Tezera Hailemichael - Ney Gela Gela

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 11 янв 2025

Комментарии • 28

  • @Yesunat
    @Yesunat 29 дней назад +1

    ወንድሜ ትልቅ ሰው ነህ እናመስግናለን❤

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  28 дней назад

      በጣም አመሠግናለሁ። መልካም ቀን።

  • @natiatme8016
    @natiatme8016 2 месяца назад +1

    I would like to Thank this channel you guys healed our ears and promoted artists who are our fathers by their age with their sweet voices and magician instrumentalists.

  • @HCFEOM
    @HCFEOM 2 месяца назад +1

    Underrated but excellent.

  • @TeferiKassa-oy9yl
    @TeferiKassa-oy9yl Месяц назад +2

    መቼም የማይጠግቡ የጥንቶችን ሙዚቃ ስላስደመጣችሁን እናመሰግናለን። የመስፍን ሀይሌ ሙዚቃ ብትለቁልን?

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  Месяц назад +1

      የድምፅ ጥራት ቢያንሰውም ለትዝታ ያህል አይከፋም በማለት ያቀረብኩት ቪዴዮ አለ
      አድራሻው የሚከተለው ነው። በጣም አመሠግናለሁ መልካም ቀን ከሠላምታ ጋር።
      Video Title: Mesfin Haile - Mengedu Rezeme
      Video URL: ruclips.net/video/1dxGpEzdoSU/видео.html
      ለድምፁ ጥራት በጣም አዝናለሁ።

    • @TeferiKassa-oy9yl
      @TeferiKassa-oy9yl Месяц назад +1

      Lovely, በጣም አመሰግናለሁ። እነዝህን ሙዚቃ ስሰማ ያ ዘመን በጣም ይናፍቀኛል ለእኔ ሙዚቃው ዘመኑን ዘመኑ ሙዚቃውን ይገልፅልኛል።

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  Месяц назад

      በትክክል ሙዚቃው ዘመኑን ዘመኑ ሙዚቃውን ይገልፃል። የብዙ ሙዚቃ አፍቃሪዎች ስሜት እንደሚሆን አልጠራጠርም። በጣም አመሠግናለሁ መልካም ቀን ከሠላምታ ጋር።

  • @GabrielSaint-cm1tf
    @GabrielSaint-cm1tf Месяц назад +4

    ስለ ተዘራ ኣዳች ነገር ሳይሉ ማለፉ ለአዳዶቻችን ሊከብድ ይችላል።ተዘራ የቅጽል ስሙ "የሙዚቃ ሳጥን ነው"። አጭር ባለጊታር፣ የክብር ዘበኛ ኦኬስትራ ደማቅ ቀለም፣ ተዘራ በዘመኑ በብዙ ይታወቃል ።" እኔነኝ እኔነኝ ተዘራ፣የማስደስታችሁ ከጊታሬ ጋራ" የሚል ዜማው የመድረክ መፈክሩ ነበር።
    ተዘራ እራሱ ከሚጫወታቸው ዘፈኖች ባሻግር የጥላሁንን፣ የብዙነሽ በቀለን ዜማዎችና ግጥሞች ፈጣሪም ነው።ተዘራ ገጣሚነቱ ይበልጥ ለሌሎች ድምጻውያን በሚያሰሙት ዜማ ጎልቶ ይሠማል።
    ከሙዚቃው ዓለም ውጪ ተዘራ በወታደርነቱም የሚኮራ ለመሆኑ ለዘፈን በነቀሰው ግጥም '"ተረኛ ነኝ እና እዳትሸበሪ፣ስለይሽ አድራለው አልማዝ ደህና እደሪ።" ሲል ለሌሊት ጥበቃ መወጣቱን ሲገልጽልን ነው።ይኸው ዘፈን" አልማዝ ደህና ደሪ"በዘመኑ ተወዳጅ ነበር።
    እንደ አገር ፣እንደ መንግሥት፣እንደ ሕዝብ ለጥበበኞቻችን ውለታ ቢስ ነን።ብዙዎቹ በድህነት ሲሞቱ ምናልባት ቀብር አድማቂ ከመሆን የዘለለ መዋጮ አላደረግንም።ታሪካቸውን በቅጡ አልጻፍነውም።ቤተስቦቻቸውን በቀጣይ ድህነት ችላ ብለናቸዋል።ይቺ አገር እንዲሁ ትቀጥል አሊያም ታበቃ ይሆን?

