Dear Dr. Mamusha, I have no enough words to express how God is working with his word through you in me. Everytime, God always left his message to me. Thank you so much and God bless all your services and everything that belongs to you. Keep on teaching the gospel.You are one of our generation' blessings. Much love.
Dr. Mamusha....Enkuwan teweledk! I am always in owe how you keep saying yes to God! How you let him show his beauty through you! We see God through you! Thank you! I long to say yes to God like you have in every way! Blessings!
#እነሆ_ንጉሥሽ
#የማቴዎስ_ወንጌል_ትምህርት
#የናዝሬቱ_ኢየሱስ
📖 ማቴ 2 : 16-23
✔️ የዛሬ አንቀጾች
* ኢየሱስ ከተሰደደ በኋላ የሆነውን አሰቃቂ ድርጊት
* ወደ ናዝሬት መመለሱ
📖 ከቁ.16- 18 (የሕፃናቱ ጭፍጨፋ)
- መሢሑን ከሄሮድስ እግዚአብሔር እንዴት እንዳዳነው የሚያሳይ አንቀጽ ነው።
- ሙሴን ባዳነበት ትድግና አዲሱን ሙሴ አዳነው (የሙሴና የኢየሱስ መመሣሠል)።
- የፍትሕ አምላክ ዋጋ ይከፍላል። ግን የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆኗል።
- ማቴዎስ በኢየሱስ መውጣት የሆነውን የመንደሯን ሐዘን ሲያስብ ያገናኘው በኤርሚያስ 31:15 ካለው ከትንቢት ፍጻሜነቱ ጋር ነው።
📖 ኤርምያስ 31 : 15፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።
- የእነኚህ እናቶች እንባና ለቅሶ የትንቢት ፍጻሜ ነው ይለናል።
* ኤርሚያስ 31 እና ማቴዎስ 2 እንዴት ሊገናኝ ቻለ?
- የራሔልን እንባ የተስፋ በር አድርጎ ያነሳዋል፤ "ራሔል አለቀሰች" ብሎ አያበቃም።
- የራሔል ለቅሶ የእግዚአብሔር አስደናቂ ተስፋ ምክንያት ነው። የእስራኤልን ተስፋ መጀመር አብሳሪ ለቅሶ ነው።
📖 ቁ. 17 "ለፍጻሜሽ ተስፋ አለ"
📖 ቁ. 27 "እመልሳለሁ"
- የራሔል ለቅሶ የረጅም ዘመን ተስፋ አመላካች ነው።
📖 ኤርምያስ 31: 31፤ እነሆ፥
ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤
- የራሔል እንባ የአዲስ ኪዳን ማብሰሪያ ነው።
📖 ቁ. 34
- የራሔል ለቅሶ ኃጢአት የተወገደበትና አዲስ ሕግ የተጻፈበት ነው። የራሔል እንባ የአዲስ ኪዳን ተስፋ ነበር።
- ራሔል ስታለቅስ ይከፈታል የተባለው አዲስ ኪዳን አምጪው ኢየሱስ ነበር።
- የራሔል እንባ የተስፋው መነገሪያ ነበር፤ የቤተልሔም እናቶች እንባ የመፈጸሚያው እንባ ነበር።
- የምርኮ ማብቂያና የአዲሱ ኪዳን ማብሰሪያ ምልክት ነው ኢየሱስ።
📖 ዕብራውያን 12 : 24፤
የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።
- ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ፣ የኃጢአት ምርኮ ዘመን ማብቂያ፣ የአዲሱ ኪዳን ጅማሬ፣ የኃጢአታችን መወገድ፤ የሕጉ በልባችን የመጻፍ ብስራት፣ በኃጢአት ምክንያት የነበረ እንባ መታበስ ምልክት፣ የተስፋ ፍጻሜ ምልክት ነው።
- እግዚአብሔር በክርስቶስ ያመጣው ዘመን፦ ለምናምን የእንባ ማክተሚያ፣ የኃጢአት ቀንበር ማክተሚያ፣ የምርኮ ማክተሚያ፣ የእንባ ማክተሚያ፣ የአዲስ ኪዳን ጅማሬ ነው።
📖 ራእይ 7 : 17፤
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፥ ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።
📖 ራእይ 21: 4
እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።
- መዳናችን ሲጠቃለል እንባ ታብሶ ነው፤ እንባ የሚያብሰው መጥቷል።
- የኃጢአትና የምርኮ ለቅሶ የሚያበቃው በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ አዲስ ልደት በመቀበል ነው።
- መሻሻል አይለውጥም፤ ጥገና ሳይሆን የሚያስፈልገን የልብ ለውጥ ነው የሚያስፈልገን። አዲስ ልብ ሲሰጠን በሕጉ መኖር የሚያስችለንን መንፈስ አብሮ ይሰጠናል።
- የራሔል ለቅሶና የቤተልሔም እናቶች ለቅሶ ወደ ኢየሱስ ሊመልሰን ይገባል።
✔️ ሁለተኛው አንቀጽ
📖 ከቁ. 19-23 የሌላ ነገር ፍጻሜ ነው
* ሄሮድስ ከሞተ በኋላ የኢየሱስ መመለስ
* "ናዝራዊ ይባላል" የተባለው መፈጸሙ
- የዚህ ቁጥር መልዕክት የንጉስን ከተማ ትት መውረዱ ነው።
* እንዴት ወረደ?
