EOTC TV | ዐውደ ስብከት | ወደ አብርሐም ተመልከቱ | በመምህር ብርሃኑ አድማስ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 9 янв 2025

Комментарии • 13

  • @MaMa-zr1ry
    @MaMa-zr1ry 10 месяцев назад

    ቃል ህይወት ያሰማልን መግስተ ሰማአትን ያውርስልን!!!

  • @fggghjii4311
    @fggghjii4311 Год назад

    ቃለ ሕይወት ያሰማልን መምሕር

  • @tes.a
    @tes.a Год назад

    ቃለ ሕይወትን ያሰማልን።

  • @frehiwot27
    @frehiwot27 2 года назад

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ሕይወት ያሰማልን
    እግዚአብሔር ይስጥልን መምራችን

  • @hulubersuhone1356
    @hulubersuhone1356 2 года назад

    መምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር የአባታችን አብርሃም እምነት ያሳድርብን አሜን አሜን አሜን

  • @brhanabi3755
    @brhanabi3755 2 года назад

    አሜን አሜን አሜን በእውነት ለመምህራችን ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር አምላክ በእድሜና በጤና ያቆይልን ይጠብቅልን
    እኛም የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርብን

  • @goodlive1573
    @goodlive1573 2 года назад

    🙏 Amen 🙏

  • @goodlive1573
    @goodlive1573 2 года назад

    🌹🌹🌹 EgiziAbiher yimesigen 🌹🌹🌹

  • @nebiyatteruzer79
    @nebiyatteruzer79 2 года назад

    Kalehywaten yasemalen.

  • @alemayehutache1711
    @alemayehutache1711 Год назад

    Memhroy qalyot yasemaln !

  • @yeshilove9429
    @yeshilove9429 2 года назад

    💕🙏💕

  • @Medehaneyalem27
    @Medehaneyalem27 Год назад

    Era U U U
    1. Eyasus kerestos
    2. Kidus Segaw 💞 kibur Damu
    BALU

  • @tewodrosshewangzaw5285
    @tewodrosshewangzaw5285 Год назад

    ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
    "እምነቱ ፍፁም የሆነ ሠው ምግባሩም ፍፁም ነው"
    በዚህ ትምህርት ላይ ያሉኝን ጥያቄዎች እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራለሁ። መልስ እንደማገኝ ተስፋ በማድረግ ነው።
    1ኛ. ታቦት: የብሉይ ሳይሆን የሐዲስ ኪዳን ታቦት ነው ያለን የሚለው ይህ ታቦት ከእንጨት ወይም ከእምነበረድ የተሰራ ሲሆን ለዚህም ታቦት ሰዎች ሲስግዱለት ይታያል። እግዚአብሔር እንደብሉይ ጊዜው በዚህ ታቦት ላይ ስለሚያድር ነው? እኛ ክርስትያኖች አይደለንም እንዴ በሐዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነው?
    2ኛ. ክህነት: አሁንም የክህነቱ ስርዓት የብሉዩ ሳይሆን የሐዲስ ኪዳን የክህነት ስርዓት ነው ያለን ተብሏል። ሮሜ 9:4 ላይ እንደተጠቀሰው የመቅደስ/ክህነት ስርዓት የተሰጣቸው ለእነርሱ እስራኤሎች እንጂ እኛ አህዛብ ለነበርን አይደለም። ታዲያ ይህ አለን የተባለው የክህነት ስርዓት ሃዲስ ኪዳናዊ የመፅሃፍ ቅዱስ መነሻው ምንድን ነው? ይህስ የክህነት ስርዓት በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከለኛ ሆኖ ያገለግላልን? መካከለኛውስ ክርስቶስ እየሱስ አይደለምን?
    3ኛ. በትምህርቱ ላይ የዕብራዊያን ፀሃፊ ጳውሎስ እንደሆነ ተደርጎ ሲገለፅ ነበር። ነገር ግን 13ቱን የጳውሎስ መልዕክቶች ብንመለከት ጳውሎስ እንደፃፋቸው የሚገልፅ ማስረጃዎች ይገኛሉ። ጳውሎስ ትምህርቱን ከእግዚአብሔር በቀጥታ እንዳገኘው ገልፆ መልዕክቱን ፅፏል። የዕብራዊያን ፀሃፊ ግን ከአባቶቻችን የሰማነውን እንነግራችኋለን እያለ ነው የፃፈው። በተጨማሪም የጳውሎስ መልዕክቶች ሁሉ ምልክት እንዳለባቸው እንዲህ ብሎ ጠቅሷል፣
    2ኛ ተሰሎንቄ 3:
    ¹⁷ በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።
    ¹⁸ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን
    ታዲያ ዕብራዊያንን ጳውሎስ ፃፈው ለማለት እንዴት ቻልን? ማስረጃ ተጠቅሶ መልስ ቢሰጥበት።
    4ኛ. ለአብርሃም ስላሴ ተገለፁለት የሚለው አስተምህሮ - ዘፍጥረት 18
    ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
    ¹ በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።
    ² ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥እንዲህም አለ፦
    ይህን መነሻ አድርጎ ከሆነ ከሶስቱ ሰዎች መካከል ስለሁለቱ በዚሁ ምእራፍ ላይ እንዲህ ይላል:-
    ¹⁶ ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ።

