ይቅርታ አልጠይቅም ቤተ-ክርስቲያን የምትፈራበት ጊዜ አልፏል | ክፍል 2
HTML-код
- Опубликовано: 20 май 2024
- እግረኛው ሚዲያ በተክለሃይማኖት አዳነ የተቋቋመ ሲሆን በምድር ያሉ ማህበራዊ እና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ቻናል ነው። ለማንኛውም መረጃና ጥቆማ 0946707555 ላይ አድርሱን!!
እግረኛው ሚዲያን ይደግፉ gofundme.com/6bcg2
በኢትዮጵያ ብር ማገዝ ለምትፈልጉ ከስር ባሉት የባንክ አካውንቶች ተጠቀሙ
ንግድ ባንክ
1000067563259
ተክለሃይማኖት አዳነ
ዳሸን ባንክ
5155131542011
ተክለሃይማኖት አዳነ
አዋሽ ባንክ
013201211642800
ተክለሃይማኖት አዳነ
ለበለጠ መረጃ
0946707555
#Ethiopia #Egregnaw-Media #Donkeytube #Seifufantahun #Yenetatube #Medlotmedia #መጋቤሐዲስ እሸቱ #Fanabc #Yegna TV #Haleta TV #hagerie tv #MK TV #Henok haile #Asterbedane #Ethiobetesb Media
gofundme.com/6bcg2
gofundme.com/6bcg2
😊😊😊😅😅😅@@HenokHenok-cj5bp
የሚደነቅ ሰው
ያሬድ ድሮ ሲያገለል በጣም የምወደው አብሮ አዲገ ነው በዚህ ቃለመጠይቅ ደስ ብሎያል
የበጋሻውን ሴራ በወላይታ ኦቶና ማሪያም ቤተክርስቲያን የነበረውን እኛ ኦርቶዶክሳዊያን መቼም አንረሳም። ወንድሜ አንተ ተባረክ።
ከዚህ ሰዉ ንግግር ሀሰት አላገኘሁም የአንደበትህን በልብህ ያድርግልህ በቤቱ ያጽናህ
amen
በፈፁም ማታለል አልነበረም ?
የእውነት በጣም ደስ ነው ያለኝ ያሬድ እድሜ ጤና ይስጥልኝ ይቅርታው አስፈላጊ ነው ለቤተክርስቲያን ታስፈልጋታልህ ዝቅ በማለት ውስጥ ከፍ ማለት አለ ተባረክ
መምህር ያሬድ ትልቅ እና አስተዋይ ሰው ነህ እግዜአብሄር ይባርክህ ደስ የሚል ማሰተዋል ነው ቅዱስ ዮሴፍ በእናተ ይደረግ በነበረው ጉባኤ የስንት ወጣቶች ነፍስ ታዱጓል
መምህር ያሬድ የዲላው ቅድስ ሚካኤል አውደምህረት ላይ በድጋሚ እንደቀድሞ ጊዜ ለማየት ያብቃን አሜን
ጀግና ነህ😍: በኛ ሀገር የተለመደው ለመወደድና ተቀባይየትን ለማግኘት ሌሎችን መስደብና መንቀፍ ነው :ይሄ ደግሞ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ ከሚሉ ሰወች አይጠበቅም ::
እግዚአብሔር ይባርክህ በራስ መተማመንህ ደስ ሲል ::🙏🙏🙏
ለቤተክርስቲያን የሚያስብ ሁሉ የመ/ር ያሬድን ሀሳብ አይጠላም
ኧረ ባክህ
What a gentle man! ያሬድ እኔ ልጅ ሆኜ ነው በወንጌል አገልግሎት የማውቅህ። ተሃድሶ ሆኗል ተብዬ ካለቀስኩላቸው መሃል አንዱ አንተ ነህ ምክንያቱም እኛ በእናንተ ትምህርት ጌታን ወደ ማወቅ ደርሰን ነበር በልጅነታችን። አሁን ግን ከእግዚአብሔር መንግሥት እንዳልወጣህ ስትናገር እንዴት ደስ እንዳለኝ። ደግሞ የተናገርከው ሁሉ ልክ ነው። እባክህ ወደ አገልገሎት ተመልሰህ በዚህ አስተሳሰብህ ከጥሩዎቹ አባቶቻችን ጋር ሆነህ ቤተክርስቲያንን ታደጉልን። ሥላሴ በቤቱ ያጽናልህ የአባቴ ልጅ❤ I wish አስተዳደሮቹ አይተውህ አስገብተው በሞያህ ለቤተክርስቲያን ሥራ ቢያሰሩህ
በጣም እጅግ ብስለት የተሞላበት ቃለ መጠይቅ እንዲህ በሳል ሰው ተመልሶ በበተክርስትያን ዐውደ ምህረት ማየት እመኛለው::
መምህር ያሬድ ክብረት ይስጥልን:: ለሠጠኸን ነፃ እይታ እና እዉነታዉን ስለገለፅክ የቅ/ማርያም ልጅ ይክበር ይመስገን:: እዉነት እዉነት ነዉ:: ክብርሞገስ ከፀጋ ጋር ይስጥህ::
