ሕገ ቤተ ክርስቲያን ምን ይላል? በተለያየ ጊዜ የተላለፉ ውግዘቶች ክህነትን በሙሉ አስረዋል? እነሆ ልዩ ዝግጅት!

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 10 сен 2024

Комментарии • 52

  • @fasilgebre4150
    @fasilgebre4150 24 дня назад +4

    እግዚአብሔር ባወቀው ይህ ውይይት ለተወሳሰቡ የቤተክርስቲያን ህብረት የእኛ ተነስህያን ችግሮች ይፈቱ ዘንድ የመፍትሔውን አንድ ጡብ የመጣል ይመስላል።እንደ ምእመን የማየው የምሰማው ነገር ሁሉ ያመኛል፣ ያሳዝነኛል ፣ያናድደኛል ትላንት አብያተክርስቲያናትና አባቶች የጥበብ፣የአገር ፍቅር ምልክቶችና፣የበጎነገሮች ትሩፋት ምንጮች ነበሩ ።ቅዱስ ያሬድን አባ ጊዮርጊስን ቅዱስና ንጉሦችን አፄ ካሌብ ላሊበላ፣ዘረያዕቆብና አፄ ገብረመስቀልን አረ ስንቱን ጠርተን እንችላለን???እነዛ በጨለማው ሰማይ የሚፈነጥቁ የአጥቢያ ኮከቦች ቤተክርስቲያን የእነዛ እናት ነበረች ዛሬ ዛሬ ቤተክርስቲያን ኑሮ ወይም ትምህርት የከበደው የሰነፎች ምሽግ ሆናለች።መፍትሔው ከራስ የሚጀምር የመንፈሳዊ ህይወት እድገት ነው።

  • @yoannesalta3930
    @yoannesalta3930 24 дня назад +6

    በጣም ታሳዝናላቹ አለቃ አያሌው ያስተላለፉት የውግዘት ቃል በመፅሐፍም በራሳቸው ድምፅም ተቀምጦአል እናንተ ግን ታደባብሳላቹ

  • @mesfinkebede9419
    @mesfinkebede9419 23 дня назад +3

    የእኔ አባት አረጋዊው ሊቅ መልአከ ብርሃን አስተራይ ፅጌ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ይጠብቅዎ።

  • @asegedechbayu3815
    @asegedechbayu3815 24 дня назад +4

    ስላም መምህሮቻችን አባታችን ቀሴስ አስትራይ እንኳን ደህና መጣችሁ!!!!❤❤❤ እንደ እናንተ ያለ አባት መከሪ፣አስተማሪ ስለስጠን እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!!!!!❤❤❤❤ይህንን ክፉ የመከራ ዘመን አሳልፎ ደግ ዘመን ያድርስን!!!!!****

  • @getachewyezengaw9638
    @getachewyezengaw9638 24 дня назад +3

    እፁብ ድንቅ ነው! መልአከ ብርሃን ቀሲስ አስተራየ ጽጌ በንጉሱና በግብፁ ጳጳስ ላይ የሰጡት ሀሳብ ማለፊያ ነው። እግዚአብር ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን። ሁላችለሁንም እግዚአብሔር በፀጋው ይጠብቃች። ጉልበት ይስጣችሁ።

  • @tamiratasefa5176
    @tamiratasefa5176 23 дня назад +1

    god bless you

  • @mesfinabate1394
    @mesfinabate1394 24 дня назад +3

    ቃለ ህይወት ያሰማችሁ አባቶቻችን

  • @Marew-p6n
    @Marew-p6n 24 дня назад +6

    በዚህም ተባለ በዚያ መጽሐፍትንም ጭምር እያወቁ የቀደሙት አባቶቻቸን እንዲያ ተወጋገዙ።
    ዳፋውም ለዛሬ ዳረገንና እንዲህ እየኖርን ነው።
    ነገር ግን ዛሬ ያለው ሁኔታና ችግር እንዳይቀጥል ከመዋቅሩ፣ ከካህናት እንዲሁም ከምእመናን ምን ብናደርግ ለነጋችን እንተርፋለን የሚለው ላይ ብዙ መነጋገር የቤት ሥራም ማስቀመጥ ቢቻል።

  • @degolabraha9972
    @degolabraha9972 24 дня назад +3

    መምሕር ፋንታሁን ዋቄ ትክክል ብለዋል ተደባብሶ ማለፍ የለበትም እንጠየቃለን ይሔንን የተሸፈነ ድብቅ ሥራቸውን ግልፅልፅ አድርጎ ማጋለጥና ለወደፊት ልጆቻችን ንፁህ የሆነ ቤተክርስቲያን ነው ማስረከብ ያለብን ሲኖዶሱ ይጋለጥ ይጥራ ያቆየን

