ትንቢተ ዳንኤል~ ክፍል 3 (ምዕራፍ 2 ፡1-49) ፓስተር አስፋው በቀለ

Поделиться
HTML-код
  • Опубликовано: 28 авг 2024
  • ናቡከደነፆር ያለመው ሕልም
    1ናቡከደነፆር በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሕልም አለመ፤ መንፈሱ ታወከ፤ እንቅልፍም ከእርሱ ራቀ። 2ያለመውንም ሕልም እንዲነግሩት ንጉሡ ጠንቋዮችን፣ አስማተኞችን፣ መተተኞችንና ኮከብ ቈጣሪዎችን እንዲጠሩ አዘዘ፤ እነርሱም ገብተው በፊቱ ቆሙ፤ 3እርሱም፣ “አንድ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም ምን እንደሆነ ለማወቅ መንፈሴ ተጨንቆአል” አላቸው።
    4ከዚያም ኮከብ ቈጣሪዎቹ ለንጉሡ በአረማይክ ቋንቋ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ! ሕልምህን ለአገልጋዮችህ ንገረን፤ እኛም እንፈታልሃለን” አሉት።
    5ንጉሡም ለኮከብ ቈጣሪዎቹ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕልሙንና ትርጒሙን ባትነግሩኝ አካላችሁ እንዲቈራረጥና ቤቶቻችሁም የፍርስራሽ ክምር እንዲሆኑ ወስኛለሁ 6ነገር ግን ሕልሙንና ትርጒሙን ብትነግሩኝ፣ ስጦታና ሽልማት፣ ታላቅ ክብርም ከእኔ ትቀበላላችሁ፤ ሕልሙን ንገሩኝ፤ ትርጒሙንም አሳውቁኝ።”
    7እነርሱም እንደ ገና፣ “ንጉሥ ሕልሙን ለአገልጋዮቹ ይንገረን፤ እኛም እንተረጒመዋለን” ብለው መለሱ።
    8ንጉሡም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ምን ብዬ እንደ ወሰንሁ ስለምታውቁ፣ ጊዜ ለማራዘም እንደምትሞክሩ ተረድቼአለሁ፤ 9ሕልሙን ባትነግሩኝ፣ አንድ ቅጣት ይጠብቃችኋል፤ ሁኔታው ይለወጣል ብላችሁ በማሰብ የሚያሳስቱ ነገሮችንና ክፉ ሐሳቦችን ልትነግሩኝ አሲራችኋል፤ ስለዚህ ሕልሙን ንገሩኝ፤ ትርጒሙንም ልትነግሩኝ እንደምትችሉ በዚህ ዐውቃለሁ።”
    10ኮከብ ቈጣሪዎቹም ለንጉሡ እንዲህ ብለው መለሱ፤ “ንጉሡ የጠየቀውን ጥያቄ ሊመልስ የሚችል ሰው በምድር ላይ አይገኝም! ማንም ንጉሥ ምንም ያህል ታላቅና ኀያል ቢሆን፣ እንዲህ ዐይነት ነገር ማንኛውንም ጠንቋይ፣ አስማተኛ ወይም ኮከብ ቈጣሪን ጠይቆ ዐያውቅም። 11ንጉሡ የሚጠይቀው እጅግ አስቸጋሪ ነገር ነው፤ በሰዎች መካከል ከማይኖሩት ከአማልክት በቀር ለንጉሡ የሚገልጽለት የለም።”
    12ይህም ንጉሡን እጅግ አበሳጨው፤ አስቈጣውም፤ በባቢሎን ያሉ ጠቢባን ሁሉ እንዲገደሉም አዘዘ፤ 13ጠቢባን ሁሉ እንዲገደሉም ዐዋጅ ወጣ፤ ዳንኤልንና ጓደኞቹን ፈልገው እንዲገድሉ ሰዎች ተላኩ።
    14የንጉሡ ዘበኞች አለቃ አርዮክ፣ የባቢሎንን ጠቢባን ለመግደል በመጣ ጊዜ፣ ዳንኤል በጥበብና በዘዴ አነጋገረው። 15የንጉሡን መኰንን፣ “ንጉሡ እንዲህ ዐይነት ከባድ ዐዋጅ ያወጣው ስለ ምንድ ነው?” ሲል ጠየቀው፤ አርዮክም ነገሩን ለዳንኤል ገለጠለት። 16በዚህን ጊዜ፣ ዳንኤልም ገብቶ ሕልሙን ይተረጒምለት ዘንድ ጊዜ እንዲሰጠው ንጉሡን ጠየቀው።
    17ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ ቤቱ ተመልሶ ለጓደኞቹ ለአናንያ፣ ለሚሳኤልና ለአዛርያ ነገሩን ገለጠላቸው። 18እርሱና ጓደኞቹ ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይገደሉ፣ የሰማይ አምላክ ምሕረት ያደርግላቸውና ምስጢሩንም ይገልጥላቸው ዘንድ እንዲጸልዩ አሳሰባቸው። 19ለዳንኤልም ምስጢሩ በሌሊት በራእይ ተገለጠለት፤ ዳንኤልም የሰማይን አምላክ አመሰገነ፤ 20እንዲህም አለ፤