በእውነት እንዳንተ ያሉ እውነትን እውነት የሚሉ በቅድስት ቤተክርስቲያን ያደጉ ሰዎች ያስፈልጉናልና እግዚአብሔር አምላክ ወደ አውደምህረት መመለሻህን ያቅርብልን።ቅዱሱን ወንጌል ሰብከህ ስትወርድ አጥንትን የሚያለመልመውን የመላዕክትን ዝማሬ ያሰማልን ብለው ከሚመርቁት ያርገኝ እኔንም 😊
መምህር ያሬድ ልጅ ሆኜ በቦሌ ደብረሳሌም መድኃኔዓለም ትምህርትህን ስሰማ አድጌያለሁ መሄድህን ስሰማም በጣም አዝኜ ነበር አሁንም ግን ቤተክርስቲያን ትፈልግሀለች ስለዚህ አብዛኞቻችን እንደሄድክ አምነናልና ይቅርታ ጠይቀህ ወደአውደምህረቱ ብትመለስ መልካም ነው ላልተረዳንህ ማረጋገጫህ በይፋ ይቅርታ ስትጠይቅ ነውና ይቅርታ የታላቅነት መገለጫ ነው
ያሬድ አደመ ቤተክርስትያን በአንተ አትለካም በልተህባታል ኖረህባታል አሳድጋሀለች መልሰህ ነክሰሀታል አዎ ቤተክርስትያን ስድብ አታስተምርም ልክነህ ይህንን አንትንኩ የሚባልበት ግዜ አልፏል አልክ ምን ልትነካ ፈለግህ እመብርሃን በቅርፊት ኢየሱስ ክርስቶስን በአስኳል መስላችሁ አስተማራችሁ የነዳችሁትን ነድታችሁ ይዛችሁ ወጣችሁ እና አሁንም ቤተክርስትያን እናት ናት አትታበይ ይቅርታ ጠይቀህ ተመለስ መንገዱ ያ ብቻ ነው
ላይከ ወንጌል መምህር ያሬድ አደመ የመካነህ ብርሃን የቃሊቲ ገብርኤል ልዩ ትውስታ አለኝ እግዚአብሔር በቤቱ ያፅናህ
ሁለቱንም ክፍል አይቼዋለው፣ ደረጃውን የጠበቀ ኢንተርቪው ነው፣ እንደዚህ አይነት ኢትዮጵያውያን እና ኦርቶዶክሳውያን ያብዛልን❤
በእውነት አንተን አለማድነቅ አልችልም በቂ የሆነ እውቀት ባለቤት ነህ ።የኛ ቤ/ክ እግዚአብሔር ይድረስላት መልካሞችን እየገፋች ሆዳሙን ትሰበስባለች ሁሉንም እያልኩ አይደለም ።
ተክለሃይማኖት ዛሬ ከሰጠኸሁ ርዕስ ጀምሮ ጥያቄዎችህ በከፊል አልተመቹኝም ።በጣም የማደንቅህ ጋዜጠኛ እንደሆንክ አውቃለሁ ስትሳሳትም እቃወማለሁ
ያሬድ ለማንም ብለህ ሳይሆን አሁንም ለእግዚአብሔር ቤት በሃቅ አገልግል።ውስጥህን የሚያውቀው አንድ አምላክ ነው።ሰውማ ....ያደክማል 😢
በጣም ልቤን የነካው ንግግርህ ሰዎችን ከመሳደብ ከማንቋሽሽ ከማሸማቀቅ እውነት ነው እንደታላቅ አባት ማስተማር ማነጋገር ሲሆንም መገሰፅ እንጂ ማመናጨቁም መቆጣቱም ማንቋሽሹም ትክክል አይደለም።በጣም ልቤን የነካው ንግግር ነው ደግሞም ትክክል ነው። ሰውን ከመግፋትና ከማበሳጨት በትዕግስት መመለሱ ሁሉም ተጠቀሚ ይሆን ነበር። በነገራችንን ላይ ንግግርህ አይጠገብም ጎበዝ ነህ የመግለፅ ችሎታህ።
በጣም ደስ ይላል አንዳንዴ ከእነ እገሌጋ አየናቸው በሚል ብቻ ብዙ የተገፉ ልጆች እንዳሉ እናውቃለን ! አገላለጽህ በጣም ደስ ይላል እንኳን ልክድ አስቤውም አላውቅ ብለሃል ይሄ ለቤተ ክርስቲያን የእውነት ፍቅርና ክብር እንዳለህ እሙን ነው! እራስህን ዝቅ አድርገህ ዝቅ የምታደርገው ለሰው ሳይሆን ለምታከብራት ቤ/ክ እራሷ ለሆነው ለሊቀ ካህኑ ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስትል ሳትበድልም ቢሆን ይቅርታ ጠይቀህ በሞያዬ ላገለግል ፈልጋለው ያልከውን ትምህርት ብትሰጥ መልካም ነው ብዬ አስባለው ! ካንተ ማግኘት ያለባቸውን ትምህርት ሳያገኙ የሚቀሩ ብዙ ትውልዶች ስለሚኖሩ ይሄን ክፍተት ብትሞላ እላለው ! ተምረው የሚያስተምሩ መምህራኖች ጥቂት ስለሆኑ! አንተም ገልጸኸዋል ዛሬ ፕሮግራም መሪ ይሆናል ነገ ቀሚስ ለብሶ ይሰብካል ግጥማቸው ዜማቸው ከየት እንደሆኑ የማይታወቁ መዝሙር መሰል ዘፈኖችም መብዛት ካለ እውቀት በቲቮዞ ብዛት ብቻ ለቤ/ክ እየተሰጡ እያየን ነው ! ወንድማችን አንተ ባሰብከው ወደ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንድትመለስ እግዚአብሄር ይርዳህ❤❤❤
ልክ ነህ አባቴ በየቤተክርስቲያናችን አባቶች ወንድሞች መስለው ሰውን የሚይሳድዱ መድርኩን መማሪያ ሳይሆን መሳደቢያ ያደረጉ ብዙ ናቸው እነሱን ፈርቶ ንፁሀኑን ከቤተክርስቲያን የሚይርቁ አሉ እውነት ነው
