የበገና መዝሙር መምህርት ሄለን ነጋ ምራኝ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 30 сен 2024
  • የበገና መዝሙር
    ምራኝ ወደ ሕይወት ምራኝ የኔ ጌታ
    በዘለዓለም ስቃይ እንዳልንገላታ
    ልሂድ በጠባቡ አበርታኝ ጌታዬ
    አንተን ልከተልህ ሁሉን ነገር ጥዬ
    ወደ ጽድቅህ ምራኝ አድርገኝ አዲስ ሰው
    ይገዛልህ ልቤ የሚመላለሰው
    አጽናኝ በመንፈስህ ራስ መሰረቴ
    አንተን ብቻ ይጥራህ ተገርቶ አንደበቴ
    የዴማስን መንገድ ረገጡ እግሮቼ
    ምድራዊውን ወደድኩ የሰማዩን ትቼ
    ብልጭልጩ ቀርቶ ልግባ ወደ ቤቴ
    ልቤን መልስልኝ የሰማይ አባቴ
    ቀንበር የከበደኝ የበደል ምርኮኛ
    ወዳንተ መጣሁኝ አልውደቅ ዳግመኛ
    ምራኝ በቸርነት ወደ ሕይወት መንገድ
    ከሰማዩ ቤቴ ኋላ እንዳልሰደድ

Комментарии • 36