    ²² ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።
    ይልና በምዕራፍ 19 ላይ እንዲህ ይላል:- “ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦”
    ስለዚህ ሁለቱ መላዕክት እንጂ የስላሴ አካል እንዳልሆኑ በግልፅ ተቀምጦ እያለ ስላሴ ለአብርሃም ተገለጡ ለማለት እንዴት ተቻለ? በአካል የመገለጥና ለሰው የመታየት ባህሪ ያለውስ ወልድ እየሱስ ክርስቶስ ብቻ አይደለምን?
    5ኛ. መፅሃፍ ቅዱስ የተፃፈው ለእስራኤልና ለአህዛብ እንደሆነ ይታወቃል። በተጨማሪም ለመቼ ዘመን ተፃፉ የሚለውን አክለን ማየት ይገባል። ለምሳሌ በግልፅነት ዕብራዉያን እና የያዕቆብ መልዕክትን መጥቀስ ይቻላል።(“የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።”ያዕቆብ 1፥1) በእነዚህ በሁለቱ መልዕክቶች ላይ የተጠቀሰ የድህነት/Salvation መንገድ ካለ ለእነርሱ እስራኤሎች እንጂ ለእኛ አህዛብ ለነበርን ዶግማ ሊሆን አይችልም። እኛ አህዛብ የነበርን አሁን ግን በአዲስ ኪዳን/new testament/ ስርዓት በክርስቶስ ኢየሱስ በፀጋው የዳንን ሰዎች የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን መፅሃፍ ሁሉ ብንቀበልም ቅሉ ለእስራኤል የተፃፈውን ለእነርሱ መተው አለብም እንጂ ለእኛ ብለን እንዴት ልንወስድ እንችላለን? የእኛ የአህዛብ ሃዋሪያ ሆኖ የተሾመው ጳውሎስ ስለሆነ የእኛ የክርስቶስ አካል የሆንን ክርስትያኖች የድህነትና መንግስቱን መውረስ ወንጌል/ዶህትሪን የሚገኘው በጳውሎስ መልዕክት ውስጥ አይደለምን? በሌሎቹ መልዕክቶች ውስጥ ልናገኘው እንችላለን?
    “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።”
    - 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17
    6ኛ. በመፅሃፍ ብቻ አለመታጠር:- አብርሃም በዘመኑ መፅሃፍን አንብቦ አላመነም። ምክንያቱም መፅሃፍ ስላልነበረ። አብርሃም አመነ እምነቱም ፅድቅ ሆኖ ተቆጠረለት ይላል መፃሃፍ ቅዱስ። በዚህ ዘመን ግን መፅሃፍ ተፅፎልናል፣ ወንጌል ተሰብኮልናል፤ ታዲያ በመፅሃፍ ብቻ መታጠር ልክ አይደለም፣ ከዚህ በላይ ከፍ ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል የሚለው ትምህርት ሌሎች ሰዎች እንደፈለጉ ዶግማና ቀኖና እንዲኖራቸው ወይም እንዲመሰርቱ አያደርግም?
    7ኛ. የአብርሃም ዘመን መከራና የዚህ ዘመን መከራ እጅግ ይለያያል ብዬ አምናለሁ።
    “እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።”
    - 2ኛ ቆሮ 5፥20
    በአሁን ዘመን በዚህ ቃል መሰረት የመልዕክተኝነትን/የአምባሳደርነትን ስራ ሰርተን መንግስቱን ለመውረስ በምናደርገው ጉዞ ማለትም የማያምኑትን ወደ ማመን እንዲመጡ ስለክርስቶስ ብለን ስንለምን የሚመጣብን ተቃርኖ፣ መገለል፣ መጨቆን፣ ድብደባ፣ ዘለፋ፣ ስደትና የመሳሰሉት ሁሉ የዚህ ዘመን መከራ አይደሉምን?
    የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የክርስቶስ ፀጋ፣ የመንፈስ ቅዱስ ህብረት ከሁላችን ጋር ይሁን።አሜን።