መምህር ያሬድ አዋሳ ግቢ ጉባኤ እያለን በጣም አድናቂህ እና ደቀ መዝሙርህ ነበርኩ የተናገርከው ነገር መልካም ነው ስለመልካም ንግግርህ እና ስለትህትናዊ አነጋገርህ በጣም አመሰግንሃለሁ አነጋገርህ መልካምነትህን ይመሰክራል:: እስካሁን ድረስ ይህን ሁሉ ጸጋ እና እውቀትህን ይዘህ በቤትህ ተደብቀህ በመቆየትህ በጣም አዝኛለሁ፡፡ እርግጥ ነው ቤተ ክርስቲያን የተማከለ (Centralized) አስተዳደር አለመኖር በጣም ጎድቶናል በተለይ አዲስ አበባ ላሉ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት የሚገባው ገቢና ንዋያተ ቅድሳት ወደ ገጠሪቱ ቤተክርስቲያን ማከፋፋል አለመቻል ቅዱስ ሲኖዶስ እነሱን እንኳ ማዘዝ አለመቻሉ (ጥርስ የሌለው አንበሳ መሆኑ) የገጠሪቱ ቤተ ክ/ን በችግር ተቆራምዳ እየኖረች የከተማ አገልጋዮች እየተቀማጠሉ መኖር በጣም ያማል፡፡ አንተ ግን ግን አሁንም ወደ አገልግሎት በቅንት ተመለስ ይቅርታም መጠየቅ ካለብህ እንደ ምርቴ ዝቅ ብለህ ይቅርታ ጠይቀህ ወደ አገልግሎት ብትመለስ ደስ ይላል አይዞህ በርታ
መምሕር እግዚአብሔር እንድታ አስተምርን ይርዳን
ልጅ ሆኜ የ ሰባኪ ያሬድን ትምህርት ደስ ብሎኝ ነበር የምሰማዉ በተኮላተፈ አንደበቱ ሲሰብክ እኔስ ከነበጋሻዉ ከነ በሪሁን ከነ ትዝታዉ ጋር የኮበለለ መስሎኝ ነበር እግዚያብሄር በአዉደ ምህረቱ ቆመህ ድጋሚ ለመስበክ ያብቃህ ይሄ ሁሉ ብጥብጥ እኮ በአገሪቱ የተነሳዉ በዘር ማጣላቱ እኮ ኦርቶድክስን ለማጥፋት ነዉ ምንጩ እባካችሁ የሚመለከተዉ የቤተክርስቲያን የሚመለከተዉ መ ምህር ያሬድን መልሱት!
ደስ የሚል ጊዜ ነበር ሁለቱንም ክፍል በደንብ ነው ያዳመጥሁት፡ centralization የሚለው ሀሳብ ሁሌም በውስጤ የሚመላለስ ነው ይህን የሚያስፈጽሙ አባቶችን እግዚብሄር ይዘዝልን፡ ይህ ያባቶችን ፍልሰት የሚያሰቀር እና በተክርስትያንንም የሚጠቅም ሀሳብ ይመስለኛል።
በጣም ደስ የሚል ቃለ መጠይቅ ነበር በጣም እናመሰግናለን።
መምህር ያሬድ ሰላየውህ በጣም ደስ ብሎኛ ል መጨረሻህን ያሳምርልህ!!!
ያሬድ የምትናገረው ንግግርህ አንደበትህ ጥሩ ነው። ከነበጋሻው ጋር ሐዋሳ ላይ ስታደርጉት የነበረው ለቤተክርስቲያን ትልቅ ፈተና ነበራችሁ። እሱን በትክክል አልገለጽክም ዋሽተሃል። አሁንም ታሪክ አይረሳውምና ላጠፋኸው ጥፋትና ትውልድ በይፋ እንደነ ምርትነሽ ይቅርታ ጠይቅ። እንደምዕመን ቤትህ መቀመጥህ ሁሉም እንዳንተ ቢያደርጉ የቤተክርስቲያን ፈተናዋ ይቀንስ ነበር በዚህ ትመሰገናለህ። ከነ እጅጋየሁና ከነ በጋሻው ጋር የነበረህን ግን እውነቱን አጋልጠህ ይቅርታ ጠይቅ....ትንሽ ኢጎህን ቀነስ አድርጋት። በክርስቶስ ህያው ፍቅር ኦርቶዶክሳውያን እንወድሃለን። እግዚአብሔር አሁንም መጨረሻህን ያሳምርልን። ማንም ወደበረቱ እንዲመለስ ሁላችን እንመኛለን።
ለክብራቸው የሚጨነቁ ሁሉ ተዋህዶ ትከብዳቸዋለች ጌታችንም ያለው መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ አላለምን
ደግመህ ደግመህ ጠይቀው የቤተክህነት ልጅ መሆኑ አንደበቱን አጣፍጦለታል አይጠገብም ጸጋም ከፊቱ ይታያል ብዙ ሌባ የተሰገሰገባት ቤተክርስቲያን አስምሳዮች የተሰገሰጉባት እንዲህ ዓይነቱን ብልህና እውነተኛ ባትገፋ ነው የሚገርመኝ
በትክክል ቤተክርስቲያንን በሰው ማንነት አልመዝናትም ።። ደስ የሚል አነጋገር።
ወንድሜ ያሬድ እጅግ በጣም ጥሩ አሳብ ነው ያነሳእው አዳማጭ ከተገኘ
እግዚሀብሔር ይባርክህ በሳል ሰው ነው ወደ ቅድስት ቤተክርሲቲያን እንድትመለስ ተስፋ አደርጋለሁ ❤❤❤
በጣም ነው ደስ የሚለው በናትህ ተክልዬ ድጋሚ አቅርበው ምንም አልጠገብኩትም
I realy love your confidence!
