Hallelujah |ሃሌሉያ | Aster Abebe Vol 2 Full Album

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 25 дек 2024

Комментарии • 1,2 тыс.

  • @AsterAbebeOfficial
    @AsterAbebeOfficial  Месяц назад +872

    ለፀጋው ክብር ይሁን
    ፀልዩልኝ 🤲🏻

    • @LegesseBurako-q6s
      @LegesseBurako-q6s Месяц назад +31

      Let God lead your way through out your life!. You are blessing to us!

    • @girumtesfaye
      @girumtesfaye Месяц назад +19

      አሜን! ጸጋ ይብዛልሽ አስቱ! ❤

    • @tesfalegntadesse3123
      @tesfalegntadesse3123 Месяц назад +5

      tebarek be geta bisema bisema alitegibewum mezimurochishin ♥♥♥♥♥♥

    • @eyerusalemmitiku1235
      @eyerusalemmitiku1235 Месяц назад +10

      አሜን!.
      እንደው ምን ልበል በሰማያዊ ቅኔ ረሰረስን, አንቺን የሰጠን እግዚአብሔር ስሙ ከፍ ይበል!!. አሁንም ይብዛልሽ ቤትሽ ያንቺ የሆነው ሁሉ ይባረክ!! ❤❤❤❤❤❤

    • @KirubelGobena
      @KirubelGobena Месяц назад +13

      ታላቅ እና የተፈራህ አምላክ ለ ክብርህ ብቻ እንዲሆን ስላረከው ዝማሬዎች እና አስቴር እናመስግንሃለን! እኔን ተነስቼ እንድዋጋ እያበረታኝ ነውና አታስቢ ለክብሩ ሆኖአል

  • @Abenezer1100
    @Abenezer1100 2 месяца назад +562

    ማጋነን አይሁንብኝ እና አብዛኛው ዘማሪያን ሁለተኛ አልበማቸውን ሲለቁ እንደ መጀመሪያ አይሆንም በጣም ስለምንጠብቅ ነው መሰለኝ! የአንቺ ግን ከላይ እንደሆነ ይናገራል እስካሁን ያልሰማዋቸው መዝሙሮች አሉ የሆነ መዝሙር ስሰማ ልቤ ይፈስና አንዱ መዝሙር ላይ ብዙ ቀን አሳልፋለው ብቻ ለወራት የምባረክበትን በረከት ነው ጌታ አንቺን ተጠቅሞ የሰጠን
    በእውነት ከፀጋው አትጉደይ ጌታ አብዝቶ ይባርክሽ ያሰብሽውን ሳይሆን እርሱ ያሰበልሽን ይስጥሽ

    • @melesetadesse1621
      @melesetadesse1621 2 месяца назад +17

      በእውነት በትክክል ሀሳቤን ገለጥከው ወንድሜ፡፡ አስቱዬ ተባረኪ ያንቺ ይለያል በርቺ ሁል ግዜ መንፍስ ቅዱስን አዳሚጭ ግዜ ስጭው በዘመንሽ ብዙ ይስራል ገና

    • @amsalemulatu7920
      @amsalemulatu7920 2 месяца назад +4

      ❤❤❤እግዚአብሔር አብዝቶ በጸጋው ይባርክሽ❤❤❤❤❤❤❤❤😂

    • @kenenimulatu1845
      @kenenimulatu1845 2 месяца назад +2

      so true

    • @sitootas
      @sitootas Месяц назад +2

      God bless you more.

    • @zewidetilay9679
      @zewidetilay9679 Месяц назад

      ❤❤❤❤

  • @Earme-x2e
    @Earme-x2e Месяц назад +86

    አስቴር አወቀ በምትባል ዘፋኝ ምድር ላይ ከተጣበኩበት ነጥቃ አስቴር አበበ የምትባል ዘማሪ ከእየሱስ ጋር አጣበቀችኝ ዘመንሽ ይባረክ!

  • @SefanitAbayneh
    @SefanitAbayneh 2 месяца назад +213

    አንድ ሺህ ጊዜ like ማድረግ ቢቻል ብየ ተመኘሁ ድንቅ ዝማሬ፡፡ ጌታ ሆይ ስምህ ብሩክ ይሁን ተባርከናል ተጠምተን ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስ በብዙ እጥፍ ይባርክሽ አስቱ፡፡

  • @kalebdawitofficial4003
    @kalebdawitofficial4003 2 месяца назад +57

    በመንሳዊ እርጅና ትውልዱ በተዋጠበት በዚህ ዘመን።አካላዊ ሳይሆን መንፈሳዊ ህይወትሽ መዘነጡን በተግባር አሳይተሽናል።ዘመንሽ ይባረክ።

    • @tesstefera6334
      @tesstefera6334 2 месяца назад +1

      Tebarek

    • @Alem-b9p
      @Alem-b9p 23 дня назад

      ጌታይክበረቅሬታዎች አሉት ❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉

  • @bettymamo909
    @bettymamo909 2 месяца назад +63

    እኔ በበኩሌ ሌላ ነገር መስማት እየቻልኩኝ አይደለም ጌታን የአስቱ ቁ 2 አልበም ከተለቀቀ በኋላ ይሄንን ብቻ ነው እየሰማሁ ያለውት💞

  • @hewis9138
    @hewis9138 2 месяца назад +96

    እግዚኣብሔር ሲወደንና ሲራራልን፡ ኣስቴርን ቀብቶ በዚህ ዘመን ሰጠን። ስሙ ይባረክ።

  • @ABENEZERTEMSGENTUMISO
    @ABENEZERTEMSGENTUMISO 2 месяца назад +125

    እኔ ላለፉት 9 አመታት እዚህ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነው የምኖረው። ከቁጥር አንድ መዝሙርሽ ጀምሮ በአገልግሎቶችሽ ስባረክ ስበረታታ ነበር አሁን ደግሞ በበለጠ ፀጋ ተገልጥሽልን። አንቺ ለኛ በበረሃ ውስጥ የፈለቅሽ ምንጭ ነሽና ሁልጊዜ ስለአንቺ ጌታን እናመሰግነዋለን❤🙏

  • @markosmarye
    @markosmarye 2 месяца назад +119

    እህታለሜ ምንጭሽ አይድረቅ! ስንት ቀን ይኸው ጠጥቼ ጠጥቼ አልረካሁም! ከየት እንደቀዳሽ ያሳብቅብሻል ። ጌታ ኢየሱስ ዘላለምሽ እየባረከ ይባርክ። ❤❤❤

  • @tinsaeabera4515
    @tinsaeabera4515 2 месяца назад +175

    Honestly መዝሙር መፃፍ ነዉር በሆነበት ዘመን ወጣቱ የሰባዎቹን እና ሰማኒያዎቹን መዝመር መዚቃዉን አሳምሮ በመድረኩ ሲያስጨፍር ለዚያዉም ኦርጅናል ዜማውን አጣሞ አንቺ ግን እንዲህ ያለ ዉድ ግጥም እና ዜማ ስላቀረብሽልን እጅግ በጣም ደስ ብሎናል፡፡ ፀጋ ይብዛልሽ ፡፡ ምርጥ ግጥም ፤ምርጥ ዜማ ፤ ምርጥ ቅንብር

