“62 አመት ያገለገልኩበትን ምስጢር ልንገራችሁ”Dr. Betta_Mengistu Pastor Mekashaw_Shimelash NikodimosShow TigistEjigu

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 18 окт 2024
  • የተወደዳችሁ የኒቆዲሞስ ሾው ቤተሰቦች፡ ከታች ያለውን link ላይክ በማድረግ facebook ገፃችንን እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ፡፡ 👇👇
    / nikodimosshow
    ፕሮግራማችንን እየተከታተላችሁ ገንቢ አስተያየታችሁን ሁል ጊዜ ስለምትለግሱን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፡፡ ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አዳዲስ ቪዲዮ እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ ማድረግ አትርሱ፡፡
    This Video Clip is Dedicated Only to Nikodimos Show Channel /Tigist Ejigu/!
    Subscribe today for latest Videos Here:- / nikodimosshow
    Facebook:- / nikodimosshow
    Instagram:- / tigisttg
    Awtaru Kebede,Ethiopia,Ethiopian Gospel Song,Amharic Gospel
    © Copyright:- #Tigist Ejigu /Nikodimos Show/ 2024

Комментарии • 191

  • @hannamankebmill
    @hannamankebmill 6 месяцев назад +15

    ለምን አይነት ሰዎች አክብሮት አለኝ መሰላችሁ
    ተበደልን ብለዉ በዳይ ላልሆኑ
    አስከፉኝ ብለዉ ለማያስከፉ
    በደረሰባቸዉ መታለል : መሸወድ : መገፋት ዉስጣቸዉ ያለዉን ቅንነትና መልካምነት አዉጥተዉ ላልጣሉ👌🥰 አባ አንተ ማለት ይሄን ነህ ከሂይወትህ ብዙ ተምሬአለሁ ደግሞም አትሪፌአለሁ
    ታላቅ ሰው ተከትለህ #ተራ ሰው ልትሆን አትችልም!
    መንፈሳዊ ሰው ተከትለህ #ስጋዊ ልትሆን አትችልም! እኔ እና ቤተሰቤ ዛሬ ለደረስንበት ቁመና እናንተን አለማመስገን ንፉግነት ነው ። አባ እንዳንተ አይነት ሰዎችን ማግኘት መባረክ ነው እኔ እና ቤተሰቤ ደሞ በእናንተ ተባርከናል አባ ስለመልከምነትህ ስለአሳቢነትህ ስለ ምሳሌነትህ ስለ ሩሁሩህነትህ ስለ አባትነትህ አመሰግናለሁ ከማለት ውጪ የውስጤን የሚገልጽ ቃል የለኝም እግዚአብሔር ያክብርልኝ።
    የኔ ደግ አባት ከፊትህ ያለው ጊዜ ሁሉ በደስታ የተዋበ እንዲሆንልህ ፀሎቴም ምኞቴም ነው ። 🙏🥰

    • @rediattelila7755
      @rediattelila7755 6 месяцев назад +4

      እኔም ስለ አባ የምናገረው አለኝ! ለእኔ እና ለቤተሰቤ እጅግ ፍቅርን፣ አባትነትን እርህራሄን ያሳየን ውድ ሰው ነው! እረኛ እና አባት በጠፋበት ዘመን ላይ እስክንገረም ድረስ እንዲህም አለ እንዴ እስክንል ለቤተሰቤ ለልጆቼ ያሳየህንን ፍቅር መቼም አንረሳም ። በተለይ ባሌ በታመመ ሰአት አንፑላስ ውስጥ ገብተክ እንደ እፃን ልጅ ፅጉሩን ያሻሸህው ነገር መቼም ካንጀቴ አይጠፋም አሁን እራሱ አይኔ በእንባ ይሞላል። አባ በጣም እንወድሃለን እናከብርሃለን!

  • @Jesusislord-th8ze
    @Jesusislord-th8ze 6 месяцев назад +3

    አቤት በችካጎ ኮንፍራንስ የነበረው ፍቅር እጅግ ይጣፍጣል አሁን ላይ ግን በዘር ቤተክርስቲያን የከፈለበት ግዜ ነው እግዚአብሔር ወደ ቀደመውፍቅርና እግዚአብሔርን መፍራት ይጨምርብን ዶር ቤተ እትዬ ሶፍ ፓስተር ገነቱይግዛው አሁንላይ ወደ ጌታ ሄደዋል ተባረኩ 🙏🙏🙏

  • @biniterefe1216
    @biniterefe1216 6 месяцев назад +3

    የኛ ዘመን ድንቅ እንቁ በብዙ እሳት የተፈተነ ፅናት ታላቅ ልበ ሰፊነት ከመጠን ያለፈ የታጋሽነት ጥግ የቤዛ international ቤተክርስቲያን ሞገስ የኛ ስጦታ ጋሽ ቤተ መንግስቱ ስለ እርሰ ቃላት ያጥረኛል የኔ ውድ አባት የማይነጥፍ ትጋት ❤❤❤❤❤❤❤

  • @bekeleemmanuel9569
    @bekeleemmanuel9569 6 месяцев назад +28

    እባክሽ ትእግስት እኝህ አባት ትልቅ የእግዛብሄር ግሬስ መንፈስ ቅዱስ የሚያናግራቸዉ ከሳቸዉ ብዙ ለትዉልድ የሚተላለፍ ነገር ስላላቸዉ አስቸግረሻቸዉም ቢሆን ለብቻቸዉ ሰፊ ጊዜ ወስደሽ እረፍት በመስጠት ተከታታይ ከመጀመሪያቸዉ አሁን እስካሉበት ቀርፀሽ ብታስተላልፊልን አንቺም ትልቅ ስራ ይሆንልሻል ለእኛም ከእኛም በሃላ ላለዉ ከፍተኛ እድል ይሆናልን እባክሽ ተባበሪን እህትዋ ::