    • @kienfemichaeltemesgen9168
      @kienfemichaeltemesgen9168 22 дня назад

      ወንድማችን መምህር ፋንታሁን ዋቄ በደንብ ገብቶሃል።ይኸውም"እውነት ዛሬ ሐማኖታችን በትክክለኛው ሃዲድ ላይ ነች?" የሚለው ጥያቄ መልስ የሚያስፈልገው ጥያቄ ነው።ይኸውም የሚመለሰውም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። አሁን ያላችሁት እውነተኛ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካህናት አንዱ ገዳም ግቡና ልዑል እግዚአብሔርን በሱባዔ ጠይቁ።እግዚአብሔር በትህትና እራሳቸውን አዋርደው በሡባኤ የሚጠይቁትን አይንተ እግዚአብሔር ካህናትን እውነቱን ይገልጽላቸዋል። በዚህ መሠረት ለዘመናት በማወቅም ባለማወቅም እየተንከባለለ የመጣውን የከዶግማና የቀኖና ጥሠት ማስተካከል ይገባል።አለበለዚያ በእውቀት ብቻ ይህንን የቤተክርስትያናችንን ሥብራት መጠገን አይቻልም። አረ ለመሆኑ መች ነው ጌታችንና አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንጠይቀው እንዲሁም ቆም ብለን የምንሰማው? እግዚአብሔር በአንድም በሌላ ይናገራል ፤ሰው ግን አያስተውልም።

  • @degolabraha9972
    @degolabraha9972 24 дня назад +2

    ትክክል ቀሲስ ዕዳ አለብን የሚጠራውን አጥርተን ካልተጓዝን ለወደፊት እንቅፋት እየገነባን ነው የምንሔደው እስከመቼ ተሸፍነው ይኑሩ ቤታችን መንኳኳቱ አይቀሬ ነው

  • @yoannesalta3930
    @yoannesalta3930 24 дня назад +6

    #ውግዘቱ_ካልተፈታ_የሚከተለው_መቅሰፍትና_ፍርድ_ነው...
    #ጥያቄ፦ በጳትርያርኩና በእርስዎ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ለምን አልተቻለም ?
    #መልስ(አለቃ አያሌው ታምሩ) ፦ አይቻልምም! አልተቻለምም! አዎ እማይፈታበት ምክንያት እሳቸው ሲመለሡ ነው የሚፈታው፡፡ ወይም በመሃከላችን ዳኛ ሲኖር ነው የሚፈታ፡፡ በመሃከላችን ጉባኤ የሚጠራ ንጉሥ የለም ዛሬ፡፡ አሪዮስ ሲወገዝ የኒቅያን ጉባኤ የጠራው ቆስጠንጢኖስ የተባለው የምሥራቁ ንጉሠ ነገሥት ነው፡፡ መቅደኒዮስ ሲወገዝ ጉባኤውን የጠራው አርቃሊዮስ የተባለው የምስራቁ ንጉሰ ነገስት ነው፡፡ ንስጥሮስ ሲወገዝ ጉባኤውን የጠራው ቴወድዮስዮስ የተባለው የምሥራቁ ንጉሥ ነው፡፡ በኢትዮጵያም ነገስታቱ በነበሩበት ጊዜ ብዙ የተደጋገመ ጉባኤ ተደርጓል፡፡
    ✔በአፄ ፋሲል ጊዜ በካቶሊክ እና በኢትዮጵያውያን መሃከል ጉባዔ ተደርጎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አፈጉባኤ እጨጌ በትረጊዮርጊስ ስለረቱ ካቶሊኮች መረታታቸውን አምነው ከሀገር እንደወጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡
    ✔በአፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት በቦሩ ሜዳ ጸጎችና ኦርቶዶክሳውያን እንዲከራከሩ ተደርጎ ጸጎች ስለተረቱ ተፈርዶባቸው ተቀጥተዋል ፡፡
    ንጉሥ ቢኖር ይሄንን በዳኝነት ጉባዔ ጠርቶ ሊፈታው ይችል ነበረ፡፡ የኢትዮጵያ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ጠባቂ ንጉሠ ነገሥት ነበረና፡፡ ዛሬ ንጉሠ ነገሥት የለም፡፡ ያለው መንግሥት በሐይማኖት አያገባኝም አለ፡፡
    ይሄንን ምክንያት አድርገው የኢትየጵያን ቤተክርስቲያን ረገጡ፣ ክብሯን አሳደፉ፣ ሐይማኖቷን አፋለሱ ፣ ሥርአቷን ጣሱ ፣ ሕጓን አፈረሡ ፣ ለጳጳሳት አቤት አልኩ አብረው አበሩ የቤተክርስቲያንን ሕግ ሽረው አባ ጳውሎስ የሚመለኩበትን ሕግ አወጡ፣ ቤተክርስቲያን የጣወት ቤት ሆነች፣ እንደገና አለቆችና ካህናት የነሡ ተባባሪ ሆነው ጉዳዩን አስፈፀሙ ስማቸውን በፀሎት ሐይማኖት አትጥሩ ብየ ጠየኩ እምቢ አሉ፡፡ ስለዚህ ሁሉም ተባብረው በእግዚአብሔር ላይ ስላመጹ ፤ ምእመናን ይፈቱታል ብየ ነበር ምእመናንም እምቢ አሉ ፣ የሠበካ ጉባኤ አባሎችም ምእመናንም አብረው ተባብረው እምቢ አሉ፡፡ ምናለበት! ምናለበት! በሚል ቋንቋ ሐይማኖት አይቆምም ፡፡ ሁሉ ለራሡ ለሐይማኖት መቆም አለበት፡፡ እና ስለዚህ ሁሉም ተባብረው ስላመጹ አውግዣለሁ፡፡ ሁሉንም! እና የሚፈታውም የለም፡፡ የሚመለስ ከሌለ፡፡ ወይ እሳቸው ካልተመለሡ፡፡ ወይ ጳጳሳት ተመልሰው ሲኖዶሱን ካላቋቋሙ ፡፡ ሲኖዶስ ፈርሷል፡፡ ወይም ካህናት ደግሞ ተመልሰው ራሳቸውን ካለወቁ እና ከምእመናን ጋር አብረው ካልቆሙ ወይም ምእመናን እምብኝ ብለው እጃቸውን ካልሰበሰቡና እንዳዘዝኳቸው ካላደረጉ መፍቻ የለኝም፡፡ የሚከተለው መቅሰፍትና ፍርድ ነው፡፡ የሚፈታ ይመጣል አይቀርም ይፈርዳል፡፡