- ናዝሬት የማትታወቅ ከተማ ነበረች
- ናዝሬት የተናቀች ከተማ ነበረች
- የማትታወቀውን ከተማ መጠሪያው አድርጎ መጣ
- "የናዝሬቱ ኢየሱስ"
✔️ የኃይል ምልክት
✔️ መጠሪያው ሆነ
* ናዝራዊ
✔️ የተለየ
✔️ የተቀደሰ
- እንዲህ ወርዶ የመጣው እኛን ለማዳን ነው። ወርዶ ነው ያገኘን፤ ልንደርስበት አንችልም ነበር።
📖 ኢሳ 53: 2-
- እኛ ተንጠራርተን ሳይሆን እርሱ ወርዶ አግኝቶናል።
- የመናቅ ምልክት የነበረውን ወስዶ የማዳን ኃይል አደረገው።
- ያዳነን በመውረድ ነው፣ በመጨረሻው ዝቅታ ነው፣ የናዝሬቱ በመሆን ነው።
- የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲባል፥ ዝቅ ያለው፣ ደም ግባት የሌለው፣ ከማትታወቀው ከተማ የመጣው ማለት ነው።
✔️ ይሔ ሁሉ ለምን?
* ጥልቅ ታች ያለነውን ለማግኘት
- ተንጠራርትችሁ ድረሱበት ብንባል አንደርስበትም ነበር፤ እኛ ከፍ ብለን ሳይሆን እሱ ወርዶልን ነው የአገኘነው።
- ለመዳን ምንም ያሟላነው ነገር የለም፤ እርሱ ነው ያዳነን።
ይህን የምትጽፍልን ስው ጌታ ኢየሱስ ዘመንህን ይባረከው ይህን በቀጥታ ማስታወሻየ ላይ የማስቀምጠው
Eeessssyyyeee
Amennenennnemnmee
Eresuse newo yadanene
Tabarkulige
Geta eyesus yibarkachu be xhuf silemtaskemtulin
Tebareku, with lot of blessings
እግዚአብሔር ይባረካችሁ ትምህሩቱ ካለቀ በዋላ ይሄን ወደ ማሰታወሻዬ ሳልቸኩል ተረጋግቸ ነዉ የምፀፈዉ 𝖙𝖍𝖆𝖐𝖚𝖘 𝖇𝖊 𝖇𝖊𝖑𝖘𝖘𝖊𝖉 𝖆𝖑𝖑
ዶ/ር ማሙሻ ጌታ ይባርክህ ጌታ እኔን ያገኝኝን ቀን አስታወስከኝ የናዝሬቱ ኢየሱስን ለዘለአለም የተመሰገነ ይሁን በእውነት አኔ ቃላት የለኝም እንደው ዝም ብዬ አመሰግንሀለው ተመስገን
ዶ/ር ከዚህም በላይ እግዚአብሄር የናዝሬቱን ኢየሱስን እንድታስተምረን እድሜም ጤናም ይስጥህ
ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ ጸጋውንና ጥበቡን ያበዛልህ ጌታ ይባረክ
የናዝሬቱ ኢየሱስ የእኛ የምስጊኖቹ የሃጢያተኞቹ
አፍቃሪያችን ነው 💚
ወዳጃችን ነው 💚
አለኝታችን ነው 💚
መጠጊያችን ነው 💚
ጌታሆይ ቃልህ ይጣፍጣል!
ወንድም ማሙሻ ይብዛልህ: ልጆችህ ይባረኩ 🙏🙏🙏
ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ቃልህ እንደት ጥልቅ ነው ኦ እግዚአብሔር ሆይ በቃልህ ያለውን ሃሳብ እንድንረዳው እርዳን።
እኛ የምናነበው እኮ ከላይ ከላይ ነው 😢
God bless you all equip media servants!