    “ጥበብና ኀይል የእርሱ ነውና፣
    የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ።
    21ጊዜንና ወቅትን ይለውጣል፤
    ነገሥታትን በዙፋን ያስቀምጣል፣
    ደግሞም ያወርዳቸዋል፤
    ጥበብን ለጠቢባን፣
    ዕውቀትንም ለሚያስተውሉ ይሰጣል።
    22የጠለቀውንና የተሰወረውን ነገር ይገልጣል፤
    በጨለማ ያለውን ያውቃል፤
    ብርሃንም ከእርሱ ጋር ይኖራል።
    23የአባቶቼ አምላክ ሆይ፤ አመሰግንሃለሁ፤
    አከብርሃለሁም፤
    ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛልና፤
    ከአንተ የጠየቅነውን ነገር አሳውቀኸኛል፤
    የንጉሡን ሕልም አሳውቀኸናል።”
    ዳንኤል ሕልሙን ተረጐመ
    24ዳንኤልም የባቢሎንን ጠቢባን እንዲገድል ንጉሡ ወዳዘዘው ወደ አርዮክ ሄዶ፣ “የባቢሎንን ጠቢባን አትግደል፤ ወደ ንጉሡ ውሰደኝ፤ እኔም ሕልሙን እተረጒምለታለሁ” አለው።
    25አርዮክም ዳንኤልን ወዲያውኑ ወደ ንጉሡ በመውሰድ፣ “ሕልሙንና ትርጒሙን ለንጉሡ መግለጥ የሚችል ሰው ከይሁዳ ምርኮኞች መካከል አግኝቻለሁ” አለው።
    26ንጉሡም ብልጣሶር የተባለውን ዳንኤልን፣ “ያየሁትን ሕልምና ትርጒሙን ልትነግረኝ ትችላለህን?” አለው።
    27ዳንኤልም እንዲህ አለ፤ “አንድም ጠቢብ፣ አስማተኛ፣ ጠንቋይም ሆነ ቃላተኛ ንጉሡ የጠየቀውን ምስጢር መግለጥ የሚችል የለም፤ 28ነገር ግን ምስጢርን የሚገልጥ አምላክ በሰማይ አለ፤ እርሱም በሚመጡት ዘመናት የሚሆነውን ነገር ለንጉሥ ናቡከደነፆር ገልጦአል፤ በዐልጋህ ላይ ተኝተህ ሳለ በአእምሮህ የነበረው ሕልምና ራእይ ይህ ነው፦
    29“ንጉሥ ሆይ፤ ተኝተህ ሳለ፣ አእምሮህ ወደ ፊት ሊሆን ስላለው ነገር ያሰላስል ነበር፤ ምስጢርን ገላጭ የሆነውም ወደ ፊት የሚሆነውን ነገር አሳየህ። 30ይህ ምስጢር ለእኔ የተገለጠው፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ ታላቅ ጥበብ ስላለኝ አይደለም፤ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትርጒሙን እንድታውቅና በአእምሮህ ታሰላስለው የነበረው ነገር ምን እንደሆነ ትረዳ ዘንድ ነው።
    31“ንጉሥ ሆይ፤ በፊት ለፊትህ ግዙፍ የሆነ፣ የሚያብረቀርቅና የሚያስፈራ ታላቅ ምስል ቆሞ አየህ፤ 32የምስሉ ራስ ከንጹሕ ወርቅ፣ ደረቱና ክንዶቹ ከብር፣ ሆዱና ጭኖቹ ከናስ የተሠሩ ነበሩ፤ 33ቅልጥሞቹም ከብረት፣ እግሮቹም ከፊሉ ከብረት፣ ከፊሉም ከሸክላ የተሠሩ ነበሩ። 34ይህን በመመልከት ላይ ሳለህ፣ አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ ወረደ፤ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የምስሉን እግሮች መታቸው፤ አደቀቃቸውም። 35ወዲያውኑም ብረቱ፣ ሸክላው፣ ናሱ፣ ብሩና ወርቁ ተሰባበሩ፤ በበጋ ወራት በዐውድማ ላይ እንደሚገኝ እብቅም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራረጋቸው፤ ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሞላ።
