“ኢትዮጵያ የሠሩላትን የምታመሰግነው በጥይት ነው“ አቶ አምደ ብርሃን አካለ ወርቅ ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓም የ60ዎቹ ግድያ 50ኛ ዓመት ማስታወሻ0708

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 29 ноя 2024

Комментарии • 125

  • @YonasElias-rp6gh
    @YonasElias-rp6gh 7 дней назад +26

    የኢትዮጵያ የመከራ ጊዜ የጀመረበት ቀን 😥😥😥

  • @7kilo853
    @7kilo853 6 дней назад +38

    ዛሬም ደርግና መንግስቱን የሚናፍቅ ትዉልድ መፈጠሩ ይገርማል።ታሪክ በሚገባ መነገር መሰነድ አለበት።ተባሪኪ መስኪ!!!

    • @EmmaPaul-n9q
      @EmmaPaul-n9q 3 дня назад +2

      ሞን ይነፈቃሉ ሁሉም ህዝብን የሚጨረሱ ገዳይ መንግስት ናቸው አሰከ አሁን ድረስ።

    • @gemirum2608
      @gemirum2608 11 часов назад

      ደርግ ቢያንስ ሰዎችን በዘር ለይቶ አስፀያፊ ስድብ እየሰደበ አይገድልም፤አሁን በእየስርቤቱ በማንነታቸው ምክንያት አስፀያፊ ስድብ እየተሰደቡ ይገደላሉ፤ሚሊዮኖች በማንነታቸው ምክንያት እየተጨፈጨፍ የሚሞቱና የሚፈናቀሉ ማንም አልደረሰላቸው❗

    • @antewifireden2134
      @antewifireden2134 3 часа назад

      በእኔ አመለካከት ግን እየባሰ እንጂ እየተሻለ የመጣ የስርዓት ለውጥ የለም ተስፋ የማደርገው የዚህች የቃል ኪዳን ሀገር የምፅዓቷ ቀን እሩቅ ስለማይሆን በቃ ብሏት ሰላምዋን አግኝታ እንደ ሩዋንዳ የመላው ዓለማት ዓይኖች የሚያርፋባት ትሆናለች ።🙏​@@gemirum2608

  • @misganabere6115
    @misganabere6115 7 дней назад +25

    ያንን የመሰለ ትውልድ ካጣን በሗላ ነው ሐገራችን ቁልቁለቷ የጀመረው so sad
    መስኪዬ እግዚአብሔር ይባርክሽ

  • @derejejeba7140
    @derejejeba7140 3 дня назад +9

    የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ የገጠሙት በጦርነት እልቂት፣ በእርስ በርስ የፍጅት (ቀይና ነጭ ሽብር፣ የጎሣ ፍጅት)፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ ስደት፣ ድህነት ሁሉ በ60 ዎቹ የግፍ ግድያ በኋላ ነው። እግዚአብሔር አምላክ በዚህ እጅግ አዝኗል። ይህንን በማያውቁ ሶሥት ትውልዶች ላይ እስካሁን የአምላክ የቁጣ ፍርድ እየሆነ ነው። በጌታ አምላክ ፊት በምድሪቱ ላይ ስለተፈፀሙት በደሎች ሁሉ ኢትዮጵያውን ሁሉ በመፀፀት የአምላክን ምህረት ለማግኘት ንሰሃ መግባት ይገባናል። ጌታ አምላክ መሃሪና ይቅር ባይ ነውና። ምህረቱን

  • @Peacefulness_3467
    @Peacefulness_3467 7 дней назад +15

    ዋው በደርግ እና በኃይለ ስላሴ ዘመን የነበሩ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁነቶችን ለህዝብ ለማቅረብ የምታደርጊው ጥረት ለኛ ታሪኩ ላልተገለጠልን ትምህርት ለአንች ደግሞ እንደ ሚዲያ በረከትና አክብሮት የምታገኝበት ጉዳይ ነውና በርች። እናመሰግናለን

  • @yohannesejigayew4616
    @yohannesejigayew4616 6 дней назад +12

    መስኪ በርቺ ታሪካችንን የኋሊት መመልከት የውደፊቱን ለማስተካከል ጠቃሚ ይመስለኛል

  • @fishatsiontadesse1868
    @fishatsiontadesse1868 3 дня назад +4

    መስከረም እግዚአብሔር ይባርክሽ በጣም እናመስግናለን እውነታ መስማት እንዴት ደስ ያላል እዲህ ዕይነት አንደበተ ትክክል የሆኑ ትልቅ አባት ከስሜት የራቀ ንግግር እንደት መታደልነው በ81 ዕመት ይሄን ያህል ያስታዋለ ንግግር እንዴት ደስ ይላል !!!! እግዚአብሔር ይስጥልን !!!!!