    • @hibisetkassay923
      @hibisetkassay923 6 месяцев назад +2

      እውንት ነው ብቻቸውን መጽሀፉ ናቸው እባክሽ ቲጂ

    • @jaspertom9527
      @jaspertom9527 6 месяцев назад +1

      እኔ ለሁሉ ሰው መልካም አስተያየት አለኝ የዶ/ር ቤተ ንግግር ግን ብዙ አላረካኝም ምክንያቱ ደግሞ ጌታዬ ኢየሱስ ከዚህ በላይ ትልቅ እንድንሆን ስላስተማረኝ ነው! የእግዚአብሔር ግሬስ መንፈስ ቅዱስ የሚያናግረው ሰው ስለ ጥሬ ስጋ፣ ስለ ልሳን፣ ስለ እንግሊዝኛ ጀርመንኛ ጥሩ መናገር ወዘተ. ተራ ተርታ የማያንጹ ነገሮች አይናገርም እንደውም ትልቅ መገለጥ ይኖረው ነበር! ይህንን የምለው በመንፈስ ቅዱስ ስለምተማመን እንጂ በራሴ በመኩራት አይደለም ያወራው ነገር ሁሉ ከተራ ወሬ አላለፈም! የኛ መንፈስ ቅዱስኮ እንዴት ያለ እንደሆነ ለማስረዳት ራሱ በዚህ ላይ ጊዜ አይበቃም! ጌታችን ኢየሱስ እጅግ ታላቅ አምላክ ነው! ተባረኩ!

    • @bekeleemmanuel9569
      @bekeleemmanuel9569 6 месяцев назад

      @@jaspertom9527 ፍፁም አንድዬ ብቻ ነዉ ::ጥቃቅን ጉድፍ ለቃሚ ሆይ እስቲ የራሳችንን ትላልቅ ግንዲላ የሚታዩ ችግሮች እንፍታ ሰዉየዉ በትዉስታ ድሮ ጥሬ ስጋ ክትፎ እንዴት እንደሚመገቡ በጋራ በግልፅ አወጉ እና ለአንተ ደስ እንዲልህ ክርስትያን ክርስትያን እንዲሸቱህ ቁሎ ቆርጥመን ሲገኝ እንጀራ በሹሮ ደቅሰን ማለት ነበረባቸዉ ? ሁሉም የየራሱ የአገር አመጋገቡን ያደንቃል ያከብራል ይወዳል በዉጭዉ አለም ደግሞ ልዩ ቦታ አለዉ :: ደግሞ አባታችን በዚህ እድሜ ለጤናቸዉ ሲሉ በአሁኑ ሰአት ሊመገቡም ላይመገቡ ይችላሉ: :ሌላዉ ቋንቋ መግባቢያ ነዉ ልጆችን በልጅነታቸዉ ከገራሀቸዉ እስከ አምስት ቋንቋ ማቀላጠፍ ይችላሉ ሰዎች ደግሞ በተለያየ አጋጣሚ በቋንቋ ሲበለፅጉ በፍሬንች በስፖንሽ እንግሊሽ............በመሳሰሉት ቋንቋ ወንጌልን በአለም ዙሪያ ማዳረስ አለብን ማለት ምንድነዉ ችግሩ ?እኔ ሌላ ምንም አልልም ከእናንተ ምንም ሀጢያት የሌለባት ይዉገራት እንዳለዉ የሳቸዉን ጉድፍ ደርዳሪ አቅሙ ካለህ መዉገር ትችላለህ ::

    • @rediattelila7755
      @rediattelila7755 6 месяцев назад

      ​@@jaspertom9527ወንድሜ ወይም እህቴ በጣም ተሳስተሻል በመንፈስ መመርመር ብትችይ ጋሽ ቤተ ላይ ያለውን መንፈስ ትረጂው ነበር! ጋሽ ቤተ ጴንጤ አይደለም የክርስቶስ ተከታይ እንጂ ለዚህም ነው አስመሳይ ያልሆነው። አየሽ ስጋዊም ስለሆንን ምድር ላይ ያለውን ኑራችንን እያዋዛ እያጫወተም ነው የሚያወራው። sense of humour ይባላል።

    • @SirakTom
      @SirakTom 6 месяцев назад

      @@jaspertom9527
      ምን አይነት አስተያየት ነው?
      ”ወንድሞቼ ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህን አስተውሉ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ፣ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና።“
      ‭‭ያዕቆብ‬ ‭1‬:‭2‬, ‭19‬-‭20‬ ‭NASV
      ጭብጥ የሌለው ትችት ነው።

  • @Abiyot_Gurasho
    @Abiyot_Gurasho 6 месяцев назад +3

    ህያዉ መስክሮቻችን "እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን...🙏

  • @almazyimam575
    @almazyimam575 6 месяцев назад +14

    ቲጂዬ በጣም አመሰግንሻለሁ እወድሻለሁ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ ምን እላለሁ ከብዙ ዘመን በኋላ ጋሼ ዶ/ር ቤተን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰርጉ ዕሀት ነበር ያየሁት አኔም የዚያን ጊዜ 6 ክፍል ነበርኩ ከዚያ በኋላ በዚህ ፕሮግራም ላይ ጸጋው በዝቶለት ሞገስ ተላብሶ ስላየሁት እጅግ ሐሴት አደረግሁ ነፍስ አለቀረልኝም ውድ ባለቤቱን እንኳን አጋጣሚ ሆኖ የዛሬ 29 ዓመት ኬንያ አንድ ምሽት መቆየት ስለነበረብኝ ኬኒያ አየር መንገድ አግቻታለሁ እንደውም ወደማርፍበት ቦታ የወሰደችኝ መልካሟ ሴት ወ/ሮ ሶፊ ናት በእውነት ድንቅ የእግዚአብሔር ሴት ናት

    • @arayakassaye
      @arayakassaye 6 месяцев назад

      Please send me contact #

  • @tgtg4562
    @tgtg4562 6 месяцев назад +2

    ፖስተር መከሻው የተወደድህ አገልጋይ እ/ር ይባርክህ። በጣም የበሰለ፣ በፀጋ የተሞላ በእ/ር ቃል የተሰራህና መልካም ሰው ነህ ተባረክልን። ኢትዮጵያ መታችሁ አዳማ ላይ በሰጣችሁን የመሪዎች ስልጠና ተባርከናል ተጠቅመናል።ቲሙን ሁላችሁን ጌታ ጸጋውን ያብዛላችሁ