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  Месяц назад +1

      የደን ውስጥ ፍሬ ሰው ሳይዘራው በቅሎ፣
      በክርስቶስ ጥበብ የሚታየው በስሎ።
      እንጆሪ ብርቱካን ሙዝ እና ፓፓዬው፣
      ፍሪው ተንዠርግጎ በዓይናችን ስናየው።
      ልቤ አውሬ ባይፈራ ብገባ ደፍሬ፣
      ሊያኖረኝ ይችላል የደን ውስጥ ፍሬ።
      በደን ውስጥ የሚገኝ እንኮይ ሆነ ኮሽም፣
      ይጣፍጣል እንጂ አይመርርም ትንሽም።
      የሸንኮራ አገዳ እንዲህም ኮኩ፣
      ከጣዕሙ ጋራ አስደሳች ነው መልኩ
      ልቤ አውሬ ባይፈራ ብገባ ደፍሬ፣
      ሊያኖረኝ ይችላል የደን ውስጥ ፍሬ። .......
      ተዘራ ኃይለሚካእል።
      ሰው የሥራውን የማያገኝበት አንዱ በደከመው ሌላው የሚያጌጥበት ናት ዓለማችን። ምን ቢደረግ ምን እንደሚሻል አላውቅም ፈፅሞ ወንጀል መሆኑን ግን ልቤ ካስተዋለ በጣም ቆይቷል። ስለ አስተያየትህ በጣም አመሠግናለሁ መልካም ቀን ከሠላምታ ጋር።

    • @GabrielSaint-cm1tf
      @GabrielSaint-cm1tf Месяц назад +1

      እኔም እጅነሳሁ!

    • @Yesunat
      @Yesunat 29 дней назад

      እናመሰግናለን❤

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  29 дней назад

      @@Yesunat አመሠግናለሁ። መልካም ቀን።

  • @baheramen267
    @baheramen267 2 месяца назад +3

    የተከበራችሁ የእድሜ መስታወት አቅራቢዎች እንደተለመደው ከማይደርቀው የወርቃማው ዘመን የሙዚቃ ምንጫችሁ የተወዳጁን ጊታር ተጫዋች፣የዜማና ግጥም ደራሲ
    ና ድምፃዊ ተዘራ ሀይለሚካኤልን ውብ ስራዎች ስላስደመጣችሁን ከልብ እያመሰገንኩ ምርቃት ሁሌም ስትሰጡ አይጉደልባችሁ።በተረፈ ሁለተኛው ትራክ ይሄም አለለካ የሚለውን ዘፈን እስከ ዛሬ ጋሽ ተፈራ ካሳ ሲዘፍነው ነበር የማውቀው ከሁለቱ ማን ቀድሞ እንደዘፈነው ያለህን መረጃ እንድታደርሰን እያልኩ በዚሁ አጋጣሚ ሌላውን የክብር ዘበኛ እንቁ ድምፃዊ እና የህክምና ዜማ ደራሲ ይተፈራ ካሳ ድንቅ ስራዎችን ጀባ ብትሉን ስል በትህትና እጠይቃለሁ አመሰግናለሁ በወዳጅነታችን እንሰንብት።

    • @leulgebremeskel5906
      @leulgebremeskel5906 2 месяца назад

      እኔም ከሁለቱ ማን ቀድሞ እንደተጫወተው ብትነግረንና ነይ ገላ ገላ የሚለውንም ካልተሳሳትኩ ጥላሁን ገሠሠ የተጫወተው ይመስለኛል የሁለቱም ሙዚቃዎች ደራሲው ተዘራ ኃ.ሚካዔል ይመስለኛል