    • @belaynegash6550
      @belaynegash6550 2 месяца назад +13

      ከምንጩ ሲቀዳ እንዲህ ነው 🎉

    • @michotamekuria89
      @michotamekuria89 2 месяца назад +7

      በጣም እንጂ ! ካሱን እኮ ቆንጆ ቆንጆ አልበም እየሰጡን ጌታ ይባርካቸው ዘማሪዎቻችንን

    • @Angela_436
      @Angela_436 2 месяца назад +9

      በትክክል እኔም የታዘብኩት ነው ፥ኧረ እንደዚ ተንበርክከው መዝሙር የሚቀበሉ ይብዙልን ።ቤተክርስቲያን እንደድሮ ለኳየር ቦታ ብትሰጥ ጥሩ ነበር አምልኮ ቡድን መሪ የሚባል ነገር መቶ ነው ትውልዱ የተበላሸው ፥ሲቀጥል የሰውንም መዝሙር ሲዘምሩ ጸልየው እንኳን አይቀርቡም ይሄ መዝሙር ከዚ ጋር ይሄዳል ይሉና ነው መድረክ ላይ ወተው የሚጨፍሪት ደግሞ የሚያሳይኑስ ስቃይ ፡ምንም በሌለበት አጨብጭቡ እጅ ወደ ላይ እልል በሉ የትዛዙ ብዛት ኡፍፍፍፍ እኔማ ይሉኝታ ስለማላውቅ ጉዳየ አይደለም ካልተሰማኝ እጄን አጣምሬ ቆሜ ነው የማየው የምቆመውም ህዝቡ ስለሚያሳዝነኝ ህዝቡን አክብሬና የዋሆቹን እንዲላሰናክል ነው ። ያ ደግሞ የፈረደበት የአዲስ አለም መዝሙር ከአመድ ላይ የተነሳ የሚለውን እማ እስክሳ መምቻ መጨፈሪያ አድርገውት ቁጭ ብለዋል እንደው አንድ አደባባይ ሰብስቦ የሚገስጽ አቅጣጫ የሚያስዝ መጥፋቱ ያሳዝናል በተረፈ እኔ መዝሙር በጣም ነው የምወደው በጣም! ጌታን ሳላውቅ ነው መዘመር የጀመርኩት ግን ዘማሪ አይደለውም ።ለእውነተኛ ዘማሪዎች በጣም ትልቅ ክብር አለኝ እወዳችኃለው ማንም ሲነካቹ አልወድም አስቱም ሁላቹም ተባረኩልኝ ጸጋ ይብዛላቹ እኔና እክስቴ በእናንተ መዝሙር ጌታን ተቀብለናል ስማቹን መጥቀስ አልፈልግም በጌታ ሳንሆን የብዙዎቻቹን እንሰማ ነበር በድጋሚ ተባረኩ።

  • @bettymamo909
    @bettymamo909 2 месяца назад +108

    የተወደድሽ ነሽ❤❤ለአመታት የሚሆን ምግብ ነው የሰጠሽን የሰጠሽ ጌታ ስሙ ይባረክ💞💞💞ፀጋ ይብዛልሽ❤

  • @bethget1850
    @bethget1850 Месяц назад +14

    የሚጣፍጥ ድምፅና ዜማ አስደናቂ በመገለጥ የተሞላ ግጥም እውነት፣ፅድቅ ፣ እ/ን መፍራት መፈለግ የተሞላ ፤ ስብከት፥ ትምህርት ፥ፀሎት የነፍስ ምግብ የሆነ ዝማሬ ዘመን ዘላለምሽ ይባረክ ይብዛልሽ ። ይኸው እስካሁን ሌላ ነገር መስማት አልቻልኩም

  • @MerakiAcademy
    @MerakiAcademy 14 дней назад +9

    ያለምንም ማጋነን፣ this is the best Christian Album of the last 20 years.

    • @LensaKebeWakjira
      @LensaKebeWakjira 10 дней назад

      Awo lik new ewunett new yihew 2 wer honegn sisemaww mezmurun hule adis ...yigrmal Geta kibrun yiwusede

  • @teferiwoldeyesus883
    @teferiwoldeyesus883 2 месяца назад +12

    የበረከት አምላክ በፀጋው ይደግፍሽ እንዳው በምኔ ቋንቋ ልግለጽሽ ወይኔ አስቱየ እንዴት የተባረክሽ ልጅ ነሽ አዝኜ ተጽናናሁበት ደክሜ በረታሁበት አጥቼ አገኘሁበት የዘለአለም አምላክ ከነ ዘሮችሽ ከክፍ ሁሉ ይጠብቅሽ ልጄ በርቺ

  • @tenaadmassu2031
    @tenaadmassu2031 Месяц назад +8

    በጣም የሚገርም መዝሙር ነው! 'ጉዳዬ' የሚለውን መዝሙር ሰምቼ ወደሌላው መዝሙር ማለፍ አልቻልኩም፡፡ ጌታ ይባርክሽ! "ሁሌ ሁሌ ሁሌ ኢየሱስን ብቻ እስክ ዕድሜዬ መቋጫ...."

  • @romankebede6548
    @romankebede6548 2 месяца назад +17

    አንቺ አስቱ የዘመናችን ልዩ ክስተት ነሽ እንዲህ ወደ ጌታ የሚያቀርቡ መዝሙሮቾ በተራብንበቶ ዘመን አንቺ ሎዩ በረከት አድርጎ ጌታ ሰጠን ተባረኪ ጸጋ ይጨመርልሽ❤

  • @abelhabtamu7995
    @abelhabtamu7995 28 дней назад +7

    ኡኡኡኡኡአኡኡኡአኡኡኡ አስቱዬ እህቴ ወድጄሽ ልሞት ነዉ በቁጥር አንድ መዝሙርሽ በጣም ተባርኬ ነበር አሁን ደግም ብሶብሻል እና ቃል አጥሮኛል አገልግሎትሽ፣ትዳርሽ ያንች የሆነዉ ሁሉ ይባረክ ቀጥይ ቁጥር ሶስት እጠብቃለሁ በድጋሜ ተባረኪልኝ ።

  • @DagimawiTeklu
    @DagimawiTeklu Месяц назад +13

    ያላነሰ ያላጠረ፣ ከላይ ከላይ ያልሆነ፣
    ለኔ ፍቅር ለእየሱሴ፣ አለኝ ምስጋና ከነፍሴ
    .
    .
    ብለሽ እንደዘመርሺው፣ በእውነትና በመንፈስ ከውስጥ የሆኑ መዝሙሮችን ስላቀረብሽልን፣ ስለተባረክንበት ክብሩን ሁሉ እሱ እግዚሃብሔር ይውሰድ፡፡ ዘመንሽ የተባረከ ይሁን!

