አዲሱ ውቅያኖስ በኢትዮጵያ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 7 окт 2024
  • በአለማችን የሚገኙ ሰፋፊ የውሃ አካላት መጠናቸው እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቀት የስነምድር ተመራማሪዎች አዲስ ውቅያኖስ በአፍሪካ ምድር ሊፈጠር ይችላል የሚል ውይይትና ምርምርን ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ውስብስብ የሆነ ገፅታ ያለው የአፍሪካ አህጉር አሁን ላይ የምድራችንን አቀማመጥ ይቀይራል የተባለውን ክስተት በዋናነት ስተናግዳል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በአፍሪካ አህጉር በቀንዱ አከባቢ ደግሞ የአፋር ትሪያንግል ይገኛል፡፡ ይሕ ስፍራ የኑቢያ ሶማሊያ እና አረብ አምባዎች ወይም በእንጊሊዘኛው ፕላቱዎች የሚሰናሰኑበት convergence ነው፡፡ ውስብስብ የሆነ የስነምድር ገፅታ ያለው የአፋር ትሪያንግል ነው እንግዲህ ይህን በንጠት ምክንያት ይከሰታል የተባለውን የስነምድር ለውጥ ሊያስተናግድ ይችላል እየተባለ ያለው፡፡
    የዊዎን መረጃ እንደሚያሳየው ከአውሮፓውያኑ 2005 ወዲህ የአለማችን ትኩረት በዚህ አከባቢ ስላለው ነገር ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ አፋር ክልል ፡፡ በአፋር በረሃ ፡፡ መረጃው እንደሚለው በዚህ አከባቢው ፈጣን ያልሆነ ነገር ግን የአፍሪካን አህጉር የሚከፍል የምድር ውስታዊ እንቅስቃሴ እየተስተዋለ ነው፡፡ በ2005 የአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 35 ማይል ገደማ የሚረዝም የመሬት መሰንጠቅ ወይም መተርተር በዚህ የኢትዮጵያ በረሃማ አከባቢ ተፈጥሯል፡፡ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ደግሞ ከመሬት የውስጠኛው ክፍል ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ መኖሩን የሚያሳዩ ናቸው፡፡
    የስነ ምድር ተመራማሪዎችን ጠቅሰው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በሚቀጥሉት ከ አምስት እስከ 10 ሚሊዮን ባሉ አመታት ውስጥ አፍሪካ ለሁለት ትከፈላለች፡፡ ይህም አዲስ ውቅያኖስ በምድራችን እንዲፈጠር እድልን ያመቻቻል፡፡
    #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #ሰበርዜና #አፋር

Комментарии • 46

  • @SantaKassa
    @SantaKassa 2 месяца назад +5

    ይህ መረጃ እውነት ቢሆን እንኴን 5 ሚሊዮን ዐመት ዋው የክርስቶስ መምጫ የዐለም ፍፃሜ ሩቅ አደለም ነገሮች ሁሉ ወደዛ እያመራ መሆኑ ግልፅ እየታየ እና ማን ነው ይሄን አውነታ ሊያይ የሚችለው በ100 ቶዎቹ እንኳን ዐለም በዚ ሰይጣናዊ ፍጥነት አትቆይም እና ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋን የማላይ ይሆናል ነገሩ ቢቻል ለእግ/ሚሳነው የለም ሁሉን ውብ ያደርጋል ከወደብ ይልቅ ለኢትዮ ሚያስፈልጋት ኢየሱስ ብቻ ነው የዘላለም ማምለጫዋ ወደ እርሱ ዘንበል ብትል ነገሮች ሁሉ መልካም በሆኑ ነበር!!!

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      ለአስተያየትዎ እናመሰግናለን! 🙏🙏🙏

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      መረጃው በሳይሳዊ ጥናቶች ላይ የተመሰረተ ነው። ክስተቱ ሊያጋጥም እንደሚችል የሚጠቁሙ ክስተቶችም እያጋጠሙ ነው። የመሬት መሰንጠቅን ጨምሮ የተለያዩ ክስተቶችን በእኛ ዕድሜ ጭምር ልናያቸው የምንችላቸው ናቸው።

    • @fisehayeaa8079
      @fisehayeaa8079 2 месяца назад

      Ewenet new

  • @tigistabera-re6cv
    @tigistabera-re6cv 3 месяца назад +5

    Abet ye Egziabher sira

    • @EN24new
      @EN24new  3 месяца назад

      🤲🧎‍♂️🤲

  • @andualemzemzem8561
    @andualemzemzem8561 3 месяца назад +4

    አስተማሪ ፕሮግራም

  • @mesihibkebede930
    @mesihibkebede930 3 месяца назад +5

    Tefetro Asgerami nw!

