ETHIODURUS QURAN AMHARIC TR. SURAH 12 YUSUF
HTML-код
- Опубликовано: 6 фев 2025
- መግቢያ
ይህ የቁርአንና የፍቺውን ትርጉም በአማርኛ የተዘጋጀው የተለያዩ የተፍሲር ኪታቦችን ዋቢ በማድረግ ነው። የተጠቀምኩት የትርጉም ስልት ቀጥተኛ የቁርአኑን ትርጉም ከቅንፍ ውጪ በማድረግ፤ የቁርአኑን ፍቺ ትርጉም በነጠላ ቅንፍ ውስጥ በማስገባት ሲሆን በተጨማሪ ማብራሪያዎችን በድርብ ቅንፍ ውስጥ በማስገባት፤ የያንዳንዱን የቁርአን አንቀፅ መልክቱን አንባቢ በቀላሉ እንዲረዳ የሚቻለኝን ሁሉ ጥረት አድርጊያለሁ።
የተለያዩ የቁርአን ኢእራብ ኪታቦችን በመጠቀም ከአማርኛ ሰዋሰው ጋር በማጣጣም የሁለቱንም የቋንቋ ስርአት በተናጥል በመገንዘብና በማዋሃድ እያንዳንዱ የቁርአን መልክት ሳይዛባ ለማስቀመጥ ከፍተኛ ጥረት አድርጊያለሁ። ቁርአን ከአለማቱ ጌታ አላህ በጅብሪል መልክተኛነት ለነብዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ.) ከወረደላቸው ዘመን ጀምሮ ለ1400 አመት ቁርአኑን ለመረዳት የአረብኛ ቋንቋ ሊቃውንቶችና ሙፈሲሮች የደከሙባቸውን አስር አይነት የተፍሲር፤ ሶሥት አይነት የኢእራብ፤ እና የአረብኛ የአማርኛ የእንግሊዘኛ መዝገበ ቃላቶችን በመጠቀሜ ይህ የቁርአን ትርጉም ሥራ የተዋጣ ሊሆን ይችላል የሚል ከፍተኛ ጉጉት አሳድሮብኛል ።
ለረዥም አመታት በአእምሮዬ ይሽከረከር የነበረና ካልተወለድኩኝ ብሎ ይጎተጉተኝ የነበረው የቁርአን ትርጉም ከፊሉ ሥራ እነሆ ተወልዶልኛልና፤ በመጀመርያ ለዚህ ሥራ ለገፋፋኝና ለረዳኝ አላህ ምስጋና ይገባው። በመቀጠል በሕይወት ዘመኔ የዲንና የአረብኛ ቋንቋ እውቀት እንድቀስም ሰበብ ለሆኑ ኡስታዞቼ ሁሉ አላህ ለመልካም ሥራቸው ምንዳውን በጀነት ይክፈላቸው በማለት ዱዓ አድርጊያለሁ። የሰው ሥራ ምንግዜም ቢሆን ለስህተትና ለሰይጣን የተጋለጠ ነውና፤ በዚህ የትርጉም ሥራ ስህተት ካለበት ከኔና ከስይጣን በመሆኑ ከወገን የሚሰጠኝን በመረጃ ላይ የተደገፈ እርምት እቀበላለሁ። በዚህ የቁርአን ሥራ የሚንፀባረቅ ስኬት ካለ ከአላህ ነውና በስኬቱ እኔም ሆንኩኝ ሕዝበ ሙስሊሙ ተጠቃሚ እንዲሆን ጌታዬን አላህ በዱዓዬ እማፀነዋለሁ።
ሰይፈዲን ሐበሻ ያሲን ሻፊ
1434 አመተ ሂጅራ (2013 ዓመተ ልደት)
WWW.HABESHAMUSLIMS.COM