  • @seyoumt9877
    @seyoumt9877 7 дней назад +11

    በርቱ ጥሩ ፕሮግራም ነው የምታካሂዱት ታሪክን ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ትልቅ ሃላፊነትን ይጠይቃልና !!!

  • @dawittube1786
    @dawittube1786 2 дня назад +1

    አባታችን አይዞት በዚህ እጅግ ክፉ የአረመኔ ድርጊት ልቡ ያልተሰበረ ኢትዮጵያዊ የለም።

  • @meseretbitsu9445
    @meseretbitsu9445 7 дней назад +18

    አክሊሉ ሀብተወልድን ሚያክል ዲፕሎማት ሀገራቭን ኖሯት አያውቅም፡ ለወደፊትም አይፈጠርም። የሳቸው ወንድም ልጅ በመሆንዎ ኩራት ሊሰማቸው ይገባል።

    • @SelamawitArega-c6z
      @SelamawitArega-c6z 5 дней назад +1

      እዉነት ነዉ።እኔ ስለእሳቸዉ ደራሲ መኮንን አብርሃ፡የፃፉትን፡መፅሃፍ፡አንብቤ፡ነዉ፡ያወቅኩት።በተጨማሪ፡እናቴ፣አያቴ፡ታሪካቸዉን፡ነግረዉኛል፡በተደጋጋሚ።

  • @lyewferede2797
    @lyewferede2797 6 дней назад +6

    መስኪ ታሪኩን አንብቤዋለሁ ያንጊዜ ነው ሃገራችን ወደ ኋላ የመለሷት እነዚያ ምጡቅ በሳል እውቀት ያላቸው አባቶታችን ሃገራችንን አገልግለዋት ኖሮ ቢሆን የት ትደርስ ነበር የሃገራችን የታሪክ ጠባስ ብለው ማጋነን አይሆንም

  • @ajjaususu5704
    @ajjaususu5704 6 дней назад +2

    እኔም ይህንን ግድያ የሰማሁት እሁድ ጠዋት ሻይ ቤት ቁርስ ልበላ ቁጭ ሰል ዘግናኙን ግድያ ሰማሁ አባቴ በአርበኝነት መብት ለማሰጠበቅ አዲስ አበባ ሄደው አክሊሉ ሰበሰበንና ምነው የጎድጓዲትን በግ መስላችሁ መጣችሁ አሉን እያለ ሁል ጊዜ ይነግረኝ ነበረ ሲገደሉ አክሊሉ አብተወልድ ሲባል በጣም ደነገጥኩ ነፍስ ይማር

  • @yonasatle5319
    @yonasatle5319 5 дней назад +2

    በጣም እናመሰግናለን ለዚህ ግሩም የሆነ ቃለ ምልልስ ። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቁጣ በግፈኞች ላይ ትመጣለች ይላል ። ኢትዮጵያ ያኔ በተሠራው ግፍ ምከንያት እስካሁን ዋጋ ትከፍላለች ። እርሱ ወደ ልቦናችን ይመልሰን ፣ ሰውን በሰውነቱ የምናከበር ሕዝቦች ያድሮገን ፤ ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞ ክብሯ ፣ ወደ እኩልነት ፣ ወደ መልካም አስተዳደር ጉዳና ላይ ያቁማት ። ለመላው አፍሪካ ነፃነት የተጫወተችውን ሚና በበለጠ አሳድጋ ከእራሷ አልፋ አፍሪካን አንድ ታድርግ አሜን ። 🙏🇪🇹🙏

  • @bashawabebayehu-hy8ng
    @bashawabebayehu-hy8ng 6 дней назад +3

    ድንቅ ሐሳብ ነው የምታቀርቢያቸው በርቱ

  • @selamdesta8678
    @selamdesta8678 3 дня назад +2

    መስከረም ድንቅ ዝግጅት
    From Atlanta, Georgia, USA

  • @assegedbezabih5776
    @assegedbezabih5776 3 дня назад +2

    ደም የጠማው እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ስለ ሀጥያታች ያመጣው መቅሰፍት መንግሥቱ ሀይለማርያም ሌሎችን ገፋፍቶ፣ በኢትዮጵያ ባለውለታዎች፣ በደም ጎርፍ ማጥለቅለቁን ጀምሮ ኢትዮጵያን ታሪክ አልባና ተረካቢ ትውልድ አልባ አደርጎ እንድትበታተን አደረገረጋት። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ምህረቱን ይላክላት።

