(Cover) ቃል አለው / እስቲ ዝቅ ልበል ከእግርህ ስር - ሙሉ ወንጌል / መካነ ኢየሱስ መዘምራን

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 19 окт 2024
  • 1. ከመባከን አርፎ ተቀምጦ ለሰማው
    ልቡን ረገብ አርጎ ታምኖ ለጠበቀው የታዘዘ
    ቃል አለው ቃል አለው ጌታ
    ሁሌ የሚናገረው
    2. ሰምቶ ለሚያደርገው እንዲቃና ኑሮው
    ልቡን ሳይወላውል ከአፉ ለማይለየው የታዘዘ
    ቃል አለው ቃል አለው ጌታ
    ሁሌ የሚናገረው
    3. በቀንም በሌሊት ሁሌ ለሚያስበው
    በህይወቱ ለሚኖር ይዞ ለሚያበራው የታዘዘ
    ቃል አለው ቃል አለው ጌታ
    ሁሌ የሚናገረው
    እስቲ ዝቅ ልበል ከእግርህ ስር (2)
    ለማየት እንድችል ጉድለቴን
    እስቲ ዝቅ ልበል ከእግርህ ስር
    1. ምንም እንዳልጎደለው እንደሙሉ ሰው መሆኔ
    ይቅርብኝ አያዋጣኝም እራሴን ማታለሌ
    ጌታዬ ሆይ ከእግርህ ስር ሁለንተናዬን ላኑረው
    ልቤን እየደቃሁኝ ህይወቴን ልመርምረው
    2. አንዳች የማይጎድልብኝ እንደ ጌታ ቃል የኖርኩኝ
    ብዬ ስሮጥ ከርሜአለሁ በውስጥ እየተጎዳሁኝ
    ምን የማይጠቅመኝን ግትር ሀሳቤን ትቼ
    ዝቅ ልበል ከእግርህ ስር እራሴን አዋርጄ
    3. ዝግ ብዬ ላስተውል ልመርምረው መንገዴን
    ከቃልህ ጋር ላመሳክረው ልፈትን አረማመዴን
    ጉድለቴን እንዳስተውል እጆቼን ወደ አንተ አንስቼ
    ዝቅ ልበል ከእግርህ ስር እራሴን አዋርጄ
    Kal Alew / Esti Zik Libel Keigrih Sir
    Mulu Wongel / Mekane Yesus Choirs
    Amharic Gospel Mezmur Cover
    2020

Комментарии •