‪@MunitMesfins‬

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 16 сен 2024
  • ‪@MunitMesfins‬
    Live your truth! Be brave! Take a chance on your dreams, so you may never regret the life you lived!
    እውነትሽን ኑሪ ~ እስቲ ~ እውነትህን ኑራት
    ውስጤን ሳልመረምር ጠልቄ ሳላውቀው
    ምኞት ፍላጎቴን ልቤን ሳላነበው
    ተስጦ እና ህልሜ በፍፁም ሳይገባኝ
    ስንት ዘመን አለፈ ግራ እንደገባኝ
    ምን ይሉኛል ብዬ ራሴን እየደበኩ
    ምኞት ፍላጎቴን ህልሜን እየበደልኩ
    ጊዜ በተአምሩ ጥሎ እየከነፈ
    ውስጤን ሳልተነፍስ ስንት እድል አለፈ
    ያንን ባደርግ ኖሮ
    ይሄን ብለው ኖሮ
    ሄጄ ቢሆን ኖሮ
    ትቼው ቢሆን ኖሮ
    ኖሮ እያሉ ኖሮ
    ከመኖር አማሮ
    ዛሬ መነሳት ነው
    እራስን መርምሮ
    በስኬት እንዲያብብ ፈክቶ ህይወታችን
    ብርሃን እንድንሰጥ በርተን እራሳችን
    ውስጣችንን አይተን ኮርተን በሀብታችን
    እንጠቀምበት በእድሜ በጊዜያችን
    እንድናይ በዓይናችን ህልማችን ተፈቶ
    ተስፋችን ለምልሞ ፍሬውን አፍርቶ
    ፈተናው ቢበዛም በእምነታችን ጸንተን
    እንጓዝ ወደፊት አንድ ህይወት ነው ያለን
    munit.mesfin
    መብቱ የተጠበቀ! All rights reserved!
    #munit #munitandjorg #noronoro #ethiopianmusic

Комментарии • 11