  • @biyadgieaschale5219
    @biyadgieaschale5219 7 дней назад +6

    ልብ ሰባሪ ታሪክ ነው። እንደ አለመታደል ሁኖ የሁሉም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስንት ከሰሩ በኃላ ማመስገንና መሸኘት ሲገባን ሁልጊዜ መጨረሻችን ይህ መሆኑ ያሳዝናል።

  • @dulahulukegna3746
    @dulahulukegna3746 19 часов назад

    አቶ አምደ ብርሃን በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መድሃኒዓለም ቁምስና በአይን አውቃቸዋል እጅግ የተከበሩ ጨዋ ሲበዛ ስርአት የተላበሱ ደስ የሚሉ ሰው ናቸው እግዚአብሔር እድሜ ከጤናና ፍፁም መፅናናትን ይስጥልን እንወዶታለን

  • @selamaraya8179
    @selamaraya8179 4 дня назад +2

    በትክክል * አባታችን አይዞኝ * እግዘብሔርን ያያል *

  • @meseretbitsu9445
    @meseretbitsu9445 7 дней назад +7

    ከባድ እንግዳ ዋው መስኪ።

  • @wondwossentiruneh4196
    @wondwossentiruneh4196 3 дня назад +1

    አቶ አምዴ ረጂም እድሜ እመኝሎታለሁ።አንድ ቀን በመፅፍ ትውልዱን እንደሚያስተምሩ ተስፋ አረጋለሁ !!

  • @habtamualemayhu1528
    @habtamualemayhu1528 6 дней назад +4

    መስኪ ጥሩ ስራ ነው። በርቺ። እግዚአብሔር ይርዳሽ።

  • @Edi-d7k
    @Edi-d7k 7 дней назад +4

    እውነት በጣም ያማል😢እንደ ዜጋ፣እንደህዝብ
    በአባቶቻችን እና በአጎቶቻችን የደረሰው ግፍ ያማል 😢 እሱ ግን አገሪቱን በደም መአበል አጥለቅልቆ ከአገር ፈረጠጠ። መቼም ከልባችን የማይጠፋ ሀዘን ነው። የግፍ ግፍ ነው!ወንበዴዎችና አረመኔዎች ውዶቻችንን በግፍ ነጠቁን😢 የአገራችንን አምባሳደሮች፣ እገር ወዳዶች እንቁ ሚንስትሮች፣ የአገራችን እንቁ አርበኞች። አባቴ ስለደረሰብዎት ስብራትና ከልብ የማይጠፋ ሀዘን የሁላችንም የልብ ቁስል ነውና በጣም አዝናለሁ። እነሱ ለአገራቸው መልካም የሰሩ ስለሆኑ ፈጣሪ የሰማይ ቤት እረፍትን ይስጣቸዋል። ያማል😢 ያቆስላል😢መቼም መቼም እነሱን የሚተካ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ዳግም አይኖርም።

  • @yemedanken7539
    @yemedanken7539 3 дня назад +1

    ብዙ ጠያቂዎች አይቻለሁ በጣም ተረጋግ የምትጠይቅ ጠያቂ ናት ተባረኪ

  • @zuriashwork6030
    @zuriashwork6030 День назад

    እኔ አባቴን ባጣሁበት ቀን ሳለቅስ እንደርዎ አታልቅሱ ስንባል አብረዉ ይግደሉኝ ብየ በሚገባ እየጮኩ ነበር ግን ያዬኝ ወታደሮች መንገድ ላይ አቁመዉ አይተዉ ተዋት ነዉ ያሉት ግን ያ ቀን አሁንም ለኔ ትኩስ ነዉ ለምን አስታሞ መቅበርን እድል ስላላገኘሁ ሁልጊዜ አዲስ የማይረሳ ሰቆቃ በህይወቴ ላ አሳርፏል አባቴ ክብሬና ማረጌ ነበር ያንን ለኔና ለ ልጆቸ አሳጥቶናል ምን ግዜም የማይረሳ የእግር እሳት ነዉ እግዚአብሔር በገነት ያኑርልኝ የዘወትር ፀሎቴ ነዉ እርሰዎም ላደረጉልን የታሪክ አደራ እኔና መላ ቤተሰቤ እናመሰግነዎታለን።

  • @ayele6173
    @ayele6173 3 дня назад +2

    የሳዝናአል ኢትዮዽያ የዉድቀት ታሪክ የጀመረበት

  • @MASRESHAMENBERU
    @MASRESHAMENBERU 7 дней назад +4

    መስኪ እናመሰግናለን!! አሁን ላለንበት ውድቀት መነሻውን ስላሳወቅሽን!! እንዲህ የተረሱ ታሪኮች ብናውቃቸው ምነኛ በታደልን!!