    36“ሕልሙ ይህ ነበር፤ አሁን ትርጒሙን ለንጉሥ እንናገራለን። 37ንጉሥ ሆይ፤ አንተ የነገሥታት ንጉሥ ነህ፤ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ሥልጣንን፣ ኀይልንና ክብርን ሰጥቶሃል፤ 38የሰው ልጆችን፣ የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶሃል፤ በየትም ቦታ ቢሆኑ፣ በሁሉም ላይ ገዥ አድርጎሃል፤ እንግዲህ የወርቁ ራስ አንተ ነህ።
    39“ከአንተም በኋላ ከአንተ የሚያንስ ሌላ መንግሥት ይነሣል፤ ቀጥሎም በናስ የተመሰለው ሦስተኛ መንግሥት ይነሣል፤ መላውን ምድርም ይገዛል። 40በመጨረሻም ሁሉን ነገር እንደሚቀጠቅጥና እንደሚሰብር ብረት ብርቱ የሆነ አራተኛ መንግሥት ይነሣል፤ ብረት ሁሉን ሰባብሮ እንደሚያደቅ ከእርሱ በፊት የነበሩትን መንግሥታት ሁሉ ሰባብሮ ያደቃቸዋል። 41እግሮቹና ጣቶቹ ከፊል ብረትና ከፊል ሸክላ ሆነው እንዳየህ፣ እንዲሁ የተከፋፈለ መንግሥት ይሆናል፤ ነገር ግን ብረትና ሸክላ ተደባልቀው እንዳየህ በከፊል የብረት ጥንካሬ ይኖረዋል። 42የእግሮቹ ጣቶች ከፊሉ ብረት ከፊሉ ሸክላ እንደሆኑ ሁሉ ይህም መንግሥት በከፊሉ ብርቱ በከፊሉ ደካማ ይሆናል። 43ብረትና ሸክላ ተደባልቀው እንዳየህ ሁሉ ሕዝቡም ድብልቅ ይሆናል፤ ብረትና ሸክላ እንደማይዋሃድ ሁሉ ሕዝቡም በአንድነት አይኖሩም።
    44“በእነዚያ ነገሥታት ዘመን፣ የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይፈርስና ለሌላም ሕዝብ የማይሰጥ መንግሥት ይመሠርታል፤ እነዚያን መንግሥታት ሁሉ ያደቃል፤ እስከ መጨረሻውም ያጠፋቸዋል፤ ይህ መንግሥት ራሱ ግን ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። 45የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ የወረደውና ብረቱን፣ ናሱን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ያደቀቀው ድንጋይ ራእይ ትርጓሜ ይህ ነው፦
    “ታላቁ አምላክ ወደ ፊት የሚሆነውን ለንጉሡ አሳይቶታል፤ ሕልሙ እውነት ነው፤ ትርጓሜውም የታመነ ነው።”
    46ከዚያም ንጉሥ ናቡከደነፆር በግንባሩ ተደፍቶ ለዳንኤል ሰገደለት፤ አከበረውም፤ መሥዋዕትና ዕጣንም እንዲያቀርቡለት አዘዘ። 47ንጉሡም ዳንኤልን፣ “ይህን ምስጢር ልትገልጥ ችለሃልና፣ በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክና የነገሥታት ጌታ፣ ምስጢርንም ገላጭ ነው” አለው።
    48ንጉሡም ዳንኤልን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ አስቀመጠው፤ እጅግ ብዙ ስጦታዎችንም ሰጠው፤ የመላው ባቢሎን አውራጃ ገዥ አደረገው፤ በባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ላይም አለቃ አድርጎ ሾመው። 49ከዚህም በላይ በዳንኤል አሳሳቢነት ንጉሡ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን የባቢሎን አውራጃ አስተዳዳሪዎች አድርጎ ሾማቸው፤ ዳንኤል ግን በቤተ መንግሥት ተቀመጠ።
  • РазвлеченияРазвлечения