    • @baheramen267
      @baheramen267 2 месяца назад

      ስለእውነት እኔም ማን ቀድሞ እንደዘፈነው አላወቅሁም የግጥም እና ዜማ ደራሲው ግን ጋሽ ተፈራ ካሳ ይመስለኛል አብዛኛውን እራሱ የዘፈናቸውን ዘፈኖች የራሱ ድርሰቶች ይመስሉኛል በተረፈ ጋሽ ጥላሁን የተጫወተው ነይ ገላገላ የሚለውን የጋሽ ተዘራን ዘፈን ሳይሆን "እቱገላ እቱገላዬነሽ ደማማዬነሽ የሚል ሌላ ዘፈን ነው የተጫወተው።

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  2 месяца назад

      እዚህ ቻናል ላይ አንድ የተፈራ ካሳ ቪዴዮ አለ ምናልባት ካላየኸው አድራሻው ይኸው።
      Title: "Tefera Kassa Woubit"
      Video URL: ruclips.net/video/QO7E7Ls-R6Y/видео.html
      የተፈራ ካሳ ስራ በ 12 ዜማዎች የሚወሰን አይደለም። አባቶቻችን አንዳሉት "ሰዶ ማሳደድ ቢያምርህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ" ሆኗል ነገሩ። ሌሎቹ የት እንደሚገኙ አላውቅም። በጣም አመሠግናለሁ መልካም ቀን ከሠላምታ ጋር።

    • @leulgebremeskel5906
      @leulgebremeskel5906 2 месяца назад

      @@baheramen267 አይደለም ነይ ገላ ገላ የሚለውንም ተጫውቶታል ጥሌ እቱ ገላ እቱ ገላ ገላ የሚለውን በካሴት መታተም ሲጀምር አካል አይንሽን ጣል አርጊብኝ እባክሽን ከሚለው ጋር የወጣነው ነይ ገላ ገላ ብሎ ጥላሁን የዘፈነውን ፈልጌ ካገኘሁት እልክልሀለሁ

    • @baheramen267
      @baheramen267 2 месяца назад +1

      ወዳጄ ልዑል በጣም አመሰግናለሁ አግኝተኸው እስክሰማው በጉጉት እጠብቃለሁ በተረፈ እኔ ጋሽ ጥላሁን እስከዛሬ የብርቅነህ ዑርጋን ወደፊት በሉለት ይለይለት የሚለውን ዘፈን ብቻ የሌላ ዘፋኝ ዘፈን የዘፈነ ነበር የሚመስለኝ ስለዚህ ሌሎችም የምታቁትን መረጃ ብታካፍሉን እያልኩ በአጠቃላይ የእድሜ መስታዎት እድምተኞች እና አቅራቢዎች ከልብ አመሰግናለሁ። በወዳጅነታችን እንሰንብት

  • @teddyhaile6755
    @teddyhaile6755 Месяц назад +2

    Agote eko nw ..Egezehabehare Gare hedale ke Ayate gare Ke Enate gare ke selam gare ke Akeseta gare ke Agote gare ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  Месяц назад

      ተዘራ ኃይለሚካኤል በዘለዓለማዊ ሥራዎቹ ዘለዓለማዊ ነው ብዬ ብል ስህተት እንደማይሆን እጅግ በጣም እርግጠኛ ነኝ። ያለፉትን ነፍስ ይማር በሕይወት ላለነው ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር እመኛለሁ። መልካም ቀን ከሠላምታ ጋር

    • @teddyhaile6755
      @teddyhaile6755 Месяц назад +1

      @@edimemestewate755 ❤❤❤ Amen wede

  • @solomontekelu3389
    @solomontekelu3389 2 месяца назад +3

    አሪፍ ኦልዲስ ምስጋና ይድረሳችሁ ሰለሞን ከ island

    • @edimemestewate755
      @edimemestewate755  2 месяца назад

      በጣም አመሠግናለሁ። መልካም ቀን ከሠላምታ ጋር።

  • @behayludinku2160
    @behayludinku2160 2 месяца назад +2

    ስራዎቹ ተደብቀው የኖሩ እንቁ አርቲስት ነው ። እባካችሁ ሌሎቹንም ስራዎቹን አጋሩን። አይቤክስ እና ሰብሊ የአባታችሁን ስራ ከያለበት ሰብስባችሁ እባካችሁ ዳግም ለህዝብ ጆሮ አብቁልን።