  • @abelzeleke8424
    @abelzeleke8424 7 дней назад +3

    መስኪ በርቼልኝ ክፍል ሁለቱ አታቆይብን🙏🏾

  • @seyoum917
    @seyoum917 7 дней назад +4

    ልዑል እግዚአብሔር ይስጥልን መስኪ።
    እግዚአብሔር ያያል አሉ አዎን ያያል ይሰማል
    አይን የፈጠረ አያያምን ጆሮንስ የተከለ አይሰማምንም ?

  • @yeshiwasewshiferaw7726
    @yeshiwasewshiferaw7726 6 дней назад +3

    የኢትዮጵያ መከራ የጀመረበት!!

  • @ethortho2409
    @ethortho2409 3 дня назад +2

    መስኪ እናመሰግናለን:: አሁንምእዳችን እየቀጠለ ነው:: ግፍ አለ እግዚአብሔር ያያል ይሰማል ልብ ያለውልብ ይበል!

  • @uppertech6672
    @uppertech6672 5 дней назад +3

    አስተምረን ተነሱብን፣
    አስተምረን ጨፈጨፉን፣
    አስተምረን እረሸኑን፣
    አስተምረን አቃጠሉን፣
    አስተምረን አሳደዱን፣

  • @antewifireden2134
    @antewifireden2134 3 часа назад

    ይህን ቻናል ለመቀላቀል የቻልኩት በዚህ ዝግጅት ምከንያት ሲሆን ጋሽ አምዴን አምላክ ረጅም ዕድሜ እና ጤናውን ከነመላው ቤተሰቡ አብዝቶ ይስጥልኝ ።ጋዜጠኛ መስኪ አልቀሰሽ ስላስለቀሽኝ እውነተኛ ሰብዓዊነትን የተላበስሽ ሆድ አደር ጋዜጠኛ አለመሆንሽን በመረዳት ልባዊ ምስጋናዬ ከነመላው የዝግጅት አባላቱ ይድረስሽ።🙏

  • @zenaprintingpress6525
    @zenaprintingpress6525 5 дней назад +5

    ወደኅላ የሔድንበት ድርጊት !

  • @dulahulukegna3746
    @dulahulukegna3746 19 часов назад

    መስኪ ድምፅሽ እጅግ ልዩ ነው በጣም ደስ የምትዪ ስርአት ያለሽ የተረጋጋሽ ጎበዝ ጥሩ አንባቢ ትመስይኛለሽ በርቺ እህቴ እናመሰግናለን

  • @user-ow6vw7ov7e
    @user-ow6vw7ov7e 3 дня назад +1

    ዝግጅትሽ የማይጠገብና የማይሰለች ነው:: እግዚአብሔር ይርዳሽ::

  • @dawittube1786
    @dawittube1786 2 дня назад +1

    እኔ እንደ አንድ የሰው ልጅም ኢትዮጵያዊም ደርግን አምርሬ የምጠላው የእነዚህ ሰዎችን ግድያ ስሰማ ነው።

  • @MeseD-d1w
    @MeseD-d1w 3 дня назад +2

    ያማል ያማል ውይ የአሁኑ ይባስ በየቀኑ በግፍ የሚገደለው በእጥፍ ጨምራል፡፡

  • @SelamawitArega-c6z
    @SelamawitArega-c6z 5 дней назад +1

    ያማል፡በጣም።

  • @haregewainfisseha5971
    @haregewainfisseha5971 6 дней назад +1

    We're in the worst situation right now. They don't learn from the past. It's great to have this kind of discussion so that people know the truth about their country. The Almighty God bless our country and people!!!

  • @dawittube1786
    @dawittube1786 2 дня назад

    አሁንም የአብይ አህመድ ዘመን የጨለማ ጊዜ ታሪክ ነው።ሚሊዮኖችን ያፈናቀለ: ሚሊዮኖችን የገደለ ስርዓት ነው።

  • @marzeneb1835
    @marzeneb1835 5 дней назад +2

    እውነት ይሄ ሁሉ ሌላ ሳይሆን በምቀኝነት በተነሳሳ እርኩስ መንፈስ በሰው ልጅ አይምሮ ሊታሰብ የማይችል አረመኔነት፤የተፈጁት እነዚህ ወገኖቻችንን የመሰለ ሁለተኛም አይኖርም፤ ይሄ ሐዘን ብቻ ሳይሆን፤ከአንጀታችን የማይጠፋ እሳተ ገሞራ የሆነ ረመጥ ጭሮ እያረርን እንድንኖር አድርጎናል፤የዛ ሐጢአት ይሄው ለ50 አመት ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል፤

  • @BekeleWolde-x9o
    @BekeleWolde-x9o 2 дня назад

    ተባረኪ! ቀጥይበት፣ አይዞሽ!!!

