ዘመን ተሻጋሪው ጋዜጠኛ፣ ደራሲና የታሪክ ተመራማሪ - ጳውሎስ ኞኞ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 18 окт 2024
  • #SUBSCRIBE # for more videos!
    Paulos Gnogno Biography
    የዛሬው የታላቅ ነፍስ ዕንግዳችን በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያ ታሪክ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ ይህ ጀግና የብዙ ሙያዎች ባለቤት፣ ሀገር ወዳድ፣ ህዝብ ወዳድ እና አክባሪ፣ እንዲሁም የንዋይ እና ዕውቀት ለጋስ ነው፡፡ የዚህ ጀግና ስም ሲነሳ ወደአብዛኛው ሰው አዕምሮ የሚመጣው በቀለም ትምህርት ብዙም ሳይገፋ በድፍን ኢትዮጵያ ዝነኛና ተወዳጅ ለመሆን ያበቃው የጋዜጠኝነት ስራው ነው፡፡ በዘመናዊ ትምህርት አራተኛ ክፍልን ያልተሻገረው ታላቅ ነፍስ፣ በተፈጥሮ የታደለው የማንበብ፣ የመጠየቅና የመመራመር ተሰጥኦ በጋዜጠኝነት ሙያው አንቱታን አትርፎለታል፡፡ እኛም ታድያ በዛሬው የታላቅ ነፍስ ዝግጅታችን የታሪክ መዛግብትን መርምረን፣ ቃላት መርጠን እና ሰድረን ጋዜጠኛ፣ ፀሐፈ-ተውኔት፣ ሰዓሊ፣ ደራሲ እና የታሪክ ተመራማሪ የሆነውን የታላቁን ኢትዮጵያዊ ጀግና የህይወት ታሪክ እንካችሁ አልን፡፡
    ቀናችን ልዩ የቅዳሜ ከሰዓት የመዝናኛ ሾው ዘውትር ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 - 11፡00 በዋልታ ኤፍ ኤም 105.3 ጣብያ፡፡ የአፍሪካ ፈርጥ፣ ልሳነ-ዜማ፣ ታላቅ ነፍስ፣ የጥበብ ስንቅ እና ሌሎች አዝናኝ እና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በቀናችን ሳምንታዊ የመዝናኛ ሾው ያገኛሉ፡፡

Комментарии •