እዴት በጥልቅ ፍቅር ህ ነዉ የወድከኝ😭 የኔጌታ ተመስገን አባ አመሰግናለሁ😭🙏🏽
አሜንንንን አሜን 🙅የናዝሩቱ እየሱስ አዳኛችን አንተ ዝቅ ብለህ እኛን ከፍ ያደረግከን ስምህ ይባረክ 🙏ዶር ማሙሽ ፋንታ ተባረክልን ይሄን መገለጥ የሰጠህ ጌታ ይባረክ ፀጋው ይብዛልህ 🙏💐
Haleluya geta eyesus yibarikih dr❤❤ bertu❤
የናዝሬቱ ኢየሱስ እርሱ ነው ክብራችን
ዶክተር እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ አተን ሳስብ ትውልድን አስባለው እደኔ የሚሰማህ ሺ ትውልድ ይኑር ጌታ እስኪመጣ ምንም አትሁን እድታረጅ ራሱ አልፈልግም በጣም ነው የምወድህ በስስት ነው የማይህ ምንም እንከን አይገኝብህ እዲው እደጨከንክ ጌታ ይምጣ የኔ እንቁ ወደ እውነት ስላስጠጋህኝ ጌታን ስላተ አከብራለው ኢየሱስ ክርስቶስ ትናትናም ዛሬም እስከ ለዘላለም ያው ነው።
ጌታ ይባርክህ
አሜን
We are millions with you, sis. God bless your generation for his glory! God bless Dr. Mamusha's generation for his glory!
amen❤
✞ክብር ለእግዚአብሔር አብ ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።✟❤
“ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
- ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)
ብዙ ፀጋ ብዙ መገለጥ ብዙ ክብር ብዙ ሰላም የእግዚአብሔር አብሮነት ይብዛላቹ እናንተን የሰጠን የተባረከ ነው!!!
ጌታ ይባርክህ ፓስተር ማሙሻ
የራሄል እንባ ተስፋ...የቤተልሔም እናቶች እንባ የተስፋው ፍጻሜ .....ለፍጻሜያችን ተስፋ ይኖር ዘንድ( የተስፋ ፍጻሜ.. ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ ) ለእንባ መታበስ ምክንያት ሆኖ የመጣው የአዲስ ኪዳን መካከለኛ(አዲስ ኪዳንኤር31÷31 ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ..) የሆነው ባይወርድልን ባይመጣልን ልንድን ልንተርፍ የማንችል ልንደርስበት የማንችል ....የማይገባን ወዶ ፈቅዶ የመጣልን የወረደልን የናዝሬቱ❤ ኢየሱስ❤ ሃሌሉያ ስሙ ለዘላለም የተባረከ ይሁን🙏
ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ ይባርክህ በጣም የምንወድህ ዶ/ር ማሙሻ ጸጋም ይብዛልህ የአንተ የሆነው ሁሉ የተባረከ ይሁን ❤🙏 ሁላችሁን እግዚአብሔር ይባርክ Thank You much love❤
ይሄን እየሱስ አስደናቂ ነው! ፍቅሩ ልቤን ይዘዋል፥ በፍቅሩን ገና ብዙዎችን ይማርካል፡ ተባረኩ የዚህ ንጉስ ቤተሰቦች፡ ወንድሜ ማሙሻ ጸጋው ይትረፈረፍልህ።
ኢየሱስዬ አይኖቼ ታውረው ብራን የጎደለኝ ነበርኩ ወደኔ መተህ አይኔን ስለከፈትክልኝ አመሰግንአለው ክብር ላተ ብቻ ይሁን እወድሃለው ጌታ
ዘመን ይባረክ ❤❤❤
ለህዝቡ ነዉ የመጣው ❤️❤️❤️
May the Lord bless you all ,🙏🙏♥️♥️
እኔ ቃል አጣሁ እንዴት ያለ መታደል ነው! ወርዶ ከፍ ላደረገኝ ለናዝሬቱ ኢየሱስ ክብር ይሁን። ወንድሜ ይብዛ ይጨመርልህ ዘመንህን ሁሉ የእርሱን በጎነት ተራኪ ያድርግህ አሜን
እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ በአገልግሎትህ በጣም እየተበረኩ ነው፡፡
tebarek
Dear Dr. Mamusha,
I have no enough words to express how God is working with his word through you in me. Everytime, God always left his message to me. Thank you so much and God bless all your services and everything that belongs to you. Keep on teaching the gospel.You are one of our generation' blessings. Much love.
ዋው የብዙ ጊዜየ ጥያቄ ዛሬ ተፈታልኝ በእውነት ዶክተር ማሙሻ ጌታ ኢየሱስ ዘመንህን ይባርከው ። ማቴዎስ 2 በፍፁም ከኤርምያስ 31 ጋር ግንኙነት ያለው አይመስለኝም ነበር ።
መፅሃፍ ቅዱሳችን ራሱን በራሱ ይተርጉማል የሚለውን እውነት ይህ ነው።
እኛንም እንድንረዳው አንተንም እንድትናገረው የረዳን ቅዱስ እግዚአብሔር አባታችን ክብር ይሁንለት ።
Tebarek 🥰❤️🌹🌹🌹
im always waitig tebareku im an student on this timrt
ተባረኩ
#የናዝሬቱ_ኢየሱስ 🙇🏻♀️
Tebareke
Tsega yebzaleh!!