  • @adambosat238
    @adambosat238 День назад

    የተከበሩ፣ አቶ፣ አምደ፣ ብረሃን፣ የእርሶ፣ አባት፣ እና፣ አጎት፣ ብቻ፣ አይደለ፣ የብዙ፣ ኢትዮጵያዊያን ፣ አባቶች፣ ነበሩ፣ አሁንም፣ ናቸው፣ ዘላለም፣ በውስጣችን ይኖራሉ።

  • @ephramabebe2323
    @ephramabebe2323 19 часов назад +1

    ምንድን ነው ፀጉርሽ ?

  • @LoveAndPeace2424
    @LoveAndPeace2424 3 дня назад +3

    ከሁሉም ደግሞ የሚያበሳጨው መንግሥቱ ይሄን አረመኒያዊ ድርጊቱን አምኖ ይቅርታ አለመጠየቁ😡

  • @berhan4301
    @berhan4301 День назад

    መንግስቱ የተባለ አረመኔ ዛሬም በህይወት መኖሩ ሁሌም ይገርመኛል። ዛሬም አዲሱ ኮነኔል መንግስቱ ህዝብን እየረሸነ ነው ግን ውድቀታችን የጀመረው የዛሬ 50 አመት ነው።

  • @Mekresilassie2Asfaw
    @Mekresilassie2Asfaw 8 часов назад

    የኔ እህት ከማለት ይልቅ የኔ ልጅ ማለት ነበረባቸው።

  • @MamiBaba-g1s
    @MamiBaba-g1s 6 дней назад +1

    መስኪየ በርች❤

  • @fredpolo1234
    @fredpolo1234 2 дня назад

    ነፍሳቸን ይማረው!

  • @frezermekonnen2172
    @frezermekonnen2172 4 дня назад +1

    በጣም እሚያም ነው 😢😢

  • @sitotaw9570
    @sitotaw9570 23 часа назад

    እንደኔ ግምት ጃንሆይ በማስተዋል ግዜያቸው ሳሉ ስልጣናቸውን ለተገቢ ሰው አስረክበው ቢሆን ኖሮ እሳቸውም አጉል ሞት ከመሞት፣ ሀገራችንም ከዚያ በኋላ ከወረደባት መዐት (ያሁኑን ሰው በላ ስርዐት ጨምሮ) የቁልቁለት ጉዞው ቢያንስ ከዚህ መከራ የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ ያመለጠ ዕድል፡፡

  • @uppertech6672
    @uppertech6672 5 дней назад +2

    ሀገራቸውን ከምንም አንስተው እዚህ ያደረሱ ሌንጮ ለታን፣ መለስን፣ ይሳያስን ያስተማሩ። ዛሬ እንደሚባለው ሳይሆን ትምህርት ቤት የከፈቱ፣ ሃኪም ቤት የከፈቱ፣ ዩኒቨርስቲ የከፈቱ፣ ባዙ የሰሩ ግን በግፍ የተገደሉ።

  • @genetseyoum5225
    @genetseyoum5225 3 дня назад +1

    ይህን ድርጊት የፈፀሙ የሞቱም አሉ በህይወት ያሉ እየኖሩ ነው እውነት ግን ምን አይነት ጊዜ ነበር ያሳለፍነው በዚ ፅህ አረመንያዊ ድርጊት የፈፀማችሁ በህይወት ካላችሁ ያልሰማነው ወንጀል ካለ ወጥታችሁ ተናዘዙ ልጆቻችሁ እንዴት ቆመው ይሄዱ ይሆን??

  • @yidnekachewhussen3734
    @yidnekachewhussen3734 2 дня назад

    እውነት ሲገለጥ !!!