  • @TsedeyEndeshaw
    @TsedeyEndeshaw Месяц назад +10

    አስቴር እግዚአብሔር በአንቺ የገለጠው የመገለጢ ሀይል እንዲህ ነው ብዬ በቃል መግለጥ ይከብዳል ብቻ እንዳልሽው የፀጋው ባለቤት ይባረክ እንችንም ለእኛ የሰጠን ከመሪት ስበት አውጥቶ አንገታችንን ወደላይኛው ቤታችን እነድናደርግ ያደረገን ስሙ ከዘላለመ እስከዘላለም ይባረክ። የእኔን ልናገር በቀን ሳደምጠው ሁሌ እንደአዲስ በየቀኑ በመደነቅ እሰማሐው እሚገርመኝ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መሆኑ በለሊት ዝማሪዬ እሲ ነው በሆነ ሰአት ስገላበጥ እየዘመር በዚማሪውስጥ ያለውን እግዛቤርን ስፈልግ እራሴን አገኘዋለው አሁንም እኔም እላለሁ የፀጋው ባለቤት ይባረክ እሰይ እልልልልልልልልልልልልልል ክብር ይሁንለት አንችም ዘመንሽ ይባረክ ከዚህ ክብር አትውሰጂ ተባረኪ

  • @solomonabu-zb7fd
    @solomonabu-zb7fd 2 месяца назад +13

    እንደዚህ መዘመር እንደሚቻል ከእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚቻል ስላሳየሽን ዘመንሽ እንደዘመርሽው ይሁንልሽ❤🎉🎉❤

  • @wubitesayasofficial6097
    @wubitesayasofficial6097 2 месяца назад +14

    በጌታ ምን አይነት ቅባት ነው❤ መንፍስ ቅዱስ የቅኔና የዜማ ቃሉን እየተረጎመልሽ መንፍሳዊዉን አለም ወደመረዳት ውቅያኖስ ውስጥ ይዞሽ ገባኮ❤❤ሰምቼ ሰምቼ ቃል አሳጣኝ የምር...ጌታ እንዴት ያለ ብሩክ አምላክ ነው እንዴት ያለ ባለጠጋ ነው ኤረ....ኡኡኡ🎤🎹🎻🥁🎸🎷🎺ድምጽ ባለው ዜማ ሁሉ ክብር በአሪያም ይሁንለት።

  • @henokbehailu5762
    @henokbehailu5762 2 месяца назад +10

    መስማት መስማት መስማት እንደገና መስማት ሌላ መረዳት ሌላ ግርምት እህቴ ዘማሪ አስቱ ተባረኪ ይህ ብርሃን እንደዋጠሽ ዘመንሽ ይድመቅ

    • @tayedue2jesus
      @tayedue2jesus 2 месяца назад

      አስቱ ተባረኪልን❤

  • @yemisrachfeseha9995
    @yemisrachfeseha9995 Месяц назад +9

    እንደዚህ ያዘመረሽ የፀጋው ባለቤት እግዚአብሄር ይመስገን ከዚ በላይ እንደባለጠግነቱ መጠን ይባርክሽ!!

  • @ruthgetachew8170
    @ruthgetachew8170 2 месяца назад +9

    በእየሱስ ስም በጣም እኮ ነው የምወድሽ፡፡
    ሁሌም የሚያረሰረሱ ዝማሬዎችሽ ለኔ ማምለኪያ ማመስገኚያ ህብረትን ማድረጊያ ብዙ ብዙ…. ናቸው፤ ሀሌሉያ ደግሞ ለኔ ብቻ እስኪመስለኝ አስተማሪ፣ መካሪ መልእክት ሆነውልኛል፡፡ አመሠግንሻለሁ ለምልሚልኝ የምወድሽ፡፡

  • @EleniKehali
    @EleniKehali Месяц назад +7

    It feels like reading Bible when i listen this album ❤❤❤God bless you astuye geta banchi eysera nw demom yeseral gena🎉🎉🎉❤❤❤

  • @menberekebede1442
    @menberekebede1442 2 месяца назад +44

    ኡ.............. አረ ምን ጉድነው ቅኔ እንዲህም ይዘረፋል? አረ እንደው ስለአንቺ ጌታ ኢየሱስ ስሙ ይባረክ ብዢልን ብዥልን አትጉደዪ ውብ አይኖቹ ከአንቺ አይነሱ እየደገመ ይይሽ እየሰጠ ይስጥሽ ኡፍ...... እንዴት አረፍኩ !!!

  • @Marcy-77999
    @Marcy-77999 Месяц назад +10

    የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ 🙌ሃሌ ሉያ!!🙌🙌

  • @GirmaKassa-rw4hm
    @GirmaKassa-rw4hm 2 месяца назад +23

    የቃሉና የመንፈሱ ሙላት ያለው እንዲህ ለሌሎች ፈውስ ይሆናል ውድ እህቴ በደሙ ተሸፈኝ ከዘመኑ ሽንገላና በሽታ ተሰወሪ ፀጋሽ ዘመኝ ዘለቅ ይሁን "በዘመኔ አያለሁ" ያልሸውን እንደ ስምኦን እና ሀና ያሳይሽ ያሳቅፍሽ እሱ የእኔም ፀሎትና መሻት ስለሆነ በወሳህና ማግስት ድንጋይ ከሚወረውሩብሽ ይሰውርሽ እየሱስን ጋርደው እነሱ በትውልድ ልብ ከተሳሉት አይነት ከሳሪዎች ተርታ ልክ እንደዘመርሽው አያድርግሽ የኔ ጣፋጭ ሁልግዜም በመንፈስ ቅዱስ የተቀመመ የነፍስ ምግብ አቅራቢ ያድርግሽ ትውልድ እና ዘመንሽ በጌታ የተጠቀለለ ይሁን በድካምና በክፍተትሽ የሚቆሙ በየ አህጉሩ ስለ አንቺ የሚፀልዩ ያኑርልሽ ።ተ ባ ረ ኪ!!!!