  • @HanaWoldehana
    @HanaWoldehana 6 месяцев назад +8

    ....ያ ለሞት በሚያደርስ፡በደም ካንሰር በሽታ ታሞ የነበረው ወንድም ዶ/ር ቤት መንግስቱ ነው።....(ሕይወቴ እና ጰንጠቆስጤአዊ እንቅስቃሴ አጀማመር በኢትዮጵያ ገፅ 55 ) ትጂዬ እጅግ ድንቅ መጽሐፍ ነው ጸሀፊው መጋቢ ዘለቀ ዓለሙ(ዶ/ር ) ሁለቱን ብታቀርቢልን መጋቢ (ዶ/ር)ቤት መንግስቱን እና መጋቢ (ዶ/ር) ዘለቀ ዓለሙን ተባረኪ❤

  • @user-cj6gn2kq2k
    @user-cj6gn2kq2k 6 месяцев назад +7

    እንቁ አባቶቻችን ጌታ ረጅም እድሜ ይስጣችሁ

  • @haimanotbelete
    @haimanotbelete 6 месяцев назад +8

    ወንድማችን ዶ/ር ቤተ መንግስቱ ለመጀመርያ ያገኘሁት ከእህታችን ሶፊ ጋር ኬንያ ፉንጅማኖ ዩኒብቨርሲቲ ህብረት አምልኮ ላይ ነው ምናልባት 1995 ይሆናል
    በጣም የተከበራችሁ የተወደዳችሁ ወገኖቻችን ቲጄዬ ፓስተርም ተባረኩልን 💕📖🇪🇹🙏✔️. አሜንንንንንንንንንንን❤️

  • @GetachewBirhan-om3oy
    @GetachewBirhan-om3oy 5 месяцев назад +1

    ጌታ ይባረክ ጋሽ ቤተ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሃብት ነው። አሁን በሚመራት ቤተ ክርስቲያን በቅርበት የማወቅ እድልን አግንቻለሁ። እና በዚች ቤተ ክርስቲያን ያነሳቸው ነገሮች ተገልጠው አይቻለሁ። ፍቅር አለ። ደግሞም ሰው ላይ ነው የሚሰሩት። ቤቱም የታበረከ ነው። ጋሽ ቤተ፣ እትየ ሶፊና ፓስተር Z የሚደንቁ የተሰበረ ልብ ያላቸው አግልጋዮች ናቸው ። ስለናንተ እግዚአብሔርን አመሰግናሁ።

  • @getachewkassahun6876
    @getachewkassahun6876 6 месяцев назад +4

    ዶ/ር ቤተ እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርኮት ከእርሶ ህይወት ምን ተማርክ ቢሉኝ እግዚአብሔር አብዝቶ መፍራት ተምሬያለሁ
    እግዚአብሔር አምላክ ያክብሮት አባቴ በጣም እወዶታለሁ ❤

  • @FrealemMengestu
    @FrealemMengestu 6 месяцев назад +8

    ጋሽ ቤተ አሜሪካን ሚሽን ዳይሬክተሬ ነበርክ ዛሬ አንተን በመስማቴ ጌታ ባንተና በ ትዪ ሶፌ ለስራው ስራ እግዚብሔር ይባረክ

  • @bizuneshmengiste130
    @bizuneshmengiste130 6 месяцев назад +10

    ጋሽ ቤተ መልካም ደግ አባት ስላየሁህ በጣም ደስ ብሎኛል ከነቤተሰብህ እግዚአብሄር አምላክ አብዝቶ ይባርካችሁ ለምድራችን ለህዝባችን በረከት ነህ የወንጌል አርበኛ ነህ እንወድሀለን ተባረክ ቲጂዬ እትዬ ሶፊንም አቅርቢልን ❤❤❤❤

  • @JoshuaTedhe
    @JoshuaTedhe 6 месяцев назад +10

    ጋሼ ዶክተር ቤቴ የእግዚአብሔር ባሪያ የዛሬ 25 አመት ፉንጉ ማኖ ቸርች የነበረን የአምልኮና የቃል ጊዜ የሚገርም ነበር ኬንያ የነበረን ፍቅር መተሳሰብ የሚገርም ነበር አዳ አዴ ጥሩ ባይሆንም ድህነት ጥሩ ነው ያፋቅራል አሁን ከአለም ለሥጋዊ ኑሮ የሚመች አሜርካ ገብተን ተመችቶን በምንኖርበት አገር አንሰማማም እግዚአብሔር ሰዉ ወደመሆን ይመልሰን ደሰ ብሎኛል ሰላየሆት ጌታ ይባርክህ ሶፊን የከበረ ሰላምታ
    ተፈራ

  • @mulugetahailu
    @mulugetahailu 6 месяцев назад +6

    ጋሽ ዳክተር #ቤተ❤❤ ያልተነገረለት የእግዚአብሔር ጀነራል ናቸው: እኔ በግለ በንግግራቸው ብቻ ሳይሆን ፍታቸውን በማየት ጭምር እባረካለው:: ቲጂዬ ብሩክ ነሽ!!