  • @abisiniaethiopia7673
    @abisiniaethiopia7673 19 дней назад +1

    ጥሩ ውይይት ነው እግዚአብሔር ያበርታችሁ

  • @Fano316
    @Fano316 24 дня назад +1

    በርቱልን እግዚአብሔር. መልካም ሀሳባቹን ያሳካልን ዘንድ የሁላችንም ምኞትና በአቅማችንም መማፀን መፀለይ የምህመናን ሀላፊነታችን ትንሹ ድርሻችንን እንወጣለን አቅሙ እውቀቱ ያለን በሐይማኖታችን የቻልነውን ማረግ የነብሳችን መዳኛ ይሆናል እግዚአብሔር ኢትዮጲያን ሲፈጥራት ፍፃሜዋንም ትንቢቷን ከሱ ሀሳብ ሚቀይር የለም ፈተናውን ሚወድቁ ይሄን ረስተውት እስከመጨረሻው ለንስሀ ሳይበቁ ሲኦል ለሚወርዱ ንቃተ ህሊናቸውን ያንቃላቸው!!!

  • @mimiworku4129
    @mimiworku4129 22 дня назад +1

    ቃለ ሕይወት ያሰማልን🙏

  • @mulugetemoch8079
    @mulugetemoch8079 3 дня назад +1

    ችግር ያለው ዋናው ጳጳስ ጋ ነዉ...

  • @zomisintu
    @zomisintu 23 дня назад +3

    በመጀመርያ ሁላችሁንም ቃለ ህይወት ያሰማልን።
    ዲ/ን ዮሴፍ ውይይቱን ስላዘጋጀህ በጣም አመሰግንሃለው መሠረታዊና ከበድ ያለ ጉዳይ ነው ከድህነታችን ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተገናኘ ነውና። ሆኖም ግን ዲ/ን ዮሴፍ በረዳህም ቀሲስን ማቋረጥህ በየትኛውም መልኩ አግባብ ነው ብዬ አላምንም። ሰሚዎቹ እኛ ለዚህ የማንሰጠው ጊዜ አይኖርም ሃሳባቸውን ጥፍጥፍ አርገው እስኪጨርሱ ትዕግስት አድርግ። ለጠየከው ጥያቄ ቀሲስ 27:15 ላይ የጀመሩትን ቁልፍ ሃሳብ ማስረጃውን አጣቅሰው ሳይደመድሙት ነው 31፡36 ላይ ያስቆምካቸው። ቅዳሴ እግዚን "በረከተ ጸጋሁ ወሀብተ ረድኤቱ የሀሉ ምስለ ሊቀ ጳጳስነ ወ__ " የሚለውን የቅዳሴ ክፍል አንስተው "ስለየትኛው በረከትና ረድኤት?" እንደሚያወራ ጠይቀው በቅዳሴው ውስጥ የተጠቀሱትን ስምንት(8) ነገሮች፤
    28:14 ከጓደኛው ጋር የተጣላ ቂም በቀል ካለው አይቅረብ
    28:30 በለቡ ጥርጥር ያለው
    29:38 ህሊናው የጎደፈበት በሰው የሚጠረጠር አይቅረብ
    29:48 በሚያስከስስ በታወቀ ሃጥያት ከወደቀ አይቅረብ
    30:03 ህሊናው የፈዘዘ የደነዘዘ አይቅረብ
    30:14 በዝሙት የተጎዳደፈ አይቅረብ
    30:27 ክርስቶስ ካዘዘው የተለየ ሰው ቢኖር ከሲኖዶሱ ይለይ። ነብያት ከተናገሩት ሁሉ ጋር የሚቃረን ይወገድ
    30:49 ገንዘብ የሚወዱ ሁሉ ይነቀሉ።
    ብለው በረከትና ረድኤቱን ስማቸው በቅዳሴው የመጠራቱን ሳያስተሳስሩት እየጠበቅሁ ነው ያቋረጥካቸው።
    እኔ ይሄን ሃሳባቸውን ለቀሲስ ዳግም አንስተህ እንድታስጨርሳቸው እፈልጋለሁ ወይም ጠይቀህ መልስልኝ።
    እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