  • @yosefephrem2082
    @yosefephrem2082 2 месяца назад +2

    ከ 5 እስከ 10 million አመታት ውስጥ ሀሀሀሀሀሀ

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      አሰገራሚ ነው። የስነ ምድር ለውጥ ብዙ ዘመናትን ይወስዳል። በእኛ እድሜ ደግሞ በምድር ውስጥ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች ምክንያት የሚፈጠሩ አንዳንድ ምልክቶችን እያየን ይመስላል።

  • @senaithailetesfa8200
    @senaithailetesfa8200 2 месяца назад

    BETAM DENKE NEWENA YEHENEN HULU SEGA BE SELAME MELA EYEFETERENE BE SELAME YEMENENOREBETENE KENE KEREB YADREGELEN AMEN 🙏 AMEN 🙏 AMEN 🙏 DENEKE AKERAREBE NEWENA ENAMESEGINALEN 🙏🙏🙏

  • @soldave319
    @soldave319 3 месяца назад +2

    tefetiro hulem asigerami new

  • @CdtDryu
    @CdtDryu 2 месяца назад

    በትርጉም ያቀረብከው ዘገባ ጡሩሆኖ ሣለ በአፋር ክልል ሁለት የተፈጥሮ ሐይቆች ሲኖሩ አደገኛ በአፍዴረ ውሰጥ ያለሲሆን በጨው በሰልፈር ማአድናት ክምች ያለባት እሣት ጎመራ የሚገጘበት የትግራያ ክልል እና ኤርትራ ደበር የሚገጘ ሲሆን በአፋርና በጂቡቲ ድበር መካከል የሚገኘው ሐይቅ የአዋሽ ውንዝ መጨረሻ ሐበይ አፈቦ ከተማ የማገጘበት የአፈር ሱልጣና መቀመጫ የሆነቸ ለምና በረከተ የቴምር ዘባባ የለባት ቴምር እና ወንዙን ተከትሎ የተለያየ ምርት የሚሰጥ ነው ያቀረብከዉ ትርጉም ሁለቱን ሐይቆች የቀለቀለ በመሆኑ እርምት ቢደረግ እላለው

  • @kidanehaddish
    @kidanehaddish 2 месяца назад +1

    ይህ የምታወሩት ጉዳይ ሊሆን መሆኑ ኣያጠራጥርም ሆኖም መቼ ከተባለ ማንም ሊያውቀው ኣይችልም ። ከዛ ይልቅ በ1000 ጊዜ ቀድሞ የሚፈፀም ነገር ግን ኣለ ። ይህም የመቐለ ምስራቃዊ ክፍል በተፈጥሮው ከባህር ከፍታ በታች በመሆኑ በቅፅበት ከውቅያኖስ ግፊት ወትሮም ኣለበት የሚፈልገው እንደተባለው የሁለት መሬቶች መገፋፋት መራራቅ ኣያስፈልገውም የመርፌ ቀዳ ብቻ እንኻ ከቀይ ባህር ምስራቅ መቐለ በቅፅበት የቀይ ባህር ድምበር ይሆናል በቅፅበትም ታላላቅና ትንንሽ ደሴቶችም ይፈጠራሉ። ይህ ጉዳይ ከሚባለው ታሪክ ይልቅ ከመቐለ ምስራቅ የሚፈጠረው ሁኔታ ቢተነተን ነገር ኣስፈላጊ የሚሆነው።

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад +2

      @@kidanehaddish በጣም እናመሰግናለን። ክብረት ይስጥልን። እጅግ ጠቃሚ ጥቆማ ነው የሰጡን። በቀጣይ ይህን እርስዎ ያነሱትንም ሀሳብ ለመዳሰስ እንሞክራለን።

  • @MahiDesalegn-eo2iz
    @MahiDesalegn-eo2iz 3 месяца назад +1

    Leka hagerachinin anawkatm waww

  • @6Sky6
    @6Sky6 2 месяца назад +1

    የ 5ዓመት የኑሮ ፓኬጅ ኢንፎርሜሽን ሲያጓጓን የ5ሚሊየን ስትዘረግፍልኝ ስልቹ ሆኜ ስልቻዬን ቋጠርሁት ::

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      @@6Sky6 😁😁😁

  • @hassnahanfere6208
    @hassnahanfere6208 2 месяца назад

    ሀሰተኛ መረጃ እና እስከዛ ጠብቁ ቀይ ባህር ወደ እነንተ ይመጣል የሚል መልክት ከጀርባ ያዘለ መልክት ስለሆነ እነስብበታለን

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      @@hassnahanfere6208 😁😁😁 እንደዛ የሚል እሳቤ በፍፁም ሊኖረው አይችልም። ጥንቅሩ ላይ እየተወራ ያለውኮ በሚሊየን ዓመታት ውስጥ ሊፈጠር ስለሚችል ነገር ነው። ኢትዮጵያ በባህር በር ላይ የምታነሳው ጥያቄ ደግሞ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም። ስለዚህ እርሶ በተሳሳተ መንገድ ተረድተውታል ማለት ነው።

  • @Meiry756
    @Meiry756 2 месяца назад +1

    Halew’low ‘’ Timbit’new ‘’ Ye’migerm’demo Aydelem !!! Ye’nante Ye’mitifelugut Filagot’new Yeh ‘’’ Y’Ethiopia Ortodox Since ‘new ‘’’