  • @haimmetyaregal
    @haimmetyaregal 6 дней назад +2

    ብዙ መናገር የሚጠበቅባቸው፤ ብዙ ማለት ያለባቸው… ነገር ግን በማድበስበስ ለማለፍ የሚፈልጉ… መስኪ ካንቺ የጎደለ የለም።

  • @eskinderteshome9681
    @eskinderteshome9681 День назад

    No justice no peace

  • @mekonnen2384
    @mekonnen2384 3 дня назад

    ፓለቲከኞች ብዙወቹ በሚሰጥር ሲሰሩት እና ማን ከጀርባቸው እንደነበር ያለመናገር ችግር አለባቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ግን አይደለም እነሱ ሳይወለዱ አያቶቻቸው እንኳ ላቅመ አዳም አልደረሱም ይሁንና ዋና የማይካድ ወደፊትም የሚኖር ጠላት ደጋፊያቸው የነበረው " ግብፅ" እንደነበረች አይረሱም አትርሱ

  • @gakitdebubu7655
    @gakitdebubu7655 6 дней назад +4

    አሁን ይህን አዙሪት ለመቀየር ለሚደረገው ጥረት ለምን ድጋፍ አንሰጥም??? ቢያንስ ከስልጣን የሚወርድ ባለስልጣን በሠላም እየተሸኘ ነው!!

    • @Hope-nh6ho
      @Hope-nh6ho 2 дня назад

      Yesenetue deme newe Yefesesewe?Seare, ere senetue hezebe kehezebe yemeyabalaee” Beletegena “ ayedrleme. Deme yemeteta? Egezabehair lebona yesetehe!

  • @AsefaChekol-ce3es
    @AsefaChekol-ce3es 7 дней назад +3

    Anich Dink set....Kal yelegnim

  • @negashassefa8058
    @negashassefa8058 15 часов назад

    እጅግ የኢትዮጵያ ጥቁር ታሪክ

  • @bezihalemkebede5109
    @bezihalemkebede5109 6 дней назад +1

    ሁሉም የዘራውን ያጭዳል እንደሚባለው ጀግናውን አርበኛ በላይ ዘለቀን በግፍ ያስገደሉት ናቸው እነሱም በደርግ በግፍ የተገደሉት :: And በወሎ ረሀብ ላይ ምን ይላሉ ተብለው ሲጠየቁ : እኔ ያኔ ገና የ31 አመት ልጅ ነኝ ብለው አደበስብሰው ያለፏትም አልተመቸኝም....አንድ ማይረሳ ሀቅ ግን የአማራ ህዝብ ስብራት የጀመረው የጃንሆይ ዘመን ካበቃ በሗላ ነው:: አማራው ተራራው ዳግም ወደ ስልጣን ሲመጣ ያኔ እርስወም ፍትህ ያገኛሉ...

    • @uppertech6672
      @uppertech6672 5 дней назад

      አንተ ደደብ ሰፈርተኛ አሀያ ነህ፣ አክሊሉ ለሀገሩ ሰርቶ ሳይወልድ እንኳ በግፍ የተገደለ እንጂ አንተ ከምታነሳው ታሪክ ጋር ምንም ግንኙንት አልነበረውም። አብዛኞቹ አርበኛ የነበሩ ጣልያንን አንተ ከምትለው ሰው ጋር ሆነው ብዙ ስራ ሰርተው አንተን አፍህን እንድትከት ያበቕ ነበሩ። እንዳተ ያል በግፍ የሚፈርድ ነው በጅምላ ውገኖቻችንን የጨፈጨፋቸው። አንተ ደደብ ሰፈርተኛ አንተ ስልጣን ብትይዝ ብዙ ሰው እንደምትገድል ግን እርግጠኛ ነን። በላይም ለሀገሩ ለፍቶ በግፍ መገደሉን ግን ማንም አይክድም። ያደደብ ጨፍጫፊ ሰይጣን መንግስቱ ግን ሲኦል ነው ቤቱ። አማራም በግፍ የጨፈጨፍፉትን ለፍርድ ያበቃል።

  • @hirutehailu4905
    @hirutehailu4905 6 дней назад +3

    ፍርድ ለ60 ዎችው አይቀርም

  • @fieshatesfamariam4882
    @fieshatesfamariam4882 3 дня назад +1

    የንጉሱም ስርአት በወሎ ድርቅ ወይም ረሀብ መከሰት ሲሆን ደርግም ወጣቱንና ጄኔራሎቹን በመፍጀት

  • @dawittube1786
    @dawittube1786 День назад

    ዛሬም ርሃብ ሚሊዮን ኢትዮጵያን እያረገፈ ነው።

  • @hiriyakos
    @hiriyakos 7 дней назад +3

    berchi berchi

  • @NebiyatZeray
    @NebiyatZeray 2 дня назад

    አሁንም ተማሪዎች ለምን ዩኒቨርስቲ እንዳይገቡ እንደሚደረግ በደንብ ገባኝ።

  • @minewyeletabeje4656
    @minewyeletabeje4656 3 дня назад

    ጋሼ አምዴ ስለዛ ወቅት ያወሩት ነገር ጥሩ ነበር። ግን የውጭ ጠላቶች እንዳሉ ሆኖ በኢትዮጵያ የነበረው ስርዓተ ማህበር ሁኔታውን ለመቀየር ምንም ርምጃ የወሰደ አልነበረም እላለሁ። እርሶ የሚያወሩት በግለሰብ ደረጃ ስለሆነ ግራ ገባኝ።

  • @eskinderteshome9681
    @eskinderteshome9681 День назад

    What a cruel time

  • @Mulugeta29
    @Mulugeta29 5 дней назад +1

    ድንቁርና ከባድ ነው!
    ጨካኝ ያደርጋል!