  • @abrahamfentekassa8764
    @abrahamfentekassa8764 6 месяцев назад +3

    እህት ትእግስት ስለ አግልግሊትሽ እ/ርን አመሰግናለሁ ጐታ ይባርክሽ ጸጋውንም ያብዛልሽ። በቅርቡ አ.አ መጥቼ ነበር የመጋቢ መረእድ ለማ "የተጠራ ሕይወት " የሚለውን መጽሃፋቸውን አግኝቼ እያነበብኩ ነው። በጣም ተደንቄአለሁ። የሃዋርያት ስራ መጽሃፍን እያነበብኩ እስኪመስለኝ ድረስ። ሃዋርያት ሳይባሉ ግን ጐታ በቀደሙት ሃዋርያት እደሰራ የሰራባቸው.....ጸልይና ከቻልሽ ጐታ ከፈቀደ ብታቀርቢያቸው.....ተባረኪ
    አብራሃም ከፊንላንድ

  • @teshomegezahegn1069
    @teshomegezahegn1069 6 месяцев назад +1

    ጋሽ ቤተ (ዶ/ር) በመፅሐፍ እጅግ አድርጌ አውቃቸዋለው በጣም እግዚአብሔር አምላክ የተጠቀመባቸው ብርቱ ጀግና የጌታ ባሪያ እንደሆኑ ተረድቻለሁ ።
    ፖስተር መካሻው ወደ ውጭ ከመሔዱ በፊት ሳር ቤት ሙሉወንጌል ፖስተሬ ሆኖ እጅጉን አንፆኛል ።
    ስለእናንተ ጌታ ኢየሱስ ክብሩን ይውሰድ ።

  • @theblessedhand3780
    @theblessedhand3780 6 месяцев назад +12

    የ ተወደዱ አባት😊 እንዲት ደሰ ይላሉ ለብዙ ትዉልድ መነሳት ምክንያት የሆኑ አባት ናቸዉ። ብቻቸዉን ደሞ ብታቀርቢያቸዉ የሕይወት ምስክር ነታቸዉ ብንሰማ🙏🏽

  • @blenlema2437
    @blenlema2437 6 месяцев назад +11

    ፖሰተር መካሻው ትሁት እግዚአብሔርን የሚፈራ የእምነት እና ራእይ ያለው የፀሎት ሰው ጌታ ይባርክህ በረከታችን ነህ ተባረክ

  • @HabitamuTamiru-o6w
    @HabitamuTamiru-o6w 6 месяцев назад +8

    ይህንን interview ሰምቶ ኮሜንት አለማድረግ ይከብዳል ረሰረስኩ ሀሴት አደረግኩ በረታሁ እንደገና በመንፈስ ተሞላሁ ተባረኩኝ ቲጂዬ ስንወድሽ በምክንያት ነው ብሩክ ነሽ ካላስቸገርንሽ ግን ጋሽ ቤተን አንዴ ብትደግሚልን አልጠገብነውም❤❤❤❤

  • @pastorberhanubiru4095
    @pastorberhanubiru4095 6 месяцев назад +3

    👏👏👏ዶክተር ቤተ ከተናገሩት “ቲዎሎጂን ቀንስ ፍቅርን እንጨምር::”
    ድንቅ አባባል ነው።
    ተዎሎጂ የሰው ሀሳብ ነው፣
    ፍቅር ግን የእግዚአብሔር ሀሳብና ባህሪም ነው።

    • @simret-
      @simret- 5 месяцев назад

      They said doctrine not theology. Less doctrine more love.

  • @aidb1275
    @aidb1275 6 месяцев назад +1

    Please we need to hear a lot from Dr Betta, please interview him again

  • @pastoryirdawtessema1426
    @pastoryirdawtessema1426 6 месяцев назад +6

    እግዚአብሔር ይባርክህ ጋሽ ቤተ! ስለ ትውልድ ቅብብሎሽ የተናገርኸውና በተለይ ስለ መንፈስ ቅዱስ ልሳን የተናገርኸው እጅግ አስዱስቶኛል። አንዳንዶች ቡትውልድ ላይ የዘሩትን ክፉ ዙር ነቅለኸዋልና ጌታ ይባርክህ። መንፈስ ቅዱስን በተለይ በልሳን መናገርንና ጥቅሙን የሚያውቀው እየተጠቀመበት ያለ ነውና በሰው አእምሮ አይወሰንም። በአግባቡ የሚጠቀምበት በግልም ሆነ በአደባባይ ራስን ያንጻል፣ በመድረክ ጸሎትም ላይ empower ያደርጋል። ብቻ ከመንፈስ ቅዱስ ይሁን እንጅ በልሳን መናገርን መከልከል እድገት አይደለምና በአግባቡ እንጠቀምበት አንከልከል! እውነቱን ለመናገር በዚህ ዘመን አዳዲስ ሰዎችን እያሰናከለ ያለው ከመንፈስ ቅዱስ የሆነው ልሳን ሳይሆን ኑሮአችን ነው!

  • @metasebiaseboka1347
    @metasebiaseboka1347 6 месяцев назад +4

    i am so impressed Tigie to saw gash dr betie. it has uncountable impact on church history. no word at all

  • @tsegerdatilahun2627
    @tsegerdatilahun2627 6 месяцев назад +7

    ጋሽ ቤተ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ የተባረከ ቤተሰብ እንወድሃለን .

  • @abebamekonenengda7730
    @abebamekonenengda7730 6 месяцев назад +3

    የሑሉ አባት የሑሉ ሰብሳቢ አባ ( ጋሽቤተ) እግዚአብሔር እረጅም እድሜና ጤና ይስጥሕ ይስጥልን ኑርልን !!!!

  • @zewdituzelleke4804
    @zewdituzelleke4804 6 месяцев назад +2

    የጋሼ ቤተና የእትዬ ሶፊ ሕይወትና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብዙ ህያዋን ምስክሮች አለን ... ያላቸውን ብቻ ሣይሆን ሕይወታቸውን አካፍለውናል! እግዚአብሔር አምላክ ከባረካቸው በላይ ይባርካቸው ይጨምርላቸውም.. 🙏👏👍🎈🌷

  • @deboamare5171
    @deboamare5171 6 месяцев назад +3

    ታድላችሁ። ሀዋርያት ጋር ወሰዳችሁኝ ለምልሙ። ፓሰተር መካሻ የቆሮንጦስ ጥናት ሠምቼዋለሁ ተጠቃሚ ነኝ። ዶ/ር ቤተ ዘሮት ይባረክ" ወረቀት ይቀደዳል አካል ይቦጨቃል" ❤❤😮😮😮😮😮😮

  • @eyesusawitgetachew4910
    @eyesusawitgetachew4910 6 месяцев назад +4

    ጋሽ ቤተ በጣም ነው ከእርሷ የምማረው ቤተሰቦዎን የምታከብሩ ደስ የምትሉ ኖት ቤዛ አመልክ ነበር እርሷን፣ እትዬ ሶፊን፣ ፖስተር ዚ እና ፓስተር ሳህሌን ሳይ የእርሷን አባትነት በደንብ ነው የምግነዘበው ተባረኩ

  • @almazfekede
    @almazfekede 6 месяцев назад +1

    ሁሉን የሚችል አምላክ እድሜና ጤና ይስጣችሁ አስፈላጊ የምድራችን በረከቶች

  • @mosessolomon3023
    @mosessolomon3023 6 месяцев назад +3

    I know Gash Bete, his words and deeds are the same. God bless him abundantly!