Комментарии • 87

  • @TruemanAyalew
    @TruemanAyalew 3 месяца назад +1

    ማራናታ አሜን ጌታ ሆይ ቶሎ ና።❤❤❤

  • @ababumegersa-yh4tr
    @ababumegersa-yh4tr 4 месяца назад

    ጌታ ፀጋውን ያብዛልዎት መጋቢ አስፋው!!!

  • @MelesechTekele-ry2er
    @MelesechTekele-ry2er 7 месяцев назад

    Amne amne amnee gata Egezbhere yebrke tabreke 👍🙏🙏❤tabrekenaleamne

  • @Wusisu
    @Wusisu 4 месяца назад

    🙏🏽 Amen We love you 🙏🏽 Geta biriiiiiiiik yadirgih🙏🏽

  • @Wusisu
    @Wusisu 4 месяца назад

    I’m listening 2nd time

  • @derejeasefa6240
    @derejeasefa6240 8 месяцев назад

    እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ ፓስተር ፀጋ ይብዛልህ ።

  • @AsterAbebeOfficial
    @AsterAbebeOfficial 4 года назад +4

    ፓስተርዬ ጌታ ይባርክህ። ሦስት ላይ ደርሻለው ። ይብዛልህ።
    ማራናታ *አሜን ጌታ እየሱስ ሆይ ቶሎ ና *

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад

      ኣሜን፥ አስቲ፤ ጎሽ በርቺልኝ፤ ተባሪኪ።

  • @raheladane9232
    @raheladane9232 4 года назад +13

    ለአገራችን እኮ እንደዚህ አይነት ትምህርት ያስፈልጋል እኛስ በውጭ ዋይፋይ አለን በደንብ እየተጠቀምን ነው

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад +13

      ሰላም ራሄል፤ አገር ቤት ይህን ትምህርት ኤዲት አድርገን በኤልሻዳይ ቲቪ ለማዘጋጀት አስበናል… ሌሎች ትምህርቶቻችንም በኤልሻዳይ ቲቪ ላይ እየተለቀቁ ነው። በጸሎትሽ አስቢን