  • @Japy-dj6uq
    @Japy-dj6uq 7 дней назад +1

    ❤🙏🙏🙏⛪

  • @mili1621
    @mili1621 2 дня назад

    ሆሆሆሆ የብልፅግና ምን ሊባል ነው????

  • @agerenewu8397
    @agerenewu8397 3 дня назад +1

    አይ ኢትዮጵያ ትውልድ አይብቀልብሽ የተባለባት አገር እነዚህ ደግሞ የባሱ አረመኔዎች ጭራሽ በማንነቱ መግደል ጀመሩ ይህ ከጥንት ጀምሮ ያለው ማንነት ጥላቻ አሁን ያለው የአማራ ምሁራን ግድያ በጣሊያንም ሆነ በደርግ ስርአት ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ያሳያል

  • @megnotdemeka1436
    @megnotdemeka1436 5 дней назад

    🙏🙏🙏🙏

  • @alemayehutafess7777
    @alemayehutafess7777 3 дня назад

    ❤❤❤❤

  • @abugida794
    @abugida794 5 дней назад +2

    ዛሬስ በግብረ ሰዶሙ አብይ አህመድ
    ስንት ስልሳዎች(60) ረሽኖ ይሆን

  • @gezegeta923
    @gezegeta923 2 дня назад

    Who must be the one to write the details of this honorable Prime Minister and his family? The details of the prime minister biography must be written!!!!! The details of the minister brothers must be written. Still we owe the PM and his brothers their biography. The people can fund it. But, we need a reliable historian to right the book. Who must write the book? The people must right the book. The family biography must be written.

  • @agerenewu8397
    @agerenewu8397 3 дня назад +1

    ያሳዝናል ያን የክፉ ዘመን አሳልፈን ዛሬ ደግሞ በቁም የሚያርድ ቤት የሚያፈርስ ትውልድ የሚያመክን ሃይማኖትን የሚያጠፋ ኢትዮጵያዊንትን የሚጠየፍ ዘረኝ መንግስት ላይ ኢትዮጵያና ህዝቧ ወድቋል የነሱም ታሪክ እንደዚህ እንደሚፃፍ ያውቁ ይሆን ❓❓
    ለነገሩ ሆዳቸው ነው ታሪካቸው‼️

  • @AntiochSpritualProgramme
    @AntiochSpritualProgramme День назад

    ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው (መስኪ) አንቺ ድንቅና ጎበዝ ጋዜጠኛ ነሽ፡፡ አሁን ወደ ትክክለኛ ቦታሽ ተመለስሽ!! ላለፉት ዓመታት በማኅበረ ጻድቃን ቲቪ ውስጥ ተደብቀሽ ይኼን የመሰለ እምቅ ችሎታሽን ነፍገሽን ነበር፡፡ እኔ አንቺን ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጀምሮ ነው ስከታተልሽ የነበረው፤ የታላቁ መሪን መለስ ዜናዊን ሕልፈት ተከትሎ ታቀርቢያቸው የነበሩ ዶክመንተሪዎች ልዩና የማይጠገቡ ነበሩ፡፡ እባክሽ የአንቺ ትክክለኛ ቦታ ይኼ ነው፡፡ ወደ ቲቪ ፕሮግራም መመለስ አለብሽ!!
    የዚያን የስመ-ጥሩ ጀግና በላይ ዘለቀ ቤተሰቦችንም አፈላልገሽ ጠይቂልን! የመለስን ቤተሰቦች ትግራይ ያሉትን አሁን ያሉበትንም ሁኔታ ዘግቢልን!

  • @BamlakTselot-
    @BamlakTselot- 2 дня назад

    ይህንን ሁሉ ግፍ ፈፅመው ተኝተው ማደራቸው ምን አይነት ሂሊና ቢኖራቸው ነው!!!
    በተለይ እንደ ጨካኙ መንግስቱ ሀይለማርያም እና ግብረ አበሮቹ!!! ጠቅላላ ስልጣን ላይ የሚቀመጡ ፖሎቲከኞች በመግደል ፣በማሰር፣ በማሰቃየት የሚደሰቱት?