    • @TunbiMedia_
      @TunbiMedia_  23 дня назад +1

      አመሰግናለሁ ቤተሰባችን! ለሚቀጥለው ለማሻሻል እጥራልሁ!

  • @zekemekonnen1478
    @zekemekonnen1478 23 дня назад +1

    Selam selam Tunbi and our memeheran.

  • @user-pe8gc4js4t
    @user-pe8gc4js4t 24 дня назад +1

    አባቴ ቡራኬዎ ትድረሰኝ። አባታችን መጽሃፍ ጽፈው ከሆነ አርስቶቹን ቢያሳውቁን

  • @MikeGeorge-bz1jr
    @MikeGeorge-bz1jr 24 дня назад +1

    ሰላም የቤተክርስቲያን ልጆች
    ይህ የቤተክርስቲያን አስቸጋሪ ጉዳይ ሊፈታ የሚችለው የቤተክርስቲያን ባለሞያዎችን ማንቃትና አድር ባዮችን ማስተማር። ትልቅ ስትራቴጂ ተነድፎ ምእመናንን አንቅቶ በተለይ ጳጳሳትን ሃይ ካልተባሉ ቤተክርስቲያኗን በአጭር ጊዜ ያፈርሷታል፣ምንም አይነት ለቤተክርስቲያኗ ርህራሄ የላቸውም።

  • @degolabraha9972
    @degolabraha9972 24 дня назад +1

    ሰላም መምሕሮቻችን በረከታችሁ ይደርብን አውጡት እንወቀው የተዳከመውን ሲኖዶስ እግዚአብሔር ይግለፅላቸው በሕዝብ ደም ተነተርሰው መነገድ ይቅር የደሃ ምስኪኑ ችግሮ ማን ይቁጠርለት ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ሀገረ እግዚአብሔር አንርሳት

  • @kasahunmatabe344
    @kasahunmatabe344 22 дня назад

    የመልአከ ብርሃን አስተርአየ ፅጌን አድራሻ ብትሰጠኝ

  • @MulualemFedessa
    @MulualemFedessa 23 дня назад +3

    ላህናት የተወገዙትን ጳጳስን በቅዳሴ አታንሱ ሲባል እንቢ ስላሉ አብረዉ በአለቃ አያሌዉ ተወገዙ ዛሬም እኮ አቡነማቲዮስም እየተጠሩ ነው የሳቸዉም ዉግዘት አልተነሳም ግን ዛሬም ስማቸዉ በቅዳሴ ላይ ኡጠራል ለምን???

  • @kienfemichaeltemesgen9168
    @kienfemichaeltemesgen9168 22 дня назад +2

    ወንድማችን መምህር ፋንታሁን ዋቄ በደንብ ገብቶሃል።ይኸውም"እውነት ዛሬ ሐማኖታችን በትክክለኛው ሃዲድ ላይ ነች?" የሚለው ጥያቄ መልስ የሚያስፈልገው ጥያቄ ነው።ይኸውም የሚመለሰውም በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። አሁን ያላችሁት እውነተኛ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ካህናት አንዱ ገዳም ግቡና ልዑል እግዚአብሔርን በሱባዔ ጠይቁ።እግዚአብሔር በትህትና እራሳቸውን አዋርደው በሡባኤ የሚጠይቁትን አይንተ እግዚአብሔር ካህናትን እውነቱን ይገልጽላቸዋል። በዚህ መሠረት ለዘመናት በማወቅም ባለማወቅም እየተንከባለለ የመጣውን የከዶግማና የቀኖና ጥሠት ማስተካከል ይገባል።አለበለዚያ በእውቀት ብቻ ይህንን የቤተክርስትያናችንን ሥብራት መጠገን አይቻልም። አረ ለመሆኑ መች ነው ጌታችንና አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንጠይቀው እንዲሁም ቆም ብለን የምንሰማው? እግዚአብሔር በአንድም በሌላ ይናገራል ፤ሰው ግን አያስተውልም።