    • @raheladane9232
      @raheladane9232 4 года назад +5

      @@asfawBekelepastor እሺ ጌታ አቅምና ጉልበት ይስጣቹ ረጅምን እድሜ ያጥግባቹ ።አገር ቤት ጌታን ብዙ ሰዎች እያገኙ ነው ባለፈው ሄጄ ነበር ግን የእግዚአብሔር ቃል የሚማሩበት ሁኔታ የለም እኔም ከቤተሰቤ ለመጀመር ተነስቼአለሁ የተማርሁትን የተረዳሁትን ።ተባረኩ

    • @kidist56
      @kidist56 4 года назад +5

      ለክርስትያናት በሙሉ መዳረስ አለበት:: እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ቃሉን ለመማር ግን ሀይማኖት አይገድበንም :: ቃሉን እንዲህ አብራርቶ የሚያስተምር ተገኝቶ ነው:: ድንቅ መምህር ነው::

  • @yonastesfay804
    @yonastesfay804 3 года назад

    Amen amen

  • @sitootas
    @sitootas 2 года назад

    God bless you pastor for you are blessings

  • @zebenayf5889
    @zebenayf5889 3 года назад

    አሜን

  • @Chris-Alone
    @Chris-Alone 2 года назад

    ፓስተር እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ። እየተጠቀምኩበት ነው። ተባረክ

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 года назад +1

    አሜን ማራ ናታ ጌታ እየሱስ ሆይ ቶሎ ና

  • @mihrettube4908
    @mihrettube4908 4 года назад +3

    Ameeeeen. P.A tabareki. ♥

  • @TruemanAyalew
    @TruemanAyalew 3 месяца назад

    God bless you pastor

  • @yohannesteferra6202
    @yohannesteferra6202 3 года назад +1

    ፓስተር እኔ አገልጋይ ነኝ የራዕይን መጽሐፍ ከዳንኤል ትንቢት ጋር አያይዤ ትምህርት እሰጣለሁና የአንተ ትምህርት ለእኔ ማረጋገጫ፣ መሠረት ሆኖኛል፡፡ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በኤልሻዳይና በዩ ቲ ዩብ የአገልግሎትህ ተጠቃሚ ነኝ፡፡ ስሰማህ ብውልና ባድር አልሰለችም የሰማይ አምላክ አብዝቶ ይባርክህ፣ ፀጋውን ያብዛልህ፡፡ ስታስተምር ግልጽ አድርገህ፣ በሚገባና በማይረሳ መልኩ ነው፡፡ አንተ የማስተማር ፀጋ የፈሰሰብህ እውነተኛ የተቀባህ አስተማሪ ነህ፡፡
    የምታቀርባቸው መረጃዎችና ማስረጃዎች ትክክለኛና አንተም ለምታስተምረው ትምህርት ሰፊ ዝግጅት አድርገህ እንደምትቀርብ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ፓስተር አስፋው ቢሮዬ እንኳን ቁጭ ብዬ ሥራዬን እየሠራሁ ዩ ቲ ዩብ ከፍቼ የአንተን ትምህርቶች እየሰማሁ ነው ሥራዬን የምሠራው፡፡ አሁንም ፀጋው ይብዛልህ እኔ ግን ለአገልግሎቴ ትምህርቶችህ እጅግ እጅግ ጠቅመውኛል፡፡

  • @greeceathens9187
    @greeceathens9187 3 года назад

    Amen

  • @eteneshdemessie8334
    @eteneshdemessie8334 4 года назад +1

    አሜን ማራናታ ጌታ እየሱስ ሆይ ና ሃሌሉያ እልልልልልልል....