  • @SAMdave183
    @SAMdave183 22 часа назад

    ኢሀዴግ የሰምእታቱን አፅም ከተጣለበት አውጥቶ ከቤተሰብ ጋ በክብር እንዲቀበሩ ማድረጉ ልብ ይሏል::

  • @fredpolo1234
    @fredpolo1234 2 дня назад

    መንግስቱ ሃይለማርያም የጨርቆስ ሰፈር ያደገ ፈሪ ማጅግራት መች ነበር 17ኣመት ቤተክርስትያን ውስጥ ተደብቆ የኖረ ፈሪ እናቶች የወንድ ኣልጫ ይሉት ነበር ስራው መደበቅ ስለሆነ ኣሜሪክን 17አመት ሱሪው ላይ እያሸናች ወስዳ 35ኣምት ዚምባቡዌ ቀረቀረችው የገደላቸው 60ሰዎች በሰላም የተያዙ የተማረኩ ማለት ነበሩ መንግስቱ የወታደር ህግ እንክዋን ኣያውቅም ምምርኮኛ መረሸን ማለት ነው ደግሞ በ ሬዲዪ ወጥቶ ገድያለሁ ብሎ ይናገራል ኣሜሪካ ቅመም ነች ቅስ ብላ በቁሙ እየገደለችው ነው

  • @kidane6165
    @kidane6165 4 дня назад

    Can you mention about the starvation of Wolo? Do you remember about The mass grave ? ?

  • @sandrasmith9668
    @sandrasmith9668 2 дня назад

    And Menghistu H/ Mariam is still alive. Where is justice?????!!

  • @aberehamab9016
    @aberehamab9016 6 дней назад

    🙏💚💛❤️🙏

  • @belaytessema3004
    @belaytessema3004 3 дня назад +1

    The evilness and depravity of Ethiopian leaders monester mengestu and his killing squad,the ugly melese the Lucifer Abyi ahemed tell it all

  • @muninitefera6728
    @muninitefera6728 4 дня назад

    Fered betes bikerbu mene lewete yemetal. Mengistu yefelegewen newe yemiferdut. Yederge Generaloch sireshenu be Mengistu Hailemariam tezaz newe yeteferedew. Dajenet lebenet newe ethiopia weste.
    Derku degmo ye Climate Change impact newe beye 7 ametu yemetal.

  • @goshumisganaw3827
    @goshumisganaw3827 3 дня назад

    As to these arrogant so called colonel or president were not Ethiopians and their intrinsic agenda was to whip out who. May be Mengistu might come to in front of justice even after death.

  • @habtamuaderaw2166
    @habtamuaderaw2166 7 дней назад

    አረ አትፍጠኝ

  • @ambaye3115
    @ambaye3115 3 дня назад

    አዛውንቶቹ በመገደላቸው ደስተኛ ባልሆንም ከተገደሉት መካከል ሞት የሚገባቸው ነበሩ:: ማንም በጉልበት የድሃውን መሬት ዘርፎ የመሬት ባለቤቶችን ገባሪና ጢሰኛ ባሪያ አርጎ በፈላጭ ቆራጭነት በአገሩ ሲወራጭ የነበረ አድሃሪ የእጁን መስጠት ፍትህ ነው:: ትክክለኛ ታሪክ ሊናገሩ የሚችሉትን አቅርቡ: የጎጃም: የባሌ የአርሲ ወዘተ ገበሬዎች የደም ዕንባ ነበር ሲያነቡ የነበሩት::

    • @HamasenBr
      @HamasenBr 2 дня назад

      የባንዳ ፡ አሰተያየት ፡ ነው።
      በወቅቱ ፡ የነበረውን ፡ አለማቀፍ ፡ ሁኔታ ፡ ግንዛቤ ፡ ውስጥ ፡ ማስገባት ፡ ያስፈልጋል።

    • @yisakmekonnen1236
      @yisakmekonnen1236 День назад

      የደርግ ካድሬ ኮመንት

    • @ambaye3115
      @ambaye3115 День назад

      @yisakmekonnen1236 ትክክል ብለኸኛል: ሙታን ሣቢ ይመሰል የዛሬ 50 ዓመት የሞተን ግለሰብ አፅም አትሰብስብ: ሞራ ገላጭ::

  • @tekletesfazgi3359
    @tekletesfazgi3359 День назад

    Funny comedy

  • @sandrasmith9668
    @sandrasmith9668 2 дня назад

    And Menghistu H/ Mariam is still alive. Where is justice?????!!