😍😍
Thank u
Thank u for sharing
Thanks for watching!
Great job ❤❤
thank u Bini
ከሰሽ በክስ ይግበኝ ቀና ቀጠሮ ለይ ሰላ አፈፃፃም ብጠያቅ እንዴት ይታጋድ?
ruclips.net/video/IH0VM2bXytI/видео.htmlsi=aD4s7n93bDMdaVz_
ቅጥሩ በ1990 ዓ/ም ቢሆን በ2016 ዓ/ም የዓመት ዕረፍት ስንት ቀን ያገኛል።እስከ 2011ዓ/ም በየዓመቱ 1 ቀን ከ2011ዓ/ም ወዲህ በየዓመቱ ግማሽ ቀን እየጨመሩ ሲሰሩ ይታያል።ምን ያህል ትክክል ነዉ?
@@berhanualemu4689 ከ1990 ጀምሮ ያለውን በምሳሌው መሰረት ማስላት ትትችላለ ነገር ግን የአመት እረፍትን ከ2 አመት በላይ ማስተላለፍ አይቻልም። ከ2011 በኋላ በየ2 አመት 1የስራ ቀን ይጨምራል በየአመቱ ግማሽ ቀን እንደ ማለት ነው። ያው ህጉ 2011 ላይ ነዉ ተሻሽሎ የወጣው
ቪዲዮውን ደግመ እየው