  • @mehretyebzalgn1786
    @mehretyebzalgn1786 6 месяцев назад +3

    እምነት ተስፋ ፍቅር እነዝህ ፀንተው ይኖራሉይቅማሉ ከእነዚከሁሉ የሚበልጠው ፍ ቅ ር ❤❤❤
    ኢየሱስ ያድናል 🙏🙏🙏💔

  • @addiszele4182
    @addiszele4182 6 месяцев назад +4

    የተባረካችሁ በረከቶቻችን ናችሁ!!!!!!
    ሰውን ያማከለ እ/ር የሚከብርበት ፕሮግራም ነው!!!!!

  • @eneyetesfaye9814
    @eneyetesfaye9814 6 месяцев назад +1

    1ኛ ሳሙ. 7:12 ,,, “እግዚአብሔር እስከ አሁን ድረስ ረድቶናል”ሲል “አቤንኤዘር”ብሎ ጠራዉ። አሜን በእግዚአብሔር ምህረትና እርዳታ ቃሉን አነባለሁ እሰማለሁ እባረካለሁ በመደነቅ ቀን 96 ደረስኩ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን🙏 ተባረኩ❤❤❤

  • @sarasolomon9031
    @sarasolomon9031 6 месяцев назад +4

    ቤተ ሶፊ ጌታ ይባርካችሁ
    እኔና ባለቤቴ ናይሮቢ እናንተ ቤት ነው ጌታን ያገኘነው::
    የጥሬ ሥጋ ነገር ብዙ ትዝታ አለን::
    ስፊ ቤተ ከነልጆቻችሁ ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ:: የሚንጋ እናት::

  • @amsaleyemer9042
    @amsaleyemer9042 6 месяцев назад +2

    Dr. Bette and your wife was a great GOD’S family served your GREAT GOD specifically with the refugees in Kenya, Nairobi. My youngest sister was there that time living around Yaya Center. She was participating all your programs. Again A Blessing upon you from above for you and your family from ABBA Father GOD all the days of your life. AMEN ❤❤❤

  • @ptegegn2
    @ptegegn2 6 месяцев назад +1

    ዶክተር ቤተል ከማከብራቸው አገልጋይ። የዶክትሪን ህብረት ሳይሆን የፍቅር ህብረት ይብዛልን ያሉት ነገር ሊሰመርበት ይገባል።

  • @RejoiceEthiopia
    @RejoiceEthiopia 6 месяцев назад +3

    Abaaaaa❤❤❤❤❤ you are a treasure for the whole Africa❤ we love you. We thank you ❤ I am blessed to call you father at Beza.

  • @sirgutretta9560
    @sirgutretta9560 6 месяцев назад +3

    Blessings to you all gashe Bete God used you in my life to get me enrolled at American mission girls school you were the director then ,where I gave my life to God.I love and respect you and Sofiye. May God bless you and your family abundantly. ❤❤❤

  • @almazmossissa7673
    @almazmossissa7673 6 месяцев назад +2

    እግዝአብሔር እብዝቶ ይባርክሽ እንቺ እህት በዝህ ፕሮግራም በጣም ትልቅ በረከት ሆነሽልናል

  • @MekonnenB
    @MekonnenB 4 месяца назад

    ሁሉም ይህን ያዳመጡ ሁሉ ይህን የነበረ ጊዜ እንዲመጣልን እግዚአብሔር ን እንለምንው እሰ ፍቅር ስለሆነ መቀየር የሚችል ነውና እጥብቀን እንለምነው በምነት እንፀልይ

  • @zuriashworkfikre1368
    @zuriashworkfikre1368 6 месяцев назад +2

    ዶክተር ቤተ እና ቤተሰቡ በዚህ ዘመንም ክርስትናን በተግባር ያሳዮን በጣም የምንሳሳላቸው ቤተሰቦች ናቸው የክርስቶስን ፍቅር አይቼባቸዋለሁ

  • @AbebaNati-ui4bg
    @AbebaNati-ui4bg 5 месяцев назад

    በጋቢ ቤቴል በጣም እወዶታለሁ፣ ጌታን ስለ እርሶ ፣ ስለ ባለቤትዎ፣ ስለ ትውልዶ ከልብ አመሰግናለሁ። In Jesus Christ name Amen!!!

  • @selamwondimu5568
    @selamwondimu5568 6 месяцев назад +1

    ቲጂዬ ተባረኪ ይህን የተወደደ ማንነትሽን ጌታ ይጠቀምበት በርቺ ።
    ግሩም ፖሮግራም ነበር ።

  • @antenehnima6318
    @antenehnima6318 6 месяцев назад +2

    ተባረኩ አሜን ሰው እንሁን ፍቅር ፍቅር እንሽተት🙏🙏🙏🙏

  • @samueleshetu7050
    @samueleshetu7050 6 месяцев назад +2

    Wawe God works amazingly with us, what a testimony
    what a teaching life
    We love you (Aba; gash Bete)

  • @ethiopiahaile6815
    @ethiopiahaile6815 6 месяцев назад +2

    Dt. Bete was my school director (yehiwot Berhan) b4 he left Ethiopia. I have a christian magazine which came out mayebe 50 years ago and he is on the cover with his family..