  • @goldentestimonies4734
    @goldentestimonies4734 4 года назад +2

    Pastorye enwedih alen , geta ybarkih

  • @eteneshdemessie8334
    @eteneshdemessie8334 4 года назад +2

    አሜን ወንድሜ ተባረክ

  • @hamkoki7803
    @hamkoki7803 3 месяца назад

    enquan kirstian honku tebarek paster

  • @saronyegeta6382
    @saronyegeta6382 4 года назад +3

    እግዚአብሔር ስለ ቃሉ ስለ ባሪያው ስሙ የተመሰገነ ይሁን ክብር ሁሉ በሰማይ በምድር ለእርሱ ይሁን ፓስተር አስፋው እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ ፀጋውን ያብዛልህ አገልግሎትህ ዘመን ሁሉ ይባረክ የመንፈስ ቅዱስ ሀይልና ፀጋ ብርታት ይሁንህ።

  • @tekashawash9742
    @tekashawash9742 3 года назад

    ጌታ ይባርክህ ፓር አስፋው
    ስለትምህርቱ ጌታ ይባርክህ ይብዛልህ መንፈስ ያለበት ስለሆነ አይን ይከፍታል በተጨማሪ የምታቀርባቸው የድሮ መዝሙሮች በጣም ይባርካል ብዙ ትዝታ ውስጥ የሚከቱ የነበረውን መንፈስ የሚያስታውሱን ናቸው በዛ ግዜ ስለነበርን ልጠይቅህ የፈለኩት የሚቻል ከሆነ በyoutube እንደ collection አድርገህ ብታሰራጨው ለብዞቻችን በረከት ይሆናልና ጌታ እንደረዳህ ተግተህ ብታደርገው ። የገረመኝ በዚህ ሁሉ አመት የድምፅ ጥራታቸውን የጠበቁ መሆናቸው ነው።
    ተባረክ

  • @thitinabirhanu1351
    @thitinabirhanu1351 4 года назад +1

    ፓስተር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባርክህ ።

  • @tsegaamentesfay2538
    @tsegaamentesfay2538 4 года назад +1

    አሜን አሜን

  • @meseretworkureta8723
    @meseretworkureta8723 3 года назад +1

    God Bless you.

  • @sosenanaser8565
    @sosenanaser8565 4 года назад +3

    አሜን ጌታ ስሙ ይባረክ ፀጋውን ያብዛልህ ዘመንህን ይባርክ

  • @luammehari4143
    @luammehari4143 4 года назад +1

    Wey Des yemlena megelet Yalew tmhrt new Tebarek pastor Tesfaye.

  • @raheladane9232
    @raheladane9232 4 года назад +1

    ማራናታ የተዘጋጀን እንሁን አቅም ስጠን ጌታ

  • @amanuelbayu5851
    @amanuelbayu5851 9 месяцев назад

    much grace upon you pastor

  • @meskeremtesfaye843
    @meskeremtesfaye843 Год назад

    አሜን አሜን አሜን ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን በአንተ ትምህርቶች ብዙ ነገር ተምሪያለው እግዚአብሔር አይቼዋለው ጌታ ዘመንህ ይባርከው እረዥም እድሜ ከጤኛ ጋር እግዚአብሔር ይስጥህ ፓስተር አስፈው ያልገባኝ በጣም ብዙ ነገር ተረድቻለው

  • @bbhuhh5737
    @bbhuhh5737 3 года назад

    ወይኔ ፓስተር ምን አይነት የቃል መገለጥ ነው ዘመንህ ይባረክ ተባረክልኝ የኔ አባት አሜን 💕💕💕🙌🙌🙌🙌🙌🙏🙏

  • @genetkersie739
    @genetkersie739 4 года назад

    እንጸናለን በጊዜውም ያለ ጊዜውም ዛሬ የጠበቀን ነገም አይተወንም እንጸናለን! ዋው!!! ድንቅ መልዕክት ድንቅ መዝሙር!