ትክክልነህ ተዋህዶን አዉቀዋት ለሚኖሩ ቀናብሎ መናገር ይቻላል
እግዚአብሄር ቀና ያደርጋል፣
ሰዉ ማዳን ስለምትችል፣ ቀናበል ወንድማችን
ወንድማችን ያሬድ ስለ ዲላ ያልከው እውነት ነው በብዙ ጊዜ ነው ያየሁህ ደስ ብሎኛል፡፡ ግን ኑፋቄ ውስጥ የገባህ መስሎኝ ነበር ለዚህም እግዚአብሔር ይመስገን ግን አገልግል ዩቱዩብ ክፈት አገልግሎት ጀምር ከዛ ቤተክርሰቲያን ታይሀለች አገልግሎትህ ይመለሳል ይሄ ፈተና ነው ነጥረህ ትወጣለህ አይዞህ በርታልን፡፡
መልካም ሰው ነህ የተረጋጋህ እግዚእብሔር ይባርክህ
እውነት ነው መምህር ያሬድ ለዲላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ትልቅ ዋጋ ነው የከፈለው እግዚአብሔር አምላክ ወደ አገልግሎት ይመልስክ🙏
ያሬድ እንኳንም ወደ መናፍቃን አልፈለስክ። እግዚአብሔር በቤቱ ያፅናህ።
የቤተክርስትያንን እና የአገራችንን ችግር ያየህበት መነፅር እንዲሁም የሰነዘርከው የመፍትሄ አማራጭ መልካም ነው። ይሁን እንጂ ጥልቀቱን እና መነሻውን የመዘነ አይደለም፣ በተለይም አሁን ዋናው ችግሩ ምን እንደሆነ ግልፅ ሆኗል:: አንተ የጠቀስካቸው ውስጣዊ አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ችግሮች ኖሩም አልኖሩም : ቤተክርስቲያን እንድትጠፋ ተግቶ የሚሰራ አላማውን ከትውልድ ትውልድ ሳይፎርሽ የሚተጋ ጠላት አላት ቤተ ክርስቲያን::
እና አንተ እሱን ትፈራዋለህ : እኔም ሁላችንም::
የተዋህዶ ትክክለኛ ልጅ ነህ መቼም ያልገባዉ ከሐሜት አይነፃም አንብቦ የተረዳዉና በብፁዕ አቡነ በርተሎሜዎስ ዶግማ የተማረ ሰዉ በተዋህዶ እምነት አይጠረጠርም ሲል ሙሉ እምነት ነበረኝ በቃለ ምልልሱ ይህንን በማረጋገጠ ደስ ብሎኛል::
ዋው ይሄን የመሰለ ፕሮግራም ብዙ እይታ አለመኖሩ ያናድዳል እረ ጎበዝ ቁም ነገር ላይ እናተኩር 🤔🤔🤔🤔
በጣምደስ የሚል ኢንተርቪው ነበር 🙏🏽
እግዚአብሔር ይባርካችሁ 🙏🏽🙏🏽🙏🏽
መምህር ያሬድ ድሮ ነው የማውቅህ በጣም ጥሩ ጊዜያትን አስታውስበታለው እናንተን ሳስብ አንተ እነ አሸናፊ ዳግማዊ ቸርነት ቴዲ … ጎበዝ ነህ ጥሩ ማይንድ ሴትአፕ አለህ ግን ትዳር ይዘህ ልጆች መውለድ ያለብህን ጊዜ አታሳልፈው መንገድህ በዓለም መኖር ከሆነ በጣም ዘግይተሃል እግዚአብሔር በመንገድህ ሁሉ ይርዳህ
ጎበዝ ልጂ ነው የነገሮች አረዳዱ የሚደነቅ ነው ።
በእውነት ያሬድዬ ስላየሁክ እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ እመቤቴ ትጠብቅህ ፈጣሪ በቤቱ ያፅናህ አሁንም እርግጠኛ ነኝ በትልልቅ አውደ ምህረት ላይ በስብከት እንደምናየክ እርግጠኛ ነኝ ለተዋህዶ የምታስፈልጋት ድንቅ አገልጋይ ነህ እባክህን ያሬድዬ አትራቅ እንወድሀለን 🙏🙏🙏
ፈጣሪ ይጠብቅህ 🙏 ተክልዬ መምህር ያሬድን ስላቀረብክልን እናመሰግንሀለን 🙏♥
በእዉነት ያሬድ ትለሰቅ ሰው ነህ አረዳድህ ይገርማል እኔ ስረዳዉ እወነት ወስጥ ገብቷል በቅርቡ በጌታ ጸጋ ውስጥ የማይህ ይመስለኛል ተባረክ
አሁን በማን ፀጋ ውስጥ ነው?
ወንድም ተባረክ !
