✍️ግጥም በትንሹ ብላቴና ☘️

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 11 сен 2024
  • 🔴 #የወንጌል_ሰነድ
    ✍️ግጥም በትንሹ ብላቴና ☘️#የወንጌል_ሰነድ ☘️ዝማሬ በዘማሪት ታደለች ደጉ💐ፍቅርን ከክርስቶስ ትትናን ከማርያም#ማዕዶት_ቲዩብ #maedot_tube
    ብሉይን ከሐዲስ የያዘች አዛምዳ
    ከብሉይ በደፍተራ ኦሪት ያለፈች በፍዳ
    የሙሴ ሀመልማል በእምነት ያያት ሳትነድ ነዳ
    መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ እንዲፀዳ
    የወንጌል ሰነድ ማርያም ፀአዳ
    ዳዊት ተናገረ የአባትሽን ቤት እርሺ
    ንጉስ ውበትሽን ወዷል ፊትሽን አትመልሺ
    ሰነድ ነሽ እናት እንባ እምታብሺ
    የብሉይ ነብያት በሚስጥር ስሟን እያነሱ
    ድንግል በድንግልና ወለደች ሲሏቸው ይነሳል መንፈሱ
    ስሟ እንዳይነሳ እንዳይከብር ቅዱሱ
    የወንጌል ሰነድን እሷን ማወደሱ
    የምህረት በር ቁልፉ መክፈቻ
    የወንጌል እናት የዓለም መባቻ
    የሌላት መተኪያ አቻ
    የወንጌል ምሰሶ ክንዱ ሲዘረጋ
    እናቱ ተብላ ተጠራች በፀጋ
    የደረቀው ለምልሞ በእምነት እንዲተጋ
    የተቆረጠው ተቀጥሏል ያለ ዋጋ
    የወንጌል ሰነድ የጠላት አለንጋ
    መገረፊያ በትሩ
    ስምሽን ይፈራል ሰይጣን ሰለጠፋ ክብሩ
    እናት ነሽ ለአዳም የምህረት አጥሩ
    በር ነሽ የወንጌል ድንበሩ
    ብሉይን ከሐዲስ ማሰሪያ ቀመሩ
    ይችን እናት ስሟን ላንሳ
    የቃል ማደሪያ የወንጌል ማሳ
    እንክርዳዱ በቤት በቅሎ
    ስሟ እንዳይነሳ በክፋት ተቃጥሎ
    እውነትን ሊቀብር የሚሮጥ ምሎ ተማምሎ
    እውነትን በክህደት ጠቅልሎ
    እንክርዳዱ ስንዴ መስሎ
    እንዲበቅል ተመሳስሎ
    የሚዘራ ወንጌል ብሎ
    የጠፋ አለ ከቤቱ ኮብልሎ
    እናትነቷ እንዳይከብር በሰው ሁሉ
    ስሟ እንዳይነሳ እንዲሻር ቃሉ
    ጠላት ደከመ ሐሰት በመሳሉ
    እውነትን ሊያጠፋ ክንዱ አለመቻሉ
    የወንጌል ሰነድ እንዲፈታ ውሉ
    ብዙ የሚደክም የማይሰራ ቅሉ
    የጠፋ ጉም አለ ሰው በሉ ሰው በሉ
    የወንጌል ሰነድ ምርቱን ከንክርዳዱ
    የወልድ እናት የቃል መወረዱ
    በእምነት መዛመዱ
    ይሄ የጠፋቸው የወንጌል ሰነዱ
    በሥጋ ህሌና በሐሰት ተነዱ
    t.me/+LeMxwBvk...
    የወንጌል ሰነድ እኔስ እላታለው
    የቃል እመቤት ስሟን አነሳለው
    በናትነት ክንዷ ተደግፌ ያለው
    ቃልን የወሰነች በእምነቷ
    ለአዳም እናት የወንጌል መብራቷ
    የወንጌል ቀንበር የድህነት ቤቷ
    ማርያም ለጨለማው መብራት
    ተስፋ ለቆረጠው የተስፋ መሰረት
    ቅድመ ዓለም ያለ እናት
    ረቂቅ የፈጣሪ ውበት
    ድህረ ዓለም ያለአባት
    ተወሰነ ቃል በድንግል ማህፀን
    ረቂቅ ነው አምላክ ሰውን ሲያድን
    የቃል እናት ሆና ጠፋ እርቃናችን
    የወንጌል ሰነድ ድንግል እናታችን
    የወንጌል እናቱ ለኛ መብራታችን
    የወንጌል ሰነዱ በእውነት አለኝታችን።
    t.me/+LeMxwBvk...
    🌹ተፃፈ በመምህር ገብረፃዲቅ በትንሹ ብላቴና
    💚🇨🇬ግንቦት 17/2061
    ✍️ግጥም በትንሹ ብላቴና ☘️#የወንጌል_ሰነድ ☘️ዝማሬ በዘማሪት ታደለች ደጉ💐ፍቅርን ከክርስቶስ ትትናን ከማርያም#ማዕዶት_ቲዩብ #maedot_tube