  • @tsiyonyegetatsiyonyegeta8094
    @tsiyonyegetatsiyonyegeta8094 6 месяцев назад +1

    ቲጁዬ ሁሌም እርጋታሽን አድማጭነትሽን አክብሮትሽን አደንቃለው ዘመንሽ ይባረክ እወድሻለው❤❤❤ጋሽ ቤተ ዘመኖት ተባርኳል ይሄን ድንቅ መልእክት ስላካፈሉን በሁሉ ተባርከናል ዘሮት ይባረክ ስለምክሮት እጅግ እጠቀማለው በጣም ቀርቶልኛል እንወዶታለን❤❤❤
    ፓስተር አንተንም እንባርክሀለው በሁሉ ተከናወን ዘመንክ ትውልድህ ይባረክ እንወድሀለን❤❤❤

  • @Ethiopia_Leikun
    @Ethiopia_Leikun 6 месяцев назад +1

    ተባረኪ የኔ እናት፣ እንድንያያዝ የምታደርጊውን ሁሉ ጌታ አስቦ ይክፈልሽ።

  • @Tube-cn1qw
    @Tube-cn1qw 6 месяцев назад +1

    እግዚአብሔር ይመስገ ይችን ጊዜ ሰጥተህ እንሂን አባት ወንድሞች እንድሰማ ፍቃድህ ስለሆነ ተመስገን ❤❤❤❤❤

  • @Kidestgirmaኢየሱስይመጣል
    @Kidestgirmaኢየሱስይመጣል 6 месяцев назад +1

    በጣም የተባረኩበት ቃለ ምልልስ ነው❤❤❤ ተባረኩ እራሴን ያየውበት

  • @tigi886
    @tigi886 6 месяцев назад +2

    እግዚአብሔር ሁሌም በዘመኑ ሰዉ ስላለዉ በብዙ ችግሮች አባቶች ሳይሰበሩ ያንን ግዜ አልፈዉ ነዉ በቅብብሎሽ ወንጌል ዛሬ እዚህ ላይ ደርሶ እኛም የዳነዉ ስለ እናንተ እግዚአብሔር ይባረክ🙏 ፓስተር መካሽ የተወደደ የልደት ቸርች አገልጋይ እንደሆነ እህቶቼ እና ወንድሞቼ በዚያ ቸርች አባል ስለሆኑ በአገልግሎትህ እንደሚባረኩ ልጆቻቸዉም ደግሞ በወጣቶቹ አገልግሎት ዉስጥ እንደሚያገለግሉ አዉቃለሁ ለትዉልዱ ወጣቶች ላይ መስራት ለነገዉ ዘመን ደግሞ ሌሎች እንዲድኑ ስለሚያደርግ በርቱ በተረፈ ሁላችሁም ዘመናችሁ ይለምልም🙏

  • @dessienedaw2856
    @dessienedaw2856 6 месяцев назад +2

    Gashe Bete I don't know you in person but some of my life principles are extracted from your sermon. Remain Blessed

  • @mekedesmezmur4057
    @mekedesmezmur4057 6 месяцев назад +1

    አሜን አሜን አሜን አሜን እግዚአብሔር ይባርካችሁ ጌታ እግዚአብሔር ለዚህ ታላቅ ቀን ስላደረሳችሁ ክብርና ምስጋና ለዘላለም ለእሱ ብቻ ይሁን አሜን አሜን አሜን
    Sis. God bless you ❤ !

  • @fikaduteshome9058
    @fikaduteshome9058 6 месяцев назад +1

    ጌታ ረጅም እድሜ ይስጦት ጋሼ ተባረክ በጣም ደስ የሚል ምስክርነት ነዉ ተነክቻለሁ

  • @geni4jesusparsagrace436
    @geni4jesusparsagrace436 6 месяцев назад +1

    በጣም የሚያስተምር ውይይት ነው። አንድ ደረጃ ከፍ አድርጎኛል።❤ ቲጂ ና ተጋባዦቿ ❤❤❤❤❤❤❤ በተለይ ሰው ሰው ላለመሽተት እሞክራለሁ ተባረኩ አባቴ

  • @sebledebele
    @sebledebele 6 месяцев назад +2

    The father of nation gashe Bete mamiye Sofi we miss you so much and love you always ❤🥰🥰❤️

  • @Abiyot_Gurasho
    @Abiyot_Gurasho 6 месяцев назад

    የተወደድሽ አህታችን ትእግስት ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ

  • @samitesfaye9177
    @samitesfaye9177 6 месяцев назад

    ጌታ ይባርካችሁ የዛን ጊዜ ኣምልኮ እና የእግዚኣብሔር ህልውና በቃላት ለመግለጽ ይከብዳል የዚህ ዘመን ያለንበት እንደመስታወት እንድናመዛዝን ኣድርጎናል ። ፓስተር ቤተ ተባረኩ !

  • @biruckmotichibesa3104
    @biruckmotichibesa3104 6 месяцев назад +1

    Dr batel appreciate your work and kindness to parishioners and your wife to the most. Betale, I am thankful for your faithful teaching of God's word. ...
    Dr batel I am thankful for your Christlike conduct. ...
    Betale, I am thankful for how you remind us there is a greater aim in life. ...Dr.betale, I am thankful for your courageous faith. ...
    Betale I am thankful for your patience with us.

  • @Mercy2Mee
    @Mercy2Mee 6 месяцев назад

    ቃለ መጠይቅ ትጂ ታድርግ በእውነት!! Journalism ሳትማሪ እግዚአብሔር ራሱ ስጦታ አድርጎ ሰቶሻል. ለዚህ ነው ሰዎች መጥተው እንደልባቸው አውርተው ለኛ በረከት የሚሆኑት.
    በርቺ sis! God bless you abundantly.