  • @amuasefa8939
    @amuasefa8939 2 месяца назад +19

    ከእግዚአብሔር ቃል የተቀዱ ቅኔዎች ብሰማ ባደምጥ አልረካ አልኩ
    ዘማሪት ዘመንሽ ይለምልም

  • @TeLa-u8l
    @TeLa-u8l 2 месяца назад +10

    አስቱ ዘመንሽ ዘር መንዘርሽ ይባረክ ይህ ከሰው ዘንድ አይገኝም ከምንጩጋ እንደቆየሽ ይታወቃል አሁንም ፍጻመሽ ከጸጋው ዙፉን ሥር ይሁንልሽ።

  • @muluneshtekletsadik8581
    @muluneshtekletsadik8581 2 месяца назад +9

    ላክልን ሊቀ ካህን ከሙሴ ከአሮን የሚልቅ አድራሻዬ ብየዋለሁ ይሄንን ዝማሬ❤❤❤❤

  • @misganaguchie9293
    @misganaguchie9293 2 месяца назад +26

    ለመንፈሳዊ ረሀቤ ምግብ የሆነ መዝሙር አገኘሁ።
    መዝሙር እየበላሁ ነው።
    አስቱዬ ተባረኪ፣ ይብዛልሽ፣ ከዚህ አትጉደዪ፣ ከኛ የተሻለ የአምልኮ ጥልቀት ውስጥ ነሽ። እኛም በማምለክ እንከተልሻለን። አትቁሚ፣ ከኛ ብትሻዪም ከእርሱ አንፃር ገና ነሽ ቀጥዪ ይብዛልሽ።

  • @muluhundabo5046
    @muluhundabo5046 Месяц назад +20

    ዛሬ በዚህ ማለዳ ቅድስናዬ ነህ የምል መዝሙር መልዕክት ሆኖ ስመጣልኝ ሰርች አረገ መስማት ጀመረኩ ከዛ ቀጥሎ በዚህ ገባሁ ቀጥታ ወደ አባቴ በመንፈስ መብረረ ጀመረኩና ግን ምን አይነት ድምፅ ምንአይነት ችሎት ጥበብ መረዳት ነው ስለ ዮሰፍ የዘመረች ብዬ ስምጥ ስል ተመለስኩና ቀና ብዬ ወደ አባቴ ሳይ ለካ ፀጋ ነው በቃ አባቴ እንዲህ የማያቋረጥ ምንጭ ያፈልቃል ይችላል ያዘምራል ሰማያዊ ዝማረ 🎉🎉🎉❤ ተባረክ እወድሻአለሁ ረጅም እድመና ጤና ይስጥሽ እሰከ ፈፃመሽ ዘምረ ተገለጭ በእየሱስ ስም አትደበቅ አዳባባዮች ለአንች ይሁኑ ገደብሽ ይከልከል ፀጋ ይብዛልሽ።❤❤

  • @Mimitwa
    @Mimitwa 2 месяца назад +11

    በዘመኔ አያለሁ ብዬ በመዝሙርሽ አብሬሽ ዘምሬ በመዝሙሩ እነዚህን ያልሻቸውን ሰዎች አንቺ ሆነሽ አየሁት የጌታ ውድና የዘወትር መጠቀሚያ አስቱ....ዘመንሽ የበረከት ነው። ለወደፊትም ፈቃዱ ብቻ ያግኝሽ። እንዳትረፈረፍሽን ተትረፍረፊ ላንቺም ሰማይ ዠቅ ብሎ ይከፈትልሽ።

  • @Marcy-77999
    @Marcy-77999 Месяц назад +8

    አቤት 🫢እግዚአብሔር እንዲህም ይሰራል በባሪያዎቹ ላይ ስሙ ይባረክ🙌 አስቱ በረከታችን ነሽ በኢየሱስ ስም ዘመንሽ ይለምልም የጌታ ፀጋና ሰላም ይትረፍረፍልሽ 🙌🙌🙌

  • @Maranata224
    @Maranata224 2 месяца назад +6

    ዘማሪት አስቴር በእውነት ከ አብ ከላይ የተሰተሽን ትልቁ ስጦታችን ነሽ አንድ ከ አንድ መዝሙርሽ መለየት ይከብዳል ሁሉም እንደ እግዝኣብሔር ቓል ና የማይጠገቡ ናቸው ::

  • @zinashhuluka-og3fd
    @zinashhuluka-og3fd 9 дней назад +4

    አስቱዬ ለምንድነዉ መዝሙሯ ሰምቼዉ ሰምቼው የማልጠግበዉ ከሚገርመው ነገር ሌላ መዝሙር ለመስማት እከፍትና ዘግቼ ተመልሼ ያንችን ከፍታለሁ ሳልሰማሽ አልዉልም እያንዳዱ መዝሙሮችስ ለኔ መልህክት አላቸው ይህ ከጌታ ካልሆነ እንደዚህ የሰው ልብ ላይ ቁጭ አይልም እኔ ምን ልበል የፀጋው ባለቤት የተባረከ ይሁን ። አንቺን መጠቀሚያ አድርጎ በመዝሙሮችሽ ሰለምንፅናና የጌታን ትልቅነት ሰለምናይበት ወድድድድ አረረግሻለሁ ይህ ፀጋ አይወሰድብሽ በረከታችን ነሽ ዘመንሽ ትዳርሽ ልጆችሽ ሁሉ ይባረክ።

  • @bettymamo909
    @bettymamo909 Месяц назад +47

    1M view 🥰🥰 like አርጉ እንጂ ወንድሞች እና እህቶች እኔ like አንዴ ብቻ ስለሚቻል እንጂ ሁላችሁንም ጨምሬ ነበር like የማረገው 😁 view 2M መግባት አለበት ከዛም በላይ

  • @Medy-qo8cq
    @Medy-qo8cq 2 месяца назад +8

    ፍፁም ደስታ ኡፍፍ ሰማይ ሰማይ የሚሸት ከምድር የሚያስለቅቅ ከሰማይ የተሰጠ የሚያረሰርስ ተባረኪ ዘመንሽ በከፍታ በቤቱ ይለቅ

  • @BanchilayAbigail
    @BanchilayAbigail Месяц назад +14

    የኔ ጌታ የኔ ውበት የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት
    የኔ ወዳጅ የኔ ውበት የኔ ፍቅር የኔ ናፍቆት መኖር አልችልም ያላንተ ያላንተ ፈራለሁ
    ሁሉም ክድንድን ያለ ነው
    መኖር አልችልም ያላንተ ያላንተ ፈራለሁ
    ሁሉም ጭልምልም ያለ ነው
    አሁንም እላለሁ ጥማኝ አሁንም እላለሁ ራበኝ
    አሁንም እላለሁ ናፍቀኝ በማንነትህ ልክ
    የረሃቤ ቁመቱ ይላቅ ከከበበኝ
    አይሰረቅ እይታዬ ዘልቆ ላያዘልቀኝ
    ከጎደለኝ ነገር ከምለው ይህ ቀረ
    ይሁንልኝ ረሃቤ ላንተ ያጋደለ
    በተጨመረልኝ እድሜ በተቀጠረልኝ ቀናት
    ነፍሴን ዝም ፀጥ አሰኝቼ ከጌታ ውጭ ላልሰጣት
    ነጥቅያት ከሌላው ጎዳና ትዋል ኮቴህ በሚረግጥበት
    ልቤን እንዲህ አስፋልኝ እና ላጊጥ በፍቃድህ ውበት
    ልመርቅ በእጆችህ ለማዶው ሽልማት
    ፍለጋህን እንድከተል ስጠኝ ፀጋህን በብዛት
    ትሁን ነፍሴ እንዳልካት ደስታህ ኃይሌ ነው የሰማይ ፍቃድህን በምድር ስኖረው
    አሜንንንንንንንንንንንንንን አሁንም አሁንም አሁንም የኔ ውድ እየሱስ

  • @AmanuelJemaneh
    @AmanuelJemaneh 2 месяца назад +8

    በእውነት ሰማያዊ ዝማሬ ማለት ይሄ አልበም ነው....ስለ ቁስ አያወራ የምድር ዝናን አይገልፅ....ኡፍ ይመክራል :ያስተምራል :ይገስፃል :ይፈውሳል :ይናገራል :ይለውጣል :ይመራል ብቻ ጌታ ባንቺ ባረከን.... ተባረኪ ፀጋሽን ጌታ ያብዛልሽ....