  • @mekdesworku4765
    @mekdesworku4765 24 дня назад +7

    መቼም በምእመናኑ ቦታ ሆናችሁ ብታዩት በጣም ከባድ ነው። የናንተ በክኽነት ውስጥ ሆናችሁ የችግሩ አካል ነን በሚል ብዙ ሊሰማችሁ ይችላል። አንዳንዱም ክኽነቴን አጣለሁ በሚል ከችግሩ ሸሽተው ከመናገር ተቆጥበው አልፈው ተርፈው የኛን ችግር በመፍታት ፈንታ ዝም በሉ እንባላለን። አልፈው ተርፈው ወደ መገዘት የሚሄዱ ካኽናት አሉ። ማስቀደስ፣ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ፣ ንስኻ መግባት ህልም እየሆነብን ነው።

    • @FikirteAsres-ng6bp
      @FikirteAsres-ng6bp 24 дня назад

      ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

    • @freeethiopia3729
      @freeethiopia3729 24 дня назад

      #መንግሥት_አለ_እንዴ⁉️
      #ፍልሚያው_ይቀጥላል‼️
      #የጥቁር_ጥሊያኖቹን_ሸለፈታሙን_አብይ_አህመድንና_ግብርአበሮቹን_በአማራ_ዘር_ማጥፋት_ለዓለም_አቀፍ_የወንጀለኛ_ፍርድ_ቤት_ሣናቀርብ_አናርፍም🩸⚖️#ፋኖ_ያሸንፋል‼️

  • @habtemariamhailu7437
    @habtemariamhailu7437 22 дня назад +1

    ውግዘትን በተመለከተ ተደባብሶ ማለፍ የለበትም።በማስረጃ አለ እኮ።እንደ አማኝ ሌሎች አኃት አብያተክርስቲያናትም አይተውት ጥንቅቅ ያለ ውሳኔ ያስፈልጋል።
    የወለደ የዘሞተ ካለም ይወገዝና ይለይ።ራሱን የሾመ በገንዘብ የተሾመ በህገወጥ የተሾመም ተወግዞ ይለይ።

  • @AW-go3su
    @AW-go3su 23 дня назад +1

    እግዚአብሔር ያበርታልን እኔም የድርሻየን ለመወጣት እግዚአብሔር ይርዳኝ

  • @KH-wy1ek
    @KH-wy1ek 24 дня назад +1

    ይፍጠኝ ባርኩኝ አባታችን እ ጥያቄው የሁሉም የመኖሩ ጥያቄ ነበረ የጥያቄ አብዛኛው ሰው ማለት ነው የሚገርመው ነገር አሁን ባላችሁት መሠረት እዛ አሜሪካን ሀገር ውስጥ ቁጭ ብሎ ራሱ መች ተስማምቶ ነው በቤተክርስቲያኑ ቤተክርስቲያኑን እየከፋፈል የከፋፈል ያለ ካንዴ አሁን ስለ ታላቁ ስለማሰብ ከባድ ነው ብዬ ነው ማስ መጀመሪያ በውጭ ሃገር ያሉት ካህናቶች ራሱ መስማማት ይቻላል ለምን እየከፈሉ አይደለም የተለያየ ቤተክርስቲያን አይደለም እንደ ቢዝነስ እየታየ አይደለም ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ራሱ ትልቅ ጥናት ያሰፈልገዋል አመሰግናለሁ

  • @cricket3806
    @cricket3806 24 дня назад +3

    #መንግሥት_አለ_እንዴ⁉️
    #ደርሰዋል_ፍልሚያው_ይቀጥላል‼️
    #የጥቁር_ጥሊያኖቹን_ሸለፈታሙን_አብይ_አህመድንና_ግብርአበሮቹን_በአማራ_ዘር_ማጥፋት_ለዓለም_አቀፍ_የወንጀለኛ_ፍርድ_ቤት_ሣናቀርብ_አናርፍም🩸⚖️#ፋኖ_ያሸንፋል‼️

  • @AMEN271
    @AMEN271 14 дней назад +2

    ዓይነ ስውር ስልጣነ ክህነት ይሰጣል ወይ ጥያቄ ነው ብትመልሱልኝ ??

    • @qobastle374
      @qobastle374 12 дней назад +1

      አዎ የተገባው ከሆነ ይሰጠዋል። የዓይን ሥራን ከሚጠይቁ የክህነት ሥራዎች ላይ ባይሳተፍም ማስተማር፣ መናዘዝ፣ ማሰር መፍታት መባረክ ሥልጣኑ አይቀርበትም።

  • @degolabraha9972
    @degolabraha9972 24 дня назад +1

    በየቀኑ ሕዝባችን እየተገደለ ነው ሲኖዶሱ ፍራቻ አይሉት መደበቅ አይሉት ነግ በኔ ነው አልተረዳቸውም የራሳቸው ቤት እንደሚንኳኳ አልተረዳቸውም የሕዝብ ደም ይቆርቁራችሁ እንጂ መቼ ነው የምትነቁት እግዚአብሔር ይመስገን