ኣገልግሎትህ ብትቀጥል ደስ ይለን ነበር፡
በእውነቱ ብዙ ሀሳቦችህ ግሩም ናቸው መምህር ያሬድ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን ይህ መረዳት ለቅድስት ቤተክርስቲያንናችን ወሳኝ ነው ብዙዎች ቢሆን ብለው ውስጥ ለውስጥ የምናዎራቸውን ትልቅ ሀሳብ በደንብ ገልጸኸዋል ደግሞ ብዙ ተስፋ አለን ወጀቡም ያልፋል ።
መምህር የምትገረም የተረጋጋክ እውነትን ይዘህ የኖርክ ነው በጣም መልካም ውይይት ነው እግዚአብሔር ምክንያት አለው ስለሁሉም መልስ ይስጣል አንተ በርታ የኔ ወንድም
ወንድሜ ያሬድ በጣም በጣም ትክክል ውይይት ነው ሁሉም እንዲህ ዓይነት ምክክር ያስፈልገናል ቀጥሉ ብዙውን እጋራዋልህ
መምህር ያሬድ - የጅማ ( ጅ ጤ ሳ ) የአጋሮ የ1988 በLab technician TTP Member - ስላየሁህ በጣም ደስ ብሎኛል ( ድሮም potential እንደነበረህ አውቅ ነበር - የድሮ አለቃህ! )
በእውነት ፡መምህር፡ስላየሁህስለሰማሁህ፡ደስብሎኛል።ለካ፡ያልሰማነው፡ብዙ፡ነገር፡አለእነምርቴን፡ቀሲስ፡አሸናፊ፡ሳይ፡አንተንና፡መምህር፡አሰግድ፡ሁሌ፡በልቤ፡ናችሁ፡የዘማሪ፡ትዝታውም፡እንዲሁ፡ኑልን፡አይኖች፡ናችሁ።የጌታ፡ፈቃድ፡ይሁን።
መምህር ያሬድ ግሩም ትምህርት ሰጡን እናመሰግናለን
Wow, I like this guy. Much respect, he knows what he is talking about. Educated, talented, and mature. Thanks Tekle, today you presented the great guy who makes you keep quiet. 👍
ያሬድ እና ጓደኞቹ ከቤተ-ክርስቲያን ወጡ ሲባል እጅግ ያዘንሁት ከሌሎቹ ይልቅ ለያሬድ ነበር ምክንያቱም ሀዋሳ እንደመኖሬ መጠን ስብከቶቹን የመከታተል ሰፊ እድል ነበረኝ።እኔ በማውቀው መጠን ነቀፋ የሌለባቸው፤ ትውልድ የሚያንጹ እና ከስሜት የጸዱ ነበሩና። ዛሬም ያንን አቀቷሙን እና የቤተክርስቲያን ፍቅሩን በማዬቴ በጣም ደስ ብሎኛል።ፈተና ይኖራል በፈተና መጽናት ግን መልካም ነው።ልብን የሚመረምር አምላክ መርምሮ በእውነት ላይ ቆመህ ካገኘህ የልብህን መሻት ይፈጽምልሃልና ተስፋ አትቁረጥ። ያኔ እነ በጋሻው በሀዋሳ ቅዱስ ስላሴ "ለካ ይህ ሁሉ ሰው የተደገፈው እኛን ነው...." እያሉ ሲመጻደቁ ከያሬድ ግን የሰማሁት የክህደትም ሆነ የነቀፋ ቃላት አልነበረምና ሁል ጊዜ ከስንዱዋ እመቤት በመራቁ አዝን ነበር።ልብህ ባለመራቁ ደስ አለኝ።
መምህር ያሬድ አደመ ዲላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ን ነው ማውቅህ ተባረክ በቤቱ ያፅናህ ዳግም በአገልግሎት እንደምናይህ ተስፋ እናደርጋለን❤
መምህር ያሬድ ስላየሁት በጣም ደስ ብሎኛል በአውነት ሁሌም ማግኘት ማዳመጥ እፈልግ ነበር ፡፡ እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁትን በሚሊኒያ አዳራሽ በነበረው ታላላቅ ጉባዔዎች ላይ ነበር፡፡ ሁሌም ተስፋ አረጋለሁ እነዛ በጣም ምርጥ የነበሩት ጊዜያት በድጋሚ በአንድነት በፍቅር …….. የወጡት ሁሉ ወደ ቤታቸው ተመልሰው አንድ እንደምንሆን ተስፋ አረጋለሁ ደግሞም ይሆናል ፡፡
ወይ ግሩም!
ሁለቱም ክፍል ሳይታወቀኝ አለቀኮ!