  • @lookinguntoJesus3.16
    @lookinguntoJesus3.16 2 месяца назад +9

    በዘላለም የፍቅር እጆቹ ውስጥ ካለች የምትጤስ ጧፉ ይህን የመሰለ ልብን የሚያረሰረስና መንፈስን የሚያድስ ተስፋንም አድሶ ያለንበትን የጨለማ ዘመን የሚያሳልፍ የቃሉን ብርሃን በእህታችን መዝሙር ያበራልን ጌታ ስሙ ይባረክ።
    ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ። ኢሳይያስ 60፥1
    የላከውን ክብር የሚፈልግ እርሱ እውነተኛ ነው በእርሱም ዓመፃ የለበትም። ዮሐንስ 7፡18

  • @mestuhumnesaduga
    @mestuhumnesaduga 29 дней назад +7

    አቤት ጌታ ሆይ ስለእህታችን ተመስገን ስምህ ብሩክ ይሁን ነፍስን የሚመልስ መዝሙር ❤❤

  • @yohannesmkfk38
    @yohannesmkfk38 2 месяца назад +30

    አላቅም ለምን እንደሆነ ልክ ልሰማ መዝሙርሽን ስከፍት ራሴን ተንበርክኬ አገኘሁት።ጸሎትን የሚያቀጣጥል የአምልኮን መንፈስ የሚያፈስ ዝማሬዎች ጸጋ ይብዛልሽ።

  • @Peak.570
    @Peak.570 2 месяца назад +31

    አቤት ምን ያህል መታደል ነው በዚህ ክብር ውስጥ መኖር ተባርከሻል 🙌🏻🙌🏻

  • @Idont7dan
    @Idont7dan 2 месяца назад +52

    ክብር ለአብ፣ ክብር ለወልድ ፣ ክብር ለመንፈስ ቅዱስ ለአንድ አምላክ ለፀጋው ባለቤት ይሁን ፡፡ 🙏🙏🙏🙏

  • @binyamabayneh1307
    @binyamabayneh1307 2 месяца назад +12

    wow wow እግዚአብሔር ይባርክሽ የእውነተኛ አምልኮ መንፈስ ያረበበት ጌታችን እና አምላካችን የተወደሰበት ድንቅ መዝሙር። ቅባቱን በእጥፍ በእጥፉ ይጨምርብሽ። አስቱ።

  • @mekdesgirma5211
    @mekdesgirma5211 2 месяца назад +64

    አስቱ ተባረኪ በቀደም አገኘው ይደግ ገነት ቤተክርስቲያን ሲናገር ምን አለ መሠለሽ የድሮ አባቶች ምን ብለው ይመክሩን ነበርከመዝሙር በኋላ ጭብጨባ ዚበዛ እየሱስ እንዳይሸፈን ተጠንቀቁ ብለው ሲመክሩን ወደጓዳ ገብተን ምህረትን እንጠይቅ ነበር ይህን ያልኩሽ እንዳትቀዘቅዠ ነው በብዙ ተባረኪ

    • @Idont7dan
      @Idont7dan 2 месяца назад +5

      Wow አዎ እሱ ብቻ ደምቆ ይታይ የፀጋው ባለቤት🙏🙏🙏

    • @diboraandsquishes1649
      @diboraandsquishes1649 2 месяца назад +3

      ድንቅ ምክር!!!

    • @LidiyaTsegaye-xr9ex
      @LidiyaTsegaye-xr9ex Месяц назад

      እውነት ልቤ የተሰማውን እውነት ገልጠሃል🙏ጌታ ይርዳት 🙏እኛንም ይርዳን 🙏

    • @GenetwadaalaroGenet
      @GenetwadaalaroGenet Месяц назад +1

      Ewnet anchi denk nesh tebareki❤️❤️

  • @Qeneni
    @Qeneni 2 месяца назад +6

    ያባቴ ልጅ በእጥፍ ተባረኪ አገልግሎትሽ ቤተሰብሽ ሁሉ ይባረክ
    የሚደንቅ ዝማሬ ነው ሁሌም አዳምጠዋለሁ እባረክበታለሁ እፅናናበታለው እበረታበታለሁ ጌታ ኢየሱስ ዘመንሽን ሁሉ ይባርክ እንደዘመርሽው እንዲሁ ዘመንሽ በቤቱ ይለቅ አሜን
    ተባረኪ

  • @birukefenie9423
    @birukefenie9423 22 дня назад +4

    መዝሙርሽ በአምሮዬና በልቤ ላይ ሲፈስ ትንሽ እንኳን ይቁም የማይባል ይልቁንም ፍሰስ በጌታ መንፈስ እኮ ነው የሚያሰኝ ድንቅ በጌታ የተቀቡና የረቀቁ መዝሙሮች ናቸው፣ በእውነት ጌታ ዘመንሽን ያለምልመው።

  • @HALELUYA62
    @HALELUYA62 2 месяца назад +18

    26 Track በአንድ አልበም
    ጌታ ኢየሱስ ዘመንሽን ይባርከው
    🙏🙏🙏

  • @eyasutamane5311
    @eyasutamane5311 2 месяца назад +10

    ምን አይነት ጸጋ ነዉ Idk there is something different about your songs. When I listen to your መዝሙር all I think about is የእግዝሐብሔር ፍቅር ፣ ስለመጸለይ ፣ being close to Jesus Christ..ስለ አንች ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን አሁንም አብዝቶ ይባርክሽ you are such blessing to our generation.