  • @yoannesalta3930
    @yoannesalta3930 24 дня назад +7

    ...ከዚያም ለዓዲስ አመት መስከረም 1, 1987 ዓ.ም ፓትርያርክ አባ ጳውሎስ ወደ ሮም ሄደው፡ በጊዜው የሮም ቫቲካን ጳጳሳት ጋር አብረው ተመግበው፡ ከእነሱም ጋር ቡራኬ ተቀብለው መምጣታቸው ተነገረ። በጊዜው የነበረው የቫቲካን ሬድዮ የአማርኛው አገልግሎትም የነበረን ሁኔታ በቀጥታ ስርጭት መስከረም 8,1987 ዓ.ም ዘገበው።
    የአለቃ አያሌው ተማሪወች ከዚያም ቀጥሎ የተከሰተውን ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ "የጥቅምት ጉባኤ ላይ 'እስክንድርያ እናቴ ፥ ማርቆስ አባቴ' የሚለው እንዲቀር እና እሳቸው(ፓትርያርኩ) ያደረጉትም ጉዞ፡ በቤተክርስትያኒቱ የክብር መዝገብ ላይ እንዲጻፍ የሚል አጀንዳ ተያዘ"።
    አለቃ አያሌውም ይህንን ተቃውመው "ከሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጋር ብዙ አመት የቆየ ውግዘት አለ። እርሶ ያደተጉት ጉብኝትም በቤተ ክርስትያኒቱ የክብር መዝገብ ላይ አይጻፍም። እርሶስ የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያንን እንዲጎበኙ እና በጸሎትም ከ እነሱ ጋር እንዲሳተፉ ማን ፈቀደልወት?" በማለት ተናገሩ። አባ ጳውሎስም መልሰው ብዙ ደስ የማይል ነገር ተናገሯቸው። አለቃ አያሌውም ነገሩ ሁሉ እንደተበላሸ ስላወቁ በጊዜው ለሲኖዶሱ አባላት ሁሉ ፡ በአካልም፥ በፖስታም በየ አድራሻቸው ያነሷቸውን ነጥቦች አቀረቡ።
    ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ እየቀጠለ እንዳለ፡ አንድ አመት ከ ሰባት ወር አካባቢ እንዳለፈ ጥር ወር ላይ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት እና የውጭ ግንኙነት" የሚል አርዕስት ያለው ብዙ ኑፋቄ እና ክህደትን በውስጡ የያዘ መጽሀፍ በፓትርያርኩ አባ ጳውሎስ ሥም ታትሞ ወጣ።
    ከዚያም ጥር 24 በደብረ አሚን ተክለ ኃይማኖት ቤተ ክርስትያን ላይ አለቃ አያሌው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ "ሰውየው ኃይማኖት ክደዋል፥ ካቶሊክ ሆነዋል። ከዛሬ ጀምሮ አውግዤያለሁ" አሉ። ነገሮች ሁሉ ተደበላለቁ። ከካህናቱም ከምእመኑም ወገን በሁለት ጎራ ተከፈለ። ምዕመኑ ማጉረምረም ጀመረ። ነገሮች ሁሉ በፍጥነት በየቦታው መሰራጨት ጀመሩ።
    እነ አባ ገሪማን ጨምሮ በፓትርያርኩ ወገን የሆኑት፡ ከአለቃ አያሌው እና ሃሳባቸውን ከሚደግፉ ሁሉ ጋር እልህ መጋባት ጀመሩ።
    ሚያዝያ 17 ቀን እነ መልአከ ታቦር ዘሩ ተሾመ፣ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ፣ መምህር ሀብተማርያም ተድላ እና መልአከ ሰላም ዳኛቸውን የያዘ "የሰላም እና ቅሬታ አስወጋጅ ኮሚቴ" የሚባል ቡድን ተቋቋመ። አላማውም በአለቃ አያሌው ጉዳይ ላይ መመርመር እና ክስ መስርቶ ውሳኔ ማሳለፍ ነበር።
    ከዚያም የተቋቋመው ኮሚቴ ከሚያዚያ 1 ቀን ጀምሮ ከሥራ ተባረካል የሚል ደብዳቤ ጽፎ ለአለቃ አያሌው ሰጣቸው። አለቃ አያሌውም ለ35 ዓመት ካገለገሉበት የሊቃውንት ጉባኤ አባልነት እና ዋና ሰብሳቢነት እስከመጨረሻው ታገዱ።
    ወቅቱ የግንቦት ሲኖዶስ ከሚያዚያ 22 እስከ ግንቦት 6 የሚካሄድበት ጊዜ ነበር።