  • @sewunetgetachew6742
    @sewunetgetachew6742 6 месяцев назад

    ጋሼ በጣም የምወዳቸዉና የማከብራቸዉ የተወደዱ የእግዚአብሔር ሰዉ እግዚአብሔር ረጅም እድሜና ጤና ተሰጥቶት ያኑርልን

  • @awothaile6602
    @awothaile6602 6 месяцев назад +1

    Assembly of God 6 kilo next to American embassy that’s where I got my Jesus Christ I will never forget get doctor ye Even Nairobi Kenya fungumano i was there too now am 40 praise Lord

  • @SimretAnega
    @SimretAnega 6 месяцев назад

    Educative, powerful,inspiring, historical,and graceful

  • @tedialemu2114
    @tedialemu2114 6 месяцев назад

    በጣም በጣም ትልቅ አባባል መጀመርያ ሰው እንሁን ሰው ሰው እንሽተት
    ፈጣሪን አንዳፈር
    በተለያየ ነገር አንጠላለፍ
    ዶ/ር ቤተ እድሜና ጤና ይስጥልኝ
    ቲጂም ተባረኪ

  • @elzaabebebeyene9308
    @elzaabebebeyene9308 6 месяцев назад

    አሜን ሰው ያድርገን በመንፈሱ ያ ጌታ ወዴት ሄደ ወይስ እኛ ሸሸን ጌታ ይርዳን ጌታ ይባርካችሁ ቲጂ በርቺ ፀጋው ይብዛ።

  • @ayiguwagu
    @ayiguwagu 6 месяцев назад +1

    ጌታ ይባርካችሁ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል:: i don't have words

  • @Kidestgirmaኢየሱስይመጣል
    @Kidestgirmaኢየሱስይመጣል 6 месяцев назад

    እውነት ነው እግዚአብሔር ስራውን ያለምስክር አይተውም ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን❤❤❤❤ ተባረኩ ረጅም እድሜ ይስጣችሁ

  • @mekdesgebrewold2687
    @mekdesgebrewold2687 6 месяцев назад

    አባ አንተ ትለያለህ! እግዚአብሔር አንተን ስለሰጠን እኛ እድለኞች ነን።
    Abba,
    Great to see you share to our generation what it means to serve. I know you only share soooo little and I pray and wish one day you shall guide us as a father through your graceful life experience with Jesus Christ.

  • @bogalechyida1924
    @bogalechyida1924 6 месяцев назад +1

    ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ፓስተር ቤተ መንፈስ ቅዱስ እውነተኛ መሪ ነው አክብር በሱ ለሚመራ ሰው ከበቂ በላይም ነው።

  • @MekonnenB
    @MekonnenB 4 месяца назад

    እግዚአብሔር አምላክ ዘመንዋትን ይባርክልዎ

  • @HirutMitiku-sj4xh
    @HirutMitiku-sj4xh 6 месяцев назад +1

    Dr. Bete selerso bezna esma neber Geta yebarek zare degmo sesema nefse alkerlgem bemenfes kedus yemumera sew bezhi zemen Wow! Pastor Mekash sarebetoch Muluwengel pasteri neberk beante weste yeneberwen sega alersawem selayhuhu dese belogal

  • @jerusalemworkenehe8146
    @jerusalemworkenehe8146 6 месяцев назад

    Dr. Betta አንተና የቤትህ ሠዎች ለእግዚ አብሔር ብሩካን ናችሁ የእግዚ. ማንነት የገባው ሰው የዘመኑ አብርሐም ነህ። ጌታ
    ዛሬም አሁንም ባንተ ደስ ብሎታል የምትለው ለገባው ሰው ሌላ የለም ፍቅርን የለበሰን ሰዎች እንሁን እሱ በቂነው ነው። ባንተ የሚሰማውና የሚታየው። “እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፦ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።”
    - ሉቃስ 17፥10
    ትእግሥት እጅጉ እግዚብሔር ፈቃድንና ሐሳቡን መግለጫው አደረገሽ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ።

  • @lensatafesse8293
    @lensatafesse8293 6 месяцев назад +1

    ዋ ፍቅር ያረሰረሰው ሰውን በሰውነቱ በፍቅር እንገለጥ
    አሜን ሁሉም ሰው ሊማርበት የሚገባ ነው

  • @joseymuluneh9370
    @joseymuluneh9370 6 месяцев назад

    ዶር ቤተ በጉባኤ እግዚአብሔር ሲሰብኩ ነው ጌታን ያገኘሁት በጉባኤ እግዚአብሔር ማደጌ እድለኛ ነኝ ባለመናወጥ አለሁ❤

  • @aidb1275
    @aidb1275 6 месяцев назад

    Wow, how wise is this man of God! May God bless you!

  • @ruthisaac3946
    @ruthisaac3946 6 месяцев назад

    I received Jesus Christ as my personal savior in Nairobi. Emmanuel Church (Fungumano). I grew up and started serving my Jesus there . Gash Bete and Sofi are our father end mom. We love them so much.

  • @Amhayesus
    @Amhayesus 6 месяцев назад

    ጋሸ ቤተ ከሰላሳ አራት አመት በፊት እኔም እነደወንድሜ ናይሮቢ ከትየ ሶፊ ጋር አውቃችኋለሁ,ዛሬ ድምፅህነ ሰሰማ በጅጉ ተደሰትኩ ጌታ በነገርህ ውሰጥ ሁሉ አብሮህ ይሁን.