  • @zekytesfaye6741
    @zekytesfaye6741 2 месяца назад +27

    የልብሽ ናፍቆት ለትውልድ መልዕክት ነው!
    እህታችን አስቴር አምላካችን እግዚአብሔር ይባርክሽ ምርኮሽ ይብዛ ፡፡

  • @mezgebuakalu6144
    @mezgebuakalu6144 2 месяца назад +9

    ጌታ ሰጠን አስቱን፣በረከትን፣ሊሊን፡ዳነኤልን፡አዜብን።እግዚአብሔር፡ይመስገን።

  • @Amauel-f7k
    @Amauel-f7k 2 месяца назад +23

    Boom🎉🎉🎉🎉🎉
    Just, Aster.A.Magersa is legend❤.
    And, your songs are spiritual gifts from GOD ALMIGHTY For us.
    26 tracks per a album is also extraordinary gift❤
    The graphics is the best. The composers and musicians are just heros❤
    Just, this is HALLELUJAH🎉
    God bless you for all reading this comment!

  • @Malikamushinat
    @Malikamushinat 2 месяца назад +4

    Wow amen amen እንደቺ ያሉ ሰዎች ስለሉ ምን እንለሌን እግዚአብሔር የመስጌን ተባረክ ውዴ ናፋቅሽ ጌታ እስክት ሔጂ በለሺባት ጌታ ይጣብቅሽ እዎድሻለው ኑሪልኝ ❤️🙏

  • @kassahunabayneh6108
    @kassahunabayneh6108 29 дней назад +17

    ፀጋ የበዛልሽ አስተር ሆይ !
    መዝሙሮችሽ መንፈሳዊ ወጌሻ ናቸዉ ስብራትን ይጠግናሉ
    አጥንትን ሰርስረዉ ለነፍስ ደስታን ይስጣሉ ብርታትን ይጨምራሉ !!
    እርግጠኛ ሆኜ የምነግርሽ ይህ የእግዚሐብሄር መንፈስ መገለጥ ነዉ የስጋ ግጥምና ዜማ የለበትም ተባርከሽ እንድንባረክ ስላደርግሽ እግዚአብሄር ፀጋዉን ያትረፍርልሽ !!!!!
    እያደሩ የምጣፍጡ መዝሙሮችን ሳደምጥ እቆያለሁ 😘😘😍😍

  • @JohnbrandJohnbrand
    @JohnbrandJohnbrand Месяц назад +12

    በዚህ ሁሉ ጌታ መመሰገኑ ትልቅ ነገር ሆኖ🤗🤗🙏 ሳሌ ቅነው ማስተዋል ይፈልጋል ደግሞ መዝሙሩን😁😁 ለመሸንደድ በመንፈስ መሆን ግዴታ ነው 😴😴ደግሞ ባንቺ በኩል እየተባርከን ነው እውነተም ክርስቶስን የምሸት መዝሙር ነው 😍😍😍😍

  • @betlamgrma8696
    @betlamgrma8696 2 месяца назад +5

    ከልቤ አይወጣም ደጋግሜ ነዉ የምሰማዉ አልምደዉም የማይጠገብ ወደዙፏኑ የሚያስጠጋ ዝማሪ በመንፈስ ቅዱስ የሚያረሰርሰ ዚማሪ ቃላት ያጥረኛል ጌታ ፀጋዉን ያብዛልሽ

  • @MulukenBayu-c7i
    @MulukenBayu-c7i 2 месяца назад +13

    ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ አሜን አሜን!!!
    ክብር ለእግዚአብሔር አብ
    ክብር ለእግዚአብሔር ወልድ
    ክብር ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን አሜን።
    “ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
    - ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

  • @ZayonZayon-fb7jf
    @ZayonZayon-fb7jf 20 дней назад +5

    በመጠጋት በቦታው በመገኘት ከ encounter የተገኘ ቅኔ እያንዳንዱን ቃላት ስሰማው የማይሰማኝ የማልሆነው ነገር የለም ማልቀስ መጮህ ሀሴት በልቤ መሙላት ሌላ ፍለጋ የእድሜ ልክ ፍለጋ ጥልቅ ፍለጋ በልቤ ይጨምርብኛል ሁሉን ትውት እርስት ያስደርገኛል የክርስቶስ እየሱስ ፀጋና ሰላም ይብዛልሽ አንቺ የምድር ወገን አይደለሽም አገር አለሽ በሰማይ በደመና ው የምትወሰጂ አንቺ የተወደድሽ ነሽ ስለማይነገረው ስጦታው Define ስለማይደረገው ፀጋው ክብር ይሉን ሁሉ ከሱ ለእሱ በእርሱ ነውና ክብር ለስሙ ይሁን

  • @barnabaszemene7530
    @barnabaszemene7530 2 месяца назад +8

    እኔ በጣም ከምወደው መዝሙር አስጀመርሽው! 😮 ዘመንሽ ይለምልም! ባንቺ ሁኔታ ልጁን የገለጠ ልዑል አምላክ ይባረክ! ለትውልድ መነሣት ምክንያት ያድርግሽ!

  • @lordismyshipperd
    @lordismyshipperd Месяц назад +8

    እንደገና ርሀብ እንደገና ጥማት
    ትላንት ምንም እንዳላየ
    እንደገና ናፍቆት እንደገና ጉጉት
    አንተ ወዳለህበት (2)
    ጥቂት አንተን ቀምሶ
    እንደጠገበ ሰው
    መሆን የጤና አይደለም
    ርሀቤን ፈውሰው (2)
    እለት እለት ባዶ ትሁንና ነፍሴ
    በመገኘትህ ውስጥ
    ይረስርስ መንፈሴ (2)
    በቃኝ የማልለው ይለፈኝ የማልለው
    ሰለቸኝ የማልለው ያንተ ህልውናህን
    ደስታዬ ያለበት ያለፈ ሰላሜ
    መገኘትህ ነው መዋያ ማደሪያዬ
    ናና እስኪ አጠጣኝ
    ናና እስኪ አጉርሰኝ
    የእጅህን ሳይሆን ክብር መልክሀን
    የምድሩን ሳይሆን በላይ ያለውን
    ሌላውን ሳይሆን አንተው እራስህን
    የፊትህን ሳይሆን ፈልጎ የጅህን
    ባትገባም ከቤቴ ላክ ብቻ ቃልህን
    የእምነቱን ቁመት አድንቀህ እንዳለፍከው
    አንተን በደጅ ትቶ ፈውሱን ብቻ እንዳለው
    አይደል መገስገሴ ፊትህን ማለቴ
    ማድጋዬን ልሞላ ላሰማምር ቤቴን
    ይሁን ሁሉ እንዳለ ከነዝብርቅርቁ
    ካንተ ካልከተመኝ ካቆመኝ በሩቁ
    ሳበኝ በእጆችህ ወደ ክብርህ ጥልቅ
    አስገባኝ ከልፍኝህ ጅምሩም ባያልቅ
    በቃኝ የማልለው ይለፈኝ የማልለው
    ሰለቸኝ የማልለው ያንተ ህልወናህን
    ደስታዬ ያለበት ያለፈ ሰላሜ
    መገኘትህ ነው መዋያ ማደሪያዬ
    😊

  • @AMER0521
    @AMER0521 2 месяца назад +13

    አስቱ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክሽ መዝሙሮችሽ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እና ሰማቸው ወይንም በፀሎት ሆኜ ሳመልክባቸው በእውነት እባረካለሁ ተባረኪልን❤❤❤❤❤