መልካም ነው።
እግዚአብሔር ይመሰገን ቤተክርስቲያን ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት ነች ❤❤❤❤❤❤❤
ከቤቱ ያቆይልን ዉንድማችን🙏🙏🙏
I'm so glad to see you Memihr Yared Ye Yemameta & Ya Ato Ademe lij.❤❤❤
😭😭😭💔💔💔 ለምን ይቅርታ ይጠይቃሉ ?? ቤተ ክርስቲያኗን አልበደሉ እንደው እነሱ ይቅርታ ሊጠየቁ ይገባል ከአውደ ምረቱ ስለተባረሩ በስንት መስዋት የተገኘን ክህነት ድቁና ....በደብዳቤ የተገፈፉ እነሱ ይቅርታ ይጠየቁ
ቤተክርስቲያኗ አልበደለችም አልተበደለችም በግለሰቦች መሐል የሚነሳ ፀቦች ችግሮች ነው
ጌታ ሆይ ልበ አምላክ .....💔😭 በጣም አዝኛለው
😭😭😭😭😭😭💔💔💔💔💔💔 እኔም ከአገር ተሰድጄ በዱባይ ስኖር በመከራቹ እከፋ ነበረ አቅም ስለሌለኝ ፀጥ አልኩ አባቶች እነ ቀሲስ ሰለሞን እነ ቀሲስ ተስፋዬን ...አውግዘው ሲነግሩኝ በጣም አዘንኩ ፀጥ አልኩ ከእናተም ከእነሱም ወገን አልሆንኩም ግን ውሎ አድሮ ተኣድሶ የሚል ነገር ሰማው አሷደዷቹ የእኔ ወገኖች ...የእናተ ከአውደ ምረቱ መጥፋት ዘረኝነት ባሰ ሞት ባሰ መከፋፈል ባሰ ንቀት ደረሰባት ብዙዎች በቤታቸው ማምለክ ጀመሩ ብዙዎች ወደ ሌላ ተሰደዱ ....እኔ ምንም አልልም የልጅነታችን አምላክ ይርዳን ልባችንን አንድ ያድርገው በቤቱ ያፅናን ❤❤❤❤❤
ነቃ በዪ/በል
ምኑን ከምንድን ነው የምታገኛኚው???
ተጠያቂዉ፡ትክክል፡ነዉ።
መምህር ያሬድ እውነትና ጠቃሚ ሀሳብ ሰጥተሀል። እግዚአብሔር ይባርክህ።
እውነት ነው የምትፈራበት ግዜ እራሳቸው ጳጳሳቱ አበላሽተውታል ከዚህ በኋላ ማንም ተነስቶ አፉን ቢከፍትባት ዞሮ የሚያይ ያለ አይመስለኝም
መምሕር ያሬድ በልጅነቴ ያንተን ትምሕርት ሥማር ነው ያደኩት
የሚገርም መረጋጋት እና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ቁጭት የተስተዋለበት ቃለ መጠይቅ ነው ፤ ያሬድ በብዙ መንገድ የተቀየረ ይመስላል፤ በትንሹም ቢሆን ግን ትንሽዬ ትዕቢት ትታያለች ሆኖም ሰዎች ይሄዳሉ ይመጣሉ፡፡ቤተክርስቲያን ግን ለዘለዓለሙ ፀንታ የኖረች ወደ ፊትም የምትኖር ናት ፡፡ ልጁን ግን እድል ተሰጥቶት በተለይ እሱ እንዳለው በስትራቴጅካዊ የቤተክርስቲያኗ ስራዎች ላይ እንዲያግዝ ቢደረግ እና በቤቱ ፀንቶ እንዲኖር ቢደረግ ባይ ነኝ ፡፡
አንደው አግዚያቡሔር የባርከህ ሃይማኖታችንን ቃሎን ቡንጠቡቅ በጣም ጥሩ የሲኖዶሰ አባላት ሰለአውነት ይሆን!!!
ያሬድ መልካም ሰው
አሳይታ ቅ ገብርኤል ከእነ በሪሁን ጋር በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ መምህር ያሬድ መልኬም ሰው ነው
ወደአሳኢታ ከመኪና አዳጋ ተርፈው አገልግሎቱን በሚገባ ያስኬዱ ወንድሞች።
ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ነች ከክብር አትወርድም ያከበራትም ክርስቶስ ነው አንተ አከበርካት አላከበርካት ከፍ ዝቅ አትልም አንተ ራሰክ ከሰውኛ ክብር ያነሰክ ነክ ሲጀመር
አቤት እውቀቀቀቀቀቀት
@@Mihiret855 የታወቀ ነው ለናንተ ቤተክርስቲያን እሳት ነች
ያወራሽው ነገር እንዴት ነው ከዚህኛው ቪዲዮ ጋር ሚገናኘው እህቴ እ🤔
@@ephrem529 ምኑን አዉቃዉ ነዉ ብለህ ነዉ የመጣላትን ነዉ የጻፈችዉኮ
😭😭😭💔💔💔💔 እንደናተ አሪዎስ ነው እነዚን ከአውደ ምረቱ ያባረረው እውነት አሪዎስ ናቹ እነሱን የመተቸት ሞራል የለባቹ ክህነትን ድቁናን ..በስንት መስዋት የተቀባን የተገኘን በወረቀት ደብዳቤ እየገፈፋቹ ከቤቱ አትቆሙም እያላቹ የምታሳድዱት እመኑኝ ይኼ ግሩፕ ትልቅ ከሆነ እናተ ተጠራርጋቹ ትጠፋላቹ እነሱ ቀኖና ትውፊት ..ሳይሻር ሳይለወጥ ቤተ ክርስቲያኗን በምመናን በዝማሬ በውዳሴ ያጥለቀልቋታል ኡኡኡኡኡ ...ይኼንን ማየት መስማት ያማል
መምህር ትንሽ ኢጎ ነገር ከንግግርህ ይታያል ታዋቂም ሽመኛም ብትሆን አዋቂዋን ቤተክርስትያን ተጠግተህ ነው ከልጅነት ጀምሮ እከታተልህ ነበር ዲላ ሀዋሳ እንደውም ስለ መዝሙረ ተዋህዶ ስታነሳ እንባዬ ተናንቆኝ ነበር ስሰማህ የነበረው ግን ኢጎዋ ቀነስ ብታደርግ እላለሁ
አዲሱ ሚካኤል ሀሙስ ሀሙስ በጉጉት እየጠበቅን እንማር ነበር በእውነት ደስ የሚል ጊዜ ነበር
Much love brother Yared! I agreed with everything you said. You stay positive and keep speaking up the truth. I am so happy you are still Tewahido. Don’t be afraid of to share your knowledge in every way possible. Please keep going to the church and pray about our Country. I don’t see what I see on the other guys ( Tehadiso guys).