May God bless you and your family what amazing preaching!!!
Dr. Mamusha....Enkuwan teweledk! I am always in owe how you keep saying yes to God! How you let him show his beauty through you! We see God through you! Thank you! I long to say yes to God like you have in every way! Blessings!
ተባረክ
Jesus of Nazareth 👌
ɢᴏᴅ ɪs ʟᴏʀᴅ dr ʙᴇ ʙʟᴇssᴇᴅ ɢᴏᴅɪs ɢʀᴇᴀᴛ hallelujah
Blessings 🙌 🙌 🙌 🙌
ያቃተው ነገር አይ ዶክተር በጣም ነው የምወድህ ደግሞ እፀልይልሃለሁ ።
አሜነ አሜን በቃሉ መገለጥ የባረከ እግዚአብሔር ይባርክ ዋጋህን እግዚአብሔር ይከፍልሀል።
የናዝሪቱ ኢየሱስ እውነተና ወዳጅ 🥰🥰🥰
ጌታ እንዲህ የወረደው እንደት ቢወደን ነው
Blessings 🙌
እልልልልልልልልልልል የናዝሪቱ ኢየሱስ እልልልልልልልልልል የኔ ጌታዬና አምላኬ።
God bless you!
May God bless you and your family what amazing preaching 🙏
አሜን አሜን ንንንንንን ♥️♥️♥️🙏🙏
ameeeen
ክብር ሁሉ ለናዝሬቱ ለኢየሱስ ይሁን
አሜሜንን
Wawu
አሜንንንንንን ምን አይነት መገለጥ ነው እንኳን ክርስቲያን ሆንኩ የዳንኩበትን እወነትን ማወቄ እደለኛ ነኝ📖🙏🙏🙏🙏❤
አሜን አልጠፋም!!!!!አሳዳጅ ቢበዛም!!!!!!
ለረጅም ግዤ ያልገባኝ ነገር ነበር የሀና ለቅሶ አሁን ገባኝ!
🙏🙏🙏🙏
ጌታ ሆሆሆሆሆሆይይይይይይ ልስማህህህህህህ!!!!
በሁለቱም ስልኬ ነው የምሰማው ሰላም እዝቅያስ በሚለውም ሁለቴ ደግሜ በራሴ ተገረምኩ ለካስ ቃሉን ሳነብ ንብብ ክድን ብቻ ነው ማደርገው እንደዚህ ጥልቅ ሚስጥር ያለው ቃል በእጄ እያለ ለኔም ቢበራልኝ ቢገባኝ በድንም ብረዳው
የናዝሬቱ ኢየሱስ ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ ወንድሜ ማሙሻ ቃላት የለኝም ይህ ትምህርት የዳንኩበትን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቄ እንድይዝ እና በውሎዬ እንዳብሰለስለው ነው ።
እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርካችሁ 🙏🙏🙏🖐🖐👏❤️❤️
እግዛብሔረ ይመስገን ተባረክ
What an amazing
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን
Always Excited. God bless you more Dr M ❤💙
EGZBHERE yebarkihi
❤
ከዚህ ትምህርት የተርዳሁት አንዱ የንባብ ድክመታችንም ነው 👇
የእግዚአብሔርን ቃል በደንብ ቆፍረው የከበረውን የሚያገኙት እንዲህ ታስተምራሉ 💚
የእኔ እና የጓደኞቸ ንባብ ግን ዶሮ ጥፌ ለመልቀም እንደምትጭረው ነው ።
😁😁😁
Amen🙏🏾
ጌታ ዘመንህን ይባርክ
😭💖❤🔥💯
መስማት ያስመልጣል!!!!!
እውነት እውነት
ምን ጥሩ ይገኛል?
መልካምስ ይወጣል? ከናዝሬት
ተብሎ ከሚባል ከተናቀ ስፍራ
የሱስ የመዳን ቀንድ ራስ ሆኖ ወጣ።
ሀሌሉያ!!!!ሄሮዶስ ሞቷል!!!!!!
ወይኔ እናንተን የመሰሉ አስተማሪዎች ባስተማሩበት የነዮናታንና ጩፋ ሲጫወቱበት ሲታይ እጅግ ያማል እናንተም ዝም አላችሁ ??? ሐይማኖቱን ሲያሰድቡ
ብስራተ ወንጌልን እየሰማን ነበር ያደግነው እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ
Amen!