  • @yeksyelij7658
    @yeksyelij7658 3 года назад

    ቃለ ህወት ያሰማልን
    እ.ር ዕድሜ ጤና ይስጥህ።

  • @eliyamakhoul5227
    @eliyamakhoul5227 4 года назад +6

    ፓስተር እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ ክዚህም በበለጠ የቃሉን እውቀት እንዲያበዛልህ ጸሎቴ ነው ለምድራችን እንዳንተ አይነቱን ያብዛልን የምታስፈልጓት እናንተ ናችሁና

  • @elizabethzemedkun6224
    @elizabethzemedkun6224 4 года назад +2

    Thanks for the amazing teaching

  • @user-gq8mk5fi5x
    @user-gq8mk5fi5x 2 года назад

    ጌታ ዘመንክን ያለምልም ትዳርክ ልጆችክ ይባረኩ ለምልምልኝ ጸጋ በጸጋላይ ጌታ ይጨምርልክ ለትውልድ የሚቀር የሚጠቅም ትምርት ነው ተባረክ

  • @yordanosdotti4876
    @yordanosdotti4876 4 года назад +2

    Amazing teaching,thanks for sharing

  • @Taredan77
    @Taredan77 4 года назад +1

    ተባረክ

  • @bbhuhh5737
    @bbhuhh5737 3 года назад

    አሜሜሜሜን ጌታችን በፊት ለፊት እናያለን ማራናታ ኢየሱስ ቶሎ ናናናናናናና🙏🙏

  • @beetybybb2576
    @beetybybb2576 4 года назад +1

    Amen God bless you🙏🙏🙏

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 года назад

    እግዚአብሔር ይባርክህ ፓስተር አስፋው ባላንስ የሆነ እውነተኛ ወንጌል ስለምታስተምር ጌታ ይብርክህ

  • @darmyelshtessema3313
    @darmyelshtessema3313 2 года назад

    አሜን ፓሰተር የሚገርም ነው ተባረክ ተባረክ በጣም የሚወደድ ነው።
    ተበረክ

  • @salamzaki409
    @salamzaki409 4 года назад +1

    ዘመን ይባረክ

  • @alphaomegagod303
    @alphaomegagod303 3 года назад

    God bless you...እፀልያለሁ ጌታ ይረዳhali

  • @user-ou3ez8rq9l
    @user-ou3ez8rq9l 11 месяцев назад

    selam paster.

  • @selamawitmulushewa4534
    @selamawitmulushewa4534 4 года назад

    እግዚአብሄርን አመሰግናለሁ እንደዚህ እግዚአብሄር የቀባቸው አስተማሪዎች ስለሰጠን . ተባረክልን

  • @lemlemghebremedhinweldeghi5205
    @lemlemghebremedhinweldeghi5205 3 года назад

    እኔ በዚህ ትምህርት በጣም ተባርኬአለሁ፡ እውነቱን የእግዚአብሄር ቃል ተምርያለሁ እና ጌታ ያስፋቹ

  • @alem.t327
    @alem.t327 4 года назад +1

    God bless you Pastor .

  • @user-gf5yn9yz9c
    @user-gf5yn9yz9c 4 года назад +2

    God bless you amazing teaching ministry I hope more ppl will benefit from your teaching!,,,

  • @tagesechtesema6195
    @tagesechtesema6195 Год назад

    Pastor you are from God our blessing
    May God bless you and your family love you from Dubai

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 года назад

    የእግዚአብሔር ቅንአት ይሄንን ያደርጋል

  • @salamsalam2325
    @salamsalam2325 4 года назад

    እግዚአብሔር ይባረክህ ዘመንህ ይለምልም ፓስተር እኔ በብዙ ተጠቅሚያለሁ በእውነት ጊታ ባንተውስጥ ሆኖ ህይወቲን አድሶታል ።በተሰቦችህ ሁሉ በኢየሱስ ስም የተባረኩ ይሁኑ

  • @goldentestimonies4734
    @goldentestimonies4734 4 года назад

    Amen amen amen amen amen Pastorye eyetemarku negn ahunim ybarkih .

