እቴሜቴ ሎሚ ሽታ/የመጨረሻዋ የቀበሌ 01 ድንግል/ደራሲ አዳም ረታ/አማርኛ ትረካ/january 2023

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 1 дек 2024

Комментарии • 31

  • @fendom-1
    @fendom-1 Год назад +1

    በጣም የሚገራም ትረካ ነዉ .በረታ ወንድሜ ና እህቴ.Thanks .

  • @ambaw1004
    @ambaw1004 Год назад +11

    አርቲስት አንተነህ አስረስ የዉብዳር እና ድምጸ ወርቃማዋ ተራኪ ብሌን ሳሙኤል ከናንተ ጋር በመስራቴ ታላቅ ደስታ እና ክብር ይሰማኛል ።
    አዳም በጣም የምንወደዉ ድንቅ ደራሲ ነዉ
    ለመረጃ ያህል ካነበብኩት እነሆኝ ።
    አዳም ረታ በ1950 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። በትምህርት አለም - በጂኦግራፊ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብሏል። ሁለተኛ (የማስተርስ) ዲግሪውን ደግሞ በውጭ ሀገር አግኝቷል። የሚፅፈው በአብዛኛው ልቦለዶችን ቢሆንም ግጥሞችንም ይፅፋል። በተለያዩ ጊዜያት ግጥሞቹ በተለያዩ መፅሔቶች ላይ ታትመዋል። ያልታተሙ ግጥሞችም አሉት።[1]
    ከተደራሲው ጋር የተዋወቀበት እና በኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ተከታታዮችና አንባቢዎች ልብ ውስጥ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበት “አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት የታተመው በ1977 ዓ.ም ነው። (በዚህ መድብል ውስጥ አራት ስራዎችን አዋጥቷል፡ “ድብድብ”፣ “ዕብዱ ሺበሺ”፣ “ሲሮኮ” እና “ሲፊንክስ”)[2] ሜጋ አሳታሚ ድርጅት በ1990 ዓ.ም ባሳተመው “ጭጋግና ጠል” የአጭር ታሪኮች ስብስብ “ዘላን” የተባለው ልቦለዱ ታትሟል። እነዚህ ሁለቱ ከሌሎች ደራሲዎች ስራዎች ጋር የታተሙለት ስለሆነ እንደ ወጥ ሳይቆጠሩ ነው ከላይ የሰፈረው የተባለው።
    በ1981 ዓ.ም በኩራዝ አሳታሚ የታተመው “ማህሌት” የደራሲው የመጀመሪያ ወጥ የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ መፅሀፍ ነው። በሻማ ቡክስ በ1997 ዓ.ም የታተመው “ግራጫ ቃጭሎች” እንደ ብሉይ (classic) ሥራ ሊታይ የሚችልና የደራሲው ልዩ ብቃት የታየበት ወጥ ረጅም ልብወለድ ነው።
    በ2001 ዓ.ም ሁለት ልዩ ስራዎች ይዞ የቀረበው አዳም፡ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው “አለንጋና ምስር” እና እርስ በርሳቸው በቀጭን የታሪክ ክር የሚገናኙ ልብወለዶች (ኖቬላዎች) ያካተተው “እቴሜቴ ሎሚ ሽታ” ለአንባቢያን አበርክቷል። ይህ የአጻጻፍ ስልቱ ሕጽናዊነት የሚባል ሲሆን ደራሲው በሌሎቹ መጻሕፍቱም ውስጥ በስፋት ተጠቅሞበታል፡፡
