በደቡብ ፈረንሳይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጦርነቱ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ያደረጉት ድጋፍ በከፊሉ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 23 авг 2022
  • በፈረንሳይ ሀገር የሚኖሩት አቶ ፋሪስ አሊ እንደገለፁት በደቡብ ፈረንሳይ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል የሚሆን 6ሽህ ዩሮ የሚገት የተለያዩ መድሀኒቶችን ድጋፍ ያደረጉት አማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ተደራሽ እንዲሆን መሆኑን ገልፀዋል፡፡
    አክለውም በደብረ ብርሀን ከተማ 1000 ለሚሆኑ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው ይህ ድጋፍ ብዙ ሆኖ ሳይሆን በቀጣይ በዲያስፖራው ዘንድ ጉዳቱን በመገንዘብ መነሳሳትን እንዲፈጥር በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
    ይህ መድሀኒት ከግምሩክ ወጥቶ ድጋፍ እንዲያደርጉ ለተባበረው ለወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ምጋና አቅርበዋል፡፡
    የኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር እንደተናገሩት የኮ/ቻ ጠቅላላ ሆስፒታል እንደሌሎች አካባቢዎች በወራሪው ሀይል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን በግምት 8መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ንብረት መዘረፉን ገልፀው ይህ ሆስፒታል ከወረራው በፊት በአጭር ጊዜ በርካታ ሀብት አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ጦርነቱ ከተማችን ላይ ሲገባ ተዘርፏል ብለው ሆስፒታሉ አፋርን ጨምሮ ለአጎራባች ወረዳዎች አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ ታካሚ የሚመጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
    ስለሆነም ከፍተኛ የሆነ የድርጅቶችና የግለሰቦች ድጋፍ የሚያስፈልገው መሆኑን ተናግረው በአቶ ፋሪስ አማካኝነት ፈረንሳይ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዲያስፖራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉና ለወገን እንዲደርሱ ጠይቀዋል፡፡ የሚመጡ ድጋፎች በቀጥታ ለማህበረሰቡ የሚደርሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Комментарии • 2