የፆም አይብ እና ክትፎ/ Vegan Kitfo and Ayib

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 10 фев 2025
  • ሰላም ጤና ይስጥልኝ
    ዛሬ አይብ፤ስጋና ቅቤ ለማትመገቡ ቀላልና ጣፋጭ የፃም አይብና ክትፎ አዘገጃጀት ይዤ መጥቻለሁ።
    መጀመሪያ ዘይቱን መቀመም(ማንጠር)
    ግብአት
    1. ሬፕ ሲድ ዘይት (እሳት ላይ የሚቆይ ማናቸውም ዘይት መሆን ይችላል)
    2. ኮረሪማ የተፈጨ
    3. የደረቀ ኮሰረት
    አዘገጃጀት
    1. ዘይቱ ሞቅ ሲል ቅመሞቹን መጨመር
    2. ለ5-10 ደቂቃ ማማሰልና ማቀዝቀዝ
    የፆም አይብ አሰራር
    ግብአት
    1. የተነጠረው ዘይት
    2. ቶፉ
    3. ኮረሪማ
    4. ሚጥሚጣ
    5. ጨው
    አዘገጃጀት
    1. ቶፉውን ውሃውን ማውጣት( ውሃው በቀላሉ እንዲወጣ ቶፉውን በረዶ ክፍል ማስገባትና ለማብሰል ስንዘጋጅ ማቀዝቀዣ ውስጥ መክተት)
    2. ቶፉውን መፈቅፈቅ
    3. ዘይቱንና ቅመሙን በማድረግ ማሸት
    የፆም ክትፎ አሰራር
    ግብአት
    1. የቬጋን ስጋ (ቴስቲ ሶያ)
    2. የተቀመመ ዘይት
    3. ኮረሪማ
    4. ጨው
    5. ሚጥሚጣ
    አዘገጃጀት
    1. ስጋውን ከዘይቲ ጋር መጥበስ
    2. ቅመሞቹን መጨመርና ማብሰል
    ጤናማ ሬሰፒዋችን ማየት ሚመቾት ከሆነ like, subscribe comment ያድርጉ።
    All the videos, songs, images, and graphics used in the video belong to their respective owners and I or this channel does not claim any right over them
    አመሰግናለሁ

Комментарии • 1