    የአለቃ አያሌው ተማሪወች ሲገልጹ፤ ሚያዚያ 30,1988 ዓ.ም ሲኖዶሱ "ቤተክርስትያን እስካሁን ስትሰራባቸው እና ስትመራባቸው የነበሩ ህጎች በሙሉ በዚህ ህግ እና ደንብ ተሽረዋል በማለት ሲኖዶሱ ተጠሪነቱ ለመንፈስ ቅዱስ ሳይሆን ተጠሪነቱ ለፓትርያርኩ ነው የሚል አምልኮተ ጣኦትን አወጁ" ይላሉ።
    አለቃ አያሌውም "ይህንን ህግ የፈረማችሁ 35 ጳጳሳት በአስቸኳይ ይህንን ህግ አሻሽላችሁ፡ አባ ጳውሎስን ከሥልጣን አንሷቸው፥ ምክንያቱም በሥጋ ወደሙ የማሉትን መሃላ አፍርሰዋል፤ የቤተ ክርስትያንን ሥርዓት እና ህግ ተላልፈዋል፥ ቤተክርስትያኒቱንም የካቶሊክ ምርኮኛ አድርገዋል" በማለት ተናገሩ። ሊሰሟቸው ግን አልፈቀዱም።
    አለቃ አያሌው ሰኔ 27, 1988 ዓ.ም ለሲኖዶሱ አባላት የመጀመሪያ ቃለ ግዝታቸውን ሰጡ። የቤተ ክርስትያናት፣ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪወችን እኚህ ሰው ሃይማኖት የለወጡ፥ የካዱ ስለሆኑ በጸሎተ ሃይማኖት ስማቸውን እንዳትጠሩ ብለው አወገዙ።
    ህዝቡንም ገንዘብ እየሰጣችሁ፣ ዳቦ እየደፋችሁ፣ ጠላ እየጠመቃችሁ፣ ሲወጡ ሲገቡ ቁጭ ብድግ እያላችሁ ሃይል የሆናችኋቸው እናንተ ናችሁ። ስለዚህ በእነሱ እጅ እንዳትሳለሙ፣ በእነሱ እጅ እንዳትቆርቡ፣ በ እነሱ እጅ ምስጢር እንዳትሳተፉ በማለት አወገዙ። ይህንን ስታደርጉ ምንድነው ጥያቄያችሁ ብለው ወደ እናንተ እጅ ይመጣሉ። ከዚያም ጥያቄያችሁን ሲቀበሉ ቤተ ክርስትያናችሁን ትቀበላላችሁ ብለው ነበር። ነገር ግን ይህ ሊሆን አልቻለም።
    ከዚያን ጊዜ ጀምረው እስከ እለተ እረፍታቸው፡ በመኖሪያ ቤታቸው ጉባኤ ዘርግተው በማስተማር ቆይተዋል።
    የተወሰኑ ቤተክርስትያናት እና ገዳማት ግን አባ ጳውሎስ እስካረፉበት እና አዲስ ፓትርያርክ እስከተሾመበት ጊዜ ድረስ ቃለ ውግዘቱን በመጠበቅ በቅዳሴ ወቅት ስማቸን ባለመጥራት ቆይተዋል።
    በዚያ ሰሞን ማህደረ ስብሀት ቅድስት ልደታ ለማርያም በተፈጠረው ሃይማኖታዊ ጥያቄ ምክንያትም በመንግስት አካላ ብዙ ሰወች ህይወታቸውን አጥተዋል። ብዙወችም ለአካል ጉዳት ሲዳረጉ፡ ሌሎችም ሃይማኖታቸውን ትተው ወጥተዋል። ቤተ ክርስትያኒቱም ለ አንድ ወር ከአስር ቀን ተዘግታለች።
    በሌሎች ቦታወችም የህገ ቤተ ክርስትያን ጥሰትን የተቃወሙ ባህታውያን አባቶች በዚያው በጥይት ተደብድበው እንደሞቱ በወቅቱ የነበሩ ሰወች ይናገራሉ።
    ቀስ በቀስም ቤተ ክርስትያናት ካቴድራል እየተባሉ መሰየም ጀመሩ፣ ተሃድሶ እና ምንፍቅና እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ መጣ፣ ሰንበትን ማክበር እየቀረ፡ ስርዓተ ቤተክርስትያንን መጣስ የአደባባይ ድርጊት ሆነ። ፈሪሃ እግዚአብሔር እየጠፋ፤ ትላንትን አልፈን ዛሬ ላይ ደረስን።
    በዚያን ዘመን በዓላት፣ ስርዓተ ቤተክርስትያን፣ ባህል እና ታሪክን በሚመለከት የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ሚድያወች፣ ጋዜጦች እና ልዩ ልዩ ፕሬሶችን ከፊት ገጽ ላይ ያደምቁ የነበሩት ብዙ ሊቃውንትንም ያፈሩት ታላቁ የቤተ ክርስትያናችን እና የሀገራችን ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ ነሀሴ 14, 1999 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
    በረከታቸው ይደርብን !!!
    ምንጭ:
    1.ደራሲ ዳንኤል ገብረ መስቀል/ያልተፈታ ውግዘት

