🔴 👉 ለኢትዮጵያዉያን በሙሉ ከባንኮች ብድር ማግኘት የምትፈልጉ ይሄንን ይሄንን ማየት አለባችሁ Addis Ababa Ethiopia

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 6 фев 2025
  • የባንኮች የብድር መመሪያና ፖለሲ ከባንክ ባንክ የተለያየ እንደመሆኑ መጠን፣ የብድር አሰጣጥ ሂደቱም በተወሰነ መልኩ ከተቋም ተቋም የተለያየ ነው፡፡ ነገር ግን ባንኮች የብድር ማመልከቻ ከመቀበል ጀምሮ ደንበኛ ወይም ተበዳሪ የሚፈልገውን የብድር መጠን ለመፍቀድ እንዲሟላ የሚፈልጉት፣ የጋራ መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም መስፈርቶች አሉ፡፡ አነዚህን መስፈርቶችና ጉዳዮች በሚገባ መገንዘብና አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በሂደት ማሟላት የብድር ጥያቄ ውድቅ እንዳይሆን ከማገዝ ባለፈ፣ የሚፈለገውን የብድር መጠን ሳይቀናነስ ከባንኮች የማግኘት ዕድልን ያሰፋል፡፡
    የብድር ጥያቄው ለአዲስ ፕሮጀክት ወይም ለነባር ፕሮጀክት ማስፋፊያ በሚሆንበት ወቅት፣ ተበዳሪው ከሚያቀርበው የአዋጭነት ዝርዝር ጥናት በመነሳት ለሌሎች ብድሮች ከሚደረገው የመመዘኛ ትንተና በተለየ ሁኔታ ስለ ገበያ ሁኔታ፣ በፍላጎትና በአቅርቦት መካከል ስላለው ክፍተት፣ ስለ ዘርፉ የገበያ ፉክክር፣ ስለ ድርጅታዊ መዋቅሩና አስተዳደሩ፣ ስለ ቴክኒካል ጉዳዮች፣ ስለ ጥሬ ዕቃ አቅርቦት መኖር፣ ስለ ምርቱ ወጪና ዋጋ፣ ስለ ህጋዊነቱና ትርፋማነቱ፣ በአጠቃላይ ስለ ንግዱ አዋጭነትና ቀጣይነት ሠፊና ጥልቅ ጥናት ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም እንዲቀርቡ የሚፈለጉት ሰነዶች እንዲሁም እንዲሟሉ የሚጠበቁት መስፈርቶች ለባንኮች የብድር ትንተና ግብዓትነት የሚያገለግሉ ወይም የሚወሉ ናቸው፡፡
    ለዛሬ ንግድ ባንኮች በብድር አሠጣጥ ሂደት በመሠረታዊ ደረጃ ትኩረት የሚያደርጉበትን ጉዳዮች፣ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሁም የሚከተሉትን የብድር አሠጣጥ ሂደትን ብቻ ለመጠቃቀስ እንሞክራለን፡፡
    🔴 👉 ለኢትዮጵያዉያን በሙሉ ከባንኮች ብድር ማግኘት የምትፈልጉ ይሄንን ይሄንን ማየት አለባችሁ Addis Ababa Ethiopia

Комментарии • 37