    በቀጠሉት ሦስት ዓመታት በየዓመቱ አንዳንድ መፅሐፍ ለአንባቢያ ያደረሰ ሲሆን በ2002 ዓ.ም “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር”፣ በ2003 ዓ.ም “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” እና በ2004 ዓ.ም “ሕማማት እና በገና” ታትመው ለንባብ በቅተዋል። “ከሰማይ የወረደ ፍርፍር” በተሰኘው መፅሀፉ ድንቅ የፋንታሲ (“ፈንጠዚያ”) ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን በ”ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ” ለመጀመሪያ ጊዜ መቼቱን ከሀገር ውጭ በማድረግ የውጭውን ሕይወት በስሱ የዳሰሰ ሲሆን ከሌሎቹ ስራዎቹ በተለየ መልኩ ስለሀገራችን ፖለቲካ ወጣ-ገባ መንገድ በታዛቢ አይን ምልከታው፣ ትውስታውን … አስፍሯል፡፡ ሕማማትና በገና የአጫጭር ልቦለዶች ስብስብ ሲሆን ለየት ያለ ቅርፅ ያላቸው አንዳንድ ልቦለዶች ተካተውበታል።
    ፍልስፍናውና ስልቱ ሕፅናዊነት በሚል ስያሜው ይፋ ሆኗል።
    አዳም ረታ በተለየ የአፃፃፍ ስልቱ እና በስራዎቹ ጥልቀት በሃያስያን ዘንድ አዎንታዊ ሂስ እና ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል። ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል…
    “…አዳም ረታ ታዋቂ ደራሲያን ከሆኑት ከሀዲስ አለማየሁ፣ በዓሉ ግርማ፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ ፀጋይ ገብረመድህን… ጋራ መመደብ የሚችል ነው ሊባል ይችላል…” Aklilu Dessalegn
    Adam Reta as a Literary Existentialist: Textual and Descriptive Criticism (2010)
    …ዳኛቸው ወርቁ በ“አደፍርስ” የኢፒሶዲክ ሕግጋትን አጋምሶ ለማስተዋወቅ ከሞከረ ወዲህ በአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ በኢፒሶዲክ ተሟልቶ የተገኘ ድርሰት “ግራጫ ቃጭሎች” ነው። … “ግራጫ ቃጭሎች” ከገፀ-ባህሪው አካልና ሥነ-ልቡና አሳሳል አልፈን ድንቅ ዓላማውን፣ ቋንቋውንና የሕይወት አተረጓጎሙን ስንመለከት የአዳም ረታ እውቀትና ልምድ ጠንከር - ጠጠር ብሎ በመዝገቡ በኩል ሲያስተጋባ ነው የምንመለከተው።…
    ዓለማየሁ ገላጋይ -
    ደራሲና ጋዜጠኛ
    ኢሜጅ መጽሔት፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 02፣ ግንቦት 1998
    ለሕትመት የበቁ የአዳም ረታ ስራዎች
    አባ ደፋር እና ሌሎች ታሪኮች - 1977 ዓ.ም (“ድብድብ”፣ “ዕብዱ ሺበሺ”፣ “ሲሮኮ” እና “ሲፊንክስ”)
    ማሕሌት - 1981 ዓ.ም
    ጭጋግና ጠል እና ሌሎች - 1990 ዓ.ም (ዘላን)
    ግራጫ ቃጭሎች - 1997 ዓ.ም
    አለንጋና ምስር - 2001 ዓ.ም
    እቴሜቴ ሎሚሽታ - 2001 ዓ.ም
    ከሰማይ የወረደ ፍርፍር - 2002 ዓ.ም
    ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ - 2003 ዓ.ም
    ሕማማትና በገና - 2004 ዓ.ም
    መረቅ - 2007 ዓ.ም
    የስንብት ቀለማት 2008 ዓ.ም
    አፍ 2010 ዓ.ም