  • @selamawittesfaye2299
    @selamawittesfaye2299 2 месяца назад +4

    አስተርዬ የዝማሬ ምንጭ ነሽ ዘመንሽ ይባረክ በጣም ነፍስን የሚያረሰርስ ጌታን የሚያስናፍቅ መልክት ዝማሬ የዘመኑ ቅሬታዎች ጌታ ስላሉት ክብር ለእርሱ ይሁን ተባረኪ በ90ናዎቹ ከተባረክንባቸው የሙዚቃ ተጫዎችች አቤኔዘር በማየቴ ደስ ብሎኛል ሁላችሁም ተባረኩ

  • @YitebarekTizazu
    @YitebarekTizazu 2 месяца назад +9

    እግዚአብሔር በፀጋ ላይ ፀጋን ይደርብልሽ ልጁን እየሱስን በመዝሙርሽ ያደመቅሽ የዘመኔ በረከት ነሽ ተባረኪ

  • @elsatesfaye2716
    @elsatesfaye2716 2 месяца назад +10

    ❤❤❤❤❤አባዬ ሁሌም እራበኝ ጥማኝ❤❤❤❤ አስቱ ጌታ ኢየሱስ ክቡር በሆነው ደም ሽፍን ያድርግሽ ከክፉ ተጠበቂ እንወድሻለን❤❤❤❤❤

  • @DeginetBerhanu
    @DeginetBerhanu 2 месяца назад +16

    እንኳንም ዘገየሽ እንደ ወይን ጠጅ የጣፈጠ ዝማሬሽ ነፍሴን አረሰረሳት እየሱስን አሳየሽኝ❤

  • @AschalewKorra
    @AschalewKorra 2 месяца назад +11

    Glory!Glory የከበደ ክብር ! አስቱ የእኛ ስጦታ በጣም እንወድሻለን። እንጸልይልሻለን።

  • @joeldejene7621
    @joeldejene7621 День назад

    እህታችን አስቱ ጌታ ብቻውን እንዴት እንደረዳሽ ከቅኔዎችሽ ያስታውቃል፡፡ እግዚአብሔር መልካም ነው፡፡
    ቁጥር ሦሥትን በጉጉት አእጠብቃለሁ፡፡ ለአንቺም ፀጋውን ለእኛም እድሜ ይስጠን፡፡ ካሆነም እዛ አብረን እንዘምራለን፡፡ ተባረኪልኝ፡፡

  • @belaynegash6550
    @belaynegash6550 2 месяца назад +28

    የተወደድሽ እህታችን ዳውንሎድ አድርገን እንድናዳምጥ ስላልቆለፍሽብን በጣም እናመሰግንሻለን ❤ዘርሽ የምድሪቱን ፊት ይውረስ ❤

  • @enedateshale
    @enedateshale День назад +1

    በቃኝ የማልለው
    ሰለቸኝ የማልለው...የኔ ኢየሱሴ
    የኔ አስቱዬ😍

  • @meskeremsimeonoffical7054
    @meskeremsimeonoffical7054 21 день назад +3

    በአንቺ ስለሚገለጠዉ ጸጋ ለመጻፍ ቃላት አጣሁኝ ለነገሩ ጸሐፊም አይደለሁም እንግዲህ ምን እንላለን......... እንዳለዉ ጳዉሎስ አንቺን የሰጠን ጌታ የተባረከ ይሁን እንደዘመርሺዉ ከአንቺ ወጥቶ ለመጽናናት፡ ለመባረክ፡ ለመጸይ.........ምክንያት ሆኖናል ዘመንሽ ይለምልም ብዙ ዘመን ኑሪልኝ እወድሻለሁ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @digafekunbi207
    @digafekunbi207 Месяц назад +2

    አስቴር ትንሽዋየ የፍሬ ዛፍ በልጅነት የነበረው ለጌታ የሚቃጠል የፍቅር ልብ ቅንአት እና መሰጠት ብዙ ነገሮችን አሳልፎ በብዙ ፍሬ ስለ ተገለጸ በጣም ደስ ብሎኛል ሁሌም የሚደመጡ ወደ ጌታ ጉያ የሚያስሮቱ ወደ ጸሎት የሚመሩ እራን እንዳይየ ሚያደርጉ መዝሞሮችሽ ሁሌም አይጠገቡም ያለስስት ስላንበሸበሽን ጌታ በትልቅ እጁ ያንበሽብሽሽ ሁል ጊዜም እንወድሻለን እንጸልይልሻለን ድጋፌ

  • @Global_c-o8u
    @Global_c-o8u Месяц назад +3

    Aster's album was born through prayers, and that is why each song is deeply touching. I can't stop listening to the songs. Zemenish yibarek, Astuye❤❤❤❤

  • @yosefgebrewold2005
    @yosefgebrewold2005 Месяц назад +2

    ቁጥር አንድ አልበም ሰምቼ ሳልጠግበው ሌላ የምንባረክበትና የምንፅናናበት መዝሙር ሰጥተሽናል በዚህ ዘመን አንቺን የሰጠን እግዚአብሄር በነገር ሁሉ ይባርክሽ። ለዚህ ድንቅ ስራ ካንቺ ጋር የተባበሩና ሁላችሁም ዘማሪዎችና ክርስቲያኖች እንወዳችኃለን ተባረኩ! ጌታ ጨምሮና አትረፍርፎ ይስጣችሁ።

  • @mogegani3332
    @mogegani3332 2 месяца назад +9

    አስቱ ሰመቼ ሰምቼ በማልጠግብ ዝማሬዎች ብቅ አልሽ።❤❤❤ በእውነት ፍጻሜሽን እግዚአብሔር ያሳምርልሽ🎉 አሜን

  • @eyesusawitgetachew4910
    @eyesusawitgetachew4910 2 месяца назад +6

    በጣም የምትወደጂ እህታችን ፀጋን ባንቺ ያስቀመጠ ጌታ ይባረክ እስከ መጨረሻ በውስጥሽ ያለውን ጠብቀሽ የምትሄጂበት ፀጋ ይብዛልሽ ❤

  • @maritu3770
    @maritu3770 2 месяца назад +7

    አሜን ለሆነው ጌታ ምሥጋና ይብዛለት ተባርከሺ ለዘላለም ኑሪልኝ።

  • @seidamhamed
    @seidamhamed 2 месяца назад +7

    አስቱዬ ጌታ እየሱስ ቅኔን ስላበዛልሽ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን🙏 በየቀኑ ስሰማ ው አዲስ አዲስ ይሆንብኛል
    ጌታ ዘመንሽን ይባርከው😇💝
    አሁንም ፀጋ ይብዛልሽ 🛐
    Love you💝