  • @atnafmedia1927
    @atnafmedia1927 5 месяцев назад +1

    👏👏👏👏 ሰው ሰው እንሽተት፣ሰው እንሁን፣ወንድሙን ያሳደደ ነፍስ ገዳይ ነው።ከአገልግሎት በፊት በመጀመርያ ከወንድሞች መታረቅ፣ይቅርታ መጠየቅ ነው። እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቤተክርስቲያን በወንጀለኞች፣በአድመኞች፣በክፍሰሪዎች፣ቤተክርስትያን አትመራም።እየሱስ ክርስቶስ የአባቴን ቤት መነገጃ አታድርጉት ብሎ በአለንጋ የገረፋችው እየሱስን ሳስታውሰው ጌታ አሁን ቢኖር ኖሮ፣ህፃናትን፣እናቶችን፣አባቶችን፣ወንድሞችን ፣በጥላቻና በንቀት የክርስቶስን እራይ ለመስራት የወጡትን በመፈንቅለ ቤተክርስቲያን የአገልጋዮችን ቤተክርስቲያን ቀምተው የቤተክርስቲያን ስሙን እንኳን ሳይቀይሩ ፣የዘመኑን ዘራፊዎች ብዙዎች የለፍበትን ቤተክርስትያን ነጥቀው ይህ አልበቃ ብሏችው የቺካጎ ስብስብ ለወንጀለኛ መሪዎች አሳልፎ መስጠት በእግዚአብሔር ቤት ዳግመኛ የተሰራ ወንጀል ነው።ስለዚህ ጅብ በማያቁት ሀገር ቁርበት አንጥፍልኝ የተባለው ተረት አሁን በግልፅ እያየን ነው ዶክተር ቤተ እግዚአብሔር ይባርክህ ሰው ሰው ሽተቱ ያልከው ትክክል ነው።በግና ተኩላ አብረው በጋራ አያድሩም።ወንድሙን የጠላ ነፍሰ ገዳይ ነውና የወንድሞቻችንን ደም፣የእህቶቻችን እንባ ከአርአያም ይጮሀል።ሰው ሰው እንሽተት፣ሰው እንሁን።የተሰበሩትን ወንድሞቻችንን ፣እህቶቻችንን እንደግፍ፣እናንሳችውና ያን ግዜ ጌታ ይከብራል እውነተኛ እርቅ ሰላም ጁብሊም ይከበራል።አለበለዝያ ወንድም ወንድሙን ገድሎ የወንድሙ ደም እንደ አቤል እና ቃየል ሆነን እርቅ እና ሰላም አይመጣእና ሁላችንም በአንድ ልብ እንነሳ።የወደቀ ይነሳ፣የበደለ ይካስ፣ይቅርታ የሚጠይቅ የበደለውን ይቅርታ ይጠይቅ ፣ያን ግዜ እኛ ዝቅ ስንል ጌታ ይከብራል የጌታ ስራም በአለም ዳርቻ ሁሉ ይሰራል።ሰው ሰው እንሽተት፣ሰው እንሁን እየሱስ ጌታ ነው አመሰግናለሁ ፋሲል አረጋ ከWashington DC.

  • @mesfindebebe9572
    @mesfindebebe9572 6 месяцев назад +1

    ቲጁ በጣም ነው የስ የሚል ጊዜ ያሳለፈችሁት የሰብ ከት ያክል ነው የሰማሁት ተባረኪ

  • @ለታሪክአበራ
    @ለታሪክአበራ 6 месяцев назад +2

    ኡፍፍፍፍ ወይ አባት መሆን አቤት ፋቅር

  • @abrshwossnu2967
    @abrshwossnu2967 6 месяцев назад +2

    ጋሽ ቤተ የቡዞቻችን ሂወት ለውጥ ምክናት ነህ ዝመንህ ይባርክ

  • @haimeteabrham722
    @haimeteabrham722 6 месяцев назад

    ቲጅየ ተባረኪ ዶ/ር ቤተን የህይወት ምስክርነት ብታቀርቢልን።

  • @antenehworku9216
    @antenehworku9216 6 месяцев назад

    Dr Betta man of faith and spiritual he love Jesus and enjoyed with holy spirit ❤❤❤

  • @AbebaNati-ui4bg
    @AbebaNati-ui4bg 5 месяцев назад

    "በጣም የምፈራውና የማከብረው የጌታዬን ድምፅ ነው።"

  • @eyesusawitgetachew4910
    @eyesusawitgetachew4910 6 месяцев назад

    ዎው driven amazing truth መነዳት እንዴት ደስ ይላል።

  • @solomonalemayehu4801
    @solomonalemayehu4801 6 месяцев назад

    እጅግ ድንቅ እና የሚባርክ አስተማሪ ምስክርነት ነው ።

  • @ebmmultiplexcinema9041
    @ebmmultiplexcinema9041 6 месяцев назад

    God Bless you Dr. Betta

  • @Joel-t9r
    @Joel-t9r 6 месяцев назад +1

    Aba Bête good to see you our beloved

  • @endunahi4546
    @endunahi4546 6 месяцев назад

    So powerful.....Glory to God!

  • @mulukenabebe8515
    @mulukenabebe8515 6 месяцев назад

    ተባረኪ ቤብዙ እየተተቀምን ነው ይብዛልሺ ፀጋው

  • @ShimelisKergo
    @ShimelisKergo 6 месяцев назад

    Ewnetem.hiywet.new.yetekafelnew.abate.tebareku

  • @abnetmihretu6940
    @abnetmihretu6940 6 месяцев назад

    wow....I'm really touched!
    thank you Tigiye!
    God bless you all!

  • @zemrobelaraya5351
    @zemrobelaraya5351 6 месяцев назад

    ❤❤❤ Sile Hibret 1 Mehon Telik Temehert New Yetemarkut Tebareku

  • @akliluteklebrhan-bf1cn
    @akliluteklebrhan-bf1cn 4 месяца назад

    50 years pass over from one to anazer with out intiosion church by visiiners great man go firward minstry God reach at these time.

  • @meluchanal
    @meluchanal 6 месяцев назад

    Dr Betel have Amazing personality much respected person.

  • @hagoswoldegebriel1137
    @hagoswoldegebriel1137 6 месяцев назад +1

    it is the real history of organic church connected in life.
    However, Now a days the recent church is more of organizational not organic.

  • @deboamare5171
    @deboamare5171 6 месяцев назад +1

    TG አባታችንን የህይወት ምስክርነታቸውን ብታቀርቢልን??? የ62 አመት የአገልግሎት ጊዜ ቀላል አይደለም ትህትና❤😮 ታዲያ እናንተን እያየን ምን ክርስትና አለ እንላለንን??? እነ ፓስተር እንደ ስምህ ካሠን በጌታ❤❤❤ ጌታ በነገር ሁሉ ይርዳችሁ😮 ቅሬታዎች ናችሁ በብዙ ተፅናናሁ ተባረኩኝ❤ ሌላ ጊዜ ምንም አልጠገብኩም!!፣••••

  • @fasimeshesha4182
    @fasimeshesha4182 5 месяцев назад

    have Beautiful memory in Kenya