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  Год назад +1

      አምብሽዬ ያለ አንተ ይህ ስራ ምንም ነበር ብሌንሻም የስራዉ ብሌን ነበረች ...ለአዳም ከዚህም በላይ ይገባዋል
      long live adam reta

  • @TadeleErdachew
    @TadeleErdachew 7 месяцев назад +2

    JUST WOW ANDE JEMIRE CHERISHE NW YETENSAWUT.

  • @wintanakibrom192
    @wintanakibrom192 5 месяцев назад +1

    Betam arif new ketlubet

  • @abebahabte8469
    @abebahabte8469 6 месяцев назад +1

    ጥሩ ነዉ 👌

  • @hayat905m
    @hayat905m 6 месяцев назад +1

    ምርጥ ደራሲ እና ምርጦች ናችሁ እናተ በትረካችሁ

  • @bellameetube4256
    @bellameetube4256 3 месяца назад +1

    Fantastic book! Thank you for the amazing narration-keep up the great work! Listening from US ❤️

  • @fekareted
    @fekareted Год назад +1

    Amazing as usual.

  • @binman3320
    @binman3320 Год назад +2

    Antenh and Blen excellent job!! amazing 👏 የአዳም እረታ ምስል ከሳች ድርሰት : የአንተነህ ድንቃ የትረካ ጉብዝና : የብሌኔየ ብቃት : ተሰረቅራቂ ድምፅ/ which is perfect intonation for the story/ ...በጣም ግሩም ድንቅ ነው :: ታሪኩንም ወድጀዋለሁ :: በርቱልኝ

  • @brukzewdu4754
    @brukzewdu4754 Год назад

    ኦ አዳም ኦ ብሌን

  • @martaababu4035
    @martaababu4035 Год назад

    በጣም እናመሰግናለን

  • @grmbyn1
    @grmbyn1 Год назад +1

    Thanks for narrating/playing this amazing novel. It gives perspective of the 70's/80's or 90s young folks

  • @yaredenayared8873
    @yaredenayared8873 6 месяцев назад +2

    እንዲህ አይነት አተራረክ የትም ሰምቼ አላውቅም ድንቅ ነው!!! እስከ ዛሬ እናንተን አለማወቄ ቆጨኝ። በርቱ አቦ!

    • @Derese-sh7dk
      @Derese-sh7dk 5 месяцев назад +1

      ደራሲውንም ስሙት ምርጥ ነው

  • @belachewshiferaw7136
    @belachewshiferaw7136 Год назад +1

    🙏🙏🙏👌👌👌

  • @biniyamdejene2138
    @biniyamdejene2138 4 месяца назад

    Still now yr channel is excellent please ye adam reta yesenbet kelematen lekekut

  • @bereketyirgu4227
    @bereketyirgu4227 Год назад

    አይ ሎቨ አኤት it is good!

  • @martaababu4035
    @martaababu4035 Год назад

    መረቅን ተርኩልን

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  Год назад +2

      መረቅን ሙሉዉን ለመተረክ የደራሲ አዳም ረታን ፈቃድ ማግኘት ይኖርብናል እንጂ ብንተርከዉ ክብሩ ለእኛ ነው
      እናመሠግናለን

    • @martaababu4035
      @martaababu4035 Год назад

      ባለፈዉ ቀርቦ ነበር ቀጣዮን

  • @abiyutamirat8187
    @abiyutamirat8187 Год назад +1

    ገጸ-ባህሪያቶችን ህይወት ነው የዘራቹሁባቸው፤ ግሩም የሆነ የትራካ ችሎታ ነው ያላቹ! ከጀርባ ያለው ድምፅ ላይ በጣም እንደ ተጠበባቹሁበት ስራቹ ይመሰክራል! በተለይ አልጋው ሲጥ ሲጥ ሲል😮 ❤👏

  • @samm8405
    @samm8405 Год назад

    Bungee jump- በንጂ ጃምፕ

  • @grmbyn1
    @grmbyn1 Год назад +1

    ምስል ከሳች

  • @demesewmereid9147
    @demesewmereid9147 10 месяцев назад

    አይስብም ለዛም የሌው ከተራኪውም ጭምር

  • @bettytube2
    @bettytube2 Год назад +1

    አለ አደል 123 የሚደጋገመው ደራሲው መቼም አይጽፈውም

    • @ambaw1004
      @ambaw1004 Год назад

      መጽሐፉ ላይ የተጻፈዉን ነዉ የተረከችልን ፤ " አለ አይደል "
      ደራሲው ለካራክተርዋ ደግሞ ደጋግሞ የጻፈዉን ነው የተረከችው ቤቲ

  • @kak7443
    @kak7443 Год назад

    ምነው ጠፈችሁ አልል ነው ያልኩት ስትመለሱ

    • @ethioemmatube
      @ethioemmatube  Год назад

      እናመሰግናለን የተሻለ ነገር ለመስራት ግዜ እየወሰድን ነበር አንጠፋም