በስመአብ ያሬዶ የልቤን ነው የተናገርክልኝ ተባረክ
በእውነት ያሬድ እምነት በሌለኝ ሠአት የግቢ ጉባኤ እከታተል ነበር ዲላ የትንሣኤ ቀን የዘመረው መዝሙር ከወገኔ ጋር እዘምራለሁ በደሥታ የዘማሪ ይልማን ከዛሬ ሀያ አመት በፊት አረሣዉም
ተክሌ ግን ምን አስቦ ነው በግድ ፖለቲካ እንዲናገር ሚገፋፋ የተናገረው እኮ ግልፅ ነው ::
God bless you more and more Memihir Yared
እኔ እንደተረዳሁት እነሱ ወጥተሃል አሉኝ እንጂ እኔ ከ ኦርቶዶክስ አልወጣሁም ባልወጣሁበት ነገር ላይ እንዴት ነው ይቅርታ የምጠይቀው ያለ ይመስለኛል።
ደስ የሚል እውነተኛ ተናጋሪ ነው ሆኖም ግን ቤተክርስቲያን አንድን አገልጋይ ለማውገዝ ከተዘረዘሩት ውስጥ ለመወገዝ የሚያበቃው እምነት ወይንም ክህደት ተጠይቀህ በግልፅ ክህደት ካልተገኘብህ ወይንም ካልተገኘበት ወይንም የተናገረው ያስተማረው ክህደት ወይንም ኑፋቄ ከሌለ ሊወገዝ አይገባም ካለ ደግሞ ያስተማረው የተናገረው ተጨባጭ መረጃ ካለ እራሱ ለመወገዝ የሚበቃው እምነት ክህደት ቃሉን ከሰጠ ብቻ ነው የዚህ ልጅ ውግዘትም መገፋትም ምክንያቱ አልገባኝም ያወገዙት ክፍሎች ቀርበው በምን ምክንያቶች እንዳወገዙት ቢያስረዱኝ
ooo what kind of progressive and rational person.
ምርጥ ውይይት ነው መጨረሻህን ያሳ ካልህ: : ግዴልህም ተባብረን ለውጥ ሕ ናምጣ እንዳይቆጨን: :
ድንቅ ውይይት ተክልዬ እጅግ በጣም አመሠግናለሁ ያሬድ አንተም ሸጋ መላሽ ነበርክ
ተክልዬ እግዚሃብሄር ይባርክህ መምህር እባክህ ስለእመቤታችን ትዝታው ዘምሯል አትበል አሁን ኦርቶዶክስን የሚሰድብ የሚያንቋሽሽ ስለታቦቱ የሚዳፈረው እንደትዝታው የሚሳደብ የለም እስቲ የሄደበት ተቋም ስድብ ዘለፉ ነው እንዴ የሚማረው እስቲ ጠይቅልን እሱ አሁን ጸጋው ተገፏል አሁን በንዴት በቅናት እየተቃጠለ ነው የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በጸያፍ ንግግሮች አትገኝም እኔስ እንደሱ አልሳደብም ምክንያቱም ቤተክርስትያኔ ስድብ አላስተማረችኝም አሁንም የጠፋውን አይንህን የተደፈነው ጆሮህን እግዚሃብሄር ይክፈትለት ትዝታው ሚሊዬን ግዜ መወገዝ አለበት።
አንደበትህን እንደቀና ልብህ የቀና የፀና ይሁን!! ከሰማሁት አንፃር ቅንነት አለህ መሸነፍም አለብህ ብዬ አምናለው የምትወደውን ነገር በብዙ ዋጋ ትይዛለህና ሀሳብህን በስራ እንድናይ እመኛለው
እኔም የመሠለኝ ከነበጋሻው ጋር አብሮ የጠፋ ነው።እሁድ ኢቢኤስ ላይ ሲያቀርቡ በጣም ነው እንከታተላቸው የነበረው ተሃድሶ ሆኑ ሲባሉ ግን ዝናቸው ከውስጣችን እንደጉም በኖ ጠፋ። አሁን ያሬድ እንደሚለው ሃሳቡን እግዚአብሔር ይፈፅምለት።
ይሁን ወድሜ ይቅርታ መጠየቅ ትልቅነት ባላደረከውም ቢሆን ጠይቀክ ብትመለስ ደስተኛ ነኝ በጋሻውንም እማምላክ ወደቤቱ እዲመልስልን የዘውትር ፀሎቴነው
ትዝታዉ ጌታን ፈፅሞ ከመጀመሪያ የማያዉቅ ነዉ
ፍቅረ እግዚአብሔሩ ሰሌላዉ ፣
ነዉሩን ገለፀዉ እጀግ ዉርደት፣ ሀጢያቱን ለመሸፈን ሰድብ ገባ ልጀ ከትዳር ዉጪ ሰለወለደ
ያያ ስምህንም አንተንም ወደድኩህ:: አደነቅሁህ::በአገሬ ተስፋ በቆረጥኩበት ወቅት እንዳንተ አይነት ቅን outstanding ወጣቶች ካሉ የሆነ የተስፋ ጭላንጭል አየሁ::
ተክሌ እባክህ ቤተክህነት ገብተህ ጠይቅና እዲመለስ አድርግ እባክህ ማጣት የለብንም እመቤቴ ትርዳን
right
እንዲህ ነው መማር። ዛሬ በቤተክርስቲያን የጠፋው ለአምላክ ከመታመን ይልቅ ለሰው እየታመኑ ክብራን ዝቅ አደረጉ። የእውነት አምላክ ይፍረድ።
ተክልዬ ከማስታወቂያህ ውስጥ የሚገርመኝ እና የሚያስቀኝ "በዋን ትኬት" አማርኛ በአንድ የሚል ቃል አጥታ ቃል ስትዋስ ተገርሞ ከመሳቅ ወዲያ ምን ልል እችላለሁ ሌላው ደግሞ "በምድር ቁጥር" የሰማዩ ቁጥር ሳይናገር መቅረቱ መገረም ብቻ ነው
መምህር ስላየንህ ደስ ብሎናል ደስ የሚል ቆይታ ነበር
ኢንተርቪው ሲያልቅ ቅር አለኝ ዝም ብሎ ሲያወራ ቢውል አይሰለችም አንደበተ ርዕቱ
ይገርማል አንዳንዳንድ ሰው ይሄን ያክል ያውቃል እና ያሰተውላል ሌላው ደሞ
እናመሰግናለን መምህር!