  • @girmishjesus
    @girmishjesus Месяц назад +5

    የደህንነት ት/ት ደቀመዝሙር የአገልግሎት ት/ት ምስጋና አምልኮ ትንቢት ፀሎት ሁሉንም አካቶ ይዟል ምን ዓይነት ፀጋ ነው? ባለጠጋው ጌታ ሆይ ስምህ ይባረክ።አስቱዬ ጌታ ይባርክሽ ያብዛልሽም።በጣም እንወድሻለን።

  • @TamenechsigaSiga
    @TamenechsigaSiga 2 месяца назад +6

    ኡዑዑዑዑፍፍፍፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ይገርማል የጌታ እርዳታ ዘመንሺ ይባረክ እግዚአብሔር አምላክ ይባርክሽ በቡዙ ፍሬ 🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍈🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍒🍓🍓🍓🍓🍓🍓🍑🍑🍑🍑🍑🍎🍎🍎🍎🍎🍅🍇🍇🍇🍇🍇🍇

  • @wongelawitgebremariam9023
    @wongelawitgebremariam9023 2 месяца назад +8

    በብዙ የተባረክንብሽ እህታችን አስቱ ስላንቺ ጌታን አመሰግናለሁ ጌታ ከዚህ በላቀ ክብርና ፀጋ ይግለጥሽ ተባረኪ❤❤❤

  • @IsraelTesfalem
    @IsraelTesfalem 2 месяца назад +11

    አስቱዬ ተባረኪ ገና ብዙ ሰምተን ማንጠግበው ዝማሬ ካንቺ እንሰማለን

  • @akaluayenewasele6458
    @akaluayenewasele6458 Месяц назад +3

    አንች የእግዚአብሔር ብሩክ በረከታችን ነሽ

  • @bethget1850
    @bethget1850 19 дней назад +3

    ይሄ አልበም የሀገራችንን የወንጌል ዝማሬ ወደ ሌላ dimension የቀየረ ነው ያለማጋነን ❤

    • @esayoabebe4083
      @esayoabebe4083 3 дня назад

      may God bless you its blessing songs , you are amazing singer!❤

  • @betheltemesgen6975
    @betheltemesgen6975 2 месяца назад +6

    አስቱዬ ሕይወት ያለው ዝማሬ ነው እየሱስን ትኩረት ያደረገ:: ፀጋውን የሰጠሽ አምላክ ይባረክ ደሞም ይህን ፀጋ ለኛ ስላበረከትሽ አንቺም ተባረኪ ♥️

  • @messimessi1490
    @messimessi1490 2 месяца назад +4

    Amen 🙌 Amen amen asutuye ziminish yibarek tsegawnim yabizalisi yene enati yetiwlidi bereketachin neysh betam kemiwodachew zemaran mekakel anidu yehonish asituye bewunet tebarekilign❤ ❤❤❤

  • @MeronAdmasu-h2x
    @MeronAdmasu-h2x 2 месяца назад +6

    እንደው የዚህ ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር ባይሆን በቃ ጨርሰሽ ዘምረሽዋል እኮ ምን አይነት ድቅ ዝማሬ ነው ይህው ፀሎት ያቆምኩት ልክ ዝማሬሽን ስሰማ መበርከክ ያምረኛል የኔ እህት እንኳን የጌታ ሆንሽ ❤❤❤

  • @almazshifaw6702
    @almazshifaw6702 2 месяца назад +5

    እህህን በእልልታ ለምኑን በአሜን ለለወጥከው ኢየሱስ እንካ ዘላለሜን የመጨረሻ የስጦታ ጥግ እኔ ይህንን አዝማች ወይም መግቢያ ስሰማ ሰውነቴ ፍርስርሰ ይላል ነፍሴ በፊቱ ትቀልጣለች የገባሽ ጌታ ይግባኝ ያገኘሽ ብርሀን ያግኘኝ በዚህ ብርሀን እየደመቀሽ ድምቀትሽ እየጨመረ ቀጥይ

  • @Raya-Rayuma
    @Raya-Rayuma Месяц назад +1

    አስቱዬ መዝሙሮችሽ ሁሉ ከላይ ከጌታ የሱስ የተቀበልሽዉ እንዴት እንደተባረክን ብታቂ ጌታ የሱስ ዘመንሽ አገልግሎትሽ ትዳርሽ ሁሉ የለመለመ ይሁን እወድሻለሁ አስቱዬ 🎉

  • @asna58
    @asna58 2 месяца назад +10

    አንቺ በረከታችን ነሽ ተባረኪ❤❤❤

  • @ngstasmare9518
    @ngstasmare9518 15 дней назад +1

    ፀጋን ሲሰጥ ከመንፈሱ ሲሆን እንዲህ ያረሰርሳል ይኸው ለአመታት በቁጥር 1ስንባረክ ቆይተን አሁንም በዚህ ቀጠለ የፀጋው ባለቤት ክብር ይብዛለት ዘመንሽ በምስጋና ይለምልም እህቴ እወድሻለሁ ሁሌም ቅኔ ይፍለቅልሽ❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉

  • @MeretMarkos
    @MeretMarkos 2 месяца назад +3

    ብቻሀ ጌታሀ ፀጋውን ያብዛልሽ ወደ ጌታሀ ይበልጥ እንድቀርብ አርግታሀል መዝሙር❤❤❤❤❤❤❤ዘመንሽ ይባረክ

  • @genetbogale2544
    @genetbogale2544 2 месяца назад +15

    ኡኡኡኡኡ ድንቅ ስብከት ድንቅ መልዕክት ድንቅ ምክር ድንቅ ዜማ ድንቅ መዝሙር ህይወት የሚለውጥ ጌታ እየሱስ ብርክ ያድርግሽ ይጨምርልሽ

  • @mercymercy9309
    @mercymercy9309 2 месяца назад +6

    ጌታ ይባርክሽ በብዙ ተባረኪ ፀጋ እንደዚህ ለሌለው ሲተርፍ ❤❤❤

  • @netsanetfrew9972
    @netsanetfrew9972 2 месяца назад +2

    ለዘላለም ተባርከሽ ቅሪ ምንም የምልሽ ነገር የለኝም የሚያለመልም መዝሙር ጌታን ለተጠማ የሚሆን በቃ😍😍😍🥰🥰

  • @delamotesfaye1363
    @delamotesfaye1363 2 месяца назад +7

    ክብር ቅባቱ ብሶብሻል አስቱ ተባረኪ፤ህልውናው በዘመንሽ ሁሉ አይራቅሽ!

  • @yordate7629
    @yordate7629 Месяц назад +4

    አስትዬ እግዚአብሔር አምላክ ዘመንሽን ይባርክ መዝሙሮችሽ ከአምላክሽ ጋር ያለሽን ህብረት ያሳያል ይብዛልሽ።

  • @emebetagezaw462
    @emebetagezaw462 Месяц назад +4

    Asterye tebarekilegn des yemil album new❤❤❤