  • @AW-go3su
    @AW-go3su 23 дня назад

    የቄስ አስተረየ በፖትሪያኩ ላይየሚሰጡት ሐሳብ አልገባኝም

  • @mulatuamogne
    @mulatuamogne 24 дня назад +1

    ስለ ሁልጊዜ ጥረታችሁ ከልብ አመሠግናችኋለሁ። ነገር ግን የጥፋቱ ምንጭ ያለው ከቅዱስ ሲኖዶሱ ስለሆነ መጀመሪያ መስተካከል ያለበት ይህ ይመስለኛል። ምክንያቱም ከአጥቢያ ያለውን አገልጋይ እንዲህ ነው ብለህ ወደ ላይ ብታመለክት ራሱ የጉዳዩ ባለቤት ሆና ታገኘውና አርፈህ ቁጭ ትላላህ።

  • @GebresilasieNigus
    @GebresilasieNigus 23 дня назад

    የታላቁ ልቅ ዉግዘት
    አንድ ጳጳሱ ራሱ ጣዓዖት ሆኖ መቀመጥ
    ሁለት ስኖዶስ ተጠርነቱ ለጳጳሱ ሙሆኑ
    ሦስት የብዙ ዘመን የኖረ ዉግዘት በጳጳሱ ተሽሮ ፖፖ መርጠዉ ሮም መሄዳቸዉ
    አራት በነገረ ማርያም ህፀፅ መኖሩ
    አምስት ጳጳሱ የፖለትከኛ ሹም በመሆናቸዉ አለቃ አያሌዉ ቤተክርስትያን የመጣባት ችግር ለህዝብ እንዳያቀርቡ ተባረሩ
    ስድስት ጳጳሱ ነበሰ ገዳይ በመሆኑ ቅዱስ ልባል አይገባም ብቻ ብዙ ነዊ የጳጳሱ ችግር

  • @yibeltalyihenew5540
    @yibeltalyihenew5540 24 дня назад +1

    ቤተ ክህነት የሞጣ ቀራንዮ መዘበቻ እስክትሆን ድረስ አፍሳለች። መፍትሔው እንዲህ ጨክኖ መነጋገር፣ መተባበርና መከወን ይመስለኛል።

  • @ghennetwoldegabrel9229
    @ghennetwoldegabrel9229 24 дня назад +1

    OH God 🙏 Mercyful God have mercy upon us!? It's so sad to hear such irresponsible behavior from those High Rank Fathers! We/I are so sorry and are full of fears. It's chilling. To give comments and suggestions are to be bold, positive boldness to tell and confront as Kessis explained,and your discussion how do we take care of ourselves? Participating the prayer, standing for more than 3 hrs, for nothing and beyond that having storms of curse. Thanks for your unlimited efforts you are struggling to save the country, Orthodox faith in Ethiopia.

  • @BelayAssena
    @BelayAssena 24 дня назад

    እባኮት አባታችን የተዋበ ቜንቃ ያለን ሕዝብ ስለሆንን እንግሊዘኛው ከተማሩ
    ሰዎች ጋር ብቻ ያውም ከርሶ ባንጠብቅ
    ም ብቻ ይጠቀሙ።

  • @danidesye9842
    @danidesye9842 21 день назад

    በአለቃ አያሌው ታምሩ ውግዘት አባ ጳውሎስ ተወግዘዋል በቅዳሴ ጊዜ የጳጳሱን ስም የጠራ ም ጭምር የተወገዘ ነው በቅዳሴ የጳጳሱ ስ እየተጠራ የተሳተፈ ምዕመንም የተወገዘ ነው እንደተባበረ ይሆናል ብለዋል እንዳውም አስራታችሁን አትስጡአቸው በናንተ አስራት በናንተ ምድዋይ ምፅዋት በምትሰጡት ገንዘብ ነው እዳሻቸው የሚሆኑት አትስጡ አውነተኛ ለሚመጣ ትሰጣላችሁ ብለዋል ኢንተርቪያቸውን አዳምጠው 1-04 ደቂቃ ነው።

  • @andualemdegu7177
    @andualemdegu7177 24 дня назад +1

    ቃለ ህይወት ያሰማችሁ አባቶቻችን

  • @tamiratasefa5176
    @tamiratasefa5176 23 дня назад +1

    god bless you

  • @KH-wy1ek
    @KH-wy1ek 24 дня назад

    ይፍጠኝ ባርኩኝ አባታችን እ ጥያቄው የሁሉም የመኖሩ ጥያቄ ነበረ የጥያቄ አብዛኛው ሰው ማለት ነው የሚገርመው ነገር አሁን ባላችሁት መሠረት እዛ አሜሪካን ሀገር ውስጥ ቁጭ ብሎ ራሱ መች ተስማምቶ ነው በቤተክርስቲያኑ ቤተክርስቲያኑን እየከፋፈል የከፋፈል ያለ ካንዴ አሁን ስለ ታላቁ ስለማሰብ ከባድ ነው ብዬ ነው ማስ መጀመሪያ በውጭ ሃገር ያሉት ካህናቶች ራሱ መስማማት ይቻላል ለምን እየከፈሉ አይደለም የተለያየ ቤተክርስቲያን አይደለም እንደ ቢዝነስ እየታየ አይደለም ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ራሱ ትልቅ ጥናት ያሰፈልገዋል አመሰግናለሁ