የቤተክርስቲያኗ አስተማሪዎች ከዚህ ቃለ መጠይቅ አስተዋይ ከሆኑ ብዙ ትምህርት ሊወስዱ ይገባል። ምክንያቱም የሰውን ሀይማኖት መንቀፍና መሳደብ ስራቸው ያደረጉ አሉ ለነሱ ትልቅ ትምህርት ነው።
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው❤❤❤❤ኢየሱስ ሐይማኖታችን ነው❤❤❤ኢየሱስ በቂያችን ነው❤❤❤❤ኢየሱስ ብቻውን ሐኪማችን / መድኃኒታችን/ፈውሳችን ነው❤❤❤
ምን ጠራህ እዛው ቁጭ በል
ደስ የሚል እንግዳ ነዉ የጋበዝከዉ ተክሌ
ወንድም ያረድ ያንተ ችግር ከንግግርህ እንደምረዳው በተክርሰቲያንን የገቢ ምንጭ ካደረጉ አካላት ጋር ማበርህና መድረክዋን የሁከትና የብጥብጥ ተባባሪ መሆንህ ይመስለኛል?
Memihire Again and again Tebarek
እባካችሁ አትሳደቡ ስድብ የአዉሬ መገለጫ ነው ።ሠላም ዋሉ
በመጀመሪያ የያዛችሁት ነገር ገፆታ ግንባታ ነው ከሁለታችሁም ጀርባ ደግሞ ሴትየዋ አለች እንደበፊቱ ቤተ ክህነት ገብታ መፈትፈት አትችልም ሰለዚህ የያዛችሁት ገፆታ ግንባታ ነዉ ቢዝነሱ ስለተበላሸበት ወደ ቤተክህነት ተጠግቶ እንደበፊቱ ለመስራት ነው ያውም ከነክህደትህ እየተመጻደክ እንጀራዋን ለመብላት ነው ጋዜጠኛው የሴትየዋ የግል ጋዜጠኛ አንተደሞ ከድሮም ጀምሮ የግል አማካሪዋ ቤተክርስቲያኗ ብዙ ሊቃውንት አላት ያንተ እርዳታ አያስፈልጋትም መጀመሪያ መች አወካትና የት ተማርክና ቃላት በማሳመር (በመደስኮር) አየደለም ይሄ ሀይማኖት ነው ቢዝነስ(ፓለቲካ) አይደለም ጋዜጤኛው ትችላለህ የሴትየዋ ጥገኛ አትሁን።
እግዚአብሔር ይመስገን እጅግ በጣም ጥሩ ምሁር ነው በተለይ በቤተክርስቲያን ትምህርትም በአለማዊ እውቀቱም ደስ የሚል የተሟል ሰው።
እኔ እምመክርህ መምህር ያሬድ በሙያህ ስራህን ቀጥል ቤተክርስቲያንን ግን እንዲህ ለነብስህ ለሰዎችም በገኘህው አጋጣሚ አስተምር እንጂ መልሰህ አትቀላቀል አሁን ያለህን ሰላምህን ያሳጡሃል ።
ፒ.ኤ.ች.ዲ ህን ያዝ !!! በርታ እግዚአብሔር ይመስገን ቤተክርስቲያን አባቶች ሆነ አገልጋዮች ግን በዘረፋ የተገኘ ገንዘብ ንብረት የምዕመናን ሀብት የቤተክርስቲያን ሀብት ሊመዘገብ ሊመረመር ከተቻለ ተጣርቶ ሊመለስ ይገባል።
ቤተክርስቲያን ለሀቀኛ በአሁን ሰአት ከባድ ነው።
አስመሳይ አባቶች፣አገልጋዮች ፣መምህራን ፣ቀሳውስት ፣ዲያቆናት ወ.ዘ.ተ...
በሌቦች፣በዘረኞች፣በፖለቲከኞች፣በአጭበርባሪዎች ተከባለች እግዚአብሔር ፍርድ ቀን እንዲሁም እንዲህ እንደሰሞኑ እያጋለጠ ያውጣቸው በአለም አደባባይ። እርስበዕርስ ይገላለጡ ይጠራል።
በትክክል ጥሩ ሀሳብ አንስተሃል