የይልማ ሥላሴን ከሰማይ መዝሙር/selasien kesemay begena
HTML-код
- Опубликовано: 30 янв 2025
- ሥላሴን ከሰማይ እስጢፋኖስ አይቶ
አይኑ በመገረም ቀረ ተሰክቶ
የድንጋዩ ናዳ ቢወርድበት እንኳ
ሥላሴን በማየት ረስቶታል ለካ
ስብሐት ለእግዚአብሔር
የሰዉ ልጅ በቀኙ ተቀምቶ ነበር
እስጢፋኖስ ሲያየዉ በሚያስፈራ ክብር
ካህናተ ሰማይ ዙፋኑን ከበዉት
ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ስብሐት ስብሐት
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ምስጢረ ሥጋዊ ተገልጦለት በአካል
ሥጋዉ ቢታመምም ሀዘኑን ሽሮታል
ነፍሱ ከፀባኦት ስታመሰጥር
ድንጋይ ይለቅማሉ ልታደሉ ፍጡር
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ለፈሪሳዊያን ተሰዉሮባቸዉ የሥላሴ ምስጢር
ድንጋይ ሰበሰቡ ጻድቁን ለመዉገር
እርሱ ግን ከሰማይ ፈጣሪዉን አይቶ
ድንጋዩን እረሳዉ ህሊናዉ ተነክቶ
ስብሐት ለእግዚአብሔር
የሰማዩ ሥርዓት ልዩ ስለነበር
ምንም አልመሰለዉ የድንዩ ክምር
የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ተገልጠዉ
ስቃዩን አስረሱት ህሊናዉን ነጥቀዉ
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ልባችሁ ጆሯችሁ መቼ ተገረዘ
የጠነከረ ነዉ ለአምላከ ያልታዘዘ
መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ
እንደገዛ ፈቃድ እየተመራችሁ
ስብሐት ለእግዚአብሔር