Комментарии • 25

  • @mekdsshiferawu-gk2gd
    @mekdsshiferawu-gk2gd 21 день назад

    አሜን አሜን አሜን

  • @SelamTube21-gq3dw
    @SelamTube21-gq3dw 2 месяца назад

    አጥንትን የሚያለመልም ዝማሬ መልእክት ያሰማልን

  • @zinashgedamu1223
    @zinashgedamu1223 2 месяца назад

    እግዚአብሔር ይመሥገን ሰላማችሁ ይብዛ ዝማሬ መላክትን ያሠማልን እህታችን

  • @abebamebratu7054
    @abebamebratu7054 2 месяца назад

    አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወትን ያስማልን🎉🎉🎉❤❤

  • @sarahethiopia2312
    @sarahethiopia2312 Месяц назад

    እልልልልልልልልልልልልልልል 👏👏👏👏👏👏እልልልልልልልል ቃል ህይወት ያሰማልን ወድማችን በርታ አበረታቱት

  • @user-zt6qs6qw1w
    @user-zt6qs6qw1w 2 месяца назад

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር❤❤❤❤አሜን አሜን

  • @TigestSemgn
    @TigestSemgn 2 месяца назад

    ቃለ ህይወት ያሰማልህ እመቤቴ በቤቷ ታጥናልን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @genetteshome8721
    @genetteshome8721 Месяц назад

    አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን ፀጋውን አብዝቶ ያድልልን በቤቱ ያፅናልን መምህር !! ❤😊 አሜን አሜን አሜን ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ለእህታችን በቤቱ ያፅናልን !!❤😊

  • @MeseretEshetu-q2e
    @MeseretEshetu-q2e Месяц назад

    ቃለሕይወት ያሰማልን ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

  • @kalkal-hk3cf
    @kalkal-hk3cf 2 месяца назад

    ፍቅርን ከክርስቶስ ትትናን ከማርያም እህታችን ዘማሪ ታደሉ ዝማሬ መላእክትን ያሰማል የወንጌል ሰነድ የተሰኘውን መንፈሳዊ ግጥም ላቀረብክልን ወንድማችን ገብረ ፃድቅ ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን በርቱልን❤❤❤❤❤❤የተዋህዶ ልጆች❤❤❤❤

  • @sarahethiopia2312
    @sarahethiopia2312 2 месяца назад

    ቃል ህይወት ያሰማልን 🤲

  • @FasikaKindu
    @FasikaKindu 2 месяца назад

    ቃለ ሕይወትን ያሰማልን👏❤❤❤

  • @BdBd-zl6rf
    @BdBd-zl6rf 2 месяца назад

    ቃለ ህይወት ያሰማልን ❤❤❤❤❤❤

  • @ሀይለማርያምሰለሞን
    @ሀይለማርያምሰለሞን 2 месяца назад

    ወንድማችን ገብረፃዲቅ በርታ ያገልግሎት ዘመንህ ይባረክ አምላክ ይጠብቅህ እህታችን ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ወንድማችንን እናግዘው እሚያስፈልገውን ነገር ከፈጣሪ በታች እናድርግለት።

  • @Birtuk-me8je
    @Birtuk-me8je Месяц назад

    ወንድማችን ፀጋውን ያብዛልኮ🍃🍃

  • @ABdulAziz-rn3kf
    @ABdulAziz-rn3kf Месяц назад

    ሰለምምህር🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

  • @abi76908
    @abi76908 2 месяца назад

    እልልልልልል❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉

  • @TigestSemgn
    @TigestSemgn 2 месяца назад

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @hagilmaryamHayela
    @hagilmaryamHayela 2 месяца назад

    ወንድማችን በርታ በጣም ደስ የሚል ብዙ አስተማሪ ነገር ከአንተ እንጠብቃለን ወንድም እህቶቼ የምንችል ከቻልንካሜራም ገዝተነሰ አግዘን የሜንችል ደግሞ ሼር ላይክ እያደረግን ብናግዘው ምን ይመስላችኋል።

  • @yonasLube
    @yonasLube 2 месяца назад

    ❤❤❤❤❤

  • @hao90
    @hao90 2 месяца назад

    🌹❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤🍇🌹🌹❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-zt6qs6qw1w
    @user-zt6qs6qw1w 2 месяца назад

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር❤❤❤❤አሜን አሜን

  • @user-nw8cp3te6d
    @user-nw8cp3te6d Месяц назад

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

  • @user-zt6qs6qw1w
    @user-zt6qs6qw1w 2 месяца назад

    ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር❤❤❤❤አሜን አሜን

  • @አልሚ
    @አልሚ Месяц назад

    ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