  • @jemo5716
    @jemo5716 2 года назад

    Amen Amen Amen. Bless you so much pastor

  • @fitsumregassa8113
    @fitsumregassa8113 4 года назад

    Pastoriyeeeee amilake egizihabiher abizto yibarikih tsegawun yabizalih betam eyetetekemku nw bante timihirt minim aygebagnim neber geta nw anten yesetegn yeminoraw 🇬🇧 uk nw

  • @sebleagede6324
    @sebleagede6324 4 года назад

    Geta yebarekh paster betam

  • @derartutola2579
    @derartutola2579 3 года назад

    አሜን ጌታ ዘመንህን ያለምልመው ወንድሜ

  • @CFWTvShow
    @CFWTvShow 3 года назад

    God bless you Pastor!

  • @masaratphonetastic4360
    @masaratphonetastic4360 4 года назад

    Hallelujah

  • @dashu777
    @dashu777 3 года назад

    Brother, thank you!

  • @liyayohannes9786
    @liyayohannes9786 4 года назад +2

    My aunt from England introduced me to this page 3days ago. I never understood the book of Daniels at this extent. You are a well informed knowledgeable person. I will keep sharing you’re page to my friends too. Thank you so much for taking you’re time to reach us.

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад +1

      Thank you so much for your kind words, Liya. We really appreciate you taking the time out to share your experience with us-We count ourselves blessed for friends like you. Please pass big thank you for your Auntie for promoting our ministry. Stay blessed and be a blessing!

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад

      Thank you so much for your kind words, Liya. We really appreciate you taking the time out to share your experience with us-We count ourselves blessed for friends like you. Please pass big thank you for your Auntie for promoting our ministry. Stay blessed and be a blessing!

  • @genetkersie739
    @genetkersie739 4 года назад

    አንተ ሰሪነህ እኔ ሸክላ!!!ገራሚ! መዝሙር !ይኼ ነው እውነቱ እንግዲህ ! ከሸክላምሸክላ! ትሰብራለህ ትጥሳለህ የለም! ጌታን ከፊት ሳስቀድም ለመውጣት ብሞክር ሸክላ ነኝ እንክትክት ነው! አየሱስ ጌታ ነው! ጌታን ሳስቀድም ግን ዘና ብዬ ያለ ትግል በስብርባሪ መውጣት እችላላሁ! ሀሌሉያ!

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 года назад

    6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
    7 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።
    6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
    7 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

  • @megersahailu6719
    @megersahailu6719 3 года назад

    may God bless you enormously. But I wonder if you could make each video free to download.

  • @user-ef9ki1he9e
    @user-ef9ki1he9e 11 месяцев назад +1

    There are 7 continents but bible tells there are 10 continents how ?

  • @hannasmith4482
    @hannasmith4482 4 года назад

    What chapter we read

  • @raheladane9232
    @raheladane9232 4 года назад

    እንደው ፓስተር እንዴት ይህን ትምህርት በ ኤልሻዳይ ቲቪ ቢቀርብ

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад

      good idea Rahel, I will let the media edit and upload it for tv. thank u sister

    • @hannahkassa6319
      @hannahkassa6319 4 года назад

      @@asfawBekelepastor Pastor, GBU! This is a great and much needed message. But I felt it was too long to share especially for those who may not be born again Christians. After you have this lesson edited for media use, would it be available in your channel to share it? Thank you. I love the old songs, too. Remain blessed brother.

    • @asfawBekelepastor
      @asfawBekelepastor  4 года назад

      @@hannahkassa6319 thank you sister Hannah for your encouraging comment. It is indeed long teaching. we are planning to edit out some of it... and add some scriptures parallel to what is being said. probably we will have three parts from one broadcast. hopefully, we will do this as soon as we finished the entire course. help me with your prayer! blessings!

    • @hannahkassa6319
      @hannahkassa6319 4 года назад

      @@asfawBekelepastor I sure will, thank you Pastor. Remain blessed.

  • @Mercylovefaith
    @Mercylovefaith 4 года назад

    አሜን