በኮለኔል መንግስቱ ለቀረበብዎ ክስ ምላሽዎ ምንድነው? Tewodros Tsegaye Interview with Dr Bereket Habtesilasie Part 1

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 21 окт 2024
  • ቴዎድሮስ ጸጋዬ ከዶክተር በረከት ሀብተስላሴ ጋር፡፡
    ከጥያቄዎቹ መሀል
    እውን ኢትዮጵያ የኤርትራ ቅኝ ገዢ ነበረች ብለው ከልብዎ ያምናሉ?
    ኤርትራን ከኢትዮጵያ የመነጠሉ ፕሮጀክት ኤርትራዊ ነበር?
    በእርግጥ በልዩ መርማሪ ኮሚሽኑ ውስጥ የነበርዎ ሚና ምን ነበር? ኮለኔል መንግስቱ በእርስዎ ላይ ያቀረቡትን ክስ እንዴት ይመለከቱታል?
    ኤርትራ ያለኢትዮጵያ ህይወት አላት?
    ዶክተር በረከት ሀብተስላሴ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ በሁለቱም በኩል በከፍተኛ የስልጣን እርከን ከሰሩና በስፋት ከተወኑ አወዛጋቢ ምሁራን አንዱ ናቸው፡፡ የተወለዱት በኤርትራ ግዛት ሲሆን፣ ያደጉት፣ የተማሩት፣ የሰሩትና ቀዳሚውን የህይወታቸውን አጋማሽ ያሳለፉት ግን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ መንግስት መዋቅር ውስጥ ነበር፡፡ ከመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸው አንስቶ፣ በዊንጌት ትምህርት ቤት፣ በኢንግሊዝና በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሩት በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ነበር፡፡ በፍርድ ሚኒስቴር ውስጥ በተለያየ እርከን፣ ከዝያም እስከንጉሰነገስቱ መንግስት ጠቅላይ አቃቢ ህግነት የደረሰ ሹመት አግኝተዋል፡፡ የአብዮቱን መፈንዳት ተከትሎ የተቋቋመው ልዩ መርማሪ ኮሚሽን አባልም ነበሩ፡፡
    ኋላ ግን፣ በኤርትራ ጉዳይ በስፋት በመሰማራት፣ በኤርትራ ከኢትዮጵያ የመነጠል ትግል ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በጦርነቱ ወቅት በተባበሩት መንግስታት የEPLF ተወካይም ነበሩ፡፡ ኋላም፣ ኤርትራ አገርነቷን ስታውጅ የኤርትራ ህገመንግስት አርቃቂ ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ህገመንግስት አስረቅቀዋል፡፡ በዚህ አሁን ሁለት ወደሆኑት ሀገራት ለሁለት በሚገመስ ህይወታቸው፣ በሚያውቋቸውና የአይን እማኝ በነበሩባቸው ታሪካዊ ሁነቶች እንዲሁም በአወዛጋቢነታቸው ምክንያት ለቃለምልልስ ጋብዘናቸዋል፡፡ ከቴዎድሮስ ጸጋዬ ጋር ጠበቅ ያለ ምልልስ አከናውነዋል፡፡ እርስዎም ውድ ታዳሚያችን ዝግጅቱን እንዲያደምጡና እንዲያስደምጡ በፍቅር ተጠይቀዋል፡፡
    ቀዳሚውን ክፍል እነሆ፡፡

Комментарии • 607