የኦንሊ ጂሰሶች አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አረዳድ በቢሾፕ ተክለማርያም እንዴት ተብራራ? መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይላል? Trinity vs Oneness Ep 14
HTML-код
- Опубликовано: 4 фев 2025
- የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በተለምዶ ኦንሊጂሰስ በመባል የሚታወቀው ቤተእምነት በጣም አደገኛ እና መፅሀፍቅዱስን የሚፃረር የሀሰት እምነት ነው:: ኢየሱስ ኢየሱስ ይላሉ ግን የመፅሀፍ ቅዱሱን ኢየሱስ ፈፅሞ አይቀበሉም:: በወንጌል የሚያምኑ ይመስላሉ ግን የአዲስኪዳንን ወንጌል ፈፅሞ ወደጎን በማለት የራሳቸውን ሰው ሰራሽ ዶክትሪን እና ሀይማኖታዊ ህግጋቶቻቸውን ከመፅሀፍ ቅዱስ በላይ የሚያምኑ ወገኖች ናቸው:: ምእመኖቻቸውም መፅሀፍ ቅዱስን እያነበቡ ስለ አምላካቸው ከማወቅ ይልቅ ድርጅቱ እና የድርጅቱ አስተማሪዎች የሚሉትን ብቻ እንዲቀበሉ ይገደዳሉ:: ኢየሱስን መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚለው በቅጡ ሳያምኑ እና ሳይቀበሉ የውሀ ጥምቀት የዘላለም ህይወት ያስገኛል ብለውም ያምናሉ::
በአጭሩ መፅሀፍ ቅዱስን ያለአግባብ በአውዱ እና በስርአቱ ካለማንበብ እና ካለመረዳት የተነሳ የተፈጠረ ድርጅት "CULT” ነው:: ከዚህም የተነሳ የኢየሱስ ማንነት ላይ እጅግ በጣም ስተዋል!
ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የወልድ እና የመንፈስቅዱስን መለኮታዊነትን የሚክድ ቤተእምነት ነው:: አንዱ እግዚአብሔር ወይም አንዱ መለኮት በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስቅዱስ ተገልጦ እንደሚኖር አያምኑም::
በኦንሊጂሰስ አስተምሮ በስጋ የተገለጠው ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ሳይሆን እግዚአብሔር አብ ነው:: ኦንሊጂሰሶች የወልድን ዘላለማዊነትም ይክዳሉ:: የእግዚአብሔር ልጅ ለነሱ ከድንግል ማርያም የተወለደ የስጋ ሰውነት ብቻ ነው:: ስጋውንም ሰማያዊ ወይንም መለኮታዊ ከሰማይ የመጣ ስጋ ነው እንጂ የዳዊትን ዘር በስጋ ተካፈለ ብለው አያምኑም:: (ሮሜ 1:3, ሮሜ 9:5, ዕብ 2:14, ራእይ 22:16)
ልጁ ከዘላለም ጀምሮ የነበረ የምድር እና የሰማይ ፈጣሪ መሆኑን ይክዳሉ (ዩሀ 1:3, ዕብ 1:2, ዕብ 1:10, ቆላስያስ 1:16) የእግዚአብሔር ልጅ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ከአባቱ ጋር ይኖር የነበረ መሆኑንም አያምኑም (ዮሀ 1:1, ዮሀ 6:38, ዮሀ 16:28, ዮሀ 17:5)
ኦንሊጂሰሶች እባካችሁ ለእግዚአብሔር ቃል ለመፅሀፍ ቅዱስ ስልጣን ሰጥታችሁ ለህሊናችሁ ታማኝ በመሆን ቃሉን ካነበባችሁት ሳታውቁት የወደዳችሁት የመፅሀፍ ቅዱሱ ኢየሱስ በሙላት ይገለጥላቹሀል:: የኢየሱስ ማንነት ላይ መሳሳት ከዘላለም ህይወት መጉደልን ያስከትላል:: 1ኛ ዮሀ 5:12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። እባካቸሁ ከቃሉ ጋር እግዚአብሔር እየተማፀናችሁ ጊዜ አሳ ልፉ:: እግዚአብሔር እውነቱን ይግለጥላችሁ ወዳጆቼ!
ዶክተርዬ እንዴት እየተጠቀምኩ እንደሆነ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ❤❤❤❤
ተባረኩ
God bless you
ፓስተር ታሪኩ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል ይህ የነበረኝን ዕውቀት ከፍ ያደርገዋል።ጌታ ይባርካችሁ። ቤተሰብህ ሠላም ነው?ከላምበረት።
Dr Tesfaye geta abezeto yebarkeh !!!
ከጥቂት ዓመት በፊት Only Jesus ነበርኩ። አሁን ጌታ ረድቶኝ ከዚህ ምንፍቅና ትምህርት ወጥቻለሁ። እንደ ኦንሊ ጅሰስ ዶክትሪን በምንፍቅና የተሞላ ትምህርት የትም የለም።
እንኳን ኢየሱስ ረዳህ ወንድም:: ብዙዎች እያመለጡ ነው::
@@miskirnegh7489 መናፍቅ ማለት አባትህ ሳባሊዮስ እና ጀሌዎቹ ናቸው።
እንኳን እግዚያብሔር ረዳህ
Wow betam Des yilal praise God EMEN
@@paulosbelete9076 ቱታ ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው የረዳኝ።
Dr tesfaye robele yesafutin mestihaf web site lay magignet ayichalim?
በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ(በተለይም በዘመናችን የክርስትና ታሪክ) በስላሴ ዙርያ አብዝቶ የጻፈና በትጋት ያስተማረ እንደ ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ያለ ሰው አለመኖሩን በድፍረት መናገር እችላለሁ።
እግዚአብሔር ብድራቱን ይክፈላቸው።
Amen!እጅግ በጣም ትክክል!
እውነት ነው ዶክተር ተባሩክ
አሜን አሜን 👏👏👏🙏🙏🙏🙏
ወንድሜ ያሁበት የሐዋርያት(only Jesus) እንድህ ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ ትምህርት እንደ ሆነ በደምብ ተረድቻለሁ በጣም ነው ማመስግንህ በርታለን። ባለሁበት እምነት ብዙ ጥያቄ እንድፈጠብ አድርገሀል። please never give up ለጥያቄዎቼ መለስ ፈልጋለሁ። ያሉትን ስህተቶችን አውጣው።
ጌታ ይርዳህ!! መጠየቅህን አታቁም። ፍቃድህ ቢሆን በቴሌግራም እናውራ!!
እንኳን ኢየሱስ ረዳህ ወንድሜ
Sile sew astemihiro bitastemiren des yilegnal
መቼ ነው መፅሐህ ኢትዮጵያ ምመጣው?
ስላሰን ከመቀበል በስተቀር ለላ አማራጭ የለም
God bless you