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      @@Meiry756 ቤተሰባችን ይህን እያሉ ያሉት የስነ ምድር ተመራማሪዎች ናቸው። ግምታቸውም ሳይንስን መሰረት ያደረገ ነው።

  • @brehanbekele1345
    @brehanbekele1345 2 месяца назад

    የገደል ማምቶ አትሁን የስነምድር ተመራማሪዋች በሚሊዮን አመት ይክስታል የሚሉት መስንጠቅ ስፍት በእንድ ቀን ሆኖባቸው ግራ ተጋብተዋል

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      @@brehanbekele1345 ማለት? ዝግጅቱ የሚያወራውኮ ስለመሬት መሰንጠቅ ሳይሆን በሚሊዮን አመት ውስጥ ሊከሰት ስላለ የምድር ቅርፅ ለውጥ ነው።

  • @ermiyaseenyew6104
    @ermiyaseenyew6104 2 месяца назад

    ሀይቅና ውቅያኖስ ለነይተህ እወቅ

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      @@ermiyaseenyew6104 ወዳጃችን ዝግጅቱን በደምብ ይመልከቱ። ፕሮግራሙ ላይ ስለ አቤ ሐይቅ በስፋት ተነስቷል። ስለዚህ ሀይቅ ገፅታ እና ስለአፋር አስገራሚ ተፈጥሮዎች ተስሷል። በሌላ በኩል ደግሞ በምድር ውስጥ በሚከሰት ለውጥ የተነሳ ደግሞ በአከባቢው ውቅያኖስ እንደሚፈጠርም ተብራርቷል።

  • @AbduAhmed-jg3wq
    @AbduAhmed-jg3wq 3 месяца назад +1

    Meche

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      ሚሊዮን አመታትን ይጠብቃል። የስነ ምድር ለውጥ ብዙ ዘመናትን ይወስዳል። በእኛ እድሜ ደግሞ በምድር ውስጥ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች ምክንያት የሚፈጠሩ አንዳንድ ምልክቶችን እያየን ይመስላል።

  • @MegersaBulcha
    @MegersaBulcha 2 месяца назад

    ይሄንን ሃሳብ የሆኑ ሽማግሌ የዛሬ 3ዓመት አካባቢ ጂቡቲ ዉስጥ ሊፍት ሰጥቼአቸዉ አብረን እየሄድን ነግረዉኛል ።

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      ክብረት ይስጥልን በጣም እናመሰግናለን። ምናልባት እሳቸው ከነገሩህ ውስጥ የምታጋራን ነገር ይኖር ይሆን?

    • @MegersaBulcha
      @MegersaBulcha 2 месяца назад +1

      @@EN24new በሰዓቱ እሳቸዉ የነገሩኝ ወደፊት ኢትዮጵያ የራሱ የባህር በር እንደሚኖራት ፤ ከላይ ቀይ ባህር እንዳለ የጂቡቲን መሬት ጠቅልሎ እስከ አፋር ( ጋላፊ ፣ ዲችኦቶን ፣ አይሻ ደዋሌን ) አንደሚያጥለቀልቅ ነግረዉኛል ፤ ትክክለኛ ግን በዚህን ያህል ጊዜ ብለዉ አልነገሩኝም ።

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      @@MegersaBulcha ይህንን ስላጋሩን እናመሰግናለን ።

  • @tigistgebretsadik4469
    @tigistgebretsadik4469 3 месяца назад +1

    😂😂😂😂😂

  • @nbreading
    @nbreading 2 месяца назад

    so wedeb linoren newa😂

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      😂😂😂

  • @540963
    @540963 2 месяца назад

    አረ ይደብራል እንደዚህ የሚሊዬኔን አመትጂል ትንቢት

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      ትንቢት አይደለም ሳይንሳዊ ጥናት ነው። ከብዙ መቶ ከመታት በፊት ተደርገው የነበሩ ሳይንሳዊ ጥናቶች(ንግግሮች) እውን ሆነው አላየንም? አሁን ላይስ አልተቀበልናቸውም?

  • @matiforethiopiandiaspora327
    @matiforethiopiandiaspora327 2 месяца назад

    ጅሎች 5000000 ዓመት ስትሉ አታፍሩም። በ 500 ዓመት የምትጠፋ ዓለምን!!!

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      ውድ ቤተሰባችን ስለ አስተያየትዎ እናመሰግናለን። አለማችን በ500 ዓመታት ውስጥ እንደምትጠፋ የሚያሳይ ጥናት ወይም ትንታኔ አለዎት? ቢያጋሩን በእጅጉ ደስ ይለናል። እኛ ያቀረብነው ፕሮግራም የሳይንቲስቶች ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ ነው።

  • @teshomebelete
    @teshomebelete 2 месяца назад

    ኧረ እባክህ አቤ ሐይቅ አፋር ውስጥ አይደለም።

    • @EN24new
      @EN24new  2 месяца назад

      @@teshomebelete ሐይቁ